Home » ጦማሮች እና አስተያየቶች » ጎሠኛነት በባዶ ሜዳ (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

ጎሠኛነት በባዶ ሜዳ (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

በተለያዩ የኢትዮጵያ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ሁሉ የሚደረገው ውይይትና ክርክር እንደተጠናቀቀ ተቆትሮ የአማራና የኦሮሞ ጎሠኛነት ትልቁ አንገብጋቢ ጉዳይ እየሆነ ነው፤ (ስለኢትዮጵያ ለማያውቅ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ከጠሩና ከጸዱ አማራና ኦሮሞዎች በቀር በአገሪቱ ውስጥ ሌላ ሰው ያለ አይመስልም!) ጎሠኛነት ጉዳያችን ያልሆነው ኢትዮጵያውያን የዳር ተመልካች መሆኑ እየሰለቸን ነው፤ ምንም እንኳን አማራና ኦሮሞ የተባሎት ጎሣዎች በብዛት ከሁሉም ቢበልጡም ከሰማንያ በላይ የሚሆኑ ጎሣዎች እንደሌሉና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ቃል እንደሌላቸው ተደርጎ የሚጎነጎነው የሚስዮናውያንና የስለላ ድርጅቶች ታሪክ ለኢትዮጵያውያን ባዕድ ነው፡፡Mesfin Woldemariam

ሌላው የሚያስደንቀውና ዓይን ያወጣው ነገር እነዚህ ኢትዮጵያን በጠዋቱ ለመቃረጥ እየተነታረኩ ያሉ በአማራና በኦሮሞ ጎሣዎች ስም መድረኩን የያዙት ሰዎች በውጭ አገር የሚኖሩ፣ እነሱ ሌሎች መንግሥታትን የሙጢኝ ብለው ከወላጆቻቸው ባህልና ታሪክ ጋር ማንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው፣ ልጆቻቸውም ከኢትዮጵያ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው የውጭ አገር ሰዎች ናቸው፤ የሚናገሩትና የሚሰብኩት ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ላለነው፣ አገራችን ያፈራችውን ግፍና መከራ እየተቀበልን ለምንኖረው የነሱ ንትርክ፣ ውይይትና ክርክር ትርጉም የለውም፤ እዚያው በያገራቸው እየተነታረኩ ዕድሜያቸውን ጨርሰው መቀበሪያ ይፈልጉ፤ ሲመች ኢትዮጵያውያን ናቸው፤ ሳይመች የሌሎች አገሮች ዜጎች ናቸው፤ ሲመች የአንዱ ጎሣ አባል ናቸው፣ ሳይመች ሌላ ናቸው፤ እነሱ በምጽዋት እየኖሩ እዚህ በአገሩ ጦሙን እያደረ ስቃዩን የሚበላውን በጎሠኛነት መርዝ ናላውን ሊያዞሩት ይጥራሉ፡፡

የኢትዮጵያን ሕዝብ በጎሣ ለያይተው የሞተ ታሪክ እያስነሡ ከአሥራ አምስት ሺህና ከሃያ ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት አዛኝ ቅቤ አንጓች እየሆኑ ተነሥ-አለንልህ! እያሉ በአጉል ቀረርቶ ጉሮሮአቸው እስቲነቃ የሚጮሁ ሰዎች ቆም ብለው ቢያስቡ እኛና እነሱ ያለንበትን የአካል ርቀት ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰበም በመንፈስም እጅግ መራራቃችንን በመገንዘብ አደብ መግዛት ይችሉ ነበሩ፤ የሥልጣን ጥም ያቅበዘበዛቸው ሰዎች የሚያስነሡት አቧራ በኢትዮጵያ የዘለቄታ መሠረታዊ ጉዳዮች ለመነጋገር እንዳይችሉ፣ እንዳይደማመጡና እንዳይተያዩ እያደረገ ነው፡፡

አገር-ቤት ያለነውን አላዋቂ ሞኞች ለማሳመን ስደተኞች በየቀኑ አዳዲስ ነገሮችን እያለሙ ያድራሉ፤ እኛ የምንኖረውን እንንገራችሁ ይሉናል፤ እኛ የምናስበውን እንምራችሁ ይሉናል፤ እኛ የሚሰማንን እንግለጽላችሁ ይሉናል፤ በአጭሩ እኛን የእነሱ አሻንጉሊቶች አድርገውናል፤ የእኛን መታፈን ከእነሱ ስድነት ጋር እያወዳደሩ፣ የእኛን የኑሮ ደሀነት ከእነሱ ምቾት ጋር እያስተያዩ፣ የእነሱን ቀረርቶ ከእኛ ዋይታ ጋር እያመዛዘኑ ያላግጡብናል፤ ይመጻደቁብናል፤ በስደት ቅዠት ያገኙትን ማንነት በእኛ ላይ ሊጭኑ ይዳዳቸዋል፡፡

ወላጆቹም እሱም የተወለደበትን አገር ትቶ በሰው አገር ስደተኛ የሆነ፣ የራሱን አገር መንግሥት መመሥረት አቀቶት የሌላ አገር መንግሥትን የሙጢኝ ያለ፣ ማንነቱን ለምቾትና ለሆዱ የለወጠ፣ የተወለደበትንና ያደገበትን ሃይማኖት በብስኩትና በሻይ የቀየረ፣ተጨንቆና ተጠቦ በማሰብ ከውስጡ ከራሱ ምንም ሳይወጣው ሌሎች ያሸከሙትን ጭነት ብቻ እያሳየ ተምሬለሁ የሚል፣ የመድረሻ-ቢስነቱ እውነት የፈጠረበትን የመንፈስ ክሳት በጭነቱ ለማድለብ በከንቱ የሚጥርና የሚሻክራን ስደት ለማለስለስ በሚያዳልጥ መንገድ ላይ መገላበጡ አያስደንቅም፤ እያዳለጠው ሲንከባለል የተነሣበትን ሲረሳና ታሪኩን ሲስት ሌሎች እሱ የካዳቸው ወንድሞቹና እኅቶቹ ከፊቱ በኩራት ቆመው የገባህበት ማጥ ውስጥ አንገባም ይሉታል፡፡

የአሊን፣ የጎበናን፣ የባልቻን፣ የሀብተ ጊዮርጊስን፣… ወገንነት ክዶና ንቆ ራቁቱን የቆመ፣ እንደእንስሳት ትውልድ ከዜሮ ለመጀመር በደመ-ነፍስ የሚንቀሳቀስ! ድንቁርናን እውቀት እያስመሰለ ሞኞችን የሚያታልል፣ ወዳጅ-ዘመድን ከጠላት ለመለየት የሚያስችለውን የተፈጥሮ ችሎታ የተነፈገ፣ አባቱን ሲወድ እናቱን የሚጠላ፣ እናቱን ሲወድ አባቱን የሚጠላ፣ ከወንድሙና ከእኅቱ ጋር የማይዛመድ ባሕር ላይ እንደወደቀ ቅጠል የነፋስ መጫወቻ ሆኖ የሚያሳዝን የማይታዘንለት ፍጡር፣ በጥገኛነት የገባበትን ማኅበረሰብ ማሰልቸቱ የማይገባው የኋሊት እየገሰገሰ ከፊት ቀድሞ ለመገኘት የሚመን የምኞት እስረኛ ነው፡፡

አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ አውስትራልያ በጥገኛነት ታዝሎ፣ ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ ከኢትዮጵያ ስለመገንጠል ይለፈልፋል! ተገንጥሎ የወጣ ከምን ይገነጠላል? ልዩ የነጻነት ታሪክ ባስተላለፉለት አባቶቹና እናቶቹ እየኮራ፣ በጎደለው እያፈረ፣ የአምባ-ገነኖችን ዱላ እየተቋቋመ በአገሩ ህልውና የወደፊት ተስፋውን እየወደቀና እየተነሣ የሚገነባው ኢትዮጵያዊ በፍርፋሪ የጠገቡ ጥገኞችን የሰለለ ጥሪ አዳምጦ የአባቶቹን ቤት አያፈርስም፤ አሳዳሪዎች ሲያኮርፉና ፍርፋሪው ሲቀንስ፣ ጊዜ ሲከፋና ጥቃት ሲደራረብ የወገን ድምጽ ይናፍቃል፤ ኩራት ራት የሚሆንበት ዘመን ይናፍቃል፡፡

