Home » ዜና » ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

በአዲስ አበባ ከተማ 22 አካባቢ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ እና በቴፒ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት የዜጎች ሕይወት በማለፉ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አመራሮች እና አባላት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን!

የሕግ አግባብን በተከተለ እና ግልፅነት ባለው መንገድ ሕግ እና ሥርዓትን ማስከበር ሲቻል ጨለማን ተገን በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ 22 አካባቢ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የተያዘን ቦታ ለማስለቀቅ በሚል በተወሰደው የኃይል እርምጃ የሁለት ወጣቶች ሕይወት ተቀጥፏል፡፡ የወጣቶቹን ሕይወት ያጣነው ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በቂ ጥረት ሳይደረግ በተወሰደ የኃይል እርምጃ መሆኑ እጅግ አሳዛኝ እና አሳፋሪ ነው፡፡

በቴፒ ከተማም በተቀሰቀሰ ግጭት የዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፤ በርካቶችም ቆስለዋል! በአካባቢው ያለው ችግር ለረጅም ጊዜ ሲንከባለል የከረመ ሲሆን በየጊዜው እያገረሸ ዜጎች ላይ ለሚደርስ ጉዳት ምክንያት እየሆነ ነው፡፡ መንግሥት በአካባቢው ያለውን ችግር ትኩረት ሰጥቶ በመፍታት ሰላም የማስፈን እና የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊኑቱን እንዲወጣ ስንል እናሳስባለን::

ኢዜማ የፀጥታ አካላት ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር በሚሠሩበት ጊዜ ሁሉ የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች እዲያክብሩ እና ዜጎችን ከጥፋት እንዲጠብቁ የተሰጣቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ እናሳስባለን! መንግሥት ሕዝብን የመጠበቅ ግዴታቸውን የማይወጡ እንዲሁም ለዜጎች መጎዳት እና መበደል ምክንያት የሆኑ አካላትን አጣርቶ በአስቸኳይ ለሕግ እንዲያቀርብ እና ለሕዝብ እንዲያሳውቅ አጥብቀን እንጠይቃለን!

ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች ልባዊ መፅናናትን እንመኛለን!

ጥር 28፣ 2012 ዓ.ም
የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት

3 comments

 1. In Abiy Ahmed & Co.’s fictionary Dictionary :

  Accusing Querro as a terrorist group= Hateful and also lie spreading Speech made with intention to bring unrests.

  Saying One ethnic only Oromo holds the key leadership positions in the national security apparatus (dehninet INSA… ) = lie spreading speech made with intention to bring unrests.

  Saying one ethnic only Oromo holds the key leadership positions in the Federal Police = Hateful and also lie spreading speech made with intention to brings unrests.

  Saying one ethnic only Oromo holds the key leadership positions in the Ethiopian AirForce = Hateful and also lie spreading speech made with intention to bring unrests.

  SAYING ONE ETHNIC ONLY OROMO HOLDS THE KEY FEDERAL GOVERNMENT LEADERSHIP POSITIONS = HATEFUL AND LIE SPREADING SPEECH MADE WITH INTENT TO BRING UNRESTS.

  Saying Chief federal Prosecutor Berhanu Tsegaye does not have legal authority to arrest , interogate , sue , prosecute the same persons all by himself = Hateful and lie spreading speech made with intent to bring unrests.

  Saying one ethnic only Oromo holds the key federal city Addis Ababa leadership positions = Hateful and lie spreading speech made with intent to bring unrests .

  WHILE PM Abiy Ahmed is saying
  “We deported TPLF out of Addis Ababa and we will not let them return to Addis Ababa” is not a hate speech .

  Saying “we deported TPLF out of Addis Ababa and made them the government of killil one Tigray region so Oromo owns Addis Ababa without a contender ” is not considered a hateful speech with intent to bring unrests

 2. #DoNotSellNileInMyName

  –Shouting for the dead is not going to bring the dead back to life .
  –Shouting for the dead doesnot protect the once that are next in line to be murdered .
  –Shouting is what the genocider Muktar Kedir want us to do, so he can aim his target.
  -Both Abiy and Jawar are Muktar Kedir’s mercinary goons.
  -Abiy is as guilty as Jawar .

  SHOUTING FOR ABAY WATER IS WHAT WE SHOULD DO NOW ASAP ,
  EVERY SECOND MATTERS !!!!!!

  WATER IS LIFE!!!

  By the year 2050 Ethiopia’s population is expected to be close to 175,000,000 and by the year 2100 Ethiopia’s population is expected to be at least more than 300,000,000 ( three hundred millions) .

  If rights from Abay water is sold to Sudan and Egypt, then future generations of the north Westerners Orthodox Ethiopians will have to rely on water they get from further South and further Eastern part of the country, the areas where all the anti Orthodox anti Amara sentiment is brewing now.

