የጎሳ ፖለቲካና የኢሳት ፈተና (ከአንተነህ መርዕድ)

ESAT television new satellite

ለብዙ ሺህ ዓመታት ነፋስ እንደሚገፋው ማዕበል ህዝቡ ከምስራቅ ወደ ምዕራብ፣ ከደቡብ ወደ ሰሜን፤ ከሰሜንም ወደ ደቡብና ምስራቅ በጦርነትና በሰላም ሲገማሸር፣ ሲቀላቀል፣ ሲዳዳጥና ሲጨፈላለቅ ብሎም ሲዋሃድ መኖሩ ይታወቃል። ከታሪካችን እንደምናስተውለው የኢዛናን፣ የካሌብን፣ የዮዲትን፣ የአምደፅዮንን፣ የግራኝን፣ የኦሮሞን መስፋፋት፣ የቴዎድሮስን፣ የዮሃንስን፣ የምኒልክን የኃይለስላሴን ኃይል እየተከተሉ በየቦታው የተዛነቁትን አያቶቻችንን ታሪክ ወደ ኋላ ብንቃኝ ማን በየትኛው ጊዜ ግፍ ፈፃሚ እንደነበር በትክክል ለማየት ከዘረኝነትና ከጠባብ የፖለቲካ ጥቅም ፀድቶ መገምገምን ይጠይቃል።

Read More »

ታሪክን ምርኮኛ የማድረግ ዘመቻ (ዶ/ር ነብዩ ጋቢሳ)

Professor Haile Larebo

በአሁኑ ወቅት ጎሰኞች የልብ ልብ አግኝተው ታሪካችንን በማጣመም ብቻ ሳይወሰኑ፣ ትክክለኛ የሆነው የሃገራችን ታሪክ እንዳይነገር የተለያዩ ማሸማቀቂያዎችን በመጠቀም የታሪክ ባለሙያዎች የዳር ቆመው ተመልካች የሆኑበት ሁኔታ ተፈጥሮአል።

Read More »

ታላቅ ህዝባዊ ውይይትና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በዋሽንግተን ዲሲ

Patriotic Ginbot 7 public meeting and support in Washington DC

የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ውስጥ እያደረገ የሚገኘውን እልህ አስጨራሽ ትግል በቀጣይነት እንዲቀጥል ለማድረግ “እኔ ለነጻነቴ” በሚል አለምአቅፍ የአንድነትና የዲሞክራሲ ትግል በደጀንነት ድጋፋችንን ለማሳየትና እንደዚሁም ትግሉ የደረሰበትን ደረጃና በቀጣይነት ምን መደረግ እንዳለበት ከከፍተኛ የድርጅቱ አመራሮች ጋር በአካልም እንደዚሁም በቀጥታ ከትግል ሜዳ ላይ ካሉ አርበኞች ጋር ለመወያየትና ከህዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ እንድንችል የድርጅቱ የድጋፍ ቻፕተር በሜሪላንድ ሲሊቨር ስፕሪንግ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል

Read More »

በሚሰማው ጉድ ኢትዮጵያውያን እግዚኦ እንበል! (ነፃነት ዘለቀ)

Prof. Haile Larebo

ችግሩ በስሜት የሚነዳ እንጂ በአስተውሎት የሚራመድ ትውልድ እያጠጠን መምጣታችን ነው፡፡ ራስን መመርመር ቀረ፤ ራስን መመዘን ፋሽኑ አለፈበት፤ ራስን ብፁዕ ሌላውን ኃጥዕ ማድረግ የዘመኑ ፈሊጥ ሆነ፡፡ ምን ይሻለናል?

