የሕወሓት ካህናት እግዚአብሔርን ይቅርታ ጠይቁ (ነፃነት ዘለቀ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

ከአንድ ማስፈንጠሪያ ተነስቼ አንድ የትግርኛ ዘፈን ኢካድፍ ድረገፅ ላይ ቪዲዮውን ተመለከትኩና ከልብ አዘንኩ፡፡ እነዚህ ወያኔዎች በፈጣሪም ላይ እንዳመፁ ተረዳሁ፡፡ ለነገሩ መረዳቴን አደስኩት እንጂ እንደአዲስ አልሆነብኝም፡፡ ምክንያቱም ከመነሻቸው ጀምሮ ፍጡራኑን ሲያጭዱና ሲረመርሙ አሁን ድረስ በመዝለቃቸው ከእግዚአብሔር መንገድ ማፈንገጣቸውን እኔ ብቻ ሳልሆን ማንም የሚገነዘበው ነው፡፡ ዘመናችን እንዳለ የቅሌት ዘመን ሆነ አይደል እንዴ! የመነኩሴ ዘፋኝ?

Read More »

ወቅታዊው የሀገራችን ፖለቲካና የአርበኛ ታጋዩ ትዝብት (ዕዝራ አስቻለው ዘለቀ ከኤርትራ – ክፍል ሁለት)

ECADF Amharic News and Views social media graphic image

በኦሮሞውም ላይ ሆነ በሌላው ወገናችን ላይ በአማራ ስም ለደረሱ በደሎች በይፋ ይቅርታ የሚጠይቅና የሞራል ካሳን ከፍሎ ሰላምና እርቅ የሚያወርድ ሕዝብ የመረጠው መንግስታዊ ኣካል በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ይህንን ሃላፊነት ስለምን እኛው በኛው ስለኛው አናደርገውም? ብሄራዊ ዕርቅና መግባባትስ ላይ ለመድረስ ምን አዳገተን? ሌላስ ከኛ የቀረበና ሊያስታርቀን የሚችል ምን ሃይል ይኖራል ስል ጠየቅኩ።

Read More »

ከእርጅናና ከሞት ማን ያመልጣል? (ነፃነት ዘለቀ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

በዚያን ሰሞን በአዲስ አበባ ከተማ የጦፈ የመንገድ ላይ ፍተሻ ነበረ አሉ፤ ይህ ነገር አልፎ አልፎ እንደሚከሰት አውቃለሁ፡፡ ወያኔዎች በተሸበሩና በደነበሩ ቁጥር በየመንዱና በየሰፈሩ ሰውንና መኪናን እያስቆሙ ይፈትሻሉ - ከዱሮም፡፡

Read More »

ወትሮም ያለ ነው ከጥንት – ሎሌ መጮሁ ከጌታው ፊት (ይገረም አለሙ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

በተለይ የድርጅት አባላት (የፖለቲካም የሌላውም) አባል እንጂ ተከታይ አትሁኑ፡፡ ድርጅታችሁ ቆሜለታለሁ የሚለውን ዓላማ አጢኑ እንጂ የመሪዎች ምርኮኛ አትሁኑ፡፡ ጣታችሁን ወደ ሌላ ከመቀሰራችሁ በፊት ራሳችሁን እዩ፣ ድርጅታችሁን መርምሩ፣ መሪዎቻችሁን እወቁ፡፡ ከአንድ ወገን ብቻ ሰምታችሁ አይታችሁ ወይንም አንብባችሁ ለጩኸት አትቸኩሉ፣ አንገት የተሰራው አዙሮ ለማየት ነው ይባላልና ዙሪያችሁን ቃኙ፣ ተቃራኒ አስተሳሰቦችን መዝኑ፣ እውነትን ፈልጉ እንጂማ እንደገደል ማሚቶ ወይ እንደ ድምጽ መቅጃ መሳሪያ የተነገራችሁን ብቻ የምትደግሙ አትሁኑ፡፡ ሙግት ክርክራችሁ ለመሸናነፍ ሳይሆን ለጋራ አሸናፊነት ይሁን፣ በመረጃ ማስረዳትን በማስረጃ መሞገትን ባህል አድርጉት፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን ከሎሌነት ተላቆ በራስ በመቆም ህሊናን ማሰራት ሲቻል ነው፡፡

