Home » ጦማሮች እና አስተያየቶች » ብአዴን የሕወሓት አሽከር መሆኑን አቶ ገዱ በግልጽ መሠከሩ (ነፃነት ዘለቀ)

ብአዴን የሕወሓት አሽከር መሆኑን አቶ ገዱ በግልጽ መሠከሩ (ነፃነት ዘለቀ)

gedu andargachew

ነፃነት ዘለቀ

“ፀጉር ሲመለጥ ነገር ካፍ ሲያመልጥ አይታወቅም፡፡” እንላለን፡፡ የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሰሞኑ ንግግር ግን ከዚህም በላይ ነው – በአማርኛው “የምላስ ወለምታ” ወይም በእንግሊዝኛው “tongue slip” ተብሎ በቀላሉ ሊታለፍ የሚችል ስህተት አይደለም፡፡  በግልጽ ነው ሕወሓትነቱን መድረክ ላይ የገለፀው – አንዳች ነገር ግምባሩ ላይ ተደግኖ መሆን አለበት እንጂ በተለይ በዚህን የሕዝብ ተስፋ በለመለመበት ወቅት እንዲህ ያለ ተስፋ አስቆራጭ ንግግር ያደርጋል ተብሎ አይታስብም፤ አይጠበቅምም፡፡ የጊዜያችን ባለሥልጣናት ብዙዎቹ የሀፍረትና የይሉኝታ ስሜታቸውን እያጡ የመጡበት የሆዳምነት ባህል መስፋፋት በጣም ያሳስባል፡፡ በአማራ መሀል ተቀምጦ ልክ እንደአለምነህ መኮንን አማራን መዝለፍና የአማራን መብት ለአጥፊዎቹ አሳልፎ ለቁራሽ እንጀራ መሸጥ ዘመናዊ ይሁዳነት ያፈራው ትልቅ የኅሊና ክስረት ነው፡፡ በአማራ ስም የሚነግዱ ገዱን መሰል ግለሰቦች ለሚያልፍ ቀን ይህን ያህል መዋረድ ለምን እንደፈለጉ ግልጽ አይደለም፡፡ በርግጠኝነት ገዱ ተሳሳተ – በውስጡ ምንም ዓይነት ድብቅ ዓላማ ይኑረው ወይም አይኑረው ሰው የሚፈርደው በውጪ በሚታየው ምግባርና የአነጋገር ለዛ ነውና የገዱን ስህተት ሊያስተባብል የሚችል ነገር ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡ ደኅና መጥቶ አሁን ምን እንደነካው አላውቅም ዘጭ ብሎ ሲወድቅ ታየኝ፡፡ ምናልባት ስህተቱን ማስተካከል ከቻለ ሳይዘገይ ቢሞክር ጥሩ ነው፤ ወዳጅ ካለውም ይምከረው፡፡ የሶማሌው ክልል “ፕሬዝደንት” አቶ አብዲ ኢሌ “ጌታቸው አሰፋ ግምባራችን ላይ ሽጉጥ እየደቀነ ሰው እንድንገድል አድርጎናል” ብሎ መናዘዙ ሰሞነኛ የሚዲያና የሕዝብ መነጋገሪያ በሆነበትና የድንገቴ ለውጥ በሚናኝበት ወቅት በተሻለ ማኅበረሰብኣዊና ፖለቲካዊ የንቃተ ኅሊና ደረጃ ላይ ይገኛል ተብሎ የሚገመተው አቶ ገዱ በዚህ አንጻራዊ የነፃነት ጊዜ እንዲህ ያለ ማፈሪያ ንግግር ማድረጉ በተለይ አማሮችን አንገት ማስደፋቱ አይቀርም – ይህ ሰው በርግጥም አማራ ቢሆን ኖሮ በዚህን የለውጥ ጊዜ እንዲህ ያለ ቅሌት ባልተናገረ፡፡ ስንት የአማራ ጀግኖች ወያኔን እያንቆራጠጡ በክብር በተሰውበት ምድር እንዲህ ያለ አሽቃባጭ የአማራ ተወካይ መታየቱ ጉዟችን ወደፊት ሣይሆን የኋሊት መሆኑን ያመለክታል፡፡ ወዴት እየሄድን ነው ግን? ገዱን ምን ነካው? አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ዕቅድ ነድፎና በጀት መድቦ የተንቀሳቀሰው ማን ሆነና ነው?