12 comments

 1. ዘረኞች ሁሉ; ኦሮሞ ነኝ ባዩ; በተለይ ጀዋር መሐመድ; ቆም ብላችሁ የዶር. መስፍንን መልእክት በጥንቃቄ ተመልከቱ! የትግራይን ጸያፍ ዘረኛነት በናንተ አሳፋሪ የኦሮሞና የአማራ ጎጠኝነት እየመነዘራችሁ መሆኑ ይግባችሁ:: ነገ ሳይሆን ማፈር የነበረባችሁ ዛሬ ነው; ሕሊናና አንጎል አለን ካላችሁ:: በሐምበርገር የጠረቃውን ሆዳችሁን እያስቀደማችሁ; ደሀውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በዘር እየከፋፈላችሁ ባታጫርሱት አይሻልም ወይ? እባካችሁ ትንሽ እንኳ አስቡ; አሰላስሉ! እነጀዋርን የምትደግፉ ሁሉ እባካችሁ ጥቂት አስቡ:: እርግፍ አድርጋችሁ ልትጠሏቸው የሚገባቸው ፍጡሮች ናቸውና!

 2. የወያኔ ጆሮ ጠቢ እንደሚሰማዎ ላርዳዎ !!

  በወያኔ ዘመን ተወልደው የተማሩ ለሁሉም ጎሳ ፍትህ ሲሉ ግድያ የበዛባቸውን እርሶ ፕሮፈሰር መስፍን አናግረው መፍትሄ ላይ ደረሱ ወይ? ምነው ማን እንደሆነ ባህል አክባሪ ማን እንደሆነ ታሪክ አክባሪ ማን እንደሆነ ጎሠኛ ተፈላሳፊ ከሚሆኑብን መፍትሄውን ቢነግሩን ለትውልዱ ሞት ? ለምንድን ነው የትግሬ ትውልድ ሲደላው የሌላው ጎሳ ትውልድ የሚሞተው? ንገሩና ታድያ ፍርዱን ማን እንደፈረደ ማን እንደሚሞት ማን እንደሚኖር በሃገሩ? ዘርን መግደል ወንጀል መሆኑ እኮ የሚካድ አይደለም::

  ደፋር ታጋዮች ባሉበት መቼም ከዲያስፖራ ተብየው ከርሶ በላይ በስልክ እና በኢንተርኔት እንዲሚነጋገር መገመት አይከብዶትም::
  ትላንት ከእርሶ ጋር አብረው ሲታገሉ የታሰሩት ዛሬ በስደት ያሉትን መከራ ላይ ያሉትን የሚሰማ እና አይዞህ የሚል ማን ሆነና ዲያስፖራ ነው እንጂ? እርሶማ ምኑን ሰምተው ?
  ትላንትና እና ዛሬ ሲገደሉ ሲታሰሩ በስንት መከራ ህይወታችውን ለማትረፍ አንድ ብለው ተራምደው ከሃገር ወተው በስደት ያሉት በየአፍሪካ ሃገር , በየመን እና በመሳሰሉት ሃገር በጉዞ ያሉት ማን ይናገርላቸው?ዲያስፖራ ወዶ አይደለም እኮ እንደዚህ የሚንገበገበው::
  ወያኔ ሰላይ እያሳደዳቸው ያሉትን ልጆች ወደ ዲያስፖራ ለመደወል ብቻ ሲሉ ወተው ተመልሰው ጉድጉአድ የሚገቡትን ልጆች ሰምቶ ዲያስፖራ አይዞዋችሁ ብሎ ካላስታወሳቸው ማን ያስታውሳቸው?

  እስር ቤት ሰብረው ወተው ሶማሌ ኬንያ ታንዛኒያ ድረስ በስደት ያሉትን ልጆች ዲያስፖራ አይዞዋችሁ ብሎ ካላስታወሳቸው ማን ያስታውሳቸው? ዲያስፖራ ይናገርላቸው እንጂ እውነቱን በእስር ቤት በወፌ ላላ መከራ ላሉት ::
  ትላንትና እና ዛሬ ሲገደሉ ሲታሰሩ በስንት መከራ ህይወታችውን ለማትረፍ አንድ ብለው ተራምደው ከሃገር ወተው በስደት ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን እርሶ ጋር ደውለው ያናግሮት ከመስሎት ተሳስተዋል:: እንኩአን የእርሶ ስልክ ንግግር ሁሉም የሰፈሮት የጎረቤት ስልክ ንግግር በሙሉ ሃያ አራት ሰአት በወያኔ ጆሮ ጠቢ እንደሚሰማ ላርዳዎ ::

