ትንሽ ስለ ተስፋዬ ገብረአብ

October 10, 2013

Abraha Desta the facebook

አብረሃ ደስታ

‘የተስፋዬ ገብረአብ ማንነት አጋለጠ’ የተባለውን ፅሑፍ አነበብኩት። ገረመኝም። ረዥም ነው። የአንድ ሰው ማንነት ለማጋለጥ አርባ ምናምን ገፅ? ተስፋዬ ገብረአብን ‘ያጋለጠ’ ፅሑፍ ለኔ ምንም ዓይነት ተጨማሪ መረጃ አልሰጠኝም።

ስለ ተስፋዬ ገብረአብ ትንሽ ለመፃፍ የተገደድኩት ምክንያት አንዳንድ የህወሓት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ‘የተስፋዬን መጋለጥ’ ምክንያት በማድረግ እኔ አንድ ነገር እንድልላቸው ስለወተወቱኝ ነው። አንዳንዴ’ኮ ጎበዞች ናቸው። ተፎካካሪያቸውን ማኖ ማስነካት ይችላሉ። እኔ ደግሞ ማኖ መንካት እወዳለሁ፤ (ማኖ ካልነካንላቸው ከስድብ ዉጭ ሌላ የሚያውቁት ነገር የላቸው)።

ተስፋዬ ገብረአብ ጎበዝ የስነ ፅሑፍ ሰው ነው። ፅሑፉን ለመገምገም ማንነቱና ስራው አያገባንም። የፅሑፉ ይዘትና መልእክት መገምገም በቂ ነው። እንደ የስነፅሑፍ ሰው ጥሩም መጥፎም ስራዎች ይኖሩታል። ለምሳሌ ‘የቡርቃ ዝምታ’ ፅሑፉ መጥፎ ዓላማ ያለው መሆኑ የሚያሳይ ነው።

አሁን ‘የተስፋዬ ገብረአብ ማንነት ተጋለጠ’ እያላችሁኝ ነው። የሻዕቢያ ቅጥረኛና ሰላይ መሆኑ እየነገራችሁኝ ነው። ለዚህ ማስረጃችሁም በኤርትራ መንግስት የተሰጠው ግዝያዊ መታወቅያና በማስታወሻ ደብተሩ ላይ በፃፈው መሰረት ነው። ጥሩ ነው። ግን ተስፋዬ ገብረአብ የኤርትራ ግዝያዊ መታወቅያ ማግኘቱና የሻዕቢያ ሰላይ መሆኑ ምን ይደንቃል? እንዳውም ሲያንሰው ነው።

በመጀመርያ የተስፋዬ ስራዎች የምናነበው ኤርትራዊ ስለሆነ ወይ ስላልሆነ አይደለም። የሻዕቢያ ሰላይ ስለሆነ ወይ ስላልሆነም አይደለም። ‘ኢትዮዽያዊ ነኝ’ ብሎ ስለነገረንና ስላመነውም አይደለም። ፀሓፊ ስለሆነ ነው። የፕሮፌሰር ክላምፓም፣ ፕሮፌሰር ለቪና ሌሎች ስለ ኢትዮዽያ የሚፅፉና የምናነብላቸው የኢትዮዽያ ደም ስላላቸው አይደለም። ስለ ኢትዮዽያ ለመፃፍ የግድ ኢትዮዽያዊ መሆን አይጠበቅብህም። የተፃፈ ለማንበብም የፀሓፊው ማንነት ማወቅ ግድ አይደለም። ግድ የሚለን የፅሑፍ ይዘት መገምገም ነው።

ተስፋዬ ገብረአብ የሻዕብያ ሰላይ ነው እንበል። ይሄ አይደንቅም። እንዳዉም የሚደንቀው ሰላይ ባይሆን ኑሮ ነው። የኤርትራ መንግስት በሰጠው ግዝያዊ መታወቅያ ላይ የትውልድ ሀገር ደብረዘይት ይላል። መኖርያውም ናይሮቢ። ተስፋዬ ደብረዘይት ተወልዶ እንዳደገና ኢትዮዽያዊ መሆኑ ነግሮናል። ከኤርትራውያን ቤተሰብ እንደተወለደ ግን ይታወቃል። ተስፋዬ ይህም ቢሆን ክዶ አያውቅም። ከኤርትራውያን ቤተሰብ ቢወለድም (ተስፋዬ ሲወለድ ኢትዮዽያና ኤርትራ አንድ ሀገር እንደነበሩ ይታወቃል) ኢትዮዽያ ዉስጥ ተወልዶ በማደጉ ብቻ የኢትዮዽያ ዜግነት የማግኘት ሕጋዊ መብት አለው። የኢትዮዽያ ዜግነት ተሰጥቶም የኢትዮዽያ ሬድዮና ምናምን ሓላፊ ሁኖ ሰርቷል (ዜግነት ሳይኖረው ስልጣን ተሰጥቶት ከሆነ የራሳቹ ጉዳይ)።

ሌላ ነጥብ ደግሞ ተስፋዬ ከኢትዮዽያ ባለስልጣናት ከተጣላ በኋላ ወደ ኬንያ መሄዱና የኢህአዴግ ባለስልጣናት የኢትዮዽያ ፓስፖርቱ እንደነጠቁት ተናግሮ ነበር። እንዴት ነው ነገሩ? ፓስፖርት መንጠቅ?! ወይስ ከኢህአዴግ ባለስልጣናት ከተጣላ በኋላ ነው ኢትዮዽያዊ አለመሆኑ ያወቁ? ይህ የሚያሳየው ነገር ቢኖር የሻዕቢያ መንግስት ግዝያዊ መታወቅያ የሰጠው ከኢትይዽያ ተጣልቶ ከወጣና ናይሮቢ ከገባ በኋላ መሆኑ ነው።

