Home » ጦማሮች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም…

ጦማሮች፣ አስተያየቶች እና ሌሎችም…

የመለስ እርኩስ መንፈስ (ኃይሉ ማሞ)

meles zenawi's gift

የመለስ ዜናዊ እርኩስ መንፈስ ጎልቶ የሚገለጽበት አንዱ ነገር ይዞት ከመጣው ስርዓት ጋር የተከለው የዘረኝነት መርዝ ነው። ኢትዮጵያ በገዛ ህገ-መንግስቷ የሀገርነት እውቅና ያላገኘች የዓለማችን ሀገር ናት። እንደሀገር ጠንካራ መሰረት ያላት ሳትሆን የጥርቅሞሽ ምድር ተደርጋ የተገለጸችው በመለስ ዜናዊ ዘመን በተጻፈ ህገ መንግስት ተብዬ ነው።

Read More »

ብሔር የሰፈረበት የሀገራችን የቀበሌ መታወቂያ ወረቀትና መዘዙ (በያሬድ አውግቸው)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

ዘረኛው የህወሐት ቡድን በበኩሉ የማእከላዊውን የመንግስት ስልጣን ከተቆጣጠረ ጀምሮ  ከተገበራቸው እኩይ እቅዶች መካከል  ተመሳሳይ ጦስ ይዞ ሊመጣ የሚችለውን ብሄርን በመታወቂያ ላይ በግዴታ ማስፈር ይገኝበታል። ላለፉት 26 ዓመታት እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው ዜጎች አስፈላጊነቱ ወይም ጥቅሙ እንዲገለጽላቸው በተደጋጋሚ  የጠየቁ ቢሆንም መልስ ሰጪ ግን አላገኙም።

Read More »

ግዜ እየጠበቀ የሚፈነዳው የመለስ ቦንብ (ይገረም አለሙ)

ye meles zskren

የሚያሳዝነው የሚያስተዛዝበውና ቀን ሲወጣ የሚያፈራርደው ይህን እኩይ ተግባር የፈጸመን ሰው ታላቅ ተግባር የከወነ ኢትዮጵያዊ መሪ እያሉ የሚያሞካሹ ለጋሲውን እናስቀጥላልን እያሉ እሱ ቆላልፎት የሄደውን የሴራ መንገድ በማያቁበትና በማይችሉት መንገድና ሁኔታ አናስኬዳለን እያሉ ሀገር እያወደሙ ህዝብ እየጫረሱ ያሉት ሰዎች ናቸው፡፡

Read More »

አጽማቸውን የፈለሰው መላከ ብርሃን አድማሱ ከአምስቱ ዘመን ተጋድሎ በኋላ (ክፍል አንድ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

ከዚህ በፊት በተከታታይ በወጡት ጦማሮች ተዋጊ ፋኖዎች በእነ በላይ ዘለቀ፣ መንገሻ ጀንበሬ፣ ራስ ሀይሉ በለው፣ በበዛብህ ነጋሽና ሌሎችም የየጦር መሪነት፤ አርበኞች ካህናት በእነ ሊቀጠበብት አድማሱ ጀንበሬ፣ መላከ ሰላም አለማየሁ ሻሾና ሌሎችም ካህናት...

Read More »

የቅማንት ካርድ (መሳይ መኮንን)

ዛሬ የሰሜን ጎንደር ሰማይ ያረገዘው ዳመና ምን ሊያዘንብ እንደሚችል አይታወቅም። ህዝብ አማራ፡ቅማንት የሚል ልዩነት ሳይገድበው ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ድምጹን እየሰጠ ነው። አንድን ሰው ለሁለት እንደመክፈል የተቆጠረው፡ ስጋና አጥንትን የመለያየት ያህል የተወሰደው ህዝበ ውሳኔ ህወሀት ስለፈለገው ብቻ እየተካሄደ ነው።

Read More »

በኢትዮጵያ ላይ ያንዣበበውን የውጭ ኃይሎች ጫናና ሴራ እንዴት ለመቋቋም ይቻላል? (ዶ/ር – አክሎግ ቢራራ)

Author, Dr. Aklog Birara

ህወሓት/ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫነው በቋንቋና በብሄር ልዩነቶች ላይ የተመሰረተው የክልል ሕገ መንግሥትና የፌደራል አስተዳደር፤ የአገራችንን ረዥም ታሪክ “ሰው ሰራሽ” ነው በሚል ብሂል ተነስቶ ለሃገራችን ዘላቂነት፤ ግዛታዊ አንድነት፤ ነጻነት፤ ደህንነትና ሉዐላዊነት ጠንቅ ሆኗል።

Read More »

ህልውናውን በህዝቦች ቅራኔ ላይ የገነባ ዘረኛ ቡድን (በያሬድ አውግቸው)

Ethiopia, TPLF officials

በአሁኑ ወቅት የህወሃት  ዋነኛ  ስራ  በህዝቦች መካከል ቅራኔዎችን መፍጠር የሚመስልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል። እንደ ጥሩ ምግባር ለቅራኔዎችም እቅድ ተዘጋጅቶና በጀት ተመድቦ  የህዝቦች ደም ሲፈስ ይታያል። ለዚህም የወቅቱ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ሃይልና የአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች ነዋሪዎች መካከል ያለው ጦርነት መሰል ግጭት አንዱ ማሳያ ነው።

Read More »

ያለ መግደርደር ኢትዮጵያዊ ነኝ (የሳዲቅ አህመድ ንግግር – ኦክላንድ ካሊፎርኒያ)

Sadik Ahmed's speech in Oakland Califoria

ኢትዮጵያዊነትን ሌሎች ብቻ ሳይሆኑ የማይረዱትና የማያዉቁት በእኛም በኢትዮጵያዉያኑ ዘንድ እራስን በራስ የመረዳት ችግር አለ። ኢትዮጵያዊነት የሚለካዉ አገርን በገዙ፣ አገርን በመሩ ባሉና በነበሩ ሐይላት ሳይሆን፤ ህዝቡ በሰነቀዉ ልዩ የፍቅር ስንቅ ነዉ። ህዝባችን እንደ ህዝብ በፍቅር ኖረ እንጂ ከጥላቻ ጋር አለተቆራኘም። ህዝባችን በባህሉ፣ በሐይማኖቱ ተከባብሮና ተዋዶ የወል እሴቶችን ገንብቶ እስካለንበት ትዉልድ ድረስ ያለችዉን ኢትዮጵያን አቆይቷል። ስለዚህ የማንነት ቀዉስን ፈጥሮ በኢትዮጵያዊነት መግደርደሩ 'ሆድ ሲያዉቅ ዶሮ' ማታ ነዉ።

Read More »

የጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ክፍተቶች… (አዜብ ጌታቸው)

ALEMNEH WASSE NEWS

አለምነህ ስለ ኢህአዴግና በውስጡ ስላሉት 4 ድርጅቶች መስተጋብር ያለው መረዳት ምንድነው? 4ቱም ድርጅቶች እውን እኩል መብትና ጉልበት አላቸው ብሎ አስቦ ይሆን ታማኝ ምንጩ የነገረውን የስራ አስፈጻሚውን ውሳኔ እንደ ዋንጫ ጫወታ አጓጊ አድርጎ ለማቅረብ የሞከረው? እውን አንድም ጉዳይ ቢሆን ያለ ህውሃት ይሁኔታ ሊተገበር ይችላል ብሎ ያስባልን? የሚሉ ጥያቄዎችን ላነሳ ተገድጃለሁ።

Read More »

የዝምታየን ግድብ አስጣሰኝ (ታምራት ታረቀኝ)

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

ከተደጋጋሚ እስር በኋላ በቅረቡ ከተፈታው ወዳጄ ዳንኤል ሽበሺ ጋር ባለፈው ሳምንት በስልክ ተገናኘን፡፡ግንኑነታችን አንድም ከረዠም አመት በኋላ ሁለትም እሱ ከእስር በተፈታ ማግስት ቢሆንም በእንዴት ነህ አንዴት ነህ መጠያየቅ ብዙ አልቆየንም፡፡

Read More »

“ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

Ethiopian Border Affairs Committee

ለ 25 ዓመት ኢትዮጵያን የገዛው የወያኔ መንግሥት፤ አገሪቱን ከተቆጣጠረበት ቅጽበት ጀምሮ በቅርብ የሚታየው ከሩቅ የሚሰማው መፍረስና መገሰስ ቢሆንም፤ በየዘመኑ ድንበር እየጣሱ ከመጡ ወራሪዎች ጋራ ለዳር ድንበር ስትፋለም የኖረች ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውህዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ወቅት ምን ትላለች?

