Home » ጦማሮች እና አስተያየቶች » የህወሓት ጉዳይ — የተገኘው ድል፤ ትልቅ ድል ነው፣ ሆኖም አንዝናና፣ አንዘናጋ!

የህወሓት ጉዳይ — የተገኘው ድል፤ ትልቅ ድል ነው፣ ሆኖም አንዝናና፣ አንዘናጋ!

በዶ/ር ታደሰ ብሩ

የህወሓት ጉዳይ!

”የህወሓት ጉዳይ አልቆለታል፤ ከእንግዲህ ያለው ጉዳይ እጅግም አያሳስብም“ የሚሉ ወገኖች ለድምዳሜ የቸኮሉ ይመስለኛል። እርግጥ ነው፤ የተገኘው ድል የሚያስደስትና የሚያኮራ ነው፤ ሆኖም ”ህወሓት ተቀብሯል“ ለማለት አለመቸኮል ብልህነት ነው። ከአሁኑ የተጠናከረ ጥረት ካልተደረገ ህወሓት ለመንቀል የሚያስቸግር የሽብር ድርጅት ሊሆን ይችላል፤ ዛሬም በትግራይም ከትግራይ ውጭም ተባባሪዎች አሉት።

ህወሓትን ከISIS ጋር ሳነፃፅር ከሀይማኖት ጋር እያያዙ አጓጉል ትርጓሜ ለሚሰጡ አንባቢዎቼ ሽብርተኝነትን እኔ እንዴት እንደምረዳው ጥቂት ዓረፍተ ነገሮችን ልበል።

ሽብርተኝነት ሀይማኖት፣ ርዕዮተ ዓለም፣ ወይም ፍልስፍና አይደለም። ሂንዱ፣ ቡድሃ፣ አይሁድ፣ ክርስቲያን፣ … ኢአማኒን የሆኑ አሸባሪዎች ነበሩ፣ አሉ። ማርክሲስት፣ አናኪስት፣ ግራ ዘመም፣ ቀኝ ዘመም፣ ብሄረተኛ፣ ፋሺስት፣ ፀረ-ኮሎኒያሊስት፣ ፀረ-ካፒታሊስት፣ ዓለም ዓቀፋዊ የነበሩ ሽብርተኞች ነበሩ፣ አሉ። ለአብዛኛዎቹ ሽብርተኛ ድርጅቶች ሽብርተኝነት በራሱ ግብ አይደለም። ሽብር ለመፍጠር ብቻ ሲሉ የሽብር ጥቃት የሚፈጽሙ ድርጅቶች እምብዛም የሉም። ብዙዎቹ ሽብርተኛ ድርጅቶች ሊያሳኩት የሚፈልጓቸው – ለአንዳንዱ ሀይማኖታዊ፣ ለሌሎቹ ዓለማዊ – ግቦች አሏቸው።

እና ሽብርተኝነት ምንድነው?

ሽብርተኝነት ስትራቴጂ ወይም ታክቲክ ነው። ለአንዳንድ ድርጅቶች ሽብርተኝነት ቋሚ ”የትግል ስትራቴጂያቸው“ ነው። እነዚህ ድርጅቶች መንግስትና ሕዝብን በማሸበር ዓላማቸውን ማሳካት እንችላለን ብለው ያምናሉ። ለአንዳንድ ድርጅቶች ደግሞ ሽብርተኝነት እንደሁኔታው ገባ ወጣ የሚሉበት ታክቲክ ነው – ሁኔታው ሲመች ሰላማዊ፣ ሳያመች ደግሞ ከሽብርተኝነት ውጭ የሆነ የአመጽ ትግል፣ ሁኔታው በጣም ሲከፋ ለአጭር ጊዜ ሽብርተኛ የሚሆኑ ድርጅቶች አሉ። ”በስትራቴጂ“ እና ”በታክቲክ“ መካከል ያለው ዋነኛው ልዩነት ጊዜ ነው። ስትራቴጂ – የረዥም ጊዜ ስልት ሲሆን፤ ታክቲክ የአጭር ጊዜ ስልት ነው።

ስለሆነም ስለ ISIS ወይም አልቃይዳ ስጽፍ ድርጅቶቹ ስለሚከተሉት እምነት አይደለም፤ የኔ ትኩረት ”የትግል ስትራቴጂያቸው“ ነው።

