ጅብ በማያውቁት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፍሉኝ አለ (ገብረመድህን አርአያ)

Ato Gebremedhin Araya former TPLF leadership member

ግደይ ዘርአፅዮን ከኢቲዮ ሚዲያ ጋር ባካሄደው ቃለ ምልልስና በጽሁፍም የተዘረጋው ባጣም አንዶታል፣ ክንክኖታልም። በዚህም ምክንያት ይመስላል ብዙ ስድቦችን አውርዶብኛል። ግደይ የተናደደበት ዋናው ምክንያት፣ ምስጢራችንን በዝርዝር አውጥቶ አጋለጠን ብሎ ነው። ይህም ይመስላል ወደ ተራ ስድብና ውሸት የከተተው። የትግራይን ሕዝብ አጸያፊ ስድብ ተሳደበ ብሎም ወንጅሎኛል። እኔ ማን ሆኜ ነው የትግራይን ወላጆችና ወንድሞቼን የምሰድበው? ሃቅ ነው ካለስ፣ የተሳደብኩትን ስድብስ ለምን አልተናገረም? ግደይና ግብረአበሮቹ የህወሓት አመራር የትግራይ ሕዝብ ፊውዳል፣ ሸዋዊ አማራ ትግሬ፣ ፀረ-ህወሓት ወዘተ እያላችሁ የገደላችሁት አንተና ጓደኞችህ አልነበራችሁም ?እኔ የነበሩትን፣ 06 ሓለዋ ወያነ፣ በነሱ ውስጥም ስንት የሰው ፍጡር፣ አማራና ትግሬ - አማራው በዝቶ የተገደለበት - ቦታዎች መሆናቸውን ነው በትክክል የገለጽኩት። ቅንጣት ውሸት አልጨመርኩበትም። ግደይ ከፈጸመው ውንጀል ነፃ የሚወጣ መስሎታል። እውነት በውሸትና በማስመሰል አትጣጠፍም።

Read More »

አንዳንዴ ሸረሪትም በራሷ ድር ትያዛለች (ከይገርማል)

Amharic News and Views in Amharic

እውነታው ግን እኒህ የወያኔ እብዶች ከስህተታቸው ተምረው ሕዝብን ከሕዝብ የሚያቀራርብ ስራ እየሰሩ አለመሆኑ ነው:: ለችግሮች ትክክለኛ መፍትሄ ክመፈለግ ይልቅ ችግሩን ለማባባስ በእሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍ መርጠው የትግራይ ሰዎችን በሙሉ አስታጥቀው ለጦርነት አዘጋጅተዋል:: ትግሬ የተባለን ሁሉ መሳሪያ ማስታጠቅና በወታደር ማስጠበቅ በምንም መለኪያ መፍትሄ ሊሆን አይችልም:: ለተቃውሞ የሚወጡትን ሰዎች በማሰርና በመግደል በግፍ ላይ ግፍ ይከምሩ ካልሆነ በስተቀር መፍትሄ ማምጣት አይቻልም:: እየተፈጠረ ያለውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የጥፋት ሀይሎች ሴራ አድርጎ ማውራትና ችግሩን ወደሌላ መግፋት ወይም በሀይል ለመፍታት መሞከር ዘላቂ ሰላም አያመጣም::

Read More »

ለ25 ዓመታት የዘለቀው የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የማይናወጥ አቋም

Reese Adbarat London Debre Tsion Ethiopian Orthodox Church

በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ለተፈጠረው መለያየትና መከፋፈል ምክንያት የሆነው ሃይማኖታዊ ሳይሆን ይህን መሰሉ አገዛዙ የሚከተለው እንደ ቅኝ ገዢ አንድ ጎሳ ብቻ የሁሉም የበላይ ሆኖ ሌላውን ሁሉ ቅኝ ተገዢና የበታች ተደርጎ ይገዛ የሚለው የእብሪት ተግባር ነው።

Read More »

የትግራዩ ወያኔ የመጨረሻው የመጥፊያው ስራ (ዶ/ር ደጀኔ አለማየሁ ላቀው)

Amharic News and Views in Amharic

ይቅር ማለትና የተጠየቁትን የመብት፤ የህልዉናና የመሬት ጥያቄወች ለመመለስና ባስቸኳይም ከስልጣን ላይ ለመዉረድ ቃል መግባት ያለብት የትግራይ ወያኔ እንጂ ተገዳዩ አማራው አይደለም።

Read More »

