Home » ዜና » ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ መገደላቸው ተገለጸ

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ መገደላቸው ተገለጸ

Ethiopian Army officer Brigadier General Asamnew Tsige.

(BBC Amharic) — ቅዳሜ ዕለት ባህር ዳር ውስጥ ተሞክሯል የተባለውን “መፈንቅለ መንግሥት” መርተዋል ተብለው ሰማቸው የተጠቀሰው የአማራ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ብርጋድየር ጄነራል አሳምነው ጽጌ መገደላቸው ተዘገበ።

ብሔራዊው ቴሌቪዥን እንደገለጸው ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ባህር ዳር ዙሪያ በሚገኝ ዘንዘልማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን አሳውቋል።

የኢቲቪ ዘገባ ጄነራሉ በምን ሁኔታ በጸጥታ ኃይሎች እንደተመቱ የገለጸው ነገር የለም። ዜናው እንዲሁ በጥቅል መመታታቸውንና ህይወታቸው ማለፉን ብቻ ነው የገለጸው።

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ የተወለደው ያደጉት ወሎ ላስታ ውስጥ ነው። አሳምነው ወደ ትግል በመግባት የወቅቱን ኢህዴን በኋላ ብአዴን የተባለውን የአማራ ድርጅትን ከመቀላቀላቸው በፊት በደሴ ከተማ በሚገኘው የመምህራን ኮሌጅው ውስጥ መምህር ሆነው አገልግለዋል።

ወታደራዊው መንግሥት በአማጺያኑ ከስልጣን ከተባረረ በኋላ በትውልድ አካባቢያቸው አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመው ነበር።

በማስከተልም ወደ መከላከያ ሠራዊቱ ገብተው በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የድንበር ጦርነት ውስጥ ተሳታፊ ሆነው ነበር። ወደ አሜሪካ በመሄድ ወታደራዊ ትምህርት የተከታተሉት አሳምነው ከጦርነቱ በኋላ የጄኔራልነት ማዕረግ አግኝተው በሠራዊቱ ውስጥ በኃላፊነት ሲያገለግሎ ቆይተዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው የመከላከያ ሠራዊቱን ኮሌጅ በበላይነት በመምራትና በማስተማር እንዳገለገሉ ይነገርላቸዋል። ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው በ2001 ዓ.ም ከሌሎች ወታደራዊ መኮንኖች ጋር መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ በማሴር ታስረው ነበር።

ጄኔራሉ በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ስለተባሉ ማዕረጋቸው ተገፎ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ለዘጠኝ ዓመታት በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ከእስር ተፈትተው ለሃገራቸው የከፈሉት መስዋዕትነትን እውቅና በመስጠ ማዕረጋቸው እንዲመለስና የሚያገኙት ጥቅም እንዲከበርላቸው አድርገዋል።

የአማራ ክልልም ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌን ተጠሪነታቸው ለክልሉ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለአጭር ጊዜ በቆዩበት የአማራ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመት ሰጥቷቸው ነበር።

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም የተሞከረውና የክልሉን ፕሬዝዳንትና የሃገሪቱን ጦር ኃይሎች ኤታማዦር ሹምንና የሌሎች ሁለት ከፍትኛ ባለስልጣናትን ህይወት ከቀጠፈው የመፈንቅለ-መንግሥት ሙከራ ጀርባ እንዳሉ የክልሉ ገዢ ፓርቲ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አስታውቋል።

የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ኃላፊነቱን የተረከቡት አቶ ላቀ አያሌው ለክልሉ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ጄኔራሉንና ሌሎች የድርጊቱ ተሳታፊዎችን ለመያዝ የጸጥታ ኃይሎች እየሰሩ መሆኑን አመልክተዋል።

3 comments

 1. SURVIVORS THAT ARE ON THE RUN WANT ALL TO KNOW THE FOLLOWING TRUTH:

  General Asaminew was the chief of Amara region’s security forces which he gladly accepted the position to serve the people. The major problem arose when the federal government obstructed General Asaminew from performing his duties by systemic bureaucracy during the Debre Berhan ATAYE area massacre.
  FEDERAL GOVERNMENT briefly sent Federal forces to Debre Berhan ATAYE area for the sole reason of fighting General Asaminew if he tried to perform his duty while the Debre Berhan area massacre was going on . Federal controlled the area just so General Asaminew Tsige doesn’t try to save the victims.
  Amara regional government told General Asaminew to not go in the massacre area at the time thinking Federal had acted to save the people, while the only reason the federal military was there at that massacre was “to stop Asaminew by any means necessary” as the military communications evidence obtained by Saere then shared with Asaminew revealed.