Read More »

ስትሄድ የመታህ ድንጋይ ስትመለስ ከደገመህ ከራስህ ጋር  ስብሰባ መቀመጥ ይገባሀል

ECADF Ethiopian News in Amharic social media graphic

በመጀመሪያ ደረጃ ህወሀት  ከምስረታው ጀምሮ በጠላትነት የሚያሳድደው አመለካከት ፍቅር፣ አንድነት እና ኢትዮጵያ የሚለውን ሀይል አይደለም እንዴ? እስከዚህ ሰዓት ድረስ  የተበዳይና የበዳይ ድርሰት እየደረሰ  በህዝቦች መካከል ቁርሾ የሚዘራው ማነው?

Read More »

የቂሊንጦ ቃጠሎና የሀሰት ክስ (ጌታቸው ሺፈራው)

Qilinto, Ethiopia’s Maximum Security Prison

ቂሊንጦ ውስጥ እስረኛ ይደበደባል፣ ተገዶ የማረሚያ ቤት ልብስ ለብሷል፣ ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ የወርና ከዛ በላይ ቀጠሮ ይሰጠዋል። እስረኛው በበርካታ ጉዳዮች ተማሯል። አሁን ደግሞ ምግብ ተከልክሏል። ይህ በሆነበት በር ዘግተውበት ወጥተዋል። ይህ ሁሉ የሚደርስበት እስረኛ በር ዘግተውበት የሄዱ ፖሊሶች ላይ ጩኸት ማሰማት ጀመረ።

Read More »

ዝምታ ሁሉ እንደማስማማት አለመቆጠሩን ለመግለጽ ስል ብቻ… (ነፃነት ዘለቀ)

Strike in the Oromia region of Ethiopia

ይህን አጭር ማስታወሻ የምጽፈው በርዕሴ ለመጠቆም እንደሞከርኩት አንድን የተነገረ ወይ የተጻፈ ነገር በዝምታ ብቻ ታዝቦ ማለፍ ስምምነትን እንደመግለጽ የሚቆጠር እንዳልሆነ ለማስገንዘብ ስል ብቻ ነው፡፡ እንጂ ሰዎች ባበዱና በሰከሩ ቁጥር ብዕር እናንሳ ብንል በቀን ውስጥ ያለው 24ቱ ሰዓትም  በጭራሽ አይበቃንም፡፡

Read More »

እንኳንስ ሲሸጡን ሲዋዋሉብን እናውቃለን፣ የመልስ መልስ ለአቶ አብርሃ ደስታ (ከጎሹ ገብሩ)

Abraha Desat, Ethiopian polititian

ለተከበሩ አቶ አብርሃ ደስታ በመጀመሪያ የከበረ ሰላምታየን አቀርባለሁ በአካል ባንተዋወቅም በተጋድሎ ሃርነት ትግራይ ተብየዋ ተዕዛዝ ዘብጥያ በወረዱበት ወቅት የሚያውቅዎትም ሆነ የማያውቅዎት አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሙሉ በተሰነዘረብዎት ጥቃት ዘርና አካባባኢ ባልለየ መልኩ ከጎኖ እንደተሰለፈ ይዘነጉታል ብዬ አልገምትም እኔም እንደሌላው ሁሉ ነፃ የሚወጡበት ቀን ስመኝልዎት የነበርኩ ስሆን ህልሙ እውን ሆኖ ይህን ልብ የሚሰብር አጭር ትረካ ለመፃፍ እንኳን አበቃዎት እላለሁ።

Read More »

