የሚንስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የኦሮምያ ልዩ ጥቅም ረቂቅ አዋጅ ላይ የEDF አቋም መግለጫ

Ethiopian Dialogue Forum logo

የሚንስትሮች ምክር ቤትን ያሳሰበው ጉዳይ በከተሞች መስፋፋት ጊዜ የሚመጣውን ችግር በተመለከ ቢሆን በመላ ሃገሪቱ ወጥነት ባለው ሁኔታ በከተሞች አካባቢ የሚኖሩ ገበሬዎችን ህይወት በሚመለከት አንድ ወጥ አሰራር ሊፈጥር ይችል ነበር። ነገር ግን መንግስትን ያሳሰበው ጉዳይ ይህ ባለመሆኑ በብሄሮች መካከል ያለውን ልዩነት ለማጉላት ሲጥር ይታያል። ወጥነት ያለው ኢትዮጵያውያንን በብሄር በሃይማኖት ሳይነጥል የሚንከባከብ ህግ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ሞገስ ያገኛል።

Read More »

ከባዶ ጣሳ ወደ ተቀደደ ጣሳ – አዲስ አበባ ወደ ፊንፊኔ! (ታሪኩ አባዳማ)

Ethiopia, Addis Ababa

ወያኔ የአዲስ አበባን ስም ለመቀየር ብሎ ባወጣው አዋጅ ሰበብ የተነሳው አተካሮ ሌላው አሳዛኝ ትርኢት ነው። ትርኢቱን በብዙሀን መገናኛ መድረክ ላይ የሚያራግቡት አብዛኞቹ ያው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ግብረ ሀይል ካድሬዎች ቢሆኑም በዚህ ከፋፋይ መረብ ውስጥ ጥልቅ ብለው አቧራ የሚያስነሱ ቅን ዜጎችም እንዳሉ ማስተዋል ይቻላል።

Read More »

የአዲስ አበባ ከተማን ህዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት የሚጥስ አዋጅ አጥብቀን እንቃወማለን! (የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ)

Semayawi party to welcome Andinet members

ይህ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተረቀቀ የተባለው አዋጅ በጥድፊያ የወጣ፣ ግልፅነት የጎደለው፣ ህገ መንግስቱን የጣሰ፣በመረጃና በጥናት ላይ ያልተመረኮዘ፣ አጠቃላይ የዴሞክሰራሲ መርሆና ከህገ መንግስቱ አንቀፅ 49 አላማ ጋር በእጅጉ የተቃረነና ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት አገዛዙ የተነሳበትን የፖለቲካ ትኩሳት ለማብረድ በማሰብ የተቀነባበረ ግልብ ሴራ ነው፡፡

Read More »

የኦሮሞ ህዝብ እኩልነት እንጂ ልዩ ጥቅም ፈላጊ አይደለም (ገለታው ዘለቀ)

Bishoftu, Irreecha massacre

የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮችም ሆኑ ዜጎች በጋራ ከመሰረቱት ሃገር ልዩ ጥቅም ፈላጊዎች አይደሉም። ኢትዮጵያውያን በመሬት ዙሪያ በኢኮኖሚ ዙሪያ ለየቡድናቸው ልዩ ጥቅም (special interest)  ይዘው በአንድ የፓለቲካ ጠገግ ዘንድ ለማረፍ አይስማሙም። አልተስማሙም። ኢትዮጵያውያን ለእንደዚህ ዓይነት ራስ ወዳድ ስምምነት ሃይማኖታዊም ባህላዊም መሰረት የላቸውም።

Read More »

ሌ/ጄነራል ጻድቃን፣ ህወሃት፣ ኤርትራ እና ቀይ ባህር (በነጻነት ቡልቶ – ክፍል ሁለት)

Tsadkan Gebretensay and Eritrea

ጄነራል ጻድቃን “ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ሀይል መሆን አለባት” የሚል አስገራሚ ሃሳብ አንስተዋል። “ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ሀይል መሆን አለባት” የሚለው ማደናገሪያ  ሃሳብ ሕወሃቶች ያዳከሙትን የኢትዮጵያን ብሄረተኝነት ስሜት ለማነሳሳት ይጠቅመናል በሚል ስሌት በእነ ጄ/ል ጻድቃን በኩል ነገሮችን ለማጥናት እየሞከሩ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል።

Read More »

