Home » ዜና » በስለላ ከሆላንድ የተባረረው የጋዜጠኛውን አንገት እቆርጣለሁ አለ

በስለላ ከሆላንድ የተባረረው የጋዜጠኛውን አንገት እቆርጣለሁ አለ

ክንፉ አሰፋ

እለተ እሁድ ከቀትር በሁዋላ አንድ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። ቁጥሩ +251 945226530 ነበር። ስልኩን አነሳሁት።

“ሃሎ”

“አቤት”

“አለማየሁ ነኝ። መን አባክ ነው የምትጽፈው። እኔ አላማዬ ነው። አንተን ግን አንገትህን ቆርጬ ነው የማሳይህ። ለማየት ያብቃህ። ያን የምትጽፈውን ጽሁፍ… እኔ ምንም ልሁን ምን እንደዚህ አይደለሁም። እሺ። እናትክን… (ይህንን ጸያፍ ቃል በድምጽ ስሙት)። … ደግሞ ኢህአዴግ ዘርህን… (ይህንንም ጸያፍ ቃል በድምጽ ስሙት)

TPLF spy in Netherlands

ከሆላንድ የተባረረው የወያኔ ሰላይ አለማየሁ ስንታየሁ(ሀለቀ ፎላ)

ይህ ጸያፍ ዘለፋ እና ማስፈራርያ እንግዲህ ወያኔ ምን ያህል እንደወረደ ያሳየናል። ከነውረኛ ስድቡ ባሻገር ደግሞ ቀላል የማይባል ድንበር ዘለል ሽብር ነው። ለዚህ ሽብር ተጠያቂ የሚሆነውም ተላላኪውና ሆድ አደሩ ብቻ ሳይሆን ላኪውም ጭምር ነው። ህወሃትን በመጠለል ልክ እንደ ISIS አንገትህን እቆርጥልሃለው ሲል መናገሩ መንግሥታዊ አሸባሪነት ለለመሆኑ ግልጽ ነው። ለዚህ ሰው ሲከራከር የነበረው ተሾመ ቶጋም ይህንን ሰምቶ ዝም የሚል ከሆነ የወንጀሉ ተባባሪ ይሆናል።

በዚህ አይነት ማስፈራራት አላማቸውን ማስፈጸም ካሰቡ ግን በጣም ተሳስተዋል። እንዲህ አይነቱ ነገር የበለጠ እልህ ውስጥ ያስገቡናል እንጂ በስራችን ላይ ቅንጣት ያህል ተጽእኖ ሊፈጥሩ አይችሉም። እንደጋዜጠኛ ለመስራት ስንነሳ ፍርሃትን ከእትብታችን ጋር ቀብረነው ነውና ይህንን የምትሞክሩ ተስፋ ቁረጡ ነው የምንላችሁ።
ይህ ሰው ከሆላንድ የመኖርያ ፈቃዱ ተነጥቆ ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሰ በተለያዩ የዜና አውታሮች መዘገቡ ይታወሳል። ስለዚህ ሰው ጉዳይ ተሾመ ቶጋ (የወያኔ አምባሳደር) ከብራስልስ ማስተባበያ ሰጥቶ ነበር። ማስተባበያው ባጭሩ፣ “አለማየሁ ስንታየሁ ሰላይ አልነበረም። ከሆላንድም አልተባረረም። የተሰደደውም ከኢሃዴግ ዘመን በፊት ነው። … ይህ ደጋፊዎቻችንን ለማሸማቀቅ በአሸባሪ የተፈረጁ ሰዎች የሚያወሩት ወሬ ነው።” ይላል።

የሶስት ልህጆች አባት የነበረው አለማየሁ (ዘለቀ ፖላ) የሆላንድ የመኖርያ ፈቃዱን እና መኖርያ ቤቱን ተቀምቶ ከሄደ ሶስት ወራት አልፈዋል። ጉዳዩን ከሚመለከተው ክፍል በማጣራት የዜናውን እውነተኝነት አረጋግጠናል።

ዜናው በውጭ ያሉ የስርዓቱ ደጋፊዎችን በእጅጉ ያስደነገጠ በመሆኑ የተሾመ ቶጋ ማስተባበል የግድ ነበር። ውሸት ነው ማለታቸውም አይደንቅም። እውነት ተናግረው ሰምተናቸው ስለማናውቅ። አለማየሁ ስንታየሁ ችግር እንደነበረበት እና አስፈላጊውን ደብዳቤ ከኤምባሲው ተቅብሎ ወደ ኢትዮጵያ መሄዱን አቶ ተሾመ በቃለ-ምልልሱ አልሸሸጉም።

የተሾመ ቶጋን ውሸት ከሰማሁ በኋላ ጉዳዩን ለማጣራት የሚመለከታቸው የሆላንድ መንግስት አካላትን አነጋግሬአለሁ። ሶስት ክሶች ተመስርተውበት ነበር። አንደኛው ከወያኔ ካድሬዎች ጋር በመመሳጠር አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሃብትን እንዲታፈን በማድረጉ፤ ሁለተኛው ክስ የአሱን ስም በማጭበርበር እና፤ ሶስተኛ የሆላንድ መንግስትን ዋሽቶ የስደት ፈቃድ ከገኘ በህዋላ ለገዢው ፓርቲ ይሰልላል የሚሉ ነቸው።

ጭንቀት ውስጥ በነበረ ጊዜ ከአንዴም ሁለቴ ደውሎ በጉዳዩ ላይ አነጋግሮኛል። ከሚኖርበት አካባቢ እንዳይርቅ በሆላንድ መንግስት ታግዶ በነበረበት ወቅትም ከመገኛኛ ብዙሃን፤ በተለይ ከጀርመን እና ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋር እንዳገናኘው ጠይቆኝ ነበር።

ይህ ሰው ወደ ሆላንድ የገባው በ1994 (ወያኔ ስልጣን ከያዘ ከአንድ አመት በህዋላ) በሰላም ተጓዥ ስም ነበር። ከዚያ ለበርካታ አመታት በስውር ከዚያም በግልጽ ለወያኔ ሲሰራ ነበር።

ጋዜጠኛ አፈወርቅ አገደው በፌስቡክ ገጹ ላይ ስለዚህ ሰው እንዲህ ሲል አስነብቦናል። “ይህን ግለሰብ በአካል አውቀወለሁ። ብዙ የቅርብ ጓደኞቼም ስለሚሠራቸው የስለላ ሥራዎቹ ያውቃሉ። ከራሱ አፍ እንደሰማሁት ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፖላ ነው። እዚህ ስደት የጠየቀበት ስሙ ዓለማየሁ ስንተሰየሁ ነው። የወላይታ አካባቢ ተወላጅ ነው። ተቃዋሚ መስሎ ለህወሓት ኤምባሲ ብዙ የስለላ መረጃዎችን የወያኔ ተቃወሚዎችን በሚመለከት እንደሚያቀብል ይታወቃል። … አንዳንዴ ስብሰባዎቹ ሌሎችን በሚያገልል መልኩ በትግርኛ ሲደረግ ዘለቀ ፖላ ይሳተፋል። ምኑ ገብቶህ ነው በማታውቀው ቋንቋ የምትሳተፈው ስንለው ጆሮዬ ክፉ ክፉውን ስለሚሰማ ለእናንተ ወሬ ለማቀበል ነው ይል ነበር።”

8 comments

 1. ኣለቃ ብሩ፦ ይህ ሁሉ ትንተና ምን ኣስፈለገ፧ ሚዛናዊ፤ ግራ ቀኝ ተመልካች፥ ነኝ ለማለት ነው ፥፥ ጉድ አኮ ነው፥፥ ሰውየው ወያኔ ከሆነ ሚዛናዊ የሚለው ቃል በራሱ ቦታ የለውም፥፥ ይልቅ ክንፉን ልጠይቀው የምሻው አንዴት ሊቀዳው ቻለ፤፤ ይህን ያልኩት ሃሎ ከሚለው ቃል ጀምሮ ከተቀዳ ክንፉ ሰውየው ማን አንደሆነ ኣያውቅም ነበር ማለት ነው፥፥ ስለዚህ አንዴት recording button on ኣድርጎ ሊጠብቅ ቻለ፥፥ ወይስ it is on by default?

  • ግራና ቀኝ ማየት ስለማትፈልግ ነው እንጅ እኮ “ሀሎ ከሚለው ጀምሮ እንዴት ቀዳው” የሚለው ጥያቄህ እኮ የሚጠቁምህ ትልቅ ጉዳይ አለ:: ምናልባትም ክንፉ እና ሰውየው በስልክ የተነጋገሩት ከአንድ ጊዜ በላይ መሆኑንና ክንፉ ቁጥሩን አይቶ የማን እንደሆነ እውቀት እንደነበረው የሚጠቁም እኮ ነው:: ክንፉ የደዋዩን ማንነት አስቀድሞ ያውቅ እንደነበር ከአመላለሱ እራሱ ማወቅ ይቻላል:: በጣም ትህትና በጎደለው መልክ ነው ጥሪውን የተቀበለው:: “ሀሎ” እንኳን አይልም::
   ሚዛናዊነት ለወያኔ አይሰራም ያልከው አከራካሪ ቢኖንም በመጀመሪያ መጠየቅ ያለብህ “በእርግጥ አቶ አለማየሁ ስንታየሁ “ወያኔ” ነው ወይ?” ብለህ ነው:: እውነቱን እየሸራረፉ ቁርጥራጭ “እውነታዎችን” በሚሰጡህ ግለሰቦች ላይ ብዙ እምነት አይኑርህ ወዳጄ !!!

   • ኣለቃ፥ ሰውዬው ወያኔ ከሆነ ሚዛናዊነት የሚለው ቃል ቦታ ኣይኖረውም ነው ያልኩት፥ (ከሆነ)፥፥ ከኣነጋገሩ ደግሞ ነው ማለት ይቻላል፥፥ ኣንገት አቆርጣለሁ፥ ጣት አቆርጣለሁ ኣይነት ቃሎች የማን አንደሆኑ አናውቃለን፥፥ ከክንፉ ጋር ችግር ካለብህ አሱን በግል ኣስተናግድ፥፥ አኔ ክንፉን የጠየቅኩት ቲክኒካል ነገር ነው፥ መስልሱን ደግሞ ኣንተ መለስከው፥ ክንፉ የሰውዬውን ስልክ ቀደም ብሎ ስለሚያውቀው ቁጥሩን ሲያየው መቅጃውን ተጫነው፥፥ ይህ ደግሞ የክንፉን ፈጣንነትና ቅልጥፍና ያሳይ አንደሆን አንጂ ኣንተ ልታሳየኝ አንደፈለከው ተንኮለኝነትን ኣያሳይም፥፥ ተንኮልማ ያለበት ኣለ፥፥ ኣገራዊ ጉዳይና ጥቃት ስናወራ ወደ ግለሰብ ጸብ ለመቀየር የሚደረገው ሙከራ ምንጩ የት አንደሆነም አናውቃለን፥፥ ክንፉ ኣሰፋ በርታ፦ ኣለቃ ስለተነቃ ካንተጋ በዚሁ ይብቃ፦

    • አቶ ብርሀኑ በጣም ዚበዛ የዋህ ሰው ነዎት:: ለምን ይበሉኝ:-
     1. አንዴ ሰውየው “ወያኔ ከሆነ” እያሉ ስለጉዳዩ እርግጠኝነት እንደለለዎት እየጠቆሙ የኔን ዋና ሀሳብ በተዘዋዋሪ ያጠናክራሉ:: ሌላ ጊዜ ደግሞ “ካነጋገሩ ወያኔ ነው ማለት ይቻላል” ይላሉ:: ሰውየው የሚናገረው ነገር በደም-ፍላት እንደሆነ እና ምንም ከሎጂክ ጋር እንደማይጣጣም በመጀመሪያው አስተያየቴ በቀልድ መልክ አቅርቤዋለሁ:: ስለዚህ ሰውየውን በወያኔነት ለመፈረጅ መጠቀስ የሌለበት ማስረጃ ቢኖር ይህ ክንፉ ቀነጫጭቦ የለጠፈው ንግግር ነው:: ስንታችን በደም-ፍላት ስንት ነገር እንላለን በየቀኑ?
     2. ለክንፉ የጠየቁትን ጥያቄ (እንዴት ንግግሩን እንደቀዳው) እኔ መልስ እንደሰጠሁዎት እና ትክክለኛ የሆነው ነገር እሱ እንደሆነ አድርገው የተቀበሉ ይመስላሉ:: እኔ የሰጠሁት ግምት ነው እንጂ መልስ አይደለም:: ትክክለኛውን መልስ የሚያውቀው ክንፉ ብቻ ነው::
     3. እኔ አንዱን የክንፉን ጽሑፍ ስለተቸሁ (ሌሎች ጽሑፎቹን እንደማደንቅ ጥቅሻለሁ) ብቻ ከክንፉ ጋር የግል ቅያሜ እንዳለኝ አድረገው ቆጥረዋል::
     4. ገና ለገና ክንፉን ስለተቸሁ ብቻ እኔን ወያኔ አድረገው ፈርጀው ከአሁን በኋላ ክእኔ ጋር ንግግር (ውይይት) ላለማድረግ ወስነዋል:: ወያኔ ባልሆንስ? በምን እርግጠኛ ሆኑ?
     5. የመጨረሻው እና በጣም ዋነኛ ነገር ደግሞ እርስዎ ክንፉን “ግፋበት” ብለው የመከረቱ ነው:: በምኑ ነው የሚገፋበት? ያልተሟላ እና የተድበሰበሰ መረጃ ለሕዝብ ማቅረቡን ነው እንዲገፋበት የመከሩት? እኔ የተቸሁት እኮ ስላድበሰበሰው እንጂ አሳማኝ በሆነ መልኩ በተሟላ መረጃ ሰውየው የተባረረበትን (ተባሮ ከሆነ) ሁኔታ ቢያቀርብ እኮ ተቃውሞ/ትችት አይኖረኝም ነበር::

     ዋናው መልዕክቴ:- ስሜተኞች አንሁን:: እንዲህ ሆነ ስንባል እንዴት? መቼ? ለምን? ወዘተ ብሎ መጠየቅ ይልመድብን::

 2. “አንገትክን ቆርጬ አሳይሀለሁ?” አቶ አለማየሁ ቆይ! ሰው አንገቱ ከተቆረጠ በምን ተዓምር ነው ማየት የሚችለው? ለፈገግታ ያህል ያልኩት ተደርጐ ይወሰድልኝ:-)))

  አቶ ክንፉ ሰውየው ይህንን ሲናገር ደሙ ፈልቶ በትክክል እያሰበ አልነበረም ማለት ነው:: አሁን ዋናው ጥያቄ “አንገት መቁረጥ/አለመቁረጡ” ሳይሆን ለምን የአቶ አለማየሁ ደም ፈላ የሚለው ነው:: ተቀድቶ የተለጠፈው የስልክ ንግግር ሙሉ ስላልሆነ የደም-ፍላቱ ምክንያት ምን እንደሆነ ማወቅ አይቻልም::
  ሚዛናዊ ጋዜጠኝነት ሙሉ መረጃን ማቅረብ ይጠይቃል:: ስለዚህ ሰውየው በደም ፍላት የተናገራቸውን ቃልቶች ብቻ ቀነጫጭቦ በማሰማት በሱ ላይ ውግዘት ለማግኘት መሞከር ትክክል አይመስለኝም:: ሲጀመር እንዲህ ዓይነት የስልክ ንትርኮች ለዜናነት ይበቃሉ የሚል እምነት የለኝም::
  ከዚህም በተጨማሪ የሰውየውን ሙሉ ስልክ ቁጥር ለህዝብ ማሳወቅ ለምን አስፈልገ? ምን ዓይነት ይዜና ዋጋ አለው? ወይስ ቂም-በቀል ነው (የተበሳጨ ሁሉ እየደወለ እንዲሰድበው ለማድረግ)? ቂም-በቀል ደግሞ ሚዛናዊነት ይሳጣል::

  በመጨረሻ ደግሞ ማለት የምፈልገው ባለፈው ከሆላንድ አገር ስለተባረረበት ሁኔታ ዘርዘር አድርጌ እጽፋለሁ ብለህ ቃል ከገባህ በኋላ እስከ ዛሬ ምንም የጻፍከው ነገር አለመኖሩ ነው:: እዚህኛው ጽሑፍህ ላይ “የሆላንድ የመንግስት አካላትን” አነጋግረህ ሶስት ክሶች ተመስርተውበት እንደነበር ገልጸሃል:: ይህንን በተመለከተ እንዳንድ ያልገቡኝ ነገሮች አሉ:-
  1. ስለአናገርካቸው የመንግስት አካላት ለምን ዘርዘር አድርገህ አልጻፍክም? ለምሳሌ የመስሪያቤት ስም እና የባለስጣን ስም ወዘተ በመጥቀስ መጻፍ ትችል ነበር::
  2. የጠቀስካቸውን ሶስት ክሶች የመስረታቸው ማን ነው? ይህም ማለት አቶ አለማየሁ በማን ነበር የተከሰሰው (በግለሰብ በቡድን ወይስ በሆላንድ አቃቤ-ህግ)?
  3. የሶስቱ ክሶች ውሳኔ ምን ነበር? በሶስቱም ወንጀለኛ ተባለ ወይስ በሁሉም ነጻ ወጣ ወይስ ሌላ?
  4. “ከሆላንድ የተባረረው” እያልክ ነው የምትጽፈው:: ስለዚህ ስለመባረሩ ርግጠኛ ነህ ማለት ነው:: የተባረረበት ምክንያት ከሶስቱ ክሶች ጋር የተያያዘ ነው ወይስ ያልጠቀስከው ሌላ ጉዳይ አለ?

  ብዙ ጊዜ የምትጽፋቸው ጽሑፎችህን በጣም እወዳቸዋለሁ:: ጥሩ የመጻፍ ችሎታ አለህ:: ይህኛው ግን በሰከነ ሁኔታ ሆነህ የጻፍከው ነው የሚል ግምት የለኝም:: እና ረጋ ብለህ ካሰብክበት በኋላ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንደምትጽፍ ተስፋ እያደርግሁ ለጊዜው ከላይ ለጠቅስኳቸው ጥያቄዎች መልስ እጠባበቃለሁ::

  ከአክብሮት ጋር
  አለቃ ብሩ

 3. This man is a total jerk and is an idiot hoddam. Seemingly, there are of similar mission scattered around the world spying for Fascist TPLF; however, by paying full attention on removing surgically these type likiskis weshoch from our societies they infiltrated into, we can eventually cleanse them out like we do dirties from the sole of our shoes. Hoddams don’t have self-respect.

 4. yehe leba enatun yemayawek ayatun yenafek pola ferenji haderaw guracha haderw

 5. also kinfa you don't write the truth. do you remember you wrote about TPLF hit Eritra's golden mine. you don't ask apologize and you don't say sorry. I no more belive you.

Comments — What do you think?