 3. ብስራት አክሊሉ : ከተ.መ.ድ. አሜሪካን

  ብስራት አክሊሉ : ከተ.መ.ድ. አሜሪካን

  ፕሮፌሰር መስፍን አንድ ጣት ሲቄስሩ ወደ ዲያስፖራ አራት ጣቶቻቸው ወደራሳቸው እንድሚቄስሩ ነው የተገነዘብነው:: ለማን አቤት እንበል ? አካውንት ያለንን ገንዘብ እንኩዋን ወርሰው በመለስ ዘመን በአክሲዮን በመሰረትነው ባንክ አቶ ሃይለማሪያም አክሲዮናችንን ወርሰው :: ባንዳ ሃገር ይዞ የበይ ተመልካች አደረገን ሃይለማርያም ደሳለን:: ሃይለማሪያም ደሳለን የመንግስቱ ሃይለማሪያም አይነት ኮንሶ ሆኖ ሳለ ወላይታን ህዝብ እወክላለሁ ብሎ ስላለ የዘር ወሬ አይነሳ ይላል:: የሃይለማሪያም ሚስትም በአባቱዋም በእናቱዋም ሙሉ ለሙሉ ኤርትራዊ ስለሆነች የዘር ወሬ አይነሳ ይላል :: እርሶም ፕሮፌሰር መስፍን የለሁበትም ለማለት ብለው ሃይለማርያምን ለማስደሰት የዘር ወሬ አይነሳ ማለቶ ያስተዛዝባል:: የዘር የማይንሳ ከሆነማ ለምን ህውሃትን መጀመርያ አይነግሩትም ነበር:: ለምን ወደ ዲያስፖራ ዘለሉ ፕሮፈሰር?
  ፕሮፌሰር መስፍን “እነሱ ሌሎች መንግሥታትን የሙጢኝ ብለው ከወላጆቻቸው ባህልና ታሪክ ጋር ማንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው፣ ልጆቻቸውም ከኢትዮጵያ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው የውጭ አገር ሰዎች ናቸው፤ የሚናገሩትና የሚሰብኩት ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ላለነው፣ አገራችን ያፈራችውን ግፍና መከራ እየተቀበልን ለምንኖረው የነሱ ንትርክ፣ ውይይትና ክርክር ትርጉም የለውም፤ እዚያው በያገራቸው እየተነታረኩ ዕድሜያቸውን ጨርሰው መቀበሪያ ይፈልጉ፤ ሲመች ኢትዮጵያውያን ናቸው፤ ሳይመች የሌሎች አገሮች ዜጎች ናቸው፤ ሲመች የአንዱ ጎሣ አባል ናቸው፣ ሳይመች ሌላ ናቸው፤ እነሱ በምጽዋት እየኖሩ እዚህ በአገሩ ጦሙን እያደረ ስቃዩን የሚበላውን በጎሠኛነት መርዝ ናላውን ሊያዞሩት ይጥራሉ፡፡” ብለውናል::
  የሌላ ዜጋ ለምን እንደሆንን ብንነግሮው አያምኑን ይሆናል እንጂ በብዛት በዲያስፖራ በስደት ያለነው የሌላ ዜጋ ለመሆን የተገደድነው ኤምባሲያችን ፓስፖርታችንን ስለወረሰብን ነው::የአባይ ግድብ ላይ ገንዘብ አልላኩም በሚል ኤርትራዊ ሳንሆን ኤርትራዊ ተብለን ፓስፖርት ተወስዶብን ሳንወድ ተገደን የሌላ ሃገር ፓስፖርት ለመያዝ ተገደድን:: ጉቦ እና ወያኔ ዘመድ የሌለው አንድም ዲያስፖራ ሰው በሰላም ፓስፖርቱ አይታደስም:: አድሱልን ብለን ስንልክ ተወርስዋል እንባላለን:: ከሃገር ቤት ጉቦ እና ወያኔ ዘመድ ከሌለው አንድም ዲያስፖራ ሰው በሰላም የትውልድ ሰርተፊኬት አያስልክም::ባለንበት ምድር እንሥሳ ከመባል የሌላ ዜጋ መሆን ተገደድን::
  ለመሆኑ ፕሮፈሰሩ ስለ በስደት ታጋዮች ዲያስፖራውች እና ስለ ዲያስፖራ ልጆች ባህል ሞራል እና ታሪክ ከማውራታቸው በፊት በአዲስ አበባ ሰፈራቸው አራዳ አከባቢ ያለውን የሰዶም መራባት ሁኔታ ከባህልም ሆነ ከሞራል ታሪክ ግንኙነት በምን መልክ አዩት ?
  ለመሆኑ ስለ ዲያስፖራ ልጆች ባህል ሞራል እና ታሪክ ከማውራታቸው በፊት በዲያስፖራም ሆነ በሃገር በየከተማው ተማሪው በጎበዝ ሲደራጅ እርሳቸው ያሉበት ከተማ አዲስ አባባን ተማሪ ለትግል አለመደራጀት በምን መልኩ አዩት? ?
  ለመሆኑ ፕሮፌሰሩ መለስ ዘናዊ ሲመቸው ኢሳያስን ሲያመሰግን ሳይመቸው ደግሞ የየመን ዜጋ መሆኑን ረሱት ወይ?
  ፕሮፈሰሩ ለመሆኑ ሮማን ተስፋዬ የተባለችው የሃይለማሪያም ደሳልን ሚስት ምን ተችተዋታል እስከአሁን በአባቱዋም በእናቱዋም ሙሉ ለሙሉ ኤርትራዊ ሆና በአዲስ አበባ ቤተመንግስት ዘመዶችዋን ሰብስባ ከአፍሪካ ህብረት የኤርትራ ተወካይ ጋር ስትዶሉት ባለበት ዘመን ከባህልም ሆነ ከሞራል ታሪክ ግንኙነት በምን መልክ አዩት ?
  ዲያስፖራ የወያኔ ባሪያ አንሆንም ብሎ የአባይ ግድብ ገንዘብ አልልክም ባለ ዜግነቱን ወሰዱበት:: ለአባይ ከምንልክ ለትግሉ መላክ በመምረጣችን የሌላ ዜጋ ተብለን መታማት አይገባንም:: የሌላ ዜጋ ማየት ከፈለጉ አዲስ አበባ ቤተመንግስት ይሂዱ ተሰግስገውሎታል::