አዋርደን አውርደን ተራርደን ተዋረድን (ዳኛቸው ቢያድግልኝ)

Amharic News and Views in Amharic

ከአንዳንድ ወጣቶች የሚደመጠው አባቶቻችን ያፈረሱትን አያቶቻችንን ያቆዩልን አገር መልሰን እንገነባለን የሚለው ቁጭታቸውን ሰምቶ እንዳልሰማ መሆን አይቻልም። አዎን ከተማሪ ረብሻ እስከ ደደቢት ወጠምሻ ድረስ ያለነው ፖለቲካ ገብቶናል መንገዳችንን እናውቃለን ብለን ዘራፍ ያልን የትውልድ ክፋዮች ታሪኳን አፋልሰናል፣ ድንበሯን አስደፍረናል አገሪቱን የደም መሬት አድርገናል። አዎን ይህንን የህዝብ ጥያቄ ተንተርስው ወጣቱ መሀል ተርመስምሰው አገር በግራመጋባት ሲተራመስ የግንጠላ ስራቸውን ለመስራት ካደቡብንና በምንም ላይ ተረማምደው ስልጣን ለመቀራመት ከባዘኑት በቀር ሌላው አገሬን ሕዝቤን ብሎ የጮኸ ለነብሱ ያልሳሳ ለጥቅሙ ያላደረ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ነው። ይህንን ከመካድ መነሳት መልሶ ማፍረስ ነው። ይህ ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለበት ሩጫ ወዴት አደረሰን? ስንል ነው የእድሜ ሙሉ ጉዞአችንን ከንቱነት የምንመለከተው። የዚሁ ተውልድ ከፋዮች የፈጠርናቸው መንግስታት በዘመነ ፊውዳል እንኳ ታይቶ የማይታወቅ ፍዳን ለሕዝባችን ያከናነቡ ናቸው። በፖለቲካ መገለባበጥ ሳቢያ የቀያየርናቸው ጃኬቶች አሳፋሪ እንጂ አኩሪ አይደሉም። ከላብ አደር አምባገነን ወደ ጎጠኛ አምባገነንት ያለሃፍረት የሄድነው የዚሁ ትውልድ ክፋዮች ነን። በዚህም አልን በዚያ አምባገነንነት ነግሶ ከሀገር ከመንደራችን ነቅሎ ሜዳ የበተነን እስርቤት ያጎረን ይኸው ግራ መጋባት ያሳደገው ትውልድ ነው።

Read More »

“የመለስ ልቃቂት” ሆድ እቃ ሲገለጥ”

Yemeles Likakit book cover

የአገሪቱን ሀብት የተቆጣጠሩት የህዉሃት የብርቅ ልጆች በአንድ በኩል በሃብት ጋራ ላይ ሰማየ ሰማያት እየረገጡ የሚሄዱበት፤ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የሃዘን ቤትነቷ የሚቀጥል ይሆናል። ይህ እንደ አሳ ከጭንቅላቱ የገማ ስርአት ያለምንም ከልካይ የአገሪቷን አንጡራ ሃብት የሚቆጣጠርበት ሁኔታ ይፈጠራል። ፀሃፊው በመጽሐፉ እንደገለጸው ሁኔታዎች በፍጥነት ካልተቀየሩ ነገ ከነገወዲያ “የኢትዮጵያ አየር መንገድ”፣ “የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ”፣ “የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን” የሚባሉ ተቋማት በባለቤትነትና በስም ተቀይረው የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። ዛሬ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰጠው ብድር 40% ያህሉን ወያኔ ኤፈርትን ለመሰሉ ዘራፊ ኩባንያዎች እንዲሰጥ ካስገደደ፤ ከአመታት በኋላ እንደ አንፀባራቂው የመቶ ፐርሰንት ምርጫ ውጤት የብድር መጠኑም ተመሳሳይ ይሆናል።

Read More »

የዕብዶች የእልቂት ነጋሪት ጕሰማ የነፃነት ትግሉን አንዲት ጋት ወደ ኋላ አያስቀረውም

Amharic News and Views in Amharic

ኢትዮጵያ በድቡሽት ላይ የተመሠረተች አገር አይደለችም፡፡ ሕዝቧም በዘመናት የአብሮ መኖር መስተጋብር በመዋለድ፣ በባህል መወራረስ፣ በእምነት፣ በታሪክ፣ በክፉም በደጉም ጊዜ በመተሳሰብ በሦስትዮሽ የተገመደ ጥብቅ ዝምድና/ትስስር ያለው ባለረጅም ታሪክና ነፃ ሕዝብ ነው፡፡