Read More »

ካናቱ የገማውን አሳ በአርቲፊሻል ግምገማ (መስቀሉ አየለ)

ECADF Amharic News and Views social media graphic image

ሲሳይ አጌና ያቀናበረውን የወያኔ ፓራዶክስ እያዳመጥኩ ነበር። በቡድን አባት ተከፋፍሎ እንደ ልጅነት ኳስ ጨዋታ በዚህ የመከራ ቀንበር በከበደበት ህዝብ ላይ ጢባጢቦ ስለሚጫወቱት የወያኔ ዘለፈቶዎች እና በህዝቡ ብሶት ላይ የእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ስለሚሆኑበት የዛሚ ሬዲዮና ኢቢስ የእርስ በርስ ፍትጊያ ነበር።

Read More »

ፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ እና “የቁቤው ትውልድ” ፖለቲካ (ክንፉ አሰፋ)

Professor Haile Larebo

ፕ/ር ኃይሌ ባለሳምንት ናቸው። ነገ ሌላም ምሁር ይቀጥላል። የአጼ ምኒሊክን ስም የሚያነሳ ምሁር በሙሉ እንዲሸማቀቅ እና ዝም እንዲል የሚድረግ ሙከራ ነው። በመገናኛ ብዙሃን ቀርቦ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚናገር ምሁር ወይንም፣ ታሪኩን እነሱ በሚፈልጉበት መንገድ ቀይሮ ካልተናገረ ላለመሰደቡ ዋስትና የለም።

Read More »

ወደ ኋላ እያዩ ወደ ፊት መሄድ (ይገረም አለሙ)

Amharic News and Views in Amharic

የመንገዳችን ርዝመት የድላችን ህልምነት ነበር የመነጋገሪያ ርእሰ ጉዳያችን፣ብዙ አይደለንም አጋጣሚ ያገናኘን ሁለት ሰዎች እንጂ፤ተቀራርቦ ለማውራት ብዙ ትውውቅ አላስፈለገንም፣በሁለታችንም ውስጥ ያለው የቁጭትና የብሽቀት ስሜት ከመቅጽበት ተናቦ ለመተዋወቂያ የሚሆን መንደርደሪያ ጨዋታም ሳያስፈልገን ነው ዘው ብለን በወያኔ ሀያ አምሰት አመታት ለመገዛት ስላበቃን ምንነትና እንዴትነት ማውጋት የጀመርነው፡፡

Read More »

የነዶን ኪሾቶች ሀገር (ምሕረቱ ዘገዬ)

Amharic News and Views in Amharic

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ፈጽሞ ባይረሳትም ተኝተን መጠበቅ የለብንም፡፡ ከዚህም በከፋ የተማረ ሰው ከዘረኝነትና ከወንዝ ልጅነት ርቆ በሰብኣዊነት መሠለፍና ኃይሉን በአንድ አሰባስቦ ለጋራ ማንነት መታገል ሲገባው አሁን በተያዘው ወያኔያዊ መስመር መንጎዱ የማታ ማታ ከናካቴው ሀገር የሚያሳጣ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ የብዙዎች ችግሮቻችን መልስ ወደጤናማ ኅሊና መመለስ ነውና በዚህ ረገድ እንበርታ፡፡

Read More »

ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ፡- ባንኪ ሙን

Journalist Anania Sori and Elias Gebru

በአንድ ሉአላዊ ሀገር ውስጥ፣ ሕዝብና መንግሥት የሚግባቡበት ጤናማ ግንኙነት እንዲኖራቸው የህግ እና ህገ-መንግሥታዊ ሥርዓት መኖሩ ቀዳሚው መሠረት መሆኑ ይታመናል፡፡ በህግ አግባብ ሥርዓትን ተከትላ የምትተዳደር ሀገርም ወደ እድገትና ብልፅግና በሂደት መሸጋገሯ አይቀርም፡፡ ከእዚህ በተቃራኒው የሚጓዙ ሀገራት ደግሞ ችግርና መከራዎቻቸው ተዘርዝረው አያልቁም፡፡

Read More »

የህወሃት ድራማ ተዋናኞች ሆይ! እጃችሁን ከወልቃይት ላይ አንሱ! (ልሳነ ግፉዓን ድርጅት)