በብአዴን ውስጥ ለሀገራቸውና ለክልላቸው ተቆርቋሪ አባላት መኖራቸው አይካድም፡፡ ይሁንና ታፍነዋል፡፡ የታፈኑትም አማራ መስለው በክልሉ ምክር ቤትና በብአዴን ውስጥ በግልጽ በሚንቀሳቀሱ ወያኔ-ትግሬዎች ነው፤ ወያኔ የአሁኑን አያድርገውና እንኳንስ የአማራን ንክር ቤት የአሜሪካንን ሴኔትና የእስራኤልን ኬኔሴት በገንዘቡና በሎቢስቶቹ አማካይነት መቆጣጠር የቻለ የዓለማችን ቁጥር አንድ ማፊያ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን የዚያ ጠባዩ ርዝራዥ በቀላሉ እንደማይጠፋ መታወቅ አለበት፡፡ ፈጣሪ ግን በአቋራጭ ደረሰበትና ከርቱዕ አንደበትና ከንጹሕ የሕዝብ ፍቅር ሌላ ማማሰያ እንኳን የሌላቸው ትናንሽ የሕዝብ ልጆችን ጣለበት፤ በፍቅር ፍላፃ ወገብ ዛላውን እያነጎዱ ከየጎሬው ያወጡት ጀመር፡፡ ዳዊት ጎልያድን፣ ሣምሶን ጥንታውያን ፍልስጥኤሞችን፣ ሙሤም ፈርዖንን እንዳዋረዱ እነዚህ ቆራጥ ልጆች በባዶ እጃቸው ሚሣይልና ኒኩሌር ይበግራቸዋል ተብሎ የማይገመቱትን የአጋንንት ልጆች ያንቀጠቅጡ ገቡ፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡ ይበል ብለናል፡፡ ከዐይን ያውጣልን፡፡ እመብርሃን ዕቅፍ ድግፍ አድርጋ ለመጨረሻው የነፃነት ቀን ታድርስልን፡፡

በኃላፊነትና በሥልጣን ከሚገኙ የብአዴን አባላት መካከል ቢያንስ ግማሽ የሚያህሉት አማራ ቢሆኑ ኖሮ ይሄኔ ብዙ ለውጥ እናይ ነበር፤ ግን ስማቸው “አገሩ አበረ” እና “አምባቸው ተሻለ” ሆኖ ሳለ ደማቸው ግን (አማራን ለማጥፋት ምሎ የተገዘተ) የወያኔ-ትግሬ ሆነና በአማራው ክልል በብአዴን አባልነት የትግራይን እንደሀገርና የሕወሓትን እንደጠባብ ቡድን ፍላጎት የሚያራምዱ የስም አማሮች ሆኑ፡፡ ይህን በተመለከተ ብዙ የተጻፈና የተነገረ ቢሆንም ታዋቂው አክቲቪስት አቻምየለህ ታምሩ በነዚህ ሁለት ቀናት ውስጥ ያወጣውን መጣጥፍ ማንበብ ይጠቅማል፡፡

አማራው አሁን የራሱን እርምጃ መውሰድ ያለበት ጊዜ ላይ መድረስ ይኖርበታል፡፡ በስሙ የሚነግዱ የሕወሓት ሠርጎ ገቦችንና ተላላኪዎችን መመንጠር አለበት፡፡ አለበለዚያ በድህነት እንደማቀቀና ዘሩም እንደተኮላሽ የወያኔ ባሪያ ሆኖ መቅረቱ ነው፡፡ ቆፍጣናዎቹ ኦህዲዶች ኦሮሞን ነፃ ሲያወጡ በሕወሓት የተቀፈደደው ብአዴን ወገቡን እንደተመታ እባብ እየተንከላወሰ ሕዝቡን ገደል ይዞት ሊገባ እየተፍጨረጨረ ነው፡፡ ይህ አካሄድ በአፋጣኝ ካልቆመ የእስካሁኑ አደጋ በሚዘገንን ሁኔታ ተባብሶ እንደሚቀጥል ግልጽ ነው፡፡ ፍቅር የሚያሸንፈው ፍቅር የሚያውቅን እንጂ ሰይጣንን አይደለም፡፡ ሰይጣን ፍቅር አያውቅም፡፡ ጥላቻ፣ ቂም በቀል፣ ግድያ፣ ራስ ወዳድነትና ስግብግብነትን የመሳሰሉ የጽልመቱ ገዢ ኃይል መገለጫዎች ብቻ ናቸው የርሱ የባሕርይ ገንዘቦች፡፡ ስለዚህ ላም ባልዋለበት ኩበት ለመልቀም ከመባዘን ፍቅር የማይገባውንና የማያውቀውን ወያኔ በሚገባው ቋንቋ ማናገር ተገቢ ይመስለኛል፡፡ በሁሉም ረገድ ያልተዘጋጀ ትግል ፍሬ አያፈራምና ይህ ማሳሰቢያየ ልብ ይባልልኝ፡፡ የዋህነት ለእንዶድም አልጠቀማትም፡፡