  General Asaminew raised this issue and had showed his concrete evidences that incriminated Abiy’s direct involvement that clearly can send Abiy to face the death penality for many charges including treason and even the Amara regional government would have faced severe legal consequences for listening to the Federal and continuing to stop General Asaminew from saving the victims while even after it became clear for all that Federal forces were not saving the victims of the massacre. This action of obstructing General Asaminew from performing his constitutional duty during the Debre Berhan area massacre was the ultimate example of how this ethnic Federalism government system has failed.

  Abiy was not about to let this evidence go around.Ambachew ADP called the urgent meeting to find out how severe the allegation of the crime was, to find out what legal consequence ADP faces if this evidence reached the courts and Abiy once again saved his skin by taking out those that were in the position to testify the truth and destroyed his personally incriminating evidence. It is said Abiy even got his own father assassinated for consistently raising several questions to him about the events that took place during the Debre Berhan ATAYE massacre.

 2. Debela

  Very perceptive comment.Now according to our culture let us respect the family of the deceased to mourn their loved ones.Some are engaged in to writing and discussing their views in public which may not be appropriate at this moment.We need to be minded also opponents are using this occasions for propaganda consumption, or desperately trying to link the situation in that happened in Baheirdar and Addis,when the two situations are entirely separate. The struggle of all Amara people under the appropriate motto of ” One Amara for all Amara”must pick up where general Asamenew left over.

  The current situation must bring all of us together than any where,and need to reach for our people. Diaspora must begin to engage in a fresh diplomatic task force in accurately informing the situation in the country to the out side world the danger posed by extremism.There is a great need to solicit funds from friendly states such as the state of Israel and civic organizations for the needs of our people.

  The task of informing the diplomatic community and international organizations must start from the present crisis.Ethiopian nationals of both Amara and Tegrians are now being targeted by the extremists as just happened these week by the death of there high ranking military officers,and civilians in Bahirdar.This naturally can bring a working relationship between the people of Tegray and Amars,as well as the traditional oromo society,particularly that of the Christina community.

  In just a year, while we were sleeping, and much unnecessary ground being given, the cheese master,Abiy Ahmed, who probably read spy tiller,has made a tremendous stride to impose extremism upon the rest us.Amaras have a natural right to defend ourselves
  as well as Ethiopians

 3. በእውነት ለመናገር የጀነራል አሳምነውን መገደል በመስማተኢ እጅግ በጣም ነው ያዘንኩት

  በባህር ዳር ላይ የተደረገውን ድርጊት ለመገመት (you don’t need no special brain) ድርጊቱ በማን እንደተካሂደ የሚያሳዩን ብዙ ነገሮችን መጥቀስ ይቻላል ( ሲራው በ OPDO እና በመሪዉ ዐብይ አህመድ እጅ ለመሆኑ)
  Questhon- How many governments do we have in Ethiopia ? I thaught it is only one country called Ethiopia.
  በመጀመሪያ ቀደም ያሉ መረጃዎችን
  1- በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በ OPDO chairman ዐብይ አህመድ የሚደገፈው የኦነግ አሽባሪ ወንበዲዎች በሰሚን ሽዋና በወሎ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ዚጎችን መግደላቸውና አብያተ ክርስትያናትን ማቃጠላቸውና መዝረፋቸውን በአደባባይ ያየነው ሃቅ ነው
  2- ከላይ የተጠቀሰውን ድርጊት የፈጸሙ የኦነግና መንግስት ነኝ የሚለው OPDO ወንበዲዎችን ድርጊት የሚከታተለውን የጽጥታ ኮሚቲ የመሩትና የወንበዲ ድርጊቱ ተጠረጣሪ የተባሉትን ስዎች በቁጥጥር ስር አድርገዉ ምርመራውን እንዲካሂድ እያደረጉ ከነበሩት መሀክል 1- ጀነራል አሳምነው 2- ጀነራል ተፈራ 3- የፖሊስ ኮሚሽነር አበረ ነበሩ
  3- የጀነራል አሳምነው አቁአም በተለያየ ጊዚ ያደረጉአቸውን ንግግሮች እንደስማነው ለ OPDO እና ለዐብይ የቁጭ በሉ ጥሩንባ የማይሸነፉ ጥሩ ኢትዮጵያዊ እንደነበሩ ቅንጣት ያህል ጥርጥር የሊለው ገሃድ ሃቅ ነው በአጠቃላይ ለተፈጥሮአዊ GOD GIVEN ነጻነታቸዉ ከማንም ጋር የማይደራደሩ የማያጎበድዱ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ለመሆናቸው ጥያቂ ውስጥ የማይገባ ነዉ