Welkait Tsegede

ህወሃት እንደ ለመደው በአንድ በኩል እውነተኛ የህዝብ ወኪሎችንና መሪዎችን በግፍ በማሰር እያሰቃየና በሽብር ወንጀል በመክሰስ በህግ ሽፋን ሞትና እድሜ ልክ እስራት ለማስፈረድ የተበላበትን የ“አኬልዳማ ክፍል ...” ድራማ ላይ እየተወነ፤ በሌላ በኩል ለጊዚያዊ ጥቅም ባደሩና በተለያዩ ህወሃታዊ የማንበርከኪያ ወጥመዶች ተጠልፈው ለህወሃት ርካሽ የጥፋት አላማ በተንበረከኩ ደካሞችና ሆድ አደሮች ተጠቅሞ ሃሰተኛ የኮሚቴ አባላትና መሪዎች እየጠፈጠፈ መክረሙንና ህዝብን እንደ ህፃን ልጅ አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ እያለ ሲጃጃል እነሆ 25 ዓመታት እንደዋዛ አለፉ።

Read More »

በነገራችን ላይ ‘ውይይቱ’ የት ደረሰ? (ክንፉ አሰፋ)

TPLF, EPRDF and Ethiopian opposition meeting

ልክ እንደቀበሌ ስብሰባ ተቃዋሚዎችን በአዳራሽ ውስጥ አጉረው ሲያበቁ እነሱ ከመድረክ ሆነው ይቀልዱባቸዋል። የNBC ውን፤ የዴቭድ ሌተርማን 'ሌት ናይት ሾው" (late night show) የሚመስል ነገር በቴሌቭዥን ለቀውብን ነበር። ሁለቱ ባለስልጣኖች፤ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እና አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ መድረክ ላይ ጉብ በለዋል። በአነስተኛና በጥቃቅን የተደራጁ 21 የፓርቲ መሪዎች ደግሞ እንደ ቲያትር ተመልካች አዳራሹ ውስጥ ተሰይመዋል። እነዚያ ከላይ፣ እነዚህ ከታች ተቀምጠዋል። እነዚያ ይናገራሉ፣ እነዚህ ደግሞ ይሰማሉ።...ሌላ ምን አማራጭ ሊኖራቸው?

Read More »

ጥብቅ መረጃ… ሕወሃት ተደማጭንት አላቸው የሚባሉ ግለስቦች እንዲታፈኑ ትእዛዝ አውርዷል

Amharic News and Views in Amharic

የህወሀቱ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት ወደ ወረዳ ፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ያወረደው ትእዛዝ አርበኞች ግንቦት7፣ 460 አባልትን በህቡሕ አደራጅቶ ከፍተኛ በጀት እያፈሰሰ ነው ከማለቱ ባሻገር 900 የታጠቁና የተበተኑ ግዳጅ ተወጪዎች መሰማራታቸውን ፍንጭ ሰጥቷል::

Read More »

አማራውን ፍለጋ (መስቀሉ አየለ)

Amharic News and Views in Amharic

የአማራው ህብረተሰብ በታሪክ አጋጣሚ እንደ ሎተሪ እጣ ከወጣላቸውና ከበታችነት ስሜት (የኢንፌሪየሪቲ ኮምፕሌክስ) ፣ ኤክዞኖፎቢያ፣ ወዘተ መገለጫ የሆነው የዘረኝነት ወይንም ስሙን ሲያጣፍጡት ብሄርተኝነት የሚሉትን የስነልቦና ቀውስ አምልጦ የወጣ፣ አማራዊነትን በኢትይጵያዊነት ተክቶ ማሳደግ (ማኒፌስት ማድረግ) የቻለ ህዝብ ነው።

Read More »

ከጥልቅ ተሃድሶው ማግስት ዘመቻ ዘ-ፀዓት (ገለታው ዘለቀ)

Amharic News and Views in Amharic

ለወትሮው ከገዢው ፓርቲ አካባቢ የተለመደው የተሃድሶ ትርጉም ለየት ያለ ነበር። “ኢህአዴግ” ስብሰባዎችን ያደርግና ሲጨርስ “የተሃድሶ ሰኣት!” ይባልና በዚያን ጊዜ የማእድ አገልግሎትና የተለያዩ መጠጦች የኪነት ትርኢት የሚቀርብበት ሰኣት ተሃድሶ ይባላል። ለአንድ የገዠው ፓርቲ አባል ተሃድሶ ሲባል ቶሎ ወደ ህሊናው የሚመጣው ነገር ድግስ ይመስላል።

Read More »

“ድሃ ተበደለ፤ ፍርድ ተጓደለ” ኢህአዴግ የማይቀርፈው ሙስና — አክሎግ ቢራራ (ዶር)

Dr. Aklog Birara

ኪራይ ሰብሳቢነት፤ አድልዎና ሙስና ስርዓት ወለድ ነው። የዚህ ትንተና መሰረተ ሃሳብ ስርዓቱ ካልተለወጠ በስተቀር፤ የፈለገው የፖለቲካ ሰበካ ቢደረግ ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስና ሊቀረፍ አይችልም የሚል ነው። መጀመሪያ በትርጉም እንስማማ።

Read More »

“እኛና ልጆቻችን!” (ኤርሚያስ ለገሰ)

Ermias Legesse, author and ESAT TV and Radio contributor

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ ያሆነኝ ባለፉት ጊዜያቶች “የለውጥ ሐይሎች ግልጽና ደፋር ውይይት ለመፍትሄና የጋራ ድል” በሚል ርእስ ተዘጋጅተው ከተሰራጩት ግብረ-መልሶች በመነሳት ነው። መጣጥፎቹ ከቀረቡና በተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ላይ ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ ሃሳቡን በመደገፍም ሆነ በመቃወም የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።

Read More »

ባንዳ ማነው? (ይገረም አለሙ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

የጽሁፉ ርዕስ “ለባንዳዎች ፕሮፓጋንዳ ምላሽ አለን በአሥራ አንደኛው ሰአት ላሉት – ለይገረም አለሙ” ይላል፡፡ መለስ ያሉት እኔ ዶ/ር ታየ ወልደሰማያት በአስራ አንደኛው ሰአት በሚል ርዕስ ላቀረብኩት ጽሁፍ ሲሆን ጸሀፊዎቹ ደግሞ ነጠላ ይሁኑ ብዙ በማይታወቅ ሁኔታ ከኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ ስዊድን ነው የሚለው፡፡

Read More »

ህዝብ መሪዎቹን መፈተሽ አለበት! (ነጋ አባተ)

Prof. Berhanu Nega, Patriotic Ginbot 7 chairman

ብርሃኑና ጓደኞቹ እያሉ ወያኔ እንቅልፍ ተኝቶ አያድርም ይህን እርግጠኛ ነኝ። እርግጠኛ የሆንኩበትም ምክኒያት አግ 7 መነሻ ነጥቡን አግኝተውታል ባይ ነኝ ከወሬ አልፈው ይነስም ይብዛም ስራ እየሰሩ ነው ወያኔን ደግሞ የሚያስደነግጠው ይህ ነው። ስራ ተሰራ ብሎ ካሰበ ይበረግጋል።

Read More »

በስናይፐር የታጀበ ጥምቀት በጎንደር (የጎህ ጋዜጠኛ ዞብል)

Timket (Epiphany) in Gonder

ታቦት በራሳቸው ላይ የተሸከሙ አባቶች ሁለት እጆቻቸው ታቦቱን ቢደግፉም እንባዎቻቸው በጎንደር አስፋልት ላይ ጠብ፣ ጠብ፣ እያሉ ሲፈሱ ከበርካታ ካህናት አይኖች ቀረብ ብዮ አስተውያለሁ፣ መስቀል ኃይልነ ብላ የምታምን ቤተክርስቲያን ዛሬ ስናይፐር ኃይልነ የሚል መንግስት በስናይፐር የጎንደር ታቦቶች እንዲታጀቡ አደረገ።

Read More »

የጥምቀት በዓል (የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በዓል በኢትዮጵያውን እይታ)

Ethiopian orthodox church cross

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ውሀ በዮሐንስ እጅ እንደተጠመቀ እንኳን ክርስቲያን፤ ከክርስትና እምነት ውጭ የሆነ ሁሉ ያውቀዋል።

Read More »
Click here to connect!