Added on: December 3rd, 2011
Recent Posts
Obama Speech at Morehouse - Full commencement speech
May 21st, 2013
Published by: dinbush
Category: News and Documentary
Ethiopian News Ethiopian family members in USA graduated with six degrees in one week
May 21st, 2013
Published by: dinbush
Category: News and Documentary

By: Alazer Ayele
Look it
By: bi
(comment on paltalk live video discussion on 3/12/2011)እኔ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ የወያኔ መንግስት እየሰራ ያለውን ነገር ሁሉ በፅኑ እቃወማለሁ፡፡ ከኔ በተሻለ መልኩ ድምፃቸውን እያሰሙ ባሉ ወገኖቼ በኩል ግን አንዳንድ የተሳሳቱ አመለካከቶች አሉ ባይ ነኝ፡፡
1.የወያኔ/ኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎችን በተመለከተ፡ ዛሬ ስራ ለማግኘትና በስራ ገበታም ላይ ለመቆየት፣በልቶ ለማደር እንዲሁም አንዳንዴም በሕይወት ለመሰንበት ያክል እስኪመስል ድረስ አባልነትና ደጋፊነት የግድ በሆነችው ኢትዮጵያችን ሁሉም አባላትና ደጋፊዎች እውነተኛ ደጋፊዎች አስመስሎ ማቅረብ በጣም የተሳሳተ አመለካከት ነው እላለሁ፡፡ ከምንምና ከማንም ምን አልባትም ከኔና ከእናንተ በበለጠ ነፃነትን የሚናፍቁና በህዝብ ስም በሚተዳደሩብን ጥቂት ግለሰቦች የሚደረገውን እንቅስቃሴ በበለጠ ሊያቀጣጥሉ የሚችሉበትን ጊዜ የሚናፍቁ ወገኖችን ሆዳም፣ ባንዳና ሌሎችንም ኢ-ሞራላዊ ቃላትን እየመረጥን መሳለቅ ተገቢ አይመስለኝም፡፡
2.ሁሉም የትግራይ ህዝብን በተመለከተ፡ ዛሬም እንደትላንቶቹ ገዥዎች በስሙ እየተነገደበት ያለ ተረኛ ህዝብ የትግራይ ህዝብ ነው ባይ ነኝ፡፡ እንደቀሪው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ዛሬም የትግራይ ህዝብ ሀሳቡን የመግለፅ፣ የፍትህና አስተዳደራዊ በደል ፅዋ እየተጎነጨ ያለ ሲከፋም በስሙ በአብራኩ የወጡ ልጆች እየተቀጠቀጠ ያለ ህዝብ ነው፡፡ ምን አልባት ከወያኔ ዘረኛ አመለካት የተነሳ ጥቂት የማይባሉ በዚህ ስርዓት የኩራት መንፈስ ሊያድርባቸው ይቸላል፡፡ እውነታው ግን ዛሬም በነዚህ መሪዎቹ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የፍትህና የአስተዳደር ግድፈት ተቋዳሽ ነው፡፡ በዚህ የተሳሳተ አመለካከት የተነሳም ብዙ የትግራይ ተወላጅ ወገኖቼ ዝምታን መርጠዋል፡፡
ስለሆነም እንደህዝብ ሚዲያ ቅድሚያ ለምንናገራቸው ቃላት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ህዝብ ይገመግማል፡፡ ዛሬ ከምንናገራቸው ቃላት ህዝብ ስለነገ ማንነታችን ይገምታል፣ ይጠራጠራልም፡፡ ለውጥ ከራስ ይጀምራል፡፡ የኛ መለወጥ ሌሎችንም ይለውጣል፡፡ የኛ የመቀስቀሻ መንገዶች የዛሬ የወያኔ አባላትንና ደጋፊዎችን አመለካከት ይለውጣን፣ ዛሬ በመንታ መንገድ ላይ ያለውን የትግራይ ህዝብ ለእንቅስቃሴው መሰረት ይሆናል፡፡
ከዛ ውጭ ግን አሁን በማየው ሁኔታ ሀገሬን ለሌላ በላተኛ አሳልፎ እንደመስጠት እቆጥረዋለሁ፡፡ በዚህ የነፃነት ጥያቄ ውስጥ ግን ከሳምንት በፊት የአንድነት ፓርቲ የሰጠውን መግለጫ ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ ለኔ ከበሰለ አመለካከት የመጣ ትክክላውን ወቅት የጠበቀ ነው ባይ ነኝ፡፡
ቢ. ከኔዘርላንድስ
By: bi
the above comment is given for a live paltalk discussion held on 3/12/2011.
By: bi
እኔ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ የወያኔ መንግስት እየሰራ ያለውን ነገር ሁሉ በፅኑ እቃወማለሁ፡፡ ከኔ በተሻለ መልኩ ድምፃቸውን እያሰሙ ባሉ ወገኖቼ በኩል ግን አንዳንድ የተሳሳቱ አመለካከቶች አሉ ባይ ነኝ፡፡