Home » ዜና » በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የህወሃት ኃይል በሰላም እጁን መስጠቱን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ

በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የህወሃት ኃይል በሰላም እጁን መስጠቱን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ

በሶሮቃ እና ቅርቃር በተደረገ ውጊያ በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የፀጥታ ኃይል በሰላም እጁን መስጠቱን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ

Temesgen Tiruneh Dinku the President of Amhara National Regional State

Temesgen Tiruneh Dinku the President of Amhara National Regional State

ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የመከላከያ ሰራዊት በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና አባላት በተቀናጀ መልኩ ያደረጉት ተጋድሎ ስኬታማ ነበር ብለዋል::

በተለይም በትናንትናው ዕለት በሶሮቃ እና ቅራቅር ከእኩለ ሌሊት እስከ ረፋድ ተደጋጋሚ ማጥቃት ተሰንዝሮብን ነበር ያሉት አቶ ተመስገን፣ ከረፋድ በኋላ በተደረገ ማጥቃት በርካታ ቦታዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል::

“በተቆጣጠርናቸው ቦታዎች ያለው የህዝብ ድጋፍ ድንቅ ነበር:: በርካታ ያለፍላጎቱ እንዲዋጋ የተገደደ የፀጥታ ኃይል በሰላም እጁን ሰጥቷል“ ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ተመስገን አክለውም “እዋጋለሁ ብሎ የመረጠም ፊቱን አዙሮ እኛን ሲያግዝ ውሏል:: ጦርነት አንፈልግም ስንል ጠላታችን ድህነት ነው ከሚል እንጂ ጦርነት ካለማወቅ አይደለም:: ዛሬም በሌላ ድል ታጅቦ ያልፋል” ብለዋል፡፡

One comment

  1. ጢሞጢውሎስ

    በዛሬው ዕለት ሰላሳ ዘጠኝ ቀንደኛ የወያኔ አመራሮች ያለመከሰስ መብታቸውን ፓርላማው በማንሳቱ ግፍ ተሠርቶብኛል የሚሉ ከሳሾች ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች ወዲያውኑ ክስ ለመመስረት የፌደራል አቃቢ ህግ ቢሮን በክስ እና ካሳ ይገባኛል በሚል ሰነዳቸውን ይዘው ሰልፍ በመውጣት ፍርድ ቤትን እያጨናነቁ ከዳያስፖራ ሳይቀር በወኪል የወያኔ አመራሮች እየተከሰሱ ነው።

    ክስ የመመስረቱ ወረፋ ታይቶ በማይታወቅ የከሳሽ ህዝብ ብዛት እና የክስ አይነቶች በመሞላቱ ወደ ልዩ ልዩ ክልሎች ክስ ሰብሳቢ ተሠማርቶም የከሳሾች ስሞችን እና አድራሻን የመሰብሰብ ሥራ እንኳን አለመገባደዱ ምን ያህል ብዛት ያለው ህዝብ ተማሮ እንደኖረ ያሳያል። ክሳቸውን ስብስቦ ለመጨረስ ተጨማሪ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልግ ታዛቢዎች ጠቁመዋል።

Comments — What do you think?