አንድ ሰው ፓስፖርቱ ከተነጠቀ ዜግነቱ ተነጠቀ ማለት ነው። በሌላ ሀገር (ለምሳሌ ኬንያ) እየኖሩ ዜግነት አልባ (Stateless) መሆን እንዴት እንደሚከብድ አስቡት። ፓስፖርት ሳይኖርህ እንዴት በሌላ ሀገር መንቀሳቀስ ይቻላል? ኬንያ እያለ ፓስፖርቱ ከተነጠቀ እንዴት ብሎ ወደ ደቡብ አፍሪካ መሻገር ይችላል? (ሻዕቢያ ሌላ ፓስፖርት ሰጥቶት ይሆናል)። ለምንድነው የኢትዮዽያ ፓስፖርቱ የተነጠቀው? የኤርትራ ደም ስላለው ነው? እንዲህማ ከሆነ የኤርትራ መንግስት መታወቅያ መስጠቱ ተገቢ ነው። ምክንያቱም ብዙ ከኢትዮዽያ የተፈናቀሉ ኤርትራውያን በሻዕቢያ መታወቅያ ይሰጣቸዋል። ትክክልም ነው። ከኤርትራ የተፈናቀሉ (የተባረሩ) ኢትዮዽያውን የኢትዮዽያ መታወቅያ እንሰጥ የለም እንዴ?! የማንሰጥ ከሆነም መስጠት አለብን።

ስለዚህ ተስፋዬ የኤርትራ መታወቅያ ማግኘቱ አይደንቅም። እንዳውም ተገቢ ነው። የኢትዮዽያ ፓስፖርቱ ከተነጠቀና በናይሮቢ የኤርትራ ግዝያዊ መታወቅያ ከተሰጠው በኋላ ኤርትራዊ ሁነዋል። አሁን ‘ኢትዮዽያዊ ነኝ’ ካለ ተቀባይነት የለውም። የኤርትራ ዜግነት ካገኘ ታድያ ለሀገሩ መስራቱ ምን ይደንቃል? የሻዕቢያ ሰላይ መሆኑ ምን ይደንቃል? ኤርትራዊ አይደለምን? አዎ! ለሀገሩ መስራት አለበት፤ በሚፈልገው ዘርፍ። ስለዚህ ተስፋዬ የሻዕቢያ ሰላይ ነው መባሉ አልገረመኝም።

መርሳት የሌለብን ነገር አለ። በፖለቲካ ብዙ ዉጣ ዉረዶች አሉ። ብዙ የተጠላለፉ ስለያዎች አሉ። ብዙ ታዋቂ ሰዎች የታላላቅ የስለላ ድርጅቶች ቅጥረኞች የሆኑ አሉ።። በተስፋዬ ‘መጋለጥ’ የተደነቀ ሰው በነዚህ ሰዎች ስራማ ጨርቁ ሊጥል ነው። የሻዕቢያ መንግስት እንኳንስ ተስፋዬ ገብረአብን የመሰለ የህወሓት/ኢህአዴግ የዉስጥ አዋቂ፣ ታማኝ ሊሆን የሚችልና የኤርትራ ደም ያለው ምርጥ ፀሓፊ አግኝቶ ኢትዮዽያን ለመበታተን ያለው መሰሪ ተልእኮ ለማሳካት ለኢትዮዽያውያንምኮ በገንዘብና በጦር መሳርያ ይደልላል። ሻዕቢያ እንኳንስ ተስፋዬ ምርጥ የሀገሩ ልጅ ለአልሸባብም ኮ ያግዛል፤ መታወቅያ እየሰጠ እንዲሰልሉና እንዲያሸብሩ ይተባበራል። ታድያ ይሄ ምን ይደንቃል?

ተስፋዬ ገብረአብ በሻዕቢያ የተላከ የሻዕብያ ቅጥረኛ ነው አላችሁኝ። በተመሳሳይ መንገድ የተላከ ስንት የሻዕቢያ ቅጥረኛ ባለስልጣን ይኖረን ይሆን? ህወሓት በራሱ ኮ የሻዕቢያ ተልእኮ ለማስፈፀም በሻዕቢያ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ህወሓት የመሰረተው ማነው? ሻዕቢያ ነው። ሻዕቢያ መሓሪ ተኽለ (ሙሴ) የተባለ ኤርትራዊ የሻዕቢያ አባል በትግራይ ለሻዕቢያ ሊያግዝ የሚችል ድርጅት እንዲያቋቁም ወደ ኢትዮዽያ ላከ። እነዚህ ህወሓት የመሰረቱ የሚባሉ ሰባት ሰዎች አሰባስቦ እንዲደራጁ አደረገ። ስለዚህ በተስፋዬ ስራ መደነቅ የሻዕቢያ ተግባር አለማወቅ ነው።