ወደ ዋናው ርዕሴ ልመለስ። አንዳንድ የህወሓት ወዳጅ የውጭ አገር ”ምሁራን“ ህወሓት ወደ ሽምቅ ውጊያ ሊመለስ ይችላል እያሉ ነው። “ሽምቅ ውጊያ” በቀጥታ በሽብርተኝነት ማዕቀፍ ውስጥ የማያስገባ የአመጽ ትግል ነው። እኔ ከዚህ የተለየ ሀሳብ አለኝ። ህወሓት የሚገኝበትንት ጂኦ ፓለቲካ ከባቢን በማጤን፣ ድርጅታዊ ባህሉ፣ አቅሙና ልምዱን እግምት ውስጥ በማስገባት ህወሓት ልክ እንደ ISIS፣ አልቃይዳ እና ቦኮ ሀራም ዓይነት ሽብርተኛ ድርጅት ይሆናል። ህወሓት አቅም እስካለው ድረስ ከተሞችን በሚሳይል ከመደብደብ፣ ሕዝብ በበዛባቸው ቦታዎች ፈንጂዎችን ከማፈንዳት የሚያቅበው የሞራልም ሆነ የድርጅታዊ ባህል ልጓም የለበትም። በክፋት ከቀድሞዎቹ መሪዎች የባሱ ወጣት መሪዎች ከህወሓት ወጣት ክንፍ፣ ዓባይ ትግራይ፣ ትግራይ ነጻነት እና ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ይወጣሉ። ይህንን ሽብርተኛ ድርጅት ለመተባበር የሚፈቅዱ ቡድኖች በሁሉም ክልሎች ውስጥ አሉ። ISIS እና አልቃይዳም ወደዚህ ማትኮራቸው አይቀርም።

ስለሆነም የደህንነቱ መስሪያ ቤት ወገቡን ጠበቅ ያድርግ። በምርጫ ለመወዳደር የሚዘጋጁትን ፓርቲዎችን ለመሰለል የሚያጠፋውን ጊዜና ሀብት ቀንሶ ይህ አደጋ ስር ከመስደዱ በፊት ይከላከል። አደጋው ለቀጠናው አገሮች በሙሉ በመሆኑ የቀጠናው አገሮች ትብብር መጠናከር ይኖርበታል። በተለይ ደግም ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ጁቡቲ ግኑኝነታቸውን ከፍ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

የፀረ-ሽብር ትግሉ ከወታደራዊ መፍትሄ በተጨማሪ የፓለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ገጽታዎች ሊኖሩት ይገባል። ሽብርተኝነት አክሳሪ ስትራቴጂ ማድረግ የሚቻለው ፓለቲካችንን ከዘርና ከሀይማኖት መካረር ነፃ ስናደርገው ነው። የሰላም ሚኒስትር እጅግ ብዙ ኃላፊነቶችን ተሸክሟል፤ ለሸክሙ የሚመጥን ትከሻ ይኑረው። የእርቀሰላም እና የድንበርና የማንነት ኮሚሽኖችም ሥራ ይስሩ። ሲቪክ ማኅበረሰቡና ኃላፊነት የሚሰማን ዜጎች ሁሉ ለጊዜው መንግስትን ማጨናነቅ ትተን እንደግፈው።

የተገኘው ድል፤ ትልቅ ድል ነው – ሆኖም አንዝናና፣ አንዘናጋ!

One comment

 1. መላኩ ግርማ

  We need to investigate the underlying reason or the underlying reasons which led the Prosperity Party members in Benishangul Gumuz Regional State Peace and Security Office loose interest to carry out their sworn duties of defending victims of the ethnic-based attacks, which currently are said to be spiraling into ethnic cleansing? Why concentrate on opposition politicians too much, while failing to concentrate on the acting State Regional government officials and City government officials within Ethiopia?

  Benishangul Gumuz is where the eyes of the world is looking at due to the fact it is the region where GERD is being constructed. The Ethiopian Federal government needs to investigate if Egypt is bribing the Benishangul Gumuz Regional State Peace and Security Apparatus officials to not build their capacity to a level where they can defend ethnic based attacks,these Benishangul Gumuz officials might have reached a point where they lost interest to perform their duties because their duties get assigned to them by Egypt, not by Ethiopia.

  In the world we are living in now it is becoming more and more common for officials to accept bribes but in most parts of the world accountability exists the , almost all Federal Governments around the world do not let such treasons continue as the Ethiopian Federal government does let it continue by exercising forgiveness and patience. For example currently in USA, the city of San Francisco , California high level government officials are being punished by the Federal Government of USA for accepting bribes from foreigners compromising the national security of USA by a tiny bit. When it comes to National Security issues a tiny bit error causes the Federal Government of USA to mobilize all available resources and nip the tiny bit national security risk in the butt. Currently starting from the Mayor of San Francisco to the bottom level government officials who worked at their posts in the past or present are getting fully investigated by the Federal Government Law Enforcement Agencies of USA. Same needed to be done by the Federal Government of Ethiopia to all of the Benishangul Gumuz State government officials . We need to know who Egypt is bribing and make an example out of those who accepted bribes from Egypt because if we fail to do that there is no point in claiming GERD anymore, we should know we failed and Egypt won if we failed to find out why the Prosperity Party members assigned at the Benishangul Gumuz Regional State Peace and Security office , lost interest and lost the capacity to defend the victims of the ethnic based.

  https://www.sfchronicle.com/bayarea/article/FBI-raids-San-Francisco-home-of-PUC-chief-Harlan-15763755.php

  San Francisco Chronicle
  Mohammed Nuru and who? These are the key players in San Francisco’s expanding corruption scandal

  https://missionlocal.org/2020/11/puc-boss-harlan-kelly-arested-by-feds-charged-in-bribery-scheme/

  Department of Justice (.gov)
  San Francisco Trash Company Executive Charged With Bribing Company’s Chief San Francisco Government Regulator

Comments — What do you think?