የሕወሓት የስንብት ዐዋጅ (ምሕረት ዘገዬ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

ለማንኛውም ወያኔ ገና ብዙ ይዘባርቃልና በጥንቃቄ መከታተል ተገቢ ነው፡፡ እነሱ ፈንጂ ባጠመዱ ቁጥር፣ እነሱ ወጥመድ በዘረጉ ቁጥር፣ እነሱ ጉድጓድ በቆፈሩልን ቁጥር እየዘለልን የምንገባ ከሆነ ስህተቱ የኛ እንጂ የነሱ አይደለምና በሚያልፍ መጥፎ ዘመን የማያልፍ ጠባሳ በታሪክ ስንክሳር ላይ ላለመተው ብዙ ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን እኛ ብዙኃኑ ነን፡፡ እመለስበታለሁ፡፡

Read More »

“በአፋን ኦሮሞ” አማካኝቶ ማስተር ፕላኑን በጓሮ በር! (ከኤርሚያስ ለገሰ)

Ermias Legesse, author and ESAT TV and Radio contributor

እናም ዛሬ "የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም" በሚለው አባይ ፀሐዬና በረከት ስምኦን የፃፈው አዋጅ ላይ "አስተዳደሩ በአፋን ኦሮሞ ልጆቻቸውን ማስተማር ለሚፈልጉ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ማደራጀት አለበት" የሚል ተፅፎ ስመለከት የተሰማኝ ከላይ የተገለጠው ነው። እነ አባይ በዚህ አዋጅ አማኸኝተው ማስተር ፕላኑን በጓሮ በር ማስገባታቸው እንዳይታወቅ "የዶሮን ሲያታልሏት" ማታለያ ይዘው ብቅ ማለታቸው እርስ በራስ ለማጋጨት ነው። ሌሎች የህጉ እሳቤዎች መሰረታዊ ምንጫቸው ይሄ እና ይሄ ብቻ ነው::

Read More »

ግልፅ ደብዳቤ ለልሳነ ግፉዓን ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች – ጉዳዩ፡ “ልሳነ ግፉዓን ከዚህ ወዴት?”

Welkait Tsegede

ዛሬ ድርጅታችን ልሳነ ግፉዓን አንግቦ የተነሳቸውንና የወልቃይት የጠገዴና የጠለምት ህዝብ ሰቆቃና የድረሱለኝ ጥሪ ልሳን መሆን፣ በግፍ ለተነጠቃቸው ሰብአዊ መብቶቹ መከበር ግንባር ቀደም ተሟጋች የመሆን፣ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ አጀንዳዎችና አላማዎቹን በሚያኮራና ታሪካዊ በሆነ ደረጃ አተሳክቷል ብዬ አምናለሁ። በዚህ አጋጣሚ ለመላው አባላቱ እና አመራሮቹ እንኳን ደስ ያላችሁ ማለትን እወዳለሁ።

Read More »

የማለዳ ወግ… ይድረስ ለሚመለከታችሁ ባለስልጣናት (ነቢዩ ሲራክ)

Ethiopian immigrants in Saudi Arabia

በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ችግር በጅዳና በሪያድ አየር መንገዶች እየተንገላታ ያለው ሰው ለቅሶ ዛሬም ደርሶኛል። በምህረት አዋጁ መራዘም ዙሪያ በሚናፈሰው መረጃ ለሚዋልለው ዜጋ እያደረጋችሁ ያለውን ጥረትና እውነቱን አስረዱት። "የምህረቱ ጊዜ አብቅቷል!" ተብሎ በሳውዲ ፖስፖርት ፖሊሶች እንዳይሳፈሩ መመለስ ስለመጀመሩ ጉዳይ ግልጽ መረጃ ከእናንተ ይጠበቃል።

Read More »

ሌ/ጄነራል ጻድቃን ፣ ህወሃት ፣ ኤርትራ እና ቀይ ባህር (በነጻነት ቡልቶ – ክፍል አንድ)

General Tsadkan Gebretensay

አርበኞች ግንቦት 7ም ሆነ ኦነግ እንዲሁም ሌሎች ጄ/ሉ ያልጠቀሷቸው ሃይሎች ህልውና መሰረት በሃገር ውስጥ ህወሃት የፈጠራቸው ሁኔታዎች፣ ጸረ ህዝብነቱና ጸረ ዴሞክራሲያዊነቱ፣ ራሱ ያወጣውን ህገ-መንግስታዊ መብቶች በተደጋጋሚ በመርገጥ ስላማዊ ህጋዊ ትግልን ለማድረግ ፈጽሞ በማይቻልበት ደረጃ የፖለቲካ ምህዳሩን በማጥፋቱ እንጂ እነዚህን የፓለቲካ ሃይሎች ሚረዱ ሁሉ፡  ኤርትራን ጨምሮ ስለፈለጉ ሊሆን አይችልም።