ተስፋዬ ገብረአብ ኤርትራዊ ከሆነ ከድሮ ጀምሮ ኤርትራዊ መሆን ነበረበት። መንግስት ሲፈልግ ዜግነትና ሓላፊነት የሚሰጥ ሲፈልግ (ከባለስልጣናት ሲጣላ) ደግሞ መንጠቅ የሚችል መሆን የለበትም። አሁን ‘ተጋለጠ’ የተባለውን ትክክል ከሆነ ተስፋዬ ኤርትራዊና የሻዕቢያ ሰላይ መሆኑ ግንዛቤ እንያዝ። ምክንያቱም መረጃ ጥሩ ነው። ሰላይ ስለሆነ መፃሕፍቶቹን አናነብም ግን አልልም። ምክንያቱም አንድ የሻዕቢያ ሰላይ የፃፈው ይቅርና የሲአይኤ (CIA) ስራ አስከያጅ የፃፈውም አነባለሁ። ሰይጣን የፃፈውም ካገኘሁ አነባለሁ። ጉዳዩ መሆን ያለበት አረዳዳችን ላይ ነው።

ተስፋዬ ስለ ፃፈው ጥሩ ወይ መጥፎ ነገር መነጋገር እንችላለን። የተስፋዬ ሁኔታ በማጋለጥ የተስፋዬን ፅሑፍና ሓሳብ ማጥቃት ግን አይቻልም። እንዳውም ህፀፅ ነው (Ad hominem Circumstantial Fallacy)። ተስፋዬ ብዙ ግዜ የሚወቀስባት መፅሓፍ ‘የቡርቃ ዝምታ’ ነች። እኔም አልወደድኳትም። አካኪ ዘራፍ ግን አላልኩም። ምክንያቱም ተስፋዬ ሓሳብ አንስተዋል። ስህተት ከሆነ ስህተት መሆኑ በፅሑፍ ማስረዳት አለብኝ እንጂ ወደ ተስፋዬ ማንነት አልሯሯጥም። ምክንያቱም ተስፋዬ ፀሓፊ እንጂ ባለስልጣን አይደለም። ፅሑፍ ሓሳብ ነው። ስልጣን ግን ተግባር አለው። ሓሳብ ሰለማዊ ነው። ስልጣን የማስገደድ ባህሪ አለው። ሓሳብ የማሳመን ስራ እስከሆነ ድረስ የጭንቅላት ጨዋታ ነው። ስልጣን ግን በሃይል የማስፈራራት እርምጃም አለው። በሓሳብ ያለመቀበል መብታችን የተጠበቀ ነው። በስልጣን ግን ያለመቀበል መብታችን ሊጣስ ይችላል።

ስለዚህ ማንኛውያም የሓሳብ ክርክር ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። ማንኛውም የስልጣን (የሃይል) እርምጃ ለመቀበል ግን አልተነሳሁም። ተስፋዬ ፀሓፊ እስከሆነ ድረስ (ኤርትራዊ ሰላይ ጭምር) አያስፈራኝም፤ ማንነቱ ስለተጋለጠም ትኩረት የምሰጠው ጉዳይ አልሆነም። ባለስልጣን ቢሆን ኑሮ ግን (አስቡት ሰላይ ሁኖ ባለስልጣን) እቃወመው ነበር። ማንነቱ በመጋለጡም ደስ ይለኝ ነበር።

ለመረጃ እንዲሆን ግን ተስፋዬ ‘የቡርቃ ዝምታ’ የፃፈው የኢህአዴግ ባለስልጣንና የኢትዮዽያ ዜግነት ጨብጦ በነበረበት ግዜ ነው። መፅሓፉም ገዢዎቻችን እያጨበጨቡ አስመርቀውለታል። ስለዚህ ኢትዮዽያዊ እያለ የፃፈው ነው። ከድሮ ጀምሮ ሰላይ ነበር ካልን ሌላ ጉዳይ ነው። እኔ ደግሞ ለምን የሻዕቢያ ሰላይ የሚድያ ባለስልጣን አድርገን ሾምን? ብዬ እጠይቃለሁ።

እንደሚድያ ሰዎች የተስፋዬ ማንነት ማጋለጣቸው ግን ጥሩ ነው። ምክንያቱም ግዴታቸው ተወጥቷል። በዚህ መሰረት ለተስፋዬም (ላልታወቁ ሌሎችም) ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። በፌስቡክም ቢሆን ስንት ያልተደረሰባቸው ሰላዮች ይኖራሉ።

13 Responses to ትንሽ ስለ ተስፋዬ ገብረአብ

 1. Girum Reply

  October 22, 2013 at 2:40 pm

  Well, I agree with Abreha. I advise all to read 20th chapter from YEDERASIW MASTAWESHA. Zer ena Zermanzer. Only then after say any words about Tesfaye. Thanks to Tesfaye I fall in love with Debrezeyet. Mention at least one writer who can give us ye enat hager fikir by expressing beautiful nature of the country.
  Regarding Chaltu, there were many and many like her before and today and it will continue.You cant avoid it.The same is true with other ethnics. The same with Gurage. But Gurages never falled under inferiority complex and hate Amharas. Concerning Eritrea, It is a matter of time. They will be happy to join us after death of Esayas`s ideolojy. Tesfaye will be in Debrezeyet and we will sing with him in Amahric and Oromifa,Read another books from his breliant mind. You cant deny he is breliant.
  Some ppl say Tesfaye is SELAY. What????? What secret can he tell to Shabya about Ethiopia when the Minilik betemengist is full of woyanes Yeshabya lijoch? As any writer he wrote what existing and happened. You know that all woyane leaders telling us via ETV many fake history about ethnics problem and wish us in public ENTERHAMWAY. In this regard Tesfaye will be the last and the least.
  Long live Oromo, Amhara,… Asmera and Ethiopia.