ሆዳምነትና አድርባይነት ለከት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ የነገዱ አንዳርጋቸው አድርባይነት ግን ድንበር አጣ፡፡ ብአዴን የሚባለው የወያኔ የትሮይ ፈረስ ውስጥ የተሰገሰጉ የህወሓት አባላት በሕዝብ ቁስል ጨው እየነሰነሱና ክልሉን ወደጋሪዮሽ ሥርዓተ ማኅበር የዕድገት ደረጃ ቁልቁል እያሽቀነጠሩ በሀገርና በሕዝብ ሊቀልዱ አይገባም፡፡ አማራው በባህላዊ የሞረሽ መጠራሪያው እየተሰባሰበ አንድ ነገር ማድረግ አለበት፡፡ በአማራ ንክር ቤት ማነው ምክር ቤት የተሰባሰቡ ማይማን የወያኔ አሽከሮች ላይም ሕዝቡ የማያዳግም እርምጃ ሊወስድ ይገባል፡፡ የማያዳግም ሲባል በግድ ግድያ አይደለም፡፡ ከዚያ በመለስ አስተማሪ የሆነ ቅጣት ሊያሳርፍባቸው ይገባል፡፡ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማድረግም አንዱ አወንታዊ የጠፋን ሰው የመመለሻ መንገድ ነው፡፡ ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ መስጠትም ሌላው መንገድ ነው፡፡ የከፋ እርምጃ ከመውሰድ በፊት በማስተማርና በመቆንጠጥ ከገቡበት የስህተት መንገድ ለመመለስ መሞከር ይገባል፡፡

አማራው በወያኔዎች ላይ ለሚወስደው ማንኛውም ዓይነት እርምጃ ከበቂ በላይ ምክንያቶች አሉት፡፡ ለምሣሌ ትግራይ ባለፉት 27 ዓመታት አውሮፓን የሚያስንቅ የመሠረታዊ ልማትና የፋብሪካና ኢንዱስትሪ ግንባታ ስታከናውን አማራው ግን በቂ የቤት ውስጥ ኮረንቲ እንኳን የለውም፤ ይህም ሆን ተብሎ የተደረገው በአማራው ስም በክልሉ የሥራ ቦታዎችና የአስተዳደር ዘርፎች በተሰገሰጉ የትግራይ ሰዎች ሻጥርና መብራት ኃይልን በተቆጣጠሩ የሕወሓት አባላት ተንኮል ነው፡፡ አማራው አካባቢ ዐይን የሚገባ ፋብሪካም ሆነ ኢንዱስትሪ የለም፡፡ ትምህርት ቤትም የለም ወይም በጥራቱ ከየትኛውም አካባቢ ሲወዳደር ዜሮና ከዜሮም በታች ነው፡፡ ስለዚህ የተፈጸመበት ግፍ ተነግሮ የማያልቅ በመሆኑ መብቱን ለማስጠበቅ የወያኔን አሽከር ብአዴንን መጠበቅ አይኖርበትም፡፡ የጎበዝ አለቃ እየመረጠ አካባቢዎቹን ነፃ ማውጣትና ቀድመው ነፃ ከወጡ አካባቢዎች ጋር ኅብረቱን ማጠናከር ይኖርበታል፡፡