  With relying on water from the Jihadist sentiment they will be forced to convert to Oromo Gadda since they will be unable to survive without water.

  The fathers of OPDO Muktar Kedir along with Abadulla Gemeda are preaching Gadda right now with Workneh Gebeyehu hunting down Orthodox refugees in Kenya refugee camps . While all these is done Their psychopath agent Abiy is finalizing the selling of Abay , instigating the war between Eritrea and Amara and Tigray while northern Ethiopians are too busy protesting about 21 abducted while not protesting about the future generations hundreds of millions of Orthodox Ethiopians state sponsored attack jihad that is in the making right now .

  #DoNotSellNileInMyName

  ecadforum.com/Amharic/archives

 3. ለክብርት መዓዛ አሸናፊ
  የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት
  አዲስ አበባ
  ————–
  ክብርት ሆይ!
  በአአምስት የተለያየ ጎሳ አባላት በተሰጠኝ ውክልና ይህን የምፅፍለዎት። የአምስታችን በብዕር ስማችን
  ቦተሬ ሀማቱራ
  ሁንዴሳ ድጉማ
  ጠንክር በርሔ
  ጎይቶም ዲሜጥሮስ ወልደሚካኤል
  ምንዳርያለው አገሬ
  እንባላለን
  በተሰጠኝ ውክልና የፃፍኩት ግን
  ሁንዴሳ ምንዳርያለው ጎይቶም
  እባላለሁ።

  ተፃፈ በጥር ወር 2012 ዓም
  ——+++———
  ሁንዴሳ ምንዳርያለው ጎይቶም

  ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት
  ———++——
  ውድ ክብርት ወሮ መዓዛ አሸናፊ!
  የፍትሕ ስርዓቱ፣ የፍትሕ ሁኔታ ፣ ዳኝነት በሁሉም ደረጃ በተለይ በመጀምርያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች እጅግ በጣም አሳዛኝ፣ አሳሳቢ እና አሳፋሪ ደረጃ ላይ ይገኛል። የዳኞች እና የጠበቆች ዕውቀት ሰማይና ምድር ተሉያይቷል። አንድ እገሌ ተብሎ ስሙ በጥሩ የሚጠራ እውቀት ሆነ ስነምግባር ያለው ዳኛ የለም። አንድ እገሌ ተብሎ ስሙ በመልካም የሚጠራ ዳኛ ለመሾም አልቻሉም ወይም አልፈለጉም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ደም እያለቀሰ ነው። ብዙ ጠበቆች የዳኛ ጉቦ አቀባይ ሆነዋል። ባለጉዳይ ጠበቃ ዘንድ ሄዶ ዳኛውን ታውቀዋለህ ወይ ብሎ ነው የሚጠይቀው። ባለ ጉዳይ የሚፈልገው ዕውቀት ስነምግባር ያለው ጠበቃ ሳይሆን ጉዳይ አስፈፃሚ ጉቦ አቀባይ ደላላ ሆኗል።ልደታ እና ጦር ኃይሎች አካባቢ ያሉ ደላሎችም በዚህ ስራ ተሰማርተዋል። የከፍተኛው ፍርድ ጦር ኃይሎች ያለውን ያላለቀ ሊፍት ያልነበረው ፎቅ ለአምስት ዓመታት በስምንት መቶ ሺህ ብር ገደማ በወር የተከራየው በኮበለሉት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በነበሩት ዘመድ ደላላ መሆኑን እርሰዎም ያውቃሉ። ለአምስት ዓመታት ስምንት ሙቶ ሺህ ብር በስልሳ ተባዝቶ የተከፈለው ገንዘብ ለህንፃው ከወጣው ገንዘብ በላይ ነው።
  ክብርት ሆይ!
  ቀደም ሲል ዳኛ የነበሩ ለጉቦ አቀባይነት በጣም ይፈለጋሉ። ምርጥ ጉቢ አቀባይ ናቸው።