  ከሰኒ 15 2011 ጀምሮ ያለዉን ሁኒታ
  1- የአብይ አህመድ ጸሃፊ ፈጣን ጋዚየጣዊ መግለጫ የመስጠት ችኮላ
  2- የመክላከያ ኢታማጆር ሹሙ በተመሳሳይ ሰዐት አዲስ አበባ ላይ መገደል
  3- ኢታማጆር ሹሙን የገደለዉን ጠባቂውን በቁጥጥር ስር አደረግነዉ ብለዉ አሁን ደገሞ መሞቱን መናገራቸዉ
  4- እንደሚባለዉ የፊደራል መንግስቱ ሰዎች በስብሰባዉ ግዚ ባህር ዳር እንደነበሩ ነው ትክክል ከሆነ ለምን አስቀድመው ሊገኙ ቻሉ?
  5- ሚስጥር እንዳይወጣ በኢንተለጀንስ ስራ ላይ መጠፋፋት ስላለ ከኢታማጆሩ ጠባቂ መሞት ሊላ የገደሉት ሰዉ አለመኖሩ ምን ማረጋገጫ አለ

  by adding all the above evidences 1+1
  የነዐብይ አህመድ OPDO MAFIA መንግስት እራሱ አማራ ብሎ በሚጠራው ክልል የነጀነራል አሳምነውና ሊሎችም እትዮጵያዉያን ጝዶቹ ለOPDO ሲራና ተንኮል አጸፋ ለመስጠት መዘጋጀት እንደዉም ካንድ ሳምንት በፊት በነጀነራል አሳምነዉ የስለጠኑ የክልሉ ልዩ ሃይል ምረቃና በምረቃዉ ወቅት የተደረጉት ቆራጥ የሆኑ ንግግሮች ባጠቃላይ የአማራ ክልል እየተባለ በሚጠራው ህዝብ ውስጥ ያለው ለተፈጥሮአዊ መብቱ ያለው ቆራጥ አንቅስቃሲ እንቅልፍ እንደነሳቸው ግልጽ ነዉ የዚህ ሕዝብ አንድነትና መነሳት ደግሞ የኪኛን የፖለቲጃ ወረበሎች የአዲስ አበባ ላይ የይገባኛል ጩህትንም ሆነ ኢትዮጵያውያንን ክገዛ አገራቸዉ ላይ ወራሪ መጢዪአ እያሉ የማፈናቀል ወንጀል በሚገባ አደብ ሊያስገዛ የሚችል ዋናው የኢትዮጵያዉያን መመኪያና ብዙሃን ሃይል መሆኑን ስለሚያውቁ ለዚህ ነዉ በነ ጀነራል አሳምነዉ ላይ የዘመቱት

  የጀነራል አሳምነውንም ሆነ የሊሎቹ ኢትዮጵያውያን የዚህ የ OPDO እና የዐብይ MAFIA መንግስት የሞት ስለባ ለሆኑት ነፍስ ይማር እያልኩ ባሁኑ ሰዐት ህገራችን ኢትዮጵያ ክወደቀችበት አስፈሪ አረንቕ ውስጥ ለማዉጣት ክነዐብይ አሀመድ የቁጭ በሉ የፍቅር ፖለቲካ ወጥተን እያንዳንዱ ስው በተፈጥሮ አምላክ ለስጠው ነጻነቱ ያለምንም ማወላወል ተባብሮ መቆመ አለበት
  ለለውጡና ለሰላም ሲባል እያሉ እነአብይና ተለጣፊዎቻቸው የሚያወሩልንን ጡሩንባ ወደ ጎን ትተን በጋራ ተነስተን የተፈጥሮ መብታችንን ማስክበር መቻል አለብን ወገኖቻችን ኢትዮጵያውያን ዚየጎች ከገዛ አገራቸዉ ላይ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎችና በአዲስ አበባና አካባቢዋ ጭምር ወራሪና መጢዪ እየተባሉ እየተፈናቀሉ መግቢያ እያጡ በዐይናችን እያየን ስለምን ሰላም እንደምናወራ ግልጽ አይደለም unless እኒን የሚያፈናቅለኝ እስካልመጣ ድረስ ስላም ነው ዝም ብዪ መኖር አለብኝ የሚል አስተሳሰብ የምንጝዝ ከሆነ በጣም ተሳስተናል ስለስላም የምናወራ ከሆነ አንድም ኢትዮጵያዊ ወገናችን ክገዛ ሃገሩ ላይ እንዳይፈናቀል ተነስተን በአንድነት ላይ መቆም አለብን የሊላው ስሚት የኛም ሊሆን ይገባል ምክንይቱም ፈጣሪ ሰዎችን ሲፈጥር ሁሉንም እኩል መብት ስጥቶ ነው የፈጠረው አንዱ አኒ ነኝ ህጋዊ አንተ ህጋዊ አይደለህም የማለት ማንም የስጠው ስልጣን የለም ደግሞስ ሊላዉን ሲያፈናቅሉ እያየን ለስላም ሲባል ነዉ እያልን ዝም ብለን ማየታችን ነገ በኛ ላይ እንደመይመጣ ምን ማረጋገጫ አለን ?

  አምላክ እትዮጵያና ሕዝቦችዋን ይጠብቅ!!!

Comments — What do you think?