ዛሬ ጧት የአቻምየለህ ታምሩን ጦማር ሳነብ ያገኘሁትን የብአዴን ጉድ ከዚህ በታች አስቀምጫለሁ፡፡ ገዱ አንዳርጋቸውም በዚህ ሁኔታ በአንድ ወይ በሌላ ጎኑ ትግሬ መሆን አለበት፤ አንድ ሰው የአማራ ስም ስላለው ብቻ አማራ ነው ማለት አይቻልም፡፡ በነገራችን ላይ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት የብአዴን አባላት ውስጥ ለምሣሌ ሐዱሽ ሐለፎም እና አብረኸት ዘርዓይ ተብለው አማራ ነን ሲሉ ቅንጣት አለማፈራቸው ይገርመኛል፡፡ ድፍን ቅል ናቸው፡፡ እንዲህ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ደግሞ ማይምነት ላይ የተደረበባቸው ጥጋብና ዕብሪት ነው፡፡ ማይም ሲጠግብ ትዕቢቱና ንቀቱ ወደር የለውም፡፡ ስለሆነም ሐዱሽ ብሎ አማራ መሆን ብቻም ሣይሆን ኮሎኔል ሐጎስ ሆኖ አንድን ሰው ከመንግሥተ ሰማይም በጠበንጃ አፈ ሙዝ አስገድዶ ማምጣት ይቻላል – የዛሬን አያድርገውና ከፀሐይ በታች ለወያኔ የሚያቅት ነገር አልነበረም፡፡ እንደጥጋበኛ ሰው እንደልቡ የሚሆን የለም፡፡ ለማንኛውም ገዱ የትግሬ ዘር ባይኖርበት ኖሮ እንዲህ በድፍረት ይህን የመሰለ ማሽቃበጥ ከአንደበቱ ሊሰማ ባልቻለ ነበር፡፡ ያው “በጌታዋ የታማመነች በግ ላቷን ከቤት ውጪ ታሳድራለች” እንደሚባለው መሆኑ ነው፡፡ ይገርማል፡፡ የሀገራችንን አለመታደል ዙሪያ-ገባነት ስናይ ካለፈው ይልቅ የወደፊቱ ጊዜ እጅግ ያስፈራል፡፡ እሱ ይሁነን እንጂ የሚታመን የለም፡፡ እንደሣሙና የሚያሙልጨልጨው ዜጋ በዛና የምናምነው እየከዳን ክፉኛ ተቸገርን፡፡ ለአንድ አሥር ወይ ሃያ ዓመታት ያህል ይሄ ሆድ የሚባል ነገር ሥራውን እንዲያቆም ቢደረግ ምን ዓይነት ለውጥ እናይ ይሆን ግን? ወደ አቻምየለህ ጽሑፍ እናምራ፡-