Read More »

አንዳርጋቸው ጽጌ የጽናታችን እና የቁርጠኝነታችን ዓርማ ነው! (አርበኞች ግንቦት 7)

Ato Andargachew Tsige, Ginbot 7

ህወአት አንዳርጋቸውን ባገተበት ወቅት የንቅናቄያችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ይሽመደመዳል የሚል ተስፋና እምነት ነበረው። ይህንን እምነቱን ጓዳችን አንዳርጋቸው ጽጌ በሚፈጸምበት ሰቆቃ ውስጥ ሆኖ እንዲያረጋግጥለትና ነጻነት ናፋቂ የሆነው ህዝባችን ተስፋ እንዲቆርጥ ብዙ ጥሯል፣ ደክሟል።

Read More »

ይድረስ ለትግል አባቴ አንዳርጋቸው ጽጌ (የአርበኛ  ታጋዩ ትውስታ)

Andargachew Tsige is Ethiopian

ያነጽከን!! የቀረጽከን!! ያንተ አርበኛ ታጋይ ልጆችህ አደራህን ዝንፍ ሳናደርግ ትግሉን አስቅጥለነዋል። እናም እልፍ ሁነናል!! በእያንዳዱ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ መግባት ችለናል። ጠላታችን ተንቀጥቅጧል!! ፈርቷል!! ርዷል!!! በዚህም እንኳን ደስ አለህ!

Read More »

ትልቁ የኢትዮጵያ ‘ፌደራል’ በጀት ድክመቱ፣ ገጽታዎቹና ውስብስብ ችግሮቹ

Ethiopia's ambitious, bold budget

የራሱ ውስጣዊ ችግሮቹ እንዳሉ ሆነው፡ ከሕዝባዊው አመጽ ወዲህ የመጀመሪያው የሆነው ይህ በጀት፡ በሕዝብ ቁጣ ወላፈን መለብለቡን በብዙ መልኩ ያሳያል። በተለይም ዛሬ ኤኮኖሚው ካጋጠመው የገንዘብ ችግሮች፣ የዕዳ ጫና፥ የምርቶች መቀነስና፣ የዋጋ ግሽበት አደጋ የኤኮኖሚው ማሽቆልቆ ከድህነት መስፋፋት ሁኔታ፣ ዜጎች በየጊዜው በሚታፈኑባትና ያለፍርድ በሚታሥሩባት እንዲሁም የሃገሪቱ ሰላም በአፈሙዝ ከሚጠበቅበት አንጻር ሲታይ — የበጀቱ አዘጋጆች በዚህ ትንተና ባይስማሙም — እነዚህ ከሃገሪቱ ፊት የተጋረጡ እውነታዎች ናቸው።

Read More »

የሜልበርን ኢትዮጵያዊ በጎንደር ህብረት በኩል ለነጻነቱ ለሚጋደለው ወገን ከ40ሺ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረገ

ye gondar hibret

የሜልበርን ኢትዮጵያዊ በጎንደር ህብረት በኩል ለነጻነቱ ለሚጋደለው ወገን ከ40ሺ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረገ (ከጎንደር ህብረት ዋና ጸሃፊ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ)

Read More »

መንግሥትነት ከቤት ይጀምራል (ምሕረት ዘገዬ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

ፈረንጆች “Charity begins at home.” ይላሉ፡፡ እንዲህ ሲሉ መልካምነት ወይም በጎነት ከቤት እንደሚጀምር ለመግለጽ ነው፡፡ እኔም ከዚህ አባባል ኮርጄ “መንግሥትነት ከቤት ይጀምራል” አልሁ፡፡ በመሠረቱ ከቤት የማይጀምር ነገር የለም፡፡ ከቤት የሚጀምር ነገር በጎም ሆነ ክፉ በውጭም ይታያል፡፡ ከቤት ያልጀመረ ከውጭ አይመጣም፡፡ ስለዚህ የብዙ ነገሮች መሠረት ቤት ነው፡፡ የሰው ዕድገት የሚጀምረው ከቤት በመሆኑ ቤታችን በኛነታችን ላይ ያለው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም፡፡ “እናቷን አይተህ ልጅቷን አግባ” መባሉም ለዚህ ነው፡፡

Read More »

ጣራው ለሚያፈስ ቤት – የወለል እድሳት (ይገረም አለሙ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

