ከድጡ ወደ ማጡ! የቀበሮ ባሕታዊ በሎንደን

July 4, 2013

ወንድሙ መኰንን፣ ሎንደን

Click here for PDF

መግቢያ

Debretsion Mariam London Ethiopian Orthodox Church

በዓለም ዙሪያ የተበተናችሁ ወገኖቻችን በኛ ሎንደን በምንኖረው የኦርቶዶክስ ