ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ በአውሮፓ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች የተሰገሰጉትን አሻጥረኞች የዲሞክራሲ ጠላቶች ይመንጥሩልን

Ethiopian Embassy in Berlin.

ስራቸው እየዞሩ ኢትዮጵያውያንን መከፋፈል እንዲሁም ያየር ባየር ንግድ እና የሌብነት ስርዐት እንዲጧጧፍ ያደረጉ ኢትዮጵያውያንን ሲከፋፍሉ ሲያመናጭቁ እና ሲያሸማቅቁ የነበሩ ተግባራቸው እየዞሩ ካደራጁዋቸው ግብረዓበሮቻቸው ጋር እድር እና ሰንበቴ ሲበሉ የከረሙ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ኤንባሲዎች የተሰገሰጉ አሻጥረኞች አምባሳደር ካውንስለር እና የዲያስፖራ ክፍል ተብዬዎችን ይመንጥሩልን።

Read More »

የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ እና የጋምቤላ ናይሎቲክ አንድነት ንቅናቄ የጋራ መግለጫ

Press Release, Ethiopia

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረዉ የጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ እና የጋምቤላ ናይሎቲክ አንድነት ንቅናቄ የዉህዴት ስብሳባ ዛሬ ህዳር 4 ቀን 2011 ዓ ም ባካሔድነዉ የጋራ ስብሰባ አንድነት ኃይል መሆኑን በማመን ሁለቱ ድርጅቶች ተዋህዳዉ በጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋ.ሕ.ነ.ን.) ጥላ ሥር በመሆን ለመሥራት ተስማምተናል፡፡

Read More »

ይህን የዐደራ መልእክት ለጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አድርሱልኝ! (ነፃነት ዘለቀ – አዲስ አበባ)

PM Abiy Ahmed to the people of Ethiopia.

የኤሌክትሪክ ፍጆታ ላይ የታሪፍ ለውጥ ማድረግ በተለይ አሁን ለምን አስፈለገ? ጭማሪ ይደረግስ ቢባል በኪሎ ዋት ከሃምሣ ሣንቲም ወደ አንድ ብር ከሃምሣ ሣንቲም ማሳደግ ምን የሚሉት ጭማሪ ነው?

Read More »

አንዳንድ የህወሃት ቁንጮዎች የእስር ማዘዣ ተቆርጦባቸዋል (መሳይ መኮንን)

Wanted former Ethiopian officials.

አሁን እንደሰማነው የስኳሩ ንጉስ አባይ ጸሀዬ፡ የሜቴኩ ባላባት ብ/ጄ ክንፈ ዳኘው እና የሳይበሩ ጠላፊ ሜ/ጄ ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የእስር ማዘዣ ተቆርጦባቸዋል።

Read More »

የኢሳትና የሪፖርተር ዜናዎች አንዳች ነገር አመልካች ናቸው (መሳይ መኮንን)

Ethiopian journalist, Mesay Mekonnen.

በኢሳት የትላንት መረጃ መሰረት ከ160 በላይ ጄነራሎችና የጦር አዛዦች በጠ/ሚር አብይ ትዕዛዝ ከሰራዊቱ እንዲሰናበቱ ተደርገዋል። አብዛኞቹ የህወሀት ጄነራሎች ናቸው። ዛሬ ደግሞ ሪፖርተር ጋዜጣ ከ40 በላይ የሜቴክና የደህንነት አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሚያትት ዜና ይዞ ወጥቷል።

Read More »

አጥብቆ ያሰረ ዘቅዝቆ ይሸከማል… (መስከረም አበራ)

Ethiopia, Raya unrest.

በ1983 ዓ.ም አዲስ አበባን የተቆጣጠረው ህወሃት ቀጣይ ሥራ ያደረገው የትግራይን ግዛት ማስፋፋት ነበር፡፡ይህ የረዥም አመት ፕሮጀክት የተጀመረው ከጎንደር ወልቃይትን የመሰሉ፣ከወሎ ራያን የመሰሉ ለም መሬቶችን ልምላሜ ወደ ሚያጥራት ትግራይ ክልል በማካለል ነው፡፡ይህ ህወሃት በአማራው ህዝብ ላይ ከሰራቸው በርካታ ግፎች ውስጥ በከፍተኛ በጥንቃቄ የተሰራው ነው፡፡

Read More »

ከ40 በላይ የሜቴክና የደኅንነት አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ

Kinfe Dagnew (B. Gen.), the chief executive officer (CEO) of the Metal & Engineering Corporation (MetEC)

ከ40 በላይ የሚሆኑ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከፍተኛ አመራሮችና የደኅንነት አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቆመ፡፡

Read More »

የአዲስ አበባ ፖሊስ ህግ አስከባሪ ወይስ ዘራፊ? (ብርሃኑ ተክለያሬድ)

Police and corruption in Addis Ababa.

ለመሆኑ ገንዘቡ ቢወረስ እንኳን ህጋዊ ደረሰኝ መስጠት አያስፈልግ ይሆን? ኮማንደሩ የኛ ልጆች ሳይፈቱ... ያሉትስ እነማንን ይሆን? ይሁን አስኪ ገንዘባችንንም ተነጥቀን ለማስፈራሪያው እያሟሟቅን ነው!

Read More »

የቁጥር ዕውቀቴ ካናካቴው ከዳኝ! (ይሄይስ አእምሮ፣ ከአዲስ አበባ)

Ethiopian birr

በየሚዲያው የምትሰሙት ቁጥር ያስበረግጋችኋል፡፡ ሰዎች በተለይም ፖለቲከኞችና በልማት ተብዬው መስክ የተሰማሩ የመንግሥት ሰዎችም የቁጥር ዕውቀታቸው እንደኔው ሳይከዳቸው የሚቀር አይመስለኝም፡፡

Read More »

ቃል በምድር፣ ቃል በሰማይ! (ከወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ)

Ethiopia's reformist politicians.

ዐቢይን የሚቃወሙም፣ ከወያኔ ውጭ አንዳንድ ሰዎች አሉ። ምክኒያት አላቸው። ምክኒያታቸውም አሳማኝ ነው። ግን ዐቢይን በጥርጣሪ እንዲያዩት የሚያደርጉ፣ ከላይ የተገለጹት ድርጊቶችን የሚፈጽሙ እነማን እንደሆኑ አሻግሮ ማየት ይኖርባቸዋል። ዛሬ እነዚህ መሠርይ ኃይሎች አመራር፣ በአብዛኛው መቀሌ መሽገዋል።

Read More »

ሚድያዎች የህብረተስብ የጀርባ አጥንት ናቸው (ከጎሹ ገብሩ)

ESAT television new satellite

ዛሬ ይህችን አጭር ጽሁፍ እንድጭር ያነሳሳኝ ዋናው ምክንያት ኢሳት ከተመሰረተ ጅምሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያደረጋቸው አመርቂ ተግባሮች እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ መብቴን ተጠቅሜ የሚሰማኝን ሃሳብ ለመግለፅ እንጅ አንዱን ኮንኘ ሌላውን ለማሸማቀቅ ወይም በጭፍን ድጋፍ ለመስጠት እንዳልሆነ ቅድሚያ ግልፅ ማድረግ እፈለጋለሁ።

Read More »

ከጥንቱም ሌባ ሲሸሽ የዘረፈውን እያንጠባጠበና መውሰድ ያቃተውን እያበላሸ ነው! (ልሳነ ግፉዓን)

People of Raya protesting against TPLF.

በአጭሩ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ጥያቄ በወረራ የተወሰደው መሬቱና በሃይል የተገፈፈው አማራነቱ  ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማስመለስ እንጂ በወረራ ለሰፈሩት የትግራይ ተወላጆች የሚያመችና ባለ ዕርስትነት የሚያረጋግጥ “የራስ ገዝ” አስተዳደር ለመጠየቅ የሚያበቃው ምንም አይነት ምድራዊ ምክንያት የለውም። አይኖረውም።

Read More »

ሸገር ደርሶ መልስ (ክንፉ አሰፋ፣ ክፍል ሦስት)

Ethiopis news paper ready to distribution.

እውቀት ወይንም ገንዘብ ያካበተን ዲያስፖራ ወደ ሃገሩ እንዲገባ ፤ ገብቶም እንዲሰራ ከማበረታታት እና ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር ሌላ ነገር ነው። ከውጭ ለሚገባውን ብቻ ለይቶ የተለየ መብት መስጠት ተገቢ አይደለም።

Read More »

ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ሀያ ስምንት ሰራተኞችን አባረረ

Kombolcha Textile.

ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክስዮን ማህበር ከተመሰረተ በርካታ አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የመንግስት የልማት ድርጅት ከነበረበት ወቅት ጀምሮ እስከ ቅርቡ በጥረት ኮርፖሬት መተዳደር እስከጀመረበት ወቀት ድረስ በነ በረከት ስምኦን እና አህመድ አብተው ተዘርግቶ በነበረው የዝርፊያ እና የሙስና ሰንሰለት ያለምንም የመዋቅር...

Read More »

… ሸገር ደርሶ መልስ (ክንፉ አሰፋ፣ ክፍል ሁለት)

Journalist Kinfu Assefa, about Ethiopia. Part 2.

በጉዞዬ ላይ አንድ ነገር አስተዋልኩ። ማንኛውም ዲያስፖራ ስለሃገሪቱ የሚኖረው የመጀመርያ እይታ ውሎ ሲያድር እንደሚቀየር። የመጀመርያ እይታ እጅግ ይጋነናል። ያስደነግጥማል። ውሎ ሲያድር ግን ሁሉም እየተለመደ ይሄዳል።

Read More »

“ቅንጅት” ዳግም ይወለድ (ዶ/ር ዘላለም እሸቴ)

Ethiopian News and Views in Amharic

ተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች ዶ/ር አብይ የተጫነባቸው ዓይነት የኢህአዴግ ቀንበር የለባቸውም።  በዚህም ምክንያት ለተስፋይቷ ኢትዮጵያ ለመታጨት ነፃ ናቸው።  ነገር ግን የኢህአዴግን አጀንዳ እያራመዱ ከኢህአዴግ የተሻለ ፓርቲ ነኝ ብሎ መንቀሳቀስ ከእውነት ስለሚርቅ አይጠቅምም።

Read More »

የወያኔ አፈና በራያ ህዝብ ላይ ትግሉን ያጠነክረዋል እንጂ አያስቆመውም (ከልሳነ ግፉዓን ድርጅት የተሰጠ መግለጫ)

People of Raya protesting against TPLF.

ሽብር ፈጣሪው የትሕነግ ልዩ ሃይል ከጀመረው እኩይ ተግባር ተቆጥቦ በአስቸኳይ ከራያና ወልቃይት መሬት ወጥቶ በምትኩ የፌደራል ሃይል ገብቶ የአካባቢውን ሰላም እንዲያስከብር እናሳስባለን።

Read More »

ሸገር ደርሶ መልስ (ክንፉ አሰፋ)

Ethiopis news paper ready to distribution.

የእልልታ ድምጽ ሰምቶ ግቢያችንን የሞላው የሰፈር ሰው ሁሉ ፈጣሪን ሲያመሰግን ሰማሁ። ከፈጣሪ ቀጥሎ ደግሞ የሚመሰገነው ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ነበር። “እድሜው ይርዘም” ሲሉ ይመርቁታል የሚያገኙኝ ሁሉ።

Read More »

በአዲስ አበባ ወጣቶች ጉዳይ አርበኞች ግንቦት 7 ዝምታን መርጧል? (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

Ethiopian political activist Birhanu Tekleyared.

የንቅናቄው መሪዎች አሁንም "ያሳስበናል" ወዘተ የሚል መግለጫ ከማውጣት ይልቅ ችግሩን ለመፍታት በሚያስችሉ የመፍትሄ ተግባራት ላይ ነበር ያተኮሩት። ከፖሊስ ኮሚሽነሩ ጀምሮ ሀገሪቷን እየመሩ እስካሉት የመጨረሻው ሰው (ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ) ድረስ በተከሰተው ጉዳይ ሰፊ ውይይቶችና ምልልሶችን አድርገዋል።

Read More »

ትኩስ ዜና ልንገርህ፤ ዘረኝነት በዘረኝነት ተተካልህ! (ይሄይስ አእምሮ)

Ethiopian opinions forum

ከአሁን በኋላ ማንም ቢሆን የኢትዮጵያን ሕዝብ ማታለል አይቻለውም፤ የኢትዮጵያና ሕዝቧን ነፃነትም ማዘግየት ይቻል እንደሆነ እንጂ ማንም ምድራዊ ኃይል ሊያስቀረው አይችልም፡፡

Read More »

“የአዲስ አበባ ወጣቶችን ለማደራጀት ተንቀሳቅሰዋል” ተብለው የታሰሩት ፍርድ ቤት ቀረቡ

Lawyer Henok Aklilu and Micael Melaek.

ቀደም ሲል ህወሃቶች "አሸባሪ" የሚል ስም እየሰጡ የስልጣን ስጋት ያሳደሩ ተቃዋሚዎችን እና አክቲቪስቶችን እንደሚያስሩ ሁሉ የጠ/ሚ አብይ አህመድ አስተዳደርም ያንኑ አይነት መንገድ እየተከተለ ይመስላል።

Read More »

አቶ ታዬ ደንደአ ዳግም መስመር ስተዋል (በመሳይ መኮንን)

Taye Dendea, Ethiopia's Oromia region official.

'ህገወጥነት' ብለው የሚከሱትን አካል በህገወጥ መስመር ለማረም ወገባቸውን ታጥቀው ተነስተዋል። ይህን ሁሉ የሚያደርጉት የመንግስትን ትልቁን ሃላፊነት ተሸክመው ነው።

Read More »

ግልጽ ደብዳቤ ለጠ/ሚ አብይ አህመድ (ግሎባል አሊያንስ)

Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE)

ፍትኅን የማረጋገጡ ጉዳይ፤ ለምንጓጓለት ለውጥ መሳካት ወሳኝ በመሆኑ፤ የታገቱት ወጣቶች ጉዳይ ተገቢው ትኩረት ተሠጥቶት፤ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤ በአክብሮት እንጠይቃለን።

Read More »

በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ የተፈጸመው የጅምላ እስር እና ግዞት አግባብነት የሌለው ነው

PM Abiy Ahmed release Addis Ababa youth.

በአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ የተፈጸመው የጅምላ እስር እና ግዞት በማንኛውም መመዘኛ አግባብነት የሌለውና የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው።

Read More »

የኢትዮጵያ ወይንስ የትግራይ አየር መንገድ? (ይሄይስ አእምሮ)

Ethiopian Airlines and it's management.

ባለፈው ሰሞን አየር መንገዱ 27 ሆስተሶችን (የሴት አስተናጋጆችን)  አስመርቋል፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ሃያ ሰባቱም ትግሬዎች ናቸው፡፡ አዲስ አበባን የማያውቁና ብዙዎቹ አዲስ አበባ ውስጥ ቤተሰብ የሌላቸው ፍጹም ባላገር ሴቶች ናቸው፡፡

Read More »
Click here to connect!