ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የ ‹‹ሰማያዊ›› ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው፡፡ ፓርቲው ከተመሰረተ ጥቂት እድሜ ያስቆጠረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚነሳ ለመሆን በቅቷል፡፡ የላይፍ መጽሄት አዘጋጅ የሆነው ዳዊት ሰለሞን ግንፍሌ አካባቢ በሚገኘው የፓርቲው ጽ/ ቤት በመገኘት ኢንጅነሩን በዋናነት ስለ አማሮች መፈናቀል አነጋግሯቸዋል፡፡…
ማክሸፍ እንደምንችልበት ከማመን እንጀምር፤ ስለዚህም ኢሳት ሊከሽፍ የሚችልበትን እያንዳንዱን መንገድ ማጥናትና በቅድሚያ ፈውሱን ማዘጋጀት የሚጠቅም ይመስለኛል፤ ይህንን ጉዳይ በትጋት ለመከታተል የኢሳትን አማራጭ የማይገኝለት የአገር ጥቅም በእውነትና በትክክል መገንዘብ ያሻል፤ ዘመን-አመጣሽ ነገር ብቻ አድርጎ መመልከቱ ለወረት ይዳርገዋል፤ ወረትን ማክሸፍ ቀላል ነው፤ ከከሸፈ በኋላ እንዲያንሰራራ ለማድረግ በጣም ከባድ ሥራን ይጠይቃል፤ ስለዚህ ከወዲሁ…
እኔ እኮ የምለው ሰው አይኑ እያየ የሰራውን ስራ እያወቀ ወደ አሜሪካ ለዛውም ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ይሄዳል እንዴ!? እውነቱን ለመናገር እኔ አቶ መለስ ዜናዊን ብሆን ኖሮ ዲቪ እንኳ ቢደርሰኝ ሀገር ይቀየርልኝ እላለሁ እንጂ አሜሪካ አልሄድም። እነ ቻይና ባሉበት አለም እነ ሰሜን ኮሪያ በሚኖሩበት ምድር ሰው እንዴት ወደ አሜሪካ ይሄዳል? (ይቅርታ ሰው…
ምን ነካዎ አቶ መላኩ፤ መንግስት በሚያውቀው በሽታዎ ነውኮ ዘብጥያ የወረዱት፤ እርግጥ ነው ይህንን በሽታ ከየትም አላመጡትም፤ ከመንግስትዎ ጋር ባደረጉት ጥንቃቄ የጎደለው እና ልቅ የሆነ የሙስና ግንኙነት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እርግጥ ነው መንግስታችን ራሱም የዚህ በሽታ ተጠቂ መሆኑ እሙን ነው፡፡ እርግጥ ነው በማራዘሚያ ብዛት እንጂ ሁሉም ባለስልጣኖቸች የዚህ ህመም ሰለባ መሆናቸውም ግልጽ…
ሳይንሳዊ ውይይትም ወይም ክርክር የሚመራው በሕገ-ኀልዮት ወይም በእንግሊዝኛ ‹‹ሎጂክ›› በሚባለው የአስተሳሰብ መመሪያ ነው፤ ይህንን አዚህ ለመዘርዘር ከባድ ነው፤ ግን ሁለት መሠረታዊ ቁም-ነገሮችን ማንሣት እንችላለን፤ አንደኛው የሕገ-ኀልዮት መንገድ ከዝርዝር ተነሥቶ ወደማጠቃለል የሚሄድ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከአጠቃላይ ወደዝርዝር የሚወርድ ነው፤ (የትና መቼ እንደሆነ አላስታውስም እንጂ ከዚህ በፊት በጻፍሁት ከታች-ወደላይና ከላይ-ወደታች በማለት እነዚሁኑ…