ጣሪያው በሚያፈስ ቤት ውስት እየኖሩ ክረምት በመጣ ቁጥር እየተሰቃዩ በጋ  ሲሆን የወቅት መለዋወጥ የተፈጥሮ ባህርይ መሆኑ ተዘንግቶ ነገር አለሙን በመርሳት ወለሉን ቢያድሱት ግድግዳውን ቀለም ቢያብሱት አይቀሬ ነውና ክረምት ሲመጣ የሚሆነውን አስቡት፤ከንቱ ልፋት አጉል ብክነት፡፡

Read More »

“ኢትዮጵያ ሀገሬ” አዳዲስ 21 የአርበኝነት ቀስቃሽ ሙዚቃዎችን በቅርብ ቀን ይጠብቁ!

Patriotic Songs from Adera band

"ኢትዮጵያ ሀገሬ" በሚል ርዕስ "በአደራ የባህል ቡድን" የተዘጋጁ 21 የአርበኝነት ሙዚቃዎች በሁለት ሲዲዮች (21 Patriotic Songs in two CDs) ተዘጋጅተው በቅርቡ ለህዝብ ይቀርባሉ።

Read More »

የሳዑዲና የቀጠር መናቆር (በሳዲቅ አህመድ)

saudi arabia and qatar

ጉዳዩ የአገራት መናቆር ነዉ። ጉዳዩ የሳዑዲዎቹ የአል ሱዑድ ቤተሰብና የቀጠሮቹ የአል ሳኒ ቤተሰብ ፉክክር ነዉ። ጉዳዩ በሳዑዲዉ ንጉስ አስተዳደር ዉስጥ የጎላ ድምጽ ያለዉ ተለዋጭ አልጋ ወራሹ መሐመድ ቢን ሰልማን ቢን አብዱል አዚዝ አል  ሱዑድ በችኮላ የሚፈጥራቸዉ  አስተዳደራዊ ወከባዎች አካል ነዉ።

Read More »

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ – በዋሽንግተን ዲሲ

Andargachew Tsige is Ethiopian

የወያኔ መራሹ ዘረኛ ስርአት አርበኛችን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን አፍኖ ከወሰደ እነሆ ሶስት አመታትን አስቆጥሯል። እኛም ይህን በደልና ግፍ በዜግነቱ ለሚመለከተው ለእንግሊዝ መንግስት ተወካይ እዚሁ ዲሲ በሚገኘው ኢንባሲ በመመላለስ ብሶታችንን ስናሰማ መቆየታችን ይታወቃል፤ ዛሬም የሶስተኛ አመት እስራቱንና በተመሳሳይ ለነፃነት ሲሉ በየእስር ቤቱ የሚንገላቱ ወገኖቻችንን ለማሰብ በእንግሊዝ ኤንባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ የተዘጋጀ ስለሆነ እርሶም በቦታው በመገኘትአጋርነትዎን እንዲያሳዩ ተጠርተዋል።

Read More »

በፎቅ ላይ ለምትኖሩ ሁሉ! ከሰማይ በታች ስካይሴቨርን ዋስትና ማድረጉ አይከፋም

SkySaver Rescue Device

በሬ ሆይ ሳሩን ስታይ ገደሉን እንዲባል ጋሻ ሻውን የአባቶቹን እርስት መሬት ለደደቢት መሳፍንቶች እያስረከበ የተወላሸሹ ኮንዶሚኒዩሞችን እንደ ቶምቦላ ለሚናፈቀው የአገሬ ሰው የሚኖረው እሳት አደጋ በሌለበት፣ ቢኖርም ውሃ በሚጠፋበት፣ ውሃ ቢኖርም እሳት አደጋው በማይመጣበት፤ በሚዘገይበት፣ ሲያስፈልግም ወያኔ እራሱ ሆነ ብሎ በውስጥ መመሪያ (በሳቦታጅ) መንደር ሙሉ ቤት በሚያቃጥልበት አገር ውስጥ እንደመኖራችን በእንዲህ አይነት ኮንዶሚኒየም ላይ የእሳት አደጋ ቢፈጠር አስቀድሞ መውጫውን መንገድ ማስላቱ አይከፋም።ይህ ማስታወሻ በተለይ በቨርጂኒያና ቺካጎ ሰማይ ጠቀስ የህንጻ ጫካዎች ውስጥ ባሉ ስካይ ስክራፐሮች ላይ ተንጠልጥላችሁ የምትኖሩ ይዲቪ ጀነሬሽን ወገኖቻችንን በእጅጉ ይመለከታል።

Read More »
Click here to connect!