 1. መብርሀቱ ገብረሕይወት [ በረከት ሰምዖን] — የብአዴን ማዕከላዊ ኮምቴ አባልና አመራር — ትግሬ
 2. መኮነን ወልደ ገብርዔል— የፌዴሬሽን ም/ቤት አባልና የአማራ ክልል ምክር ቤት ህግ መወሰኛ ክፍል ሰብሳቢ— ትግሬ
 3. ከበደ ጫኔ — የንግድ ሚኒስትር የነበረ፤ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ ሚኒስትር —ትግሬ
 4. ካሳ ተ/ብርሃን— የፌደራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስትር— ትግሬ
 5. ሕላዌ ዮሴፍ— በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር — ትግሬ
 6. ዮሴፍ ረታ — የአማራ ክልል ፕሬዝደንት የነበረ—ትግሬ
 7. ገነት ገ/እግዚአብሄር—የአማራ ክልል ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ—ትግሬ
 8. መለስ ጥላሁን— የብዓዴን ማዕከላዊ ኮሜቴ አባልና የጥረት ኮርፖሬት ምክር ቤት ሊቀመንበር—ትግሬ
 9. ታደሰ ካሳ — የጥረት ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ — ትግሬ
 10. ተሠማ ገ/ሕይወት— የርዕሰ መስተዳድሩ አማካሪ —ትግሬ
 11. ተተካ በቀለ — የብዓድን አባልና የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ — ትግሬ
 12. ልዑል ዮሐንስ — «የአማራ ክልል» ባህልና ቱሪዝም ቢሮም ክትትል — ትግሬ
 13. ጸሃዩ መንገሻ — የወልዲያ ከተማ ከንቲባ— ትግሬ
 14. ሙሌ ታረቀኝ [አምባሳደር] — የብአዴን ከፍተኛ አመራር፣ የኢሕአዴግ ጽ/ቤት ሕግ ክፍል ሀላፊና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የካቢኔ ጽህፈት ቤት ኃላፊ —ትግሬ
 15. ሐዱሽ ሐለፎም — የደ/ጎንደር ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ — ትግሬ
 16. ጀኔራል ስዩም ሀጎስ — የምዕራብ እዝ አዛዥ ሆኖ የሰራ፤ መጀመርያ የሕወሓት ታጋይ የነበርና “አማራ ነኝ” ብሎ ኢሕዴንን የተቀላቀለ—ትግሬ
 17. ሃዲስ ሃለፎም — የአማራ ክልል የገንዘብ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር— ትግሬ
 18. የማነ ታደሰ — የአማራ ክልል የጸጥታ ዘርፍ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር— ትግሬ
 19. ተክሉ የማነ ብርሃን — በአማራ ክልል በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር — ትግሬ
 20. ተክለሃይማኖት ገብረሕይወት —በአማራ ክልል የጢና ጥበቃ ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ዋና የስራ ሂደት መሪ — ትግሬ
 21. ካሳሁን አብርሃ — የጎንደር ኢርፖርት ደሕንነት ኃላፊና የጎንደር ከተማ ወጣቶች ሊግ— ትግሬ
 22. አብርሃም ገብረመድህን — የደብረብርሃን ገቢዎች ዳይሬክተር— ትግሬ
 23. ፍስሃ ወልደሰንበት —የአማራ ግብርና ቢሮ ኃላፊ— ትግሬ
 24. አብርሃም ወልደግብርኤል —በአማራ ክልል የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት— ትግሬ
 25. አቶ በርሄ ገብረማሪያም— የከሚሴ ከተማ ሆስፒታል ዳይሬክተር— ትግሬ
 26. ብርሀኔ ቸኮል —የደብረብርሃን ከተማ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ— ትግሬ
 27. አብረሀት ዘራይ — የምስራቅ ጎጃም የመምህራንና የትምህርት ተቋማት ዘርፍ አስተባባሪ— ትግሬ
 28. ኪዳነማሪያም ፍስሃ — የጎንደር ከተማ የህብረት ስራ ማህበር ማሰተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ— ትግሬ
 29. ሰለሙን ሙሉጌታ — የጎንደር ከተማ ብአዴን ኃላፊ— ትግሬ
 30. ተሰፋይ ሞገሰ — የጎንደር ከተማ ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ— ትግሬ
 31. ትዕዛዙ አፅብሃ — የጎንደር ከተማ የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ— ትግሬ
 32. አብዮት ብርሃኑ ገ/መድህን—የጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ— ትግሬ
 33. ቻላቸው ዳኛው—የጎንደር ከተማ ፅዳት ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ— ትግሬ
 34. አባዲ አበበ —የጎንደር ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የሰራ ሂደት አሰተባባሪ — ትግሬ
 35. ጉኡሽ አምባዬ–የይልማና ዴንሳ ወረዳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል—ትግሬ
 36. ሲሳይ ዘሪሁን –የደ/ወሎ ዞን ብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ — ትግሬ
 37. አለም ግዴይ– የደሴ/ዙሪያ ወረዳ መሬት አስተዳደር ኃላፊና የደሴና አካባቢው የሕወሓት መረጃ ኃላፊ [2 ደመወዝ የሚከፈለው] — ትግሬ

 

2 comments

 1. The author of the article is a hateful person for that it written unprofessionally. For example, the writer of the article didn’t provide evidence to his accusations against Ato Gedu Andargachew. Its contents made it clear to me that the author harbors enmity against Gedu Andargachew.

  I think the list that contains names and positions of the officials along with their ethnic group could be helpful.