“አሸንዳ” ባህል የማን ነው? (በነጋ አባተ)

ashenda in amhara region

“አሞራው” በተሰኘው ሙዚቃዊ ድራማ ውስጥ  ከተካተቱት ዜማዎችና ውዝዋዜዎች መካከል አንዱ አሸንዳ ነበር። “አሞራው”  የሚለው ስያሜም የጀግናው ራስ ውብነህ ተሰማ የአርበኝነት ስም ነው። ውብነህ በጎንደር ክ/ሃገር በወገራ አውራጃ ቆላ መረባ በ1884 ተወልደው በአካባቢው ባህልና እምነት መሰረት ተኮትኩተው ያደጉና በኢትዮጵያዊነት ተጠምቀው ለኢትዮጵያውያን የኖሩ ስመ-ጥር ጀግና ናቸው።

Read More »

መለኛው ምኒልክና የዘመናዊ ወፍጮ አገባብ

መለኛው ምኒልክና የዘመናዊ ወፍጮ አገባብ

በኋለኛው ግዜ የማንኛውንም ውግዘትም ሆነ ተቃውሞ አሸንፈው ወፍጮን ያቋቋሙት ምኒልክ ናቸው። በአድዋ ዘመቻ ጊዜ ጓዙን ያበዛው የፈጪና የወፍጮ ጭነት መሆኑን ያወቁት አጼ ምኒልክ ለግላቸው ብዙ እህል የሚፈጭ ወፍጮ እንዲያስመጣላቸው እስቲቬኒን አዘዙት። ወፍጮውም መጥቶ በ1893 ተተከለ። ወፍጮው የሚፈጨው በሰይጣን ሳይሆን በሰው መሆኑን ለማሳየት ምኒልክ ራሳቸው ወፍጮ ቤት እየሄዱ በአስፈጪነት ተካፋይ ሆኑ።

Read More »

ዘረኝነት የወያኔ መጠባበቂያ ካርድ (ይገረም አለሙ)

Ethiopia, TPLF officials

ወያኔ አንድም ተረጋግቶ ኢትዮጵውያንን መግዛትና  የሀገሪቱንም ሀብት ለመዝረፍ  ሁለትም ጸሀይ ጠልቃበት ሥልጣኑን ቢያጣ ኢትዮጵያ አንደ ሀገር መቀጠል አንዳትችል ለማድርግ የሚያስችለው የዘር ፖለቲካን ማስፋትና ማስፋፋት ሲችል መሆኑን አምኖ አቅዶና ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ሲያደርግ ብዙዎች በዝምታ፣ ከፊሎች ከጳጳሱ ቄሱ ሆነው ይህንን መንገድ በመከተል ወያኔ የዘራው ዘረኝነት ተመችቶች እንዲበቅል አብቦም አንዲጎመራ ተባብረናል፡፡

Read More »

አልገብርም ሲል እንደመንግስት አላውቅህም ነው (ዳዊት ዳባ)

Small business owners strike in Ethiopia

አላማው ግልፅ ባይሆንመ አንዳንዶች ህዘብ የጀመረውን ትግል  ቆሟል ብሎ ለማወጅ ዳር ዳር ሲሉ ሁሉ ይታያል። እውነታው ትግሉ በተጠናከረ መንገድ ቀጥሏል። ይህን እየፃፍኩ ደንቢዶሎና ጊነቢ ላይ ህዝብ ለአራተኛ ቀን ከተማውን ዘግቷል። ይህን አይነት ትግል ካደባባይ ተቃውሞዎች በላይ ያገዛዙን ፍፃሜ ከመስራት አኳያ ጉልበታም ነው።

Read More »

የመለስ አስከሬን… (አትክልት አሰፋ – ከቫንኩቨር)

ye meles zskren

መለስ የሞተ ሰሞን አንድ ወዳጄ ኢትዮጵያ ሄዶ ነበር። ለቀብር ሽር ጉድ በሚባልበት ጊዜ መሆኑ ነው። ያኔ ስለዚያ ሰሞን ሁኔታ ስናወራ አንድ የቆዳ ሃኪም የሆነ ዘመዱ የመለስ አስከሬን አዲስ አበባ ገባ በተባለበት ወቅት ቤተ መንግስት ተጠርቶ ሙያዊ እገዛ ተጠይቆ ነበር።

Read More »