 4. Thank you Prof. Your are a man of great wisdom and courage. You always tell the truth. Some diaspora elites have become naive, always overestimate themselves. They ignore the awareness of the people of Ethiopia, the youth in particular. Most claim to be political organizations, actually they are business entities that strive on members’ contributions. They talk all nonsense, the irritating thing is, stick they have some adherents. The good thing is they are not strong force that can affect the struggle towards unity, peace and democracy.
  It won’t be long that their confused followers regain their stamina, start seeing the truth and withdraw their support.
  It is obvious they can not come with agreeable political solutions, but as a business entity with different product that can be sold to confused individuals.
  The important thing is let honest Ethiopian give any attentions to such kind group. That is what they want.

 5. I am always surprised by the stand you have and I really appreciate but I am sorry that you don’t have a disciple.

  • discipline? what exactly offended you, his boldness?…that has always been his character

  • Professor Mesfin has no discipline and strategy and this time he wrote some material to be used By TPLF media and TPLF supporters. I would rather ignore this nonsense article (if it counts as an article) since it neither contribute to the struggle nor has an objective except the writer tries to tell us he is more Ethiopian than any one of us. He also failed that he can speak only for himself and doesn’t represent 30+ Million Amhara. Yes I am an Ethiopian but this doesn’t mean I am not Amhara. So, Professor, stop lecturing us on existence of Amhara.

   He failed to understand the contribution of a united diaspora in supporting the struggle. Few years ago Mesfin told us not to call Woyane an enemy since he believes they will come to their senses and respect human right. Well, they are conducting #genocide on Amhara and Oromo. So why should we listen to him.

 6. Professor you are one of the most progressive thinker and treasure of Ethiopia and I admire you for speaking and standing for the truth at all times. As you clearly indicated that the struggle for democracy and good governance in Ethiopia will be won by Ethiopians who make great sacrifices inside the country. People in the diaspora such as Jawar Mohammed and the so called professor Ezekiel Gebissa who live in the oversees want to sabotage the struggle of the Ethiopian people by creating ethnically based narrow and divisive politics among Ethiopians. These people are the enemy of Ethiopia and they only serve the interest of Ethiopia’s enemies such as Egypt and Saudi Arabia in which they get their funds to destroy Ethiopia. People who live in Ethiopia whether they are Amhara, Oromo, Gurage … etc., are making the sacrifices to change the country’s political system for the better future of all Ethiopians. As you are I am against and don’t like ethnically based narrow politics and would like opposition party and community leaders should take significant care and measures to avoid divisive politics like the one we have in Ethiopia today.

