Home » ዜና » ጠ/ሚ አብይ አህመድን ለመግደል የተደረገውን ሙከራ ኦነግ እንዳቀነባበረው ተገለጸ

ጠ/ሚ አብይ አህመድን ለመግደል የተደረገውን ሙከራ ኦነግ እንዳቀነባበረው ተገለጸ

ከፋሲል የኔአለም

Ethiopian government accused OLF for July, 2018 bomb explosion.

ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓም ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ለመግደል የተደረገውን ሙከራ ኦነግ እንዳቀነባበረው አቃቢ ህግ ገልጿል። ምክንያታቸው ደግሞ አገሪቱ በኦነግ መመራት አለባት የሚል ነው። የግድያው አቀናባሪም ገነት ታምሩ (ቶለሺ ታምሩ) የምትባል ናይሮቢ የምትኖር ሰው መሆኗን አቃቢ ህግ ገልጿል። ይህ መረጃ ትክክል እንደሆነ ባምንም አጠቃላዩን ምስል ያሳያል የሚል እምነት ግን የለኝም። ከዚህ ሙከራ ጀርባ ኦነግ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ አክቲቪስቶችና ህወሃትም ሊኖሩበት እንደሚችል አስባለሁ።

ህወሃት በመቀሌ ለኦነግ ያደረገው አቀባበል ለግድያ ሙከራው የቀረበ የምስጋና ዝግጅት አድርጌ እቆጥረዋለሁ። ህወሃት ኦነግን በአብይ መንግስት ላይ ለማስነሳት እቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለጽ የቆዬ ነገር ነው። በቡራዩና የተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች የተፈጸሙ ጭፍጨፋዎች የመንግስት ግልበጣው አንድ አካል እንደሆነ ከኦነግ የሁዋላ ታሪክ ተነስተን ብንናገር ‘አላዋቂ” አንባልም።

ከዚህ የግድያ ሙከራ ጀርባ ግን ኦነግ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ “አክቲቪስት” ነን የሚሉትም እጃቸው እንዳለበት መገመት አያዳግትም። በእነዚህ አክቲቪስቶችና በኦነግ መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየ ጸብ ነበር። በቅርቡ እንኳን ” ቄሮ የማን ነው?” በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ከፍተኛ ውዝግብ ፈጥረው ሲዘላለፉ እንደነበር እናስታውሳለን። የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን ለአመታት በእነዚህ “ አክቲቪስቶች” በሚመራው ሚዲያ ቀርቦ አያውቅም ። መግለጫቸውን ስለማያወጡላቸውም ኢሳት ነበር የሚያስተናግድላቸው። ታዲያ እንዲህ ለሞት ይፈላለጉ የነበሩት ሃይሎች እጅና ጓንት እንዲሆኑ ያደረጋቸው በአብይ መንግስት ላይ ያላቸው የጋራ ጥላቻ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም። እነዚህ አክቲቪስቶች አብይን “አጭበርባሪ፣ ደካማ፣ አድርባይ” እያሉ በመዝለፍ አብይ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳያገኝ ከፍተኛ ስራ ሲስሩ ቆይተዋል። እንደነሱ ምኞትማ አብይ አይደለም ጠ/ሚኒስትር የወረዳ አስተዳዳሪ እንኳን እንዲሆን አይፈቅዱለትም ነበር። አብይ ከእነሱ አቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወደ ስልጣን ከመጣ በሁዋላ የተከተሉት አማራጭ ደግሞ አገርቤት ገብቶ ሴራ በመጎንጎን የአብይ ራዕይ እንዳይሳካ ማድረግ ነው። ኦነግን አካተው 6 ድርጅቶች ያወጡት መግለጫ በኢሳትና በግንቦት7 ላይ ያነጣጠረ ቢመስልም፣ ዋና ኢላማው የአብይ መንግስት እንደሆነ ማንም አይስተውም። ከዚያም አልፎ “ በአንድ አገር ሁለት መንግስት አለ” እያሉ የአብይን መንግስት ሲንኳስሱ እና ደካማ ተደርጎ እንዲቆጠር ከፍተኛ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ እየታዘብናቸው ናቸው።

እንደሚታወቀው የአነግ ዋና መቀመጫ ከአስመራ ቀጥሎ ናይሮቢ ነው። አንዳንድ አክቲቪስቶች ደግሞ ናይሮቢ ሲመላለሱ እንደነበር ራሳቸው ተናግረዋል። እነዚህ ሰዎች ናይሮቢ የተቀመጠውን የኦነግ ክንፍ ለማነጋገር ካልሆነ በስተቀር ከኬንያ መንግስት ጋር ለመነጋገር ሊሄዱ አይችሉም ። ከኦነግ በተጨማሪ ህወሃትም በናይሮቢ ጠንካራ ህዋስ አለው። ሁለቱ ሃይሎች ናይሮቢ ላይ እየተገናኙ ሊመካከሩ የሚችሉበት እድል ከፍተኛ ነው። ህወሃት በቀጥታ ከአብይ መንግስት ጋር ከመፋለም ለተለያዩ ጸረ-አብይ ድርጅቶችና ግለሰቦች የፋይናንስ ድጋፍ እያደረገ በእጅ አዙር ለመፋለም መምረጡን እየታዘብን ነው።

