Home » ዜና » በወንድማችን ብሩክ ማሞ (ህዝብ ባለው) ዜና እረፍት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን

በወንድማችን ብሩክ ማሞ (ህዝብ ባለው) ዜና እረፍት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን

Hizb Balew (Biruk Mamo)

በወንድማችን ብሩክ ማሞ (ህዝብ ባለው) ዜና እረፍት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልፃለሁ። (Hailu Mamo)

ብሩክ ማሞ (በከረንት አፌይር መጠሪያው ህዝብ ባለው) ከዚህ አለም በሞት የመለየቱን አሳዛኝ ዜና ሰምተናል። ብሩክ የሀገር ፍቅር ምን ማለት እንደሆነ ሆኖ ያስተማረ፣ የባንዲራን ፍቅር በምሳሌነት ያሳየ፣ የንባብንና የእውቀትን ጥቅም ያሳወቀ አይረሴ አርአያችን ነበር። ብሩክ የኢሳት ደጋፊ ብቻ ሳይሆን እስከመጨረሻው በቋሚ ደጋፊነት ያለማዛነፍ የዘለቀ፣ በሙኒክ ኢሳት ቤተሰቦችም ውስጥ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን እስከ ስፖንሰርነት ብዙ ያደረገ ወንድማችን ነበር። በትግሉ ሂደትም የለውጥ ፈላጊው ክፍል ደጋፊ ብቻ ሳይሆን እስከ አግ7 አባልነት ብዙ ብዙ አበርክቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ በታየው ለውጥ ምክንያት ከረጅም አመታት ወዲህ የሚሳሳላትን ሀገሩን ለማየት የበቃ ሲሆን ህልፈቱም እዚያው በሀገሩ ሆኗል።

(ከስር ያለው ምስል ከሰባት አመታት በፊት ህወሀት ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ስላለው ጥፋት ኢሳት ላይ ውይይት ስናደርግ የተነሳ ነው።)

Hizb Balew (Biruk Mamo)

Comments — What do you think?