  ክብርት ፕሬዝዳንት!
  በአሁን ወቅት ግምድል ፍርድ መፍረድ የዕለት ተዕለት ያላሰለሰ ተግባር ሆኗል። ለመድኃኒት፣ ለናሙና አንድ ሐቅ በሐቅ የተፈረደ ፍርድ የማይገኝበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። በመጀመርያ ደረጃ እና ክፍተኛ ፍርድ ቤት ጉቦ የማይፈልግ ዳኛ የለም። በጠራራ ፀሐይ ዝርፊያ ሆኗል። ሌብነታቸውን ለመሸፈን ስድብ ይቀናቸዋል። ችሎቶች በጣም ይደብራሉ። በሚዘገንን ሁኔታ በፍትህ እየተቀለድ ነው። ያሁኑን ያህል በዚህ ከፍተኛ ደረጃ በደርግም ጊዜ በፍትህ አልተቀለደም። ደርግ ዳኞችን እንደ አሻንጉሊት አላላገጠባቸውም። ደርግ እዚያው ራሱን ችሎ ግፍ ሰራ እንጂ ፍርድ ቤትን የግፍ መሳርያ አድርጎ አልተጠቀመም። ወያኔ ነው የፍትህ ስርዓቱን ብልሽትሽቱን ያወጣው። እርሰዎ ስልጣን ላይ እንደወጡ የኢትዮጵያን ህዝብ በወያኔ የ27 ዓመታት ያስሉቀሰውን ፍርድ ቤት ግልብጥብ አድርጌ በበጎ መልኩ እቀይረዋለሁ ብለው ቃል ገብተው ነበር። ሁለት ዓመታት ሊሆነው ነው። ምንም አልታየም።እስካሁን አንዲት እርምጃ አልተራመዱም። ምንም የቀየሩት ነገር የለም። ያንኑ የተግማማ ፍርድ ቤት ይዘው ቢሮ ይገባሉ፣ ይወጣሉ፣ ወር ጠብቀው ደመወዝ ይወስዳሉ። ውጭ ሀገርም ይሽከረከራሉ። በቲቪ በጋዜጣ ምንም ሳይሰሩ መግለጫ ኢንተርቪው ይሰጣሉ። ያሳዝናል!
  ክብርት ወሮ መዓዛ
  ለአንድ ደቂቃ ቆም ብለው ባለፉት ከአመት በላይ ጊዜያት ምን ሰራሁ ብለው ራስዎን ይጠይቁ። ምንም አልሰሩም። ዕውቀት ያለው ዳኛ አልመደቡም። አሁንም ካድሬ ዳኞችን ይዘው ነው የሚተራመሱት። አሁንም ጉቦኞቹን ይዘው ነው በቲቪ በጋዜጣ መግለጫ የሚሰጡት።
  የእኔ እመቤት!
  ለአንድ ደቂቃ ቆም ብለው ምን አዲስ ነገር አመጣሁ ብለው ራስዎን ይጠይቁ። ብዙ ሰዎች ገና ሲሾሙ ራሳቸውን ይዘው ፍትህ ተቀበረ እያሉ ስጮሁ እኔ አልተቀበልኳቸውም ነበር። እርስዎን ደግፌ ሙግት ገጥሜያለሁ እኚህ ሴት በሴቶች የጠበቆች ማህበር፣ በእናት ባንክ ዙርያ የታወቁ ናቸው። ለውጥ ያመጣሉ ብዬ ተስፋ ጥየበዎት ነበር። ግና አልሆነም። ይመሻል ይንጋል። ምንም ለውጥ የለም። የበፊቱ ፕሬዝዳንት ማን ዳኜ ነው የሚባሉት ተነስተው የእርስዎ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መሆን በርኖስ ቢገለብጡት በርኖስ፣ ቂጣ ቢገለብጡት ቂጣ ሆነብኝ። ለአንድ ደቂቃ ቆም ብለው የማጊሉ ምሩቅ እነ አፈንጉስ ተቮመ ኃይለማርያም የተቀመጡበት ወንበር ላይ ነው የተቀመጥኩት ብለው ሊከብዱዎት ሰቅጠጥ ሊሉ ይገባል። ትንሽ ደንገጥ፣ ምን እየሰራሁ ነው፣ ምን ለውጥ አመጣሁ፣ ምን አሻሻልኩ ብለው ሊቸገሩበት ይገባል። ነገ ከነገ ወድያ ታሪክ ሆኖ ዝምብላ ከምንም ተንስታ ላይ ተሰቀለች አንቀላፍታ አንኮራፍታ ወረደች የሚል ስም የሚያሰጠዎትን የቁልቁለት መንገድ ጀምረውታል። በየቀኑ እንደውም በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ የሚታይ ልውጥ ያካሂዱ። ፍርድ ቤት ሪፎርም ሳይሆን ሪቮሉሽን ነው የሚያስፈልገው። ወያኔ በሀያ ሰባት ዓመት ውስጥ ቅርንት ግምት እስኪል በከፍተኛ ደረጃ ያጠነባው ተቋም ፍርድ ቤት ነው። እርሰዎ ደግሞ የዚህ የጠነባ ተቋም የመጨረሻው ትልቁ ባለስልጣን ከሆኑ ዓመት አለፈ። የፍርድ ቤቶች ግማት መጥፎ ሽታ ቅርናት እርሰዎ ከመምጣትዎ በፊት ከነበረው አምስት ስድስት እጥፍ ጨምሯል።
  በአስቸኳይ እራስዎን ያስተካክሉ። ሊወድቁ፣ ሊባረሩ ጫፍ ደርሰዋል። ከተባረሩ በኋላ ከሚቆጩ ስልጣኑ በእጅዎ እያለ ለውጥ ያምጡ።

Comments — What do you think?