 2. ገዱ አንዳርጋቸው ምን እያለን ነው?
  ይች መደመር የሚሉ ማሽቋለጥና ማሽቃበጥ ሁላችንም ወያናይት ነን( በረከት ስምዖን) የሚለው ሁላችንም ኢህአድጎች ነን (ኮ/ል ዓብይ አህመድ) የሚለው ቀስ በቀስ እየተገለጠ መጣ !?
  **************
  —- «በአማራ ክልል ሰላም እንዲደፈርስና ሥርዓት አልበኝነት እንዲነግስ ሕወሓት ምክንያት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም። ሕወሓት እያስተዳደረ ያለው የትግራይን ክልል ነው። አለማም አጠፋም መወቀስም ካለበት በዚያው በክልሉ ነው።»
  **የሥልጣንና የኢኮኖሚ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ቢኖር ፍትህ ከነበር ለምን ሀገር በአድማ ተሽመደመደ?
  — ገዱ «የብአዴን የቀድሞ ነባር አመራሮች» ስላላቸውም ተናግሯል። «ይኼ ሕዝብ እንዲለወጥ የበኩላቸውን ድርሻ ተወጥተዋል» ሲልም አሞካሽቷቸዋል።
  ** አማራ ጠል በድኑ ብአዴን ባለፉት ፳፯ ዓመት አንድም የኃይል ማከፋፈያ ፋብሪካ ስላልተገነባበት ጨለማ ክልል ካሉት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ፹፫ በመቶው፤ እንዲሁም በክልሉ ካሉት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ውስጥ ፹ በመቶው የትምህርት ቤት ደረጃቸውን ያልጠበቁ፣ ዳስና ዛፍ ስር ትምህርት የሚሰጡ አእምሮ ማጫጫዎች የክልሉ አይነተኛ ገጽታነው።«የአማራን ክልል ሕዝብ ልማትና ሰላም ወደ ኋላ እንዲመለስ የሚያደርጉ ክስተቶች» ታይተዋል አሉን !?
  እዋይ ጉድ አርጋቸው
  ** እንግዲህ ለሥርዓት ዓልበኝነት ህወሓት ምክንያት ካልሆነ ምክንያቶቹ ገዱ አንዳርጋቸው እና ቡድኑ ሙሉ ተጠያቂነትና ኅላፊነትን ወስዷል ሌባ ተይዞ ዱላ አይጠየቅም!
  —- «አንድ መሆናችን እንቅልፍ የነሳቸው፣ ያልታደሰውና የአሮጌው ዘመን ቁማርተኞች ከእግራችን እየተከተሉ ሰላማችን ለማወክ እየጣሩ ነው» ያላቸው እነማንን ነው? ገዱ አንዳርጋቸው በባለፈው ንግግሩ «ሰላማችን ለማወክ እየጣሩ ነው» ሲል የገለጻቸው የየት ሀገር ዜጎች ናቸው? መቼም አሸባሪው ሁሉ ተደምሮ ቤተ ኢህአዴግ ባንዲራወን እየለበሰ ፎቶ እየተነሳ ነው?
  **(ገዱና ብአዴን አንድ የሆነው ከማን ነው? ሁሉም አማራ ለብአዴ ሁሉም ብአዴን ህወሓት/ኢህዴግ ሆነ ማለቱ ነው?) (ያልታደሱና የአሮጌ ዘመን ቁማርተኞች እነማን ናቸው አሮጌውን ዘመን እነማን መሩት ?
  አሮጌ ዘመን ከመቼ ጀምሮ ነው?
  **ያው አማራ መሰል አማሳይ በዳይ (ብአዴን) የተባለው ጥርቅም መሆኑን አምኗል ፡፡ እያንዳንዱና ሁሉም አካባቢውን ቢያፀዳ ሀገራችን ውብ ትሆን ነበር…ገበሬ አውድማ እንድሚለቀልቅ ክልሉንም ሳርና ዓረሙን መለየት የግድ ይላል። ሰሚ ካለ ገዱ ተጣርቷል።

  ***”ጤና ይስጥልኝ ጉዱ አርጋቸው? ከሁለት አመት በፊት ሐምሌ አምስት ቀን የትግራይን ወሰን ተሻግረው ደመቀ ዘውዱን ለመግደልና ሌሎችን የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት ለማፈን ከትግራይ የተሰማራው ማን ነው? የጎንደርን መሬት ምዕራብ ትግራይ፤ የወሎን መሬት ደቡብ ትግራይ ያደረገው ማነው? የጎጃምን መሬት በመውሰድ ቤንሻንጉል የሚል ክልል ፈጥሮ አማራን ከዕርስቱ እያፈናቀለ መተከል ትራክተር ይዞ የገባው ማን ነው? ፍኖተ ሰላም የነበረውን የጎጃም የወባ ማጥፊያ ድርጅት፣ የጎንደርን ጀኔሬተሮችን፣ የጣና በለስን ፕሮጀክት፣ የደብረ ማርቆስን የድንጋይ ፋብሪካ፣ ወዘተ እየነቀለ ወደ ትግራይ ያጋዘው ማነው? ”
  ገዱን ምን አንገዳገደው?

Comments — What do you think?

Click here to connect!