 2. betti Reply

  October 15, 2013 at 2:02 am

  AGAIN
  Hi Teasfaye G/ebab,
  why the silence? Are words failing you now? Not healthy for you. Take a deep breath and come out of the closet. “Coming out of the closet” has an additional meaning, as you might know. Both contexts apply to you.

 3. betti Reply

  October 15, 2013 at 1:59 am

  Hi Teasfaye G/ebab,
  why the silence? Are words failing you now? You hired this Abrha Desta from Makalle?

 4. Yequaraw Reply

  October 13, 2013 at 1:07 pm

  ስለ ተሰፋዮ ገ/አቭ ብዙ ማለት ይቻላል።ቀደም ብሉ ባሳተማቸው ተራሮችን ያንቀጠቀተ ትውልድ፤የቡርቃ ዝምታ፤አሁንም የስደተኛው ማሰታወሻ የወጡት ጭብጦች ምንም እውነትነት የሌላቸው ዓላማቸውም አንዱን ብሄር በሌላው ላይ ለማነሳሳት በተለይም በርካታ ቁጥር ያላቸውን የአማራውን ብሄረሰብ ከኦሮሞው ብሄረሰብ ተወላጅ ጋር
  ለማጣላት እና እልቂትን መናፈቅ በዚህም ኢትዮጵያን ማፈራረስን አላማው አድርጎ የተሰራ ፕሮፖጋ እንጂ ስነ-ቱፋዊ ይዘት አላቸው ለማለትም ያዳግታል።አሁንም የስደተኛው ማሰታወሻ ብሉ ባሳተመው መጥሀፉ አማራዎች በሀረሬዎች ላይ ከፍተኛ ግፍ ፈጥመዋል ሲለ በተለመደው መርዛማ ብዕሩ መርጨቱን ልብ ይላል። አማሮች ዛፉን መነጠሩት ይለናል። አቶ መለስ ስለ ተፈናቀሉ አማሮች ሲጠየቅ ዛፍ ስለቖረጡ ነው እንዳለው ነው። ማነው ለዚህ ሰው ጥብቅና የሚቆመው ሌትኛው ስራው ነው። አሁንም ይህን መጣፍ ማን ገንዘቡን እስፖንሰር አድርጎት በነጣ በየዌብ ሳይቱ ሲለቀቅ መገመት የሚቻለው ሰወች ይህን የተንኮል ድር ሳያዩ ወጥመዱ ውስጥ እንደገቡ የተዘጋጀ ነው።ዻኛ ወልደ ሚካኤል እና አለማየሁ የፈጠሙት አኩሪ ተግባር ግለሰብን የማጥቃት ሳይሆን ሀገርን እና ትውልድን የመታደግ አኩሪ ገድል ነው። ሌላውም የተስፋየን መሰሪ ተንኮል በመረዳት የመሰሪ አላማው ሰለባ እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ከዚሁ መጣፍ አቶ መለስን አሰመልክቶ ሲገልጥ ያጠፋነው የለም ይቅርታ የሚያስጠይቅ ስህተትም አልሰሩም ያለናል።ተስፋዩ ይሁዳ ነው የበላበትን ወጭት ሰባሪ እንደ እርጎ ዝንብ ያለቦታው የሚገባ!

 5. Abel Reply

  October 13, 2013 at 10:06 am

  It is true, Abrha Desta is one of the rebellious voices against the regime of injustice in Ethiopia. I do have respect for what he believe and the courage he displayed in otherwise repressive environment.
  Nevertheless, I will not agree with the entire piece of his opinion regarding Tesfaye G. A.
  Though by definition ones right to express his or her mind shall be respected, he/she cannot escape to take responsibility from the contents of his/her works.
  Let me make it simple. One can’t get away by espousing slander or libel just because he/or she is free to express own mind. Tesfaye’s “The Burka’s Zimita” is much different than a freedom of thought or for that matter a work of art. Hate speech or inciting riot are tantamount to criminal act.
  Therefore, in the context of Ethiopia, anyone who promoted hatred, ethnic slur or suspicion could damage the integrity of the nation and the well-being of the people. The lesson from Rwanda and Yugoslavia are still a fresh memory of human tragedy in our generation. Those tragedies would have been prevented if there was swift action taken to expose and isolate the culprits.
  I personally do not read books for the sake of reading. It is to get an emotional or educational rewards. Our imagination could have been influenced by the experience we might go through in our surrounding environment. For brother Abrha, to loose free from the collective gag order EPRDF puting upon us could be more pressing. But, national security has much more urgency and weight. Balancing the freedom of speech and national security has to be evaluated on the actual circumstances where our country is. In my view, we don’t have the luxury of entertaining such a nuisance as Tesfaye Gebreab at this juncture of time.
  Good day!

 6. Taye Eshetu Reply

  October 12, 2013 at 7:55 pm

  Hi Ecadforum. I enjoyed your website message. Could you post what was written about Tesfaye GA from Judge Woldemichael.