Read More »

አሣ ጎርጓሪ ዘንዶ አወጣ (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

Ethiopian orthodox church cross

የዚህች ጦማር ዋና ዓላማ፡ “ያዲስ አበባው ሲኖዶስ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ከቀሩት አኀት አብያተ ክርስቲያናት ተነጥላ ከሀያ በላይ ስህተት ሰርታለችና ትመርመር የሚል ክስና ወቀሳ አቀረበ” ብሎ ሀራ ዘተዋህዶ ባቀረበው ዜና፤ ግራ የተጋባችሁ ክርስቲያኖች፤ “በአኀት አብያተ ክርስቲያናት ሐዋርያዊ ትውፊት አንጻር እንዴት ትመለከተዋለህ“ ብላችሁ ላቀረባችሁልኝ ጥያቄ ለመመለስ ነው።

Read More »

ድውያን አክሊሉን በደፉ ግዜ (መስቀሉ አየለ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

ይህን ቪዲዮ ተርጉመው የላኩልኝ የወልቃይት ወንድሞቸ ናቸው። ወያኔ ለክፋት የጫነባቸውን የትግርኛ ቁዋንቁዋ እነሱ ለበጎ እያዋሉት ነው።ቢያንስ እንዲህ ያለውን ነውር እያወጡ ያሳዩናል። ቋንቋ መግባቢያ እንጅ ዘር እንዳልሆነ ወልቃይቴዎቹ እያሳዩት ነው። ትርጉሙ ሲጠቃለል እንዲህ የሚል ይዘት አለው አሉ። በትግርኛ " እዛ ምርኩሰይ ጠመንጃ ተትኸውን ነዚ ግፍዐኛ አምሓራይ ምቀተልኩላ አነውን" ይሄ በቀጥታ ሲተረጎም ይሄ የያዝኩት ምርኩዝ ጠበንጃ ቢሆን ኖሮ ግፈኛውን አማራ በገደልኩበት ነበረ የሚል ትርጉም ይሰጠናል።ስላጠለቁት ኮፍያም ልክ እንደዛው እየዘፈኑ ነው ሲጀምሩ በኮፍያቸው ነው የሚጀምሩት። "ኮፍያዬ ቦንብ ቢሆን ኖሮ አማራን በገደልኩበት ነበር። ምርኩዜ ጠመንጃ ቢሆን ኖሮ አማራ በገደልኩበት ነበር። ረሽነው እምበር ተጋዳላይ "

Read More »

የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል (መስቀሉ አየለ)

Time to think

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ግምቱ ከአምስት ሚሊዮን ብር የሆነ የዐማራ ተወላጆች ንብረት ከሰኔ ፬ እስከ ሰኔ ፮ ቀን ፪፻፱ ዓ።ም በቀቤና ብሔረሰብ አባላት መውደሙን ከቦታው ዛሬ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል ዕ የሚል ዜና እራሳቸውን የአማራ አክቲቪስት ነን በሚሉ ሰውች ተለቆ በመራገብ ላይ ነው። እንደ ዜናው አገላለጥ ሰውየው ይህ ሁሉ የደርስበት አማራ ስለሆነ ብቻ ነው የሚል ሲሆን አቀራረቡም የአማራዎችን ትኩረት በመሳብ ወደ ሌላ ዙር አቅጣጫ የመሳብ ሂደት ነው። እውነቱ ግን ይኽ አይደለም።

Read More »

