Home » ዜና » አለማየሁ በላይነህ (ጉዱ ካሳ) ከዚህ አለም በሞት በመለየቱ አዝነናል (ECADF)

አለማየሁ በላይነህ (ጉዱ ካሳ) ከዚህ አለም በሞት በመለየቱ አዝነናል (ECADF)

ለሀገሩ እና ለወገኑ እጅግ ተቆርቋሪ የነበረው የመብት ተሟጋች ወንድማችን አለማየሁ በላይነህ (ጉዱ ካሳ) በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች የውይይት መድረክ (Ethiopian Current Affairs Discussion Forum) ከጅምሩ አንስቶ ለበርካታ አመታት በመላው አለም ተበትነው የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማሰባሰብ በህወሃት (ወያኔ) መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫናን መፍጠር ከቻሉ የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ልጆች ውስጥ ግምባር ቀደም ነበር።

“ጉዱ ካሳ የህወሃት (ወያኔ) የሚዲያ ሞኖፖሊን መስበር አለብን በማለት” እንደ ኢሳት ያሉ ከዲያስፖራ ወደ ሀገር ቤት ሊደርሱ የሚችሉ ሚድያዎች እንዲቋቋሙና ውጤታማ እንዲሆኑ የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ ኖሯል።

ወንድማችን አለማየሁ በላይነህ (ጉዱ ካሳ) ከዚህ አለም በሞት በመለየቱ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለትግል አጋሮቹ መጽናናትን እንመኛለን።

አለማየሁ በላይነህ (ጉዱ ካሳ)

3 comments

  1. ይህ ‘ጉዱ ካሳ’ በሚል የብዕር ሥም የሚፅፈው ነው? ወይንስ ‘ዳግማዊ ጉዱ ካሳ’ በሚል ብዕር ሥም የሚፅፈው ነው? ኧረ እየተስተዋለ! ያሳዝናል በለው!

  2. Zewdu Gebre-Hiwet

    ዳግማዊ ጉዱ ካሣ እያዝናና መልእክቶችን ማስተላለፍ የሚችል ግሩም ጸሃፊ ነበር። በ አጭር መቀጨቱ ለ ቤተሰቦቹ ብቻ ሳይሆን እኛም በ ድህረ ገጽ ብቻ የምናውቀው በጣም አዝነናል። እግዚአብሔር ነፍሱን በ ገነት ያኑርልን። ለ ቤተሰቦቹና ዘመዶቹ መፅናናትን ይስጥልን።

  3. ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

    ነፍሱን በገነት ያኑርልን፤ የልፋቱን ውጤት ሳያይ መሰናበቱ ቢያሥከፋም ሁላችንም ወደማንቀርበት ቀድሞን መሄዱ እንግዳ ነገር ባለመሆኑ ለቤተሰብና ዘመድ አዝማድ እንዲሁም ጓደኞቹና የሙያ አጋሮቹ መጽናናትን እመኛለሁ።

Comments — What do you think?