 7. በለው! Reply

  October 12, 2013 at 4:58 pm

  >>>አቶ አብርሃ ደስታ ከመቐለ ” አንዳንድ የህወሓት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ‘የተስፋዬን መጋለጥ’ ምክንያት በማድረግ እኔ አንድ ነገር እንድልላቸው ስለወተወቱኝ ነው። በማስተባበል ተባበረን ይሆን? “ተስፋዬ ገብረአብ የኤርትራ ግዜያዊ መታወቂያ ማግኘቱና የሻዕቢያ ሰላይ መሆኑ ምን ይደንቃል? እንዳውም ሲያንሰው ነው። የሚቆጨው ሥልጣን አለመያዙ ነው።”የአንድን ሰው ማንነት ለማጋለጥ ፵ ምናምን ገፅ? ሲሉ ይቀውጡታል። *እውነት ነው መለስ ዜናዊ፣ አረጋዊ በረሄ፣ እና ሌሎች ኤርትራውያን፣ ኦነጎች፣ኦብነጎች፣ ሚሽነሪዎች(ዲቃሎች) ኢትዮጵያን ለማጥፋት፣ትውልድ ለመበረዝና ለማምከን ስንት የውሸት መፅሐፍ ፅፈዋል ያላነበቡት ተደንቀው መርቀዋል።!!

  ማሽቋለጥ፦ ፩)ተስፋዬ ገብረአብ ጎበዝ የስነ ፅሑፍ ሰው ነው።(ይህ የድሃና መሃይምን ሀገሮች ብሄራዊ ፉገራ ነው።)
  በቀጥታ ወደ ማሽቃበጥ እንገባለን “ተፎካካሪያቸውን ማኖ ማስነካት ይችላሉ፡ እኔ ደግሞ ማኖ መንካት እወዳለሁ፤ (ማኖ ካልነካንላቸው ከስድብ ዉጭ ሌላ የሚያውቁት ነገር የላቸው)።
  __________——————-________________——————
  *ድሮ ተስፋዬ ገብረአብ ማለት፦ ከአማራ ደጅ ተባሮ ኦሮሞ ደጅ ጥገኝነት የተጠየቀ ኮስማና ቀጥን አሳዛኝ የኤርትራ ስደተኛ ይመስለኝ ነበር። አሁን አንዳንድ ቦተአ ሳየው ግን “የኦሮሞ እርጎ ጠትቶ ከኦሮሞ ባላይ ኦሮሞ ፈርስት ያለ ጆሌ ብሸፍቱ! ሲፈልግ ሀረሪ ሲያሻው ብሔር ብሔረሰብ አለዚያም የትግራይ ነፃ አውጭ አባል፣ የኤርትራ አፈቀላጤ፣ የኦሮሞና አማራን ልዩነት የሚያጠና የፖለቲካ ተንታኝም፣አፋተሪክ ‘ተባለ አሉን’ ወደ የታሪክ የሚተረጉም ጎበዝ የስነ ፅሑፍ ፀሐፊ ነው። ለዚህም ነው አቶ አብርሃ ደስታ ዘራፍ ያሉት።አራት ነጥብ። አስደናቂው ጉዳይ ተስፋዬ ገብረእባብ የሚጠቅሳቸው ሰዎች ሁሉ ሞተዋል ጠፍተዋል። በዚህ ሥራ የተካኑ ግርማ ካሳ፣ያሬድ አይቼህ፣ክፍሉ ሀሰን፣ክንፉ አሰፋ፣ ይጠቀሳሉ።

  *ባለፉት ፮-፰ ዓመት በአቡጊዳ ድረ ገፅ፡
  ፩) አበበ ቀልቤሳ፦ “የጋዜጠኛውን ማስታወሻ የጻፈው ጋዜጠኛ እስካሁን ት ነበር”? ፳፻፱
  ፪) አጎናፍር ደመላሽ፦ “ከሀምሳ ጦረኛ አንድ ወሬኛ”፳፻፱
  ፫) እጅግአየሁ አወቀ፦ “ተስፋዬ ገብረአብና ሁለት ዝሆኖች”፳፻፲
  ፬) መክብብ ማሞ፡- “ኢትዮጵያን አማራ ያደረጋት ማነው?፳፻፲
  ፭) ጀማል መሀመድ፡- “ተስፋዬ ገብረአብ ደራሲ ወይንስ መረጃ ሠራተኛ/ ፳፻፲፩ …በሌሎችም ሲብጠለጠል ኖሯል የሚገርመው ፂሙን እያንዘረፈፈ ቀበሮ ባዕታዊ ሆኖ “የኦሮሞ ሙስሊም ነፃ አውጭ ግንባርን ተቀላቅሎ ሜንጫ አብዮትን መሠረተ “መለስ ሰጠ መለስ ነሳ” ጃንዋሪ ፳፭/፳፻፲፩ በደ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ላይ መተኮስን ተያያዘው ተገንጣይ ጀዋሪዎችን ይዟል የውሸት ታሪኩን መፅሐፍ እየጀወረላቸው ያስፈነድቃቸው ጀመር ኤርትራ ገባችበትን አዘቅት አሳአቸው ተደሰቱ ዶ/ር መራራ ጉዲና የተከበሩ አቶ ቡልቻ ደመቅሳም አልቀረላቸውም ጭራሽም ኦሮሞ አደሉም ሲል ይሞግታል። ከላይ ደራሲነቱን የሚያዳንቁ ደንቆሮዎች ሁሉ አደነቆሩን እኛም ለሚያነብና ለሚረዳ ሁሉ ሐሳብ ሰጥተናል።