Read More »

የህወሃት መከላከያ ሰራዊት እጁን እየሰጠ ወደ ኤርትራ እየገባ ይገኛል

Ethiopian Soldiers

ከምእራብ ትግራይ ወደ ኡምሃጅር የተወረወረ የህወሃት መከላከያ ሰራዊት የግንባር ጦር በገጠመዉ ድንገተኛ የተኩስ ልዉዉጥ ምክንያት እጁን እየሰጠ ወደ ኤርትራ እየገባ ይገኛል።

Read More »

አቶ ገዱ ለምን አለቀሱ? ሀገር በደምና በአጥንት እንጅ በእምባ አልተገነባችም (ከይገርማል)

gedu andargachew

ከይገርማል የሰው ልጅ እንባ በተለያየ ምክንያት ሊፈስ ይችላል:: የአይን ህመም ያለባቸው ...

Read More »

የፓትርያርኩ ልዩ ጸኃፊ፣ ወይንስ የህውኃት ጉዳይ አስፈጻሚ (ይገረም አለሙ)

TPLF cadre in the Ethiopian Orthodox Church Aba Sereke Berhan

አማርኛ ከእንግሊዘኛ እየደባለቁ የሚናገሩት አባ ሰረቀ ብርሀን አንደበታቸው ፈጽሞ የሀይማኖት አባት አይመስልም፡፡ከጠቅላይ ምኒስትሩ ጀምሮ የተለያዩ ባለሥልጣኖች ጥፋቱ የእኛ የእኛ ነው በማለት ለማታላያም ቢሆን አምነው ለዚህም ጥልቅ ተሀድሶ ያስፈልገናል በማለት እየተውተረተሩ ባለበት በዚህ ወቅት እኝህ የጳጳሳችን ልዩ ጸሀፊ ግን ከጳጳሱ ቄሱ አንዲሉ ሆነው “ለጠፋው ህይወት መንግስትን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ አይቻልም” በማለት በተከላካይነት ቆሙ፡፡

Read More »

በዘ-ህወሀት የውሸት ምድር የማወንበጃ መረጃ ዘመቻ፡ ቀጣፊው በኢትዮጵያ ዉሸትን እዉነት ነው እያለ ሲሰብክ?

Debre Tsiyon and TPLF lie

በእኔ ዘመን ሳሙና የሆኑ አእምሮአቸው በዉሸት የተበከለ ቀጣፊዎችን አጋጥመዉኛል፡፡ እናም አንድ ቁልጭ ያለ እና በግልጽ የማስታውሰው ነገር ቢኖር እነዚህ አእምሮአቸው የታመመ ቀጣፊዎች እራሳቸዉን እንጂ ሌላ ሰው ስያታለሉ አላየሁም፡፡

Read More »

ታምራት ላይኔ–የፖለቲካ አማካሪ?

Amharic News and Views in Amharic

ኢትዮጵያዊያን አርበኞቻችንን/ጀግኖቻችንን እናወድሳለን? በበቂ ባናደርገውም እያደረግነው እንደሆነ ለምሳሌ የሜልቦርኑ ኢሳት እገዛ ማሰባሰቢያ ላይ ያየነውን፤ በዚያ ግሩም ሰዓሊ የተሰራው አይነት የኮሎኔል ደመቀ እና የአትሌት ፈይሳ ምስል ተሰብሳቢውን ብቻ ሳይሆን እኔንም ስሜቴን ወጥሮ የያዘ ነበር።

Read More »

ወያኔ ዘር ማጥፋት (genocide) ጀምሯል

Amharic News and Views in Amharic

በነሐሴ መጨረሻ ላይ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባደረገው ንግግር፣ ኢህአዴግ ስህተት መፈጸሙን ይጠቅስና፣ የእርምት እርምጃ ሊያቀርብ ነው ተብሎ ሲጠበቅ፣ ‘የፀጥታ ኃይሎች ህግ እንዲያስከብሩ’ ሙሉ ትእዛዝ ሰጥቻለሁ አለ።

Read More »