ህወሃት በሜካናይዝድና (ብረት ለበስ በከባድ መስራያ የታገዘ) ጦርነት ተጋርጦብኛል ይላል

Patriotic Ginbot7 attacked TPLF troops

በሰሜን ግንባር ሁለት የጦር ቀጠናዎች ቀይ መስመሩን ማለፋቸዉ እየተነገረ ነዉ። ሦስት የህወሃት ክ/ጦሮች በመረባረብ ላይ ናቸዉ።

Read More »

ዕንቆቅልህ ምን ዐውቅልህ! (ነፃነት ዘለቀ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

“ወዴት እያመራን ነው?” ወይም “ወዴት እየሄድን ነው?” የሚለውን መልስ-አልባ ጥያቄ ራሳችንን እንደጠየቅን ይሄውና በትንሹ ዐርባ ዓመታትን ያህል አሳለፍን፡፡ እኔ ራሴ ለአቅመ ጥያቄ ከደረስኩ ጅምሬ ይህንኑ ጥያቄ ከመጠየቅ ቦዝኜ አላውቅም፡፡ በርግጥም “ወዴት እየሄድን ነው?”

Read More »

ጊዜው የሕዝባዊ አሻጥር ነው!!! (አርበኞች ግንቦት 7)

Patriotic Ginbot 7

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ “ሴፍ ሀውስ” እያሉ የሚያቆላምጧቸው ከ50 በላይ ድብቅ የማሰቃያ ቦታዎች አሉ። ከፊሎቹ የምድር ውስጥ ዋሻዎች አሏቸው። ብዙዎቹ መሀል ከተማ ውስጥ ሲገኙ ጥቂቶቹ በከተማው ዳርቻዎች ይገኛሉ። በማዕከላዊና በሌሎች እስር ቤቶች ውስጥም የማሰቃያ ቦታዎች ያሉ ቢሆንም ወገኖቻችን ከፍተኛ ፍዳ እንዲደርስባቸው የሚደረገው በእነዚህ ከእይታ በተሰወሩ የማሰቃያ ቦታዎች ነው። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማ በናዚ ፋሽስቶች ይፈፀሙ ከነበሩ ሰቆቃዎችን የባሱ አስነዋሪና ኢሰብዓዊ ግፎች በእነዚህ የማሰቃያ ቦታዎች ውስጥ ይፈፀማሉ።

Read More »

ሞረሽ – ዋናውን ነገር ገሸሽ (ይገረም አለሙ)

ECADF Amharic News and Views social media graphic image

ሞረሾች እውነቱም ድፍረቱም ካላቸው ሻ/ቃ ዳዊት በገለጹት ሀገራዊ ንቅናቄውን ለመመስረት በተደረገ ረዥም ጉዞ ውስጥ መጠየቃቸው እውነት ነው ወይስ አይደለም? ከተጠየቁ ምላሻቸው ምን ነበር? ሀገራዊ ንቅናቄውን የሚመጥን ቁመና ያጡበት ምክንያትስ የፖለቲካ ድርጅት ባለመሆናቸው ወይንስ ድርጅታዊ ጥንካሬ በማጣታቸው? ሂደቱ ረዥም ግዜ የፈጀ ነበርና የጎደለውን አሟልቶ ለመሳተፍ ምን የተደረገ ጥረት ነበር ለምንስ አልተሳካም? ምላሽ መስጠት አለባቸው፡፡

Read More »

ሱዳን ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በተባበሩት መንግስታት የሥደተኞች ጉዳይ መ/ቤት (UNHCR) የሚደርስባቸው ግፍ እና መድሎ የተሞላበትን የተወላገደ ስራ በሚመለከት የተጻፈ