  **”ድብረዘይት አማራዎችን “የሞጃ ልጆች እንላቸዋለን። “ፀጋዬ ገብረመድህን እንዲህ ይሉ ነበር። ሃማሴን፣ ሃም-ሴን። አማራ፣ አም-ሃራ፣ ሃም-ሃራ። ሃማሴን እና አማራ የሃም ልጆች ናቸው ሁለቱም። ነፍሳቸውን ይማርና ጋሽ ፀጋዬ፣ እንዲህ ያለ የቃላት ወግ ይወዱ ነበር። ይሄ ታሪክ አይደለም። ወግ ነው።”
  **”መለስ አዝማሪ አደለም!”(መለስ አባይን ለመገደብ በወኔ ዘሎ ገባበት…! መለስ አርባው ሳይወጣ ስሙን ለፖለቲካ ፍጆታ ተጠቀሙበት።” አዘንና ፍቅሩን በመቆርቆር ይቀውጠዋል።
  **”በጎ ምክር ለጓዶች” ለታጋዮች ለጓደኞቼ ሲልም ከውጭ ቃረማትን ሁሉ ለኢህአድጎች ይነፋላቸዋል። “ደርዘን ትአቄዎች ከተስፋዬ ገብረአብ ሲልም ዲያስፖራውንና ሌሎችንም አስቴአየት ለኢህዴግ ትንካሬ የሌላውን ድክመት በራሳቸው ድረ-ገፅ ጥናታዊ ስለላውን ይፅፋል፤ በፓል-ቶክ ያደንቁታል፣ ያጨበጭባሉ አባባ ይበትናሉ፣ ይሳለቅባቸዋል፣ ያስቅባቸዋልም ቆይቶም ይበትናቸዋል። በለው!

  ፪) *ሰሞኑን የአንበሳውን ድረሻ በመያዝ ለተነሱ ሐሳቦች ሁሉ ፖለቲካውን፣ ሳይንስና ኢኮኖሚውን፣ ህግና ታሪክን የውጭ ጉዳይን ሁሉ የሚተነትኑት አቶ አብርሃ ደስታ ከመቐለ ናቸው።በኢምግሬሽን አሠራር በውጭ ሀገር ዝውውር ማስተባበያን በማቅረብ ለተስፋዬ ገብረአብ አረናንና ህወአት ወክለው ቆመዋል። እርግጠኛ ነኝ ግለሰቡ እንኳን ውጭ ሀገር ሰው ለመሸነት አውሮፕላን ጣቢያም አልሔዱም።ተስፋዬ ይበልጣቸዋል ተስፋዬ ፂም ያለው እባብ ስንለው በኤርትራዊነቱ አደለም!ኦሮሞንና አማራን በማጋጨቱም አደለም! በመጥፎ ባሕሪውና ውሸቱ እንጂ፤ ማናቸውንም ፀሑፉንና ቃለመጠይቆች ይገንዘቡ፡!ተስፋዬ ያማያውቀው ሰው የለም!አብሮት ያልዋለ ያላደረ ባለሥልጣን የለም!ያልተካፈለበት ስብሰባ የለም!ያልዋለበት ቡና ቤትና መጠጥ ቤት፣ ያላመሸበት ድራፍት ቤት የለም! ያላደረበት ሆቴልና ከተማ የለም!የሀገሪቱን አዋቂና ታዋቂዎችን አነጋግሯል!። አቶ አብርሃ ለመሆኑ አቶ መለስ ዜናዊ ስንት ሀገር ፓስፖርተ ነበራቸው?”ፓስፖርት ሳይኖርህ እንዴት በሌላ ሀገር መንቀሳቀስ ይቻላል? ለሚለው’ሰላይ፣ ሹምባሽ በክቡር አቶ ገብረመድክን አርዓያ መዝገበ ቃል (እንቁላልና ዶሮ ለጠላት ሻጭ) ጆሮ ጠቢ፣ ባንዳ፣ ሀገር ስለሌለው ፓስፖርት አይኖረውም!።አራት ነጥብ። አቶ መለስ ሱዳንን፣ ሱማሌን፣ ኤርትራን፣ ኬንያን፣ ውስጣዊ የሀገራቸውን የፖለቲካ ሚስጥር የሸጡት በገዛ ፓስፐርታቸው በመጓጓዝ ነበር ለሰሩት ውለታ አሜሪካዊቷ ‘ሩዝ’እንደበቆሎ(ፋንዲሻ)ለዜጋው በተከለከለው በመስቀል አደባባይ ስትንጣጣ አላዩምን? በመሠረቱ “በፖለቲካ ብዙ ዉጣ ዉረዶች አሉ። ብዙ የተጠላለፉ ሰለዮዎች አሉ። ብዙ ታዋቂ ሰዎች የታላላቅ የስለላ ድርጅቶች ቅጥረኞች የሆኑ አሉ።”በማለት አብራርተዋል ማመንዎም ጥሩ ነው።እኔም አልተሳሳትኩም!!