እንባችን ተሟጧል፣ በኢትዮጵያ እና በዓለም ዙሪያ በሩቁ ያላችሁና በፊታችሁ ቆሜ የምታዩኝ

Amharic News and Views in Amharic

ሁላችንም የምንስማማበትን በሙስሊሙ አባባል ዘቡር በሚባለው በዳዊት መጽሐፍ የተመዝግበውን በውስጥ ከሚሰቃየው ወገናችን ጋራ በመተባበር “ተካውኩ ከመ ማይ ወተዘርዎ ኩሎ አዕጽምትየ ወኮነ ልብየ ከመ ሰም ሰይትመሰው በማእከለ ከርስየ” (መዝሙር 22፡ ) ለማለት በዚህ ቦታ ተሰብሰበናል። ይህም “መላ ሰውነቴ ወደ ውሀነት ተለውጦ ተደፋ። አጥንቴም ደቅቆ ወደ አፈር ትቢያነት ተለውጦ ተበታተነ። ልቤም እንደሰም ቀልጣ በአንጀቴ ፈሰሰች” ማለት ነው።

Read More »

በቫንኮቨር ካናዳ ኢትዮጵያ ውስጥ በሕወሃት አገዛዝ ላይ ተቃውሞ በማሰማታቸው ለተጠቁ ዜጎች የገንዘብ ማሰባሰብ ተደረገ

Fundraising for victims of protests in Ethiopia held in Vancouver

ኢትዮጵያውያን በቫንኮቨር ካናዳ ቅዳሜ ሴፕቴምበር 24 2016 በኤድሞንድስ ኮሚኒቲ ሴንተር በመሰባሰብ በሀገር ቤት በሕወሃት አገዛዝ ላይ ተቃውሞ በማሰማታቸው ለተገደሉ፣ ለቆሰሉና በየእስርቤቱ ለታጎሩ እንዲሁም ለተጎጂ ቤተሰቦች እርዳታ የሚውል ገንዘብ ሲያሰባስቡ ውለዋል።

Read More »

Protected:

Ethiopians protest in Vancouver, Canada

There is no excerpt because this is a protected post.

Read More »

ለቀነኒሳ በቀለ – እልህና ቅናት ለበጎ ሲሆን ያሳድጋል (ደረጀ ሃብተወልድ)

Kenenisa Bekele and Feyisa Lilesa

ካሳምንት በፊት ደግሞ ፈይሳ ሌሊሳ ፦” እነ ኃይሌና ቀነኒሳ ህዝብ እየተገደለ ባለበት ሰዓት ስለውጤት መጥፋት ከሚብሰከሰኩ እየሞተ ላለው ሕዝብ ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ አቀርብላቸዋለሁ።” ብሎ ነበር። ለዚህ የፈይሳ ጥሪ እነሆ የቀነኒሳን ምላሽ አዬነው።

Read More »

የዲምክራሲለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ እና የኢትዮጵያ የጋራ መድረክ የተሰጠ የአቋም መግለጫ !!

Norway protest against the Ethiopian regime

በአገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት የትግል ወቅት በንጹሃን ዜጎች ላይ በአረመኔው የወያኔ አግዓዚ ጦርና ልዩ ኃይል የተወሰደውንና እየተወሰደ ያለውን እጅግ ዘግናኝ አረመኔያዊ ግድያዎችን አምርረን እናወግዛለን፤ ገዳዮችንም በህግ እንፋረዳቸዋለን፤ ሰማዕታትንም በታሪክ ለዘላለም እንዘክራቸዋለን!

Read More »

የሆላንዱ ወርክሾፕ – ኢትዮጵያ እና መጭው የርስበርስ ጦርነት (ክንፉ አሰፋ)

Ethiopian current affairs discussion in Holland

ተናጋሪዎቹ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ከፍተኛ ቀውስ በማስረጃ እያጣቀሱ ካብራሩ በኋላ የገዥው ፓርቲ አጠያያቂ ህጋዊነት እና የማክተሙ አዝማምያን ያመላከተ ድምዳሜ ሰጥተዋል።

Read More »

ለአገር ሰላም መፍትሔው… (ከደጉ ዘመን – አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ)

Amharic News and Views in Amharic

ስለዚህ በግልፅ እንደሚታየው በወያኔ መንግሥት እና በሕዝቡ መካከል መጠነ ሰፊ ክፍተት ታይቶአል፡፡ ኢትዮጵያም በአደጋ ላይ ትገኛለች፡፡ ሕዝቡ ጥያቄ አንግቦ ሆ! ብሎ ተነሥቶአል፡፡ የሕዝቡን ጥያቄ የወያኔ መንግሥት መመለስ አልቻለም፤ ወይም ደግሞ ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡

Read More »
Click here to connect!