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

የዚህ የብሦትና የምሬት ፁሁፍ መነሻ መጋቢት 3/2017 በሱዳን ካርቱም የ UNHCR ቅርጫፍ መ/ቤት ፕሮቴክሽን ኦፊሠር የሆነው ሚስተር ሮን የተባለ በ2000 ዓ.ም ሥክሪኔንግ አድርገው የነበሩና ሥደተኝነታቸው የተረጋገጠላቸው ሥደተኞችን በመ/ቤቱ ሥብሠባ ጠርቶ ባነጋገረበት ወቅት ኢትዮጵያዊ ሥደተኞችን አስመልክቶ የተናገራቸውን ጉዳዮች መነሻ በማድረግ ነው።

Read More »

አስቸኳይ ማሳሰቢያ ለአማራ ምሁራንና ለአማራው በዲያስፖራ (በእውቀቱ ዘኢትዮጵያ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

በማንኛውም ማህረሰብ ውስጥ በፅንፈኝነት፣ በስሜትና በፖፕሊዝም የሚሸነፍ ምሁር ይኖራል። አሳዛኙ ጉዳይ ግን ይህንን በፅንፈኝነት፤በስሜትና በፖፕሊዝም የሚመራና የሚረጭ አስተሳሰብን በድፍረትና በጥንካሬ ሊቃወሙ የሚችሉ ምሁራን ከአማራው ማህበረሰብ ውስጥ በርክተው መውጣት አለመቻላቸው ነው።

Read More »

የዕውቁ ኢትዮጵያዊ አርበኛ፣ ዲፕሎማትና ደራሲ የክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ መኪና በቅርስነት መጠበቅ ሲገባት የስጥ ማስጫ የሆነችው በምን ምክንያት ይሆን?!

ለታሪኩ ለሥልጣኔው፣ ለባህሉ፣ ለቅርሱ ባዕድና እንግዳ የሆነ ትውልድ ከራሱ ከማንነቱ እየሸሸና እየተንሸራተተ የራሱን ንቆ የሌላውን ናፋቂ የመሆኑ ጉዳይ ብዙ የተባለበት፤ የተጻፈበት ነው። ባለፈው ሳምንት የሸገር ሬዲዮ ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ወንድሙ ኃይሉ በልዩ ወሬው ዝግጅቱ ዕረቡ ማለዳ ላይ አንድ አሳዛኝና አሳፋሪ የሆነ ዜና አሰምቶን ነበር።

Read More »

የፍጹም ሰላም የከፍታ ነጥብ (The Quantum understanding of peace) የት ላይ ነው ?… (በጽሞና ውስጥ ካሰላሰልኩት)

Peace of Mind

ባጠቃላይ ምኞት ሲሸነፍ ፍላጎት ምሉዕ ሆኗል ማለት ሲሆን የፍጹም ሰላም መገኛዋ ነጥብም እርሷ ናት። አዳም ሰላሙን አስረክቦ ስደት የወጣው ከዚህ አይነት አለም ነው።

Read More »

የሰኔ አንድ ሰማዕታት አደራ በትግላችን እውን ይሆናል! (አርበኞች ግንቦት7)

Patriotic Ginbot 7

የሰኔ 1 ሰማዕታትን አደራ ጠብቀው የተጓዙ በርካታ ወጣቶች የህይወት መስዋትነት ከፍለዋል፣ እየከፈሉም ይገኛሉ። ከሰኔ 1 ቀን 1997 ዓም ወዲህ በማላ አገሪቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ለነጻነታቸው የህይወት መስዋትነት ከፍለዋል። በአወዳይ፣ አምቦ፣ ሃሮማያ፣ አርሲ፣ ጎንደር፣ ጎጃም እና በሌሎች በርካታ የአገሪቱ ክፍሎች በተካሄዱ የነጻነት ትግሎች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ2 ሺ ያላነሱ ሰዎች በአረመኔው አገዛዝ በግፍ ተገድለዋል።

Read More »

ዘረኝነት የጀኖሳይድ እርሾ ነው! (ታሪኩ አባዳማ)