  ፫) በተመሳሳይ መንገድ የተላከ ስንት የሻዕቢያ ቅጥረኛ ባለስልጣን ይኖረን ይሆን?
  *ምን የተላከ ብቻ ሀገርህን የሚመሩት እነማን ናቸው? ደብረፂዮን ገብረሚካኤል…ቴዎድሮስ አድሃኖም…በረከት ስምኦን… አቦይ…እረ ስንቱ!? ማይክዱት ሀቅ ደሞ ” ህወሓት በራሱ እኮ የሻዕቢያ ተልእኮ ለማስፈፀም በሻዕቢያ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ህወሓትን የመሰረተው ማነው? ሻዕቢያ ነው። ሻዕቢያ መሓሪ ተኽለ (ሙሴ) የተባለ ኤርትራዊ የሻዕቢያ አባል በትግራይ ለሻዕቢያ ሊያግዝ የሚችል ድርጅት እንዲያቋቁም ወደ ኢትዮጵያ ላከ። እነዚህ ህወሓት የመሰረቱ የሚባሉ ሰባት ሰዎች አሰባስቦ እንዲደራጁ አደረገ።(ማህበረ ገስገስቲ ትግራይ(ማገብት)ተሓህት ዶ/ር አታክልት ቀፀላ አቦይ ጸሀዬ፣ስብሃት ነጋ፣መለስ ዜናዊና ዶ/ር አረጋዊ በረሄ አቶ ስዬ አብርሃም ሰላይ ናቸው ግን የአረና ትግራይ?
  ግለሰቡ እደግፋለሁ ብለው ተደግፈው ሊመለሱ ነው። እግዚኦ ማህረነ….በለው!
  ፬) “ሓሳብ የማሳመን ስራ እስከሆነ ድረስ የጭንቅላት ጨዋታ ነው”
  *ስለዚህ የቡርቃ ዝምታን አንብበው የተንቦረቀቀ አፍ ያላቸው ሁሉ ጭንቅላታቸው ባዶ ነው ተስፋዬ ገብረእባብ በጭንቅላታቸው ተጫውቶባቸዋል ማለት ነው። እሪ በል ጃዋር ኦሮሞ ፈረስት!
  ፭)ሰሞኑን አቶ አብርሃ “በፈሪደም ፎር ኢትዮጵያ” በተሰኘ ድረገጽ ላይ “ፖሊሲ የሚፈፀም ህገመንግስት የሚከበር” ሲሉ ሕገመንግስቱ “የህወአት ማኒፌስቶ” እንዳልሆነ ተከላክለዋል። ህገምንግስት አይነካም! አይፈፀምም! ይከበራል ብለዋል እኔ ካልተተገበረ የተፃፈው በሥራ ላይ ተፈጻሚ ካልሆነ ይቀበር እላለሁ!።
  ፮) “ተስፋዬ ስለ ፃፈው ጥሩ ወይ መጥፎ ነገር መነጋገር እንችላለን። የተስፋዬ ሁኔታ በማጋለጥ የተስፋዬን ፅሑፍና ሓሳብ ማጥቃት ግን አይቻልም። እንዳውም ህፀፅ ነው (Ad hominem Circumstantial Fallacy)
  * አቶ አብርሃ ደስታ ከመቐለ ተስፋዬን ከመከላከል አልፈውም አጥቂዎቹን ለማጥቃት እንደተዘጋጁም ይናገራሉ። “ተስፋዬ ፀሓፊ እስከሆነ ድረስ (ኤርትራዊ ሰላይ ጭምር) አያስፈራኝም፤ባለስልጣን ቢሆን ኑሮ ግን (አስቡት ሰላይ ሁኖ ባለስልጣን) እቃወመው ነበር። የተቃወማችሁ ሁሉ ጉዳችሁ ፈላ!!ለመሆኑ አቶ አብርሃ ተስፋዬ የሻቢያ ሰላይ የህወአት ቃል አቀባይ መሆኑን አውቅ ነበር። ግን ዝም ያልኩት ሥልጣን እስኪይዝ ነበር ይላሉ። ግለሰቡ ሌት ተቀን የሚፅፉት ማንን ወክለው እየሰለሉን ይሆን? ጠርጥር!!አቶ ጌታቸው እረዳ የተባሉ በዘ-ሀበሻ ድረገጽ ላይ ጠቁመዋል።

  **እዚህ ላይ አቶ አብርሃ የተቆጩት በመቀደማቸው ኢመስላል” እንደሚድያ ሰዎች የተስፋዬን ማንነት ማጋለጣቸው ግን ጥሩ ነው። ምክንያቱም ግዴታቸውን ተወጥቷል። በዚህ መሰረት ለተስፋዬም (ላልታወቁ ሌሎችም) ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። በፌስቡክም ቢሆን ስንት ያልተደረሰባቸው ሰላዮች ይኖራሉ። በእኔ እምነት አቶ አብራሃ ደስታ ከመቓለ እነደ አቶ ገብረመድክን አርዓያ ጥሩ ቆራጥ የትግራይ ኢትዮጵያዊ ሰው እንዲሆኑ እመክራቸዋለሁ ። መልስ ዜናዊ, ኢሳያስ አፈወርቂና ባንዳ(ሰላይ) ብቻ አደለም ተተኪ የሚኖራቸው። በተስፋ ነው በለው! ከሀገረ ከናዳ በቸር ይግጠመን <

 8. dagmawi Reply

  October 12, 2013 at 12:00 pm

  ECADEF it is really sad to see you mute about the article written by JUDGE WOLDEMICHALE exposing the work and his mission of dismantling and weakning Ethiopia by playing OROMOS against AMHARAS and he did that again when he writes about CHALTU which is completley false however ECADEF and other news media websites who claim they are independent ETHIOPIAN WEBSITES SHUT THEIR MOUTH atleast to post articles who exposed TESFAYE
  ECADEF it seems that you have no principle at all now we learn that who are real ETHIOPIAN MEDIAS rather you post the article defends TESFAYE it is rather to see you defending this criminal who incite hate against AMHARAS