የአብይ መንግስት ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለ እንደሆነ እረዳለሁ። እነዚህን ሰዎች የሚፋለምበት ትክክለኛ ጊዜ እየመረጠ እንደሆነም አስባለሁ። ጠላትን የምትፋለምበትን ትክክለኛ ጊዜ መምረጥ ተገቢ ነው። ያ ትክክለኛ ጊዜ እስኪመጣ ግን የእነሱ ጊዜ ደርሶ የከፋ እርምጃ እንዳይወስዱ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው። በመንግስት መስሪያቤቶችና በጸጥታ ተቋማት ውስጥ ያሉትን የህወሃትና የኦነግን ህዋሶች መበጣጠስ ቀላል ስራ ባይሆንም በጥንቃቄ ከተሰራ ማጥራት ይቻላል።።

እነዚህ ሰዎች ከልክ በላይ የሚጮኹት ወንጀላቸውን ለመሸፈን መሆኑ ግልጽ ነው። ወንጀል እና እውነት ግን ተደብቆ አይቀርም። አብይ መስቀልን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልዕክት ላይ ይህንኑ እውነታ እንዲህ ሲል ገልጾታል፦ “ እውነት የቱንም ያህል ዘመን፣ በምንም ያህል ውሸትና ቅጥፈት- ተንኮልና ሤራ፣ በየትኛውም ስልጣን እና ክፋት ብትሸፈንም በዘላቂነት ልትቀበር እንደማትችል አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ ለጥቂት ጊዜ ፀሐይን እንደሚሸፍን ደመና እውነትን ለተወሰነ ጊዜ መከለል፣ ውሸትንም እውነት ማስመሰል ይቻል ይሆናል፡፡ በመጨረሻ ግን እውነት እንደምታሸንፍና ከተቀበረችበትም ወጥታ ቀባሪዎቿን እንደምታሳፍር ለማስረዳት የክርስቶስ መስቀል ታሪክ ግሩም ማስረገጫ ነው፡፡”

የአብይ ራዕይ ለኢትዮጵያ መድህን ነው።

One comment

 1. This article gave no detail save these three lines about culprits of the assassination of P/M Abiy.

  “”The charges say the five acted on the premise that Prime Minister Abiy Ahmed is not popular among Oromos, Ethiopia’s largest ethnic group, and wanted to pave the way for the once-banned Oromo Liberation Front”.

  In our times many love to suppress the truth. Nevertheless, no matter how often we try to spin, deceive,misinform no one has power to permanently muzzle it. In due time it is the nature of truth itself to come to the fore and dispel the darkness lies and deceit.We know now the master mind behind the assassination attempt against the P/M Abiy Ahemed on June 16, at Meskel square is The Oromo Liberation Front. How shocking for some can this be?

  For years I contended , against the accepted convention, not to meddle or give room in Ethiopian media with fringe views and organizations.This is because with out any steady fast strategic principle no cause can be won.Had the political party I had in mind listened to our views over this matter they might have saved much heart ache.For instance,I knew jawar Mohamed to be a known flip flap, unstable ,zealot and one with exaggerated self regard.But he was made to be the center of media attention,and look what this lead to now.

  Dr.Dawed Ibsa and his legions are frustrated, bitter and angry folks who carry with them unresolved personal baggage . That explains why they entertain the attitude of entitlement. According to them no other Oromo can claim to power but only the OLF. Observe how far they went to plan to remove the P/M by force from office,because they reasoned he is not for the interest of Oromo . They try to justify this illogical and irrational opinion by actually assassinating the P/M.This is odium no matter how one sees it!

  This findings of the investigation also opens our eye to see the massacre of Burayo ,as many have believed,is the work of OLF. It is only principle that wins not lies not media spins.
  Blaming G- 7 for the Burayo massacre hardly stick.That is why it is very crucial the media(ESAT) to behave and present only facts and truth..Ethiopia is build with hared core of facts. What the public ask you guys is to present facts.We should not try to win an argument emotionally, when we do we defeat the whole purpose. It is my observation on the other side of the camp much of the info is in consistent,and it is expressed withe exaggerated emotion.
  Therefore what ever appeal one has to made it needs to reach the people and the rational element of Oromo society.

  On the basis of this findings I ask now the Addis Police, which appear to have come under the direct influence of OLF, to release the Addis Ababa youth.I ask the residents of Addis to gather as many petition they can and present your petition to the federal court asking for the release of innocent youth that are rounded up in and around Addis by the Police.Increasingly it becomes clear now Addis Police is politicized. Police need to abide by its constitutional mandate and professional ethic.We demand rule of law takes precedent in Ethiopia and in all cities.

Comments — What do you think?

Click here to connect!