Home » ዜና » በዋሽንግተን ዲሲ የዶክተር ዓቢይ የዲያስፓራ ጉብኝትን የማደናቀፍ ሴራ

በዋሽንግተን ዲሲ የዶክተር ዓቢይ የዲያስፓራ ጉብኝትን የማደናቀፍ ሴራ

በዋሽንግተን ዲሲና አከባቢዋ የሚኖሩ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ስብስብ የዶክተር ዓቢይ የዲያስፓራ ጉብኝትን የማደናቀፍ ሴራ እየሰሩ መሆናቸውን ተጋለጡ።

ከወልደሩፋኤል ዘመድኩን

Ethiopia's PM Abiy Ahmed at Addis Ababa, Mesqel Square rally.

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ በህወሓት የሚደጎሙና በተለይም ከነ ስብሓት ነጋ ጋር ወግነው ለውጡን ለመቀልበስ ሲንቀሳቀሱ የቆዩና አሁንም የዶክተር ዓቢይ አህመድ የዲያስፓራ ጉብኝትን ለማጨናገፍና ለመበተን ከኤምባሲው ጋር ግንባር ፈጥረው በከፍተኛ ደረጃ በማሴር ላይ ከሚገኙት አቀነባባሪዎችና አወናባጆች ውስጥ የሚከተሉትን በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ::

አንደኛ አቶ ሙሉ ሰንደቅ ፋንታሁን :- የህወሓት ታጋይ ነበርና የስብሓት ነጋ የቅርብ ታማኝና ዘመድ ሲሆን በቅርቡ ህወሓትን እናድን በሚል ዘመቻ ዙሪያ በሰፊው በመንቀሳቀስ በአብዛኛው የቀድሞ የህወሓት ነባር ታጋዮች የተሰባሰቡበት “ሰብ ሕድሪ“ በሚል ስያሜ የሚታወቅ ሲቪክ ማሕበር በማቋቋምና በሊቀ መንበርነት በመምራት ከመቀሌ ከህወሓት ቢሮ የተሰጠውን ግዳጅ ሲፈፅም መቆየቱ ይታወቃል:: ዛሬም የዶክተር ዓቢይን የዲያስፓራ ጉብኝት ለማኰላሸት ሲባል የአዳናቃፊ ኮሚቴ አስተባባሪ በመሆን ቤት ለቤት ስልክ እየደወለ ድጋፍ ለማሰባሰብ በማሴር ላይ ይገኛል::

ሁለተኛ አቶ አማረ ሉቃስ:- በዋሽንግተን ዲሲ የትግራይ ኮሚኒቲ ሊቀ መንበር ሲሆን ከአቶ ሙሉ ሰንደቅ ካሳሁን ጋር በመተባበር የሴራውን ተባባሪና አቀነባባሪ ሆኖ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል::

ሶስተኛ አቶ አሉላ ሰለሞን :- የህወሓት ተቀጥላ የሆነውን “ ማሕበር ተጋሩ ሰሜን አሜሪካ ” ሊቀ መንበር ሲሆን የለውጡን ሂደት በማጥላላትና በማንቋሸሽ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘላብድ መቆየቱ ይታወቃል:: ዛሬም የዶክተር ዓቢይን ጉብኝት እንዳይሳካ ለማድረግ በትዕቢት በመነሳት ከላይ የተጠቀሱትን የየማሕበራቱ መሪዎች በማሰባሰብና በማቀናጀት እኩይ ዘመቻውን በማራመድ ላይ መሆኑን ከውስጥ የደረሰን መረጃ ያስረዳል::

አዎ!! በዶክተር ዓቢይ የሚመራው የለውጥ ሂደት እንደ ጠላት በመቁጠር የሚሰጉትና የሚበረግጉት ጭቁኑ ሕብረተ ሰብ ሳይሆን በአንፃሩ ለውጡን እንደ ኮሶ የመረራቸው በህዝብ ደም ሲነግዱ የነበሩት፣ በጠራራ ፀሐይ የሀገርንና የህዝብን ሀብት በመዝረፍ ለራሳቸውና ለልጅ ልጆቻቸው ያካበቱ፣ ዘርን ከዘር ጋር በማጋጨት እጃቸውን በንፁሃን ደም የተነከሩት፣ ዜጎችን በጨለማ እስር ቤት በማጎር ጭካኔ የተሞላበትን ዘግናኝ ተግባር ሲያካሄዱ የነበሩት ፣ በሀገርና በህዝብ ላይ ክሕደት የፈፀሙና ለወደፊትም ሀገሪቷን በበላይነት ተቆጣጥረው አልፋ ወ ኦሜጋ ስልጣን ይዘው 100 ሚሊዮን ህዝብን ረግጠው ለመግዛት ህልምና ዕቅድ የነበራቸው የህወሓት መሪዎችና ተላላኪዎቻቸው መሆናቸውን ከራሱ ከኢትዮጵያ ህዝብ በላይ ሌላ ምስክር አይኖርም::

እነዚህ ጥቅማቸው የተነካባቸው የቀን ጅቦችን መሳሪያ በመሆን በዲያስፓራም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚፈፅሙትን ሴራ ከወደቁ በሗላ መንፈራገጥ ትርፉ መላላጥ መሆኑን በፍፁም አልገባቸውም:: ስለሆነም የዲያስፓራ እንግዳ ተቀባይ ኮሚቴ ስራውን ውጤታማ ይሆን ዘንድ በመጀመሪያ ውስጡን ማፅዳትና አካባቢውን በንቃት መከታተል አስፈላጊ ይመስለናል:: ሌባን ሌባ ካላሉትና ካላጋለጡት ገብቶ መፈትፈቱ የማይቀር ነው:: በፍፁም የበሰበሰ የህወሓት መሪዎች አረሜናዊ ስርዓት ዳግም ዕድል መሰጠት የለበትም:: ጊዜው የሐቀኛ ታጋዮች ዘመን እንጂ የዘራፊዎች ጊዜ አይደለም አክትሟል::

የለውጡን ሂደት መጠበቅና መንከባከብ የያንዳንዳችን ኢትዮያውያን ሃላፊነት ነው!

ከወልደሩፋኤል ዘመድኩን

One comment

  1. ከከፍተኛ አክብሮት ጋር የአቶ ወልደሩፋኤል ዘመድኩ መልዕከት- መልዕክት ሊባል ከቻለ – ለሀገራችን የለውጥ ጉዞ እንቅፋት እንጂ ደጋፊ አይደለም ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን የፖለቲካና ማህበራዊ ችግሮች ከይቅርታ፤ ከፍቅርና ከመደመር ጋር ካልሆነ መፍታት ይከብደናል የሚል እምነት አለኝ

Comments — What do you think?

Click here to connect!