 9. mega Reply

  October 11, 2013 at 4:19 pm

  የሚያሳዝነኝ በእንደነተስፋየ ገብረ አብ አይነት ካለዉ በላ ሰወች በጻፉት መጽሀፍ የሚነዳዉ ሰዉ ነዉ፡ የዉሸት ታሪክ የ ቡርቃ ዝምታ ኦ ህዝብን ከህዝብ ለመለያየት ፃፈዉ፡ ወያኔም አጨበጨበለት ከዛ ደግሞ ተከታዮችን አፈራ ለምሳሌ እንደነ ኦነጉ አባል ጃዋር መሀመድ አይነቶቹ በዉሸት ፕሮፓጋንዳ ኢትዮጵያዊነታቸዉን መካዳቸዉ ነዉ፡ ፓስፓርታቸዉ ኢትዖጵያ ይላል፡ ሀገሪቱን እንደመጠቀሚያ ዉጭ ለመሄድ እና ለመማር ይጠቀሙባታል። ከዛ ደግሞ የክህደት መርዛቸዉን እና ጠባብ የፓለቲካ አላማቸዉን ያራምዱባታል። ወይ ሀገሬ

 10. Nega Reply

  October 11, 2013 at 1:35 pm

  ገጽ 585

 11. Nega Reply

  October 11, 2013 at 1:33 pm

  በነብስ በላዎች መሃል ሁነህ የምትጽፋቸው ገንቢ ጽህፎችህ ይደነቃሉ፣ በርታ እንዳንተ ወንድ ነው ያጣነው። በተስፈየ ከተጻፉት ኣስተያየቶች ያንተው ለየት ያለ እና ተቃዋሚን የማስተናገድና የመቻቻል ባህል ስለምደግፍ በዚህ መንፈስ ይንተው ኣደንቃለሁ። ኣንድ ነገር ግን በጣም ተሳስተሀል። እዲህ ያልከው: “ሻዕቢያ መሓሪ ተኽለ (ሙሴ) የተባለ ኤርትራዊ የሻዕቢያ አባል በትግራይ ለሻዕቢያ ሊያግዝ የሚችል ድርጅት እንዲያቋቁም ወደ ኢትዮዽያ ላከ። እነዚህ ህወሓት የመሰረቱ የሚባሉ ሰባት ሰዎች አሰባስቦ እንዲደራጁ አደረገ”።” ፤ ይህ ውሸት ነው። ሰባቱ ስምንተኛ ኣቶ ገሰሰ ኣየለ ተኃህት/ህወሓት የመሰረቱት September 11, 1974 ኣዲስ ኣበባ ነው፤ መሴ የተመደበላቸው ስዮም እና ዶ/ር ኣረጋዊ ከኣዲስ ኣበባ ኣስመራ ከሄዱ በኃላ November 1974 ነው። ዝርዝር ከዶ/ር ኣረጋዊ በርሀ ጽሁፍ ገጽ 858 ከዚህ ሊንክ http://www.addisvoice.com/wp-content/uploads/2010/03/The_Origins_Of_TPLF.pdf ታገኘዋለህ። ስለዚህ የራህን ታሪክ መጀመርያ ኣጣርተህ ያዝ። ከዘረጋሀው ኣይቀር ኣርመህ ኣስተካክለህ መጻፍ ኣለብህ ኣብነት ሁን።
  ነጋ, October 11, 2013

 12. solomon Reply

  October 11, 2013 at 1:50 am

  The lone voice of reason in the wilderness. I am so proud of this young Ethiopian (Abraha) for his calm, cool and collected thinking.

  For ppl living in eminent social upheaval, there is default yearning to find somebody to throw our ills on him/her. The fact that Tesfaye G/Ab is Eritrean spy is a news. However, to spin it to the level as if we have found the key to the holy grail of our problem is insanity.

  thank you Abraha Desta and way to go……

 13. አራጋው Reply

  October 11, 2013 at 1:30 am

  መምህር አብርሃ ደስታ፤ በተለያየ ጊዜ የምታወጣቸውን ጽሁፎች አነባለሁ። በወያኔ አፋኝ ስርዓት ውስጥ ሆነህ እንደዚህ አይነት በእውነት ላይ የተመሰረቱ ስርዓቱን የሚቃወሙ ጠንካራ ሀሳቦችን በማቅረብህ አደንቅሀለሁ። አሁን ግን “ትንሽ ስለ ተስፋዬ ገብረአብ” በሚል ርዕስ ያወጣሀት ከአንተ አስተሳሰብ ፈጽሞ ያፈነገጠች ሆና ታይታኛለች። አንተ ምሁር የዩኒቨርሲቲ መምህር በመሆንህ የተስፋዬን መጻህፍት አንብበህ የመገምገም አቅም አለህ። ገምግመህም ክፉውንና በጎውን ትለያለህ። ነገር ግን ማሰብ ያለብህ ስንቱ ሰው እንደ እኔ ሊያስብ ይችላል የሚለውን ነው። ስለዚህ ተስፋዬ በመጻህፍቱ አያዋአዛ የሚተክላቸውን የመርዝ ችግኞች አጣጥለህ መፃፍህ ፈጽሞ ተገቢ አይደለም እላለሁ። “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው።” የሚለውን ተረት አስታውስ። ነገሩን ከሚገባው በላይ አቃለልከው።
  አመሰግናለሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>