  • “አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ አውስትራልያ በጥገኛነት ታዝሎ፣ ከኢትዮጵያ ተገንጥሎ ከኢትዮጵያ ስለመገንጠል ይለፈልፋል! ተገንጥሎ የወጣ ከምን ይገነጠላል?” It’s great saying & it’s a fact. Jawar & ezkiel gabissa are playing TPLF,s role. One Ethiopian professor who used to teach in New York high class universities once said “we would be glad if we manage to get out of the abyss by being united & stay as one, …leave alone divided…”.
   The abyss we have been pushed is so deep & scary, … but, I think we still have some, if not many, great positive people who still hope for the better & are working towards that road–Professor Mesfin & professor Birhanu Nega.
   We have to be the part of these great Ethiopias struggle.

 7. Pro. Mesfen, Let me ask you some questions, in your own word you have denied the existence of the Amhara people in Ethiopia, why today you are concerned regarding the organisation of The Amhara people? Do you think the Amhara people should do nothing until they vanished from the face of the earth by their deadly enemies? Even though the Amhara people are organised in order to defend themselves, they never deny their Ethiopian identity and never abandon their love for Ethiopia. To my surprise, you tried to assimilate the hero Amhara people who stand for the unity Ethiopia with the extremist Oromos who seek the destruction of Ethiopia. Do you think, is this a fair comparison for the people of Amhara who love their mother land – Ethiopia? How you dare to insult millions Ethiopian diaspora and tried to deny their Ethiopian identity? These diaspora Ethiopians who are doing their best for the freedom of Ethiopian people are exposing the evil deed of weyanie to the world and contributing their part in the struggle against the weyanie junta. You have told us your origin is enticho – Tigray, is that the reason why yod don’t care about the systematic genocide of the Amhara people caring out by weyanie? From now on you need to now that the Amhara people have awaked about the hidden agenda of the enemy and have determined to organise and defend themselves. No conspiracy will stop the Amahara people from organising and self defending, eventually struggling for the unity of Ethiopia.

  God bless Ethiopia

 8. Thank you, Prof. Mesfin, for your brilliant piece. Ethiopiawinnet is our only salvation!

  Would individuals without any shame of adopting a tribalist/ethnic mentality, both of Oromo and Amara ilk, such as Jawar Mohammed, wake up from their blunder of being the other side of the Woyane/TPLF coin?!!!

 9. 13 የሃይማኖት አባቶችና ካህናት በረሃ ወርደው አርበኞች ግንቦት 7ትን ተቀላቅለው ህዝብን በማስተባባር ላይ መሆናቸውን ገለጹ ።
  .በዋልድባ ገዳም እና በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች ሲያገለግሉ የነበሩ 13ቱ አባቶች ወደ በረሃ ለመውረድ የወሰኑት አገዛዙ በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እያዩ ዝም ለማለት ህሊናቸውና ሃይማኖታቸው ስላልፈቀደ መሆኑን ተናግረዋል።
  ጠመንጃ ይዘን ባንዋጋም ፣ በረሃ ወርደን ህዝቡ ለነጻነቱ እንዲነሳ እየቀሰቀስነው ነው ያሉት አባቶች፣ በረሃ ውስጥ ከአርበኞች ግንቦት7 አደራጆች ጋር ከተገናኙ በሁዋላ የኢትዮጵያ ወጣት ትግሉን እንዲቀላቀል ትምህርት በመስጠት ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
  ከአርበኞች ግንቦት7 መሪ ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና ከሌሎችም የድርጅቱ መሪዎች ጋር በቅርበት በመነጋገር በአካባቢው የተጀመረው ትግል ዳር እንዲደርስ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑንም አባቶቹ ተናግረዋል። የአርማጭሆና የአካባቢው ህዝብ ከጎናችን ተሰልፎ ድጋፉን እየሰጠን ነው የሚሉት ሌላ አባት፣ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እየተቀጣጠለ የመጣውን ትግል ተቀላቅሎ የአገዛዙን እድሜ እንዲያሳጥር መልዕክት አስተላልፈዋል።
  እኝህ አባት ጳጳሳትና መነኮሳት ሌላውም እንደየስጦታው ተነስቶ ይህን አሸባሪ አገዛዝ ሊያስወግደው ይገባል ብለዋል።
  አባቶቹ ቀደም ብለው በሰሜን ጎንደር ሲካሄድ የነበረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሲያስተባባሩ እንደነበር ይታወቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*

Click here to connect!