Stop Genocide in Ethiopia

እንደ ሩዋንዳ አይነት ፍጅት ለመጠንሰስም ሆነ ለመፈፀም ተፈጥሮው የሚፈቅድለት ብሎም አቅሙ ያለው ጡንቻው የደነደነው ፣ ልቡ ያበጠበት ህወሀት ብቻ ነው። እናም በሁሉም አቅጣጫ ዝግጁ ሆኖ ጭፍጨፋውን ላለፉት 26 ዓመታት እና አሁንም በቀጣይነት ለማቀላጠፍ በተጠንቀቅ ተሰልፏል።

Read More »

ወርቃማው የጵጵስና ዘመን እንዲህ ነበር! (መስቀሉ አየለ)

Archbishop history in Ethiopian Orthodox Church

በግብጽ ይኖር ስለነበረ እልመፍርያኖስ ስለሚባል ደገኛ አባት ስንክሳሩ ላይ ከሰፈረው በድንግዝግዝ እንደማስታውሰው እንዲህ ይላል። እርሱ ከጥንት የግብጽ ገዳማት በአንዱ በኖረበት ዘመን ሊቀ ጳጳሱ እድሜው ይገፋና እረፍተ ስጋው ይሆናል። እርሱን ሲረዳው የነበረው አቃቤ መንበሩ ደግሞ በግዜው አልነበረም። እንደምን የለም ቢሉ መንገድ ሄዶ ነው ይላል፤ ጳጳሳት ከየአገሩ ተሰብስበው ቀብሩከተፈጸመ በኋላ አቃቤ መንበሩን ሾመው ሊሄዱ ቢጠብቁት ሊመጣ አልቻለም። በዚህ መሃል ቀኑ ገፋባቸው። መንበር እንበለ ጳጳስ አለ አርባ ቀን አይቆይምና እልመፍሪያኖስን ሹመውና በእስክንድሪያ መንበር ላይ አስቀምጠውት ሄደዋል።

Read More »

ሰውም እንደ ጊንጧ (ይገረም አለሙ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

ከሚናገሩት ከሚጽፉት (ከዚህ የዘለለ ተግባር የላቸውም) ድርጊታቸው ማረጋገጥ እንደሚቻለው እነዚህ የጊንጥ ባህርይ የተላበሱ ወገኖች ከወያኔ ተስማምቶ አለያም ጎመን በጤና ብሎ የሚኖረውንም ሆነ እኔ ከደላኝ ምን አገባኝ አለም ደህና ሰንብች ብሎ የተኛውን ወይንም በአፉ ከማውገዝ በመግለጫ ከመፎከር ያለፈ እንቅስቃሴ የማያሳየውን መንደፍ አይደለም እስከ መኖሩም አያውቁትም፡፡ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪው ዓለም በጎሳም ሆነ በሀራዊ ስም የሚጠሩ ብዙ ድርጅቶች አሉ፣የራዲዮና የቴሌቭዥን ጣቢያዎችም እንዲሁ፣ ተዲያ ጊንጦቹ መንከስ መንደፉ ባይሆንላቸውም የቃላት አረራቸውን የሚተኩሱት የሀሜት አሉባልታ ናዳቸውን የሚለቁት በእነማን ላይ አንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ግን ለምን?

Read More »

ሰበር ዜና – በሰሜን ጎንደር ዋግ ሃምራ ወያኔ ጥቃት ደረሰበት

TPLF security members killed in Gondar

የህወሃት ወታደራዊ ደህንነቶች ባቀረቡት መረጃ መሰረት በምእራብ አቅጣጫ በሰሜን ጎንደር ዋግ ሃምራ፣ እንዲሁም ደባርቅ፣ ዳባትና፣ እንፍራዝ አካባቢዎች ላይ ወታደራዊ አሰሳና ጥቅት ለማድረግ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ኦፐሬሽኑ ትናንት ሙሉ ለሙሉ ተሰርዟል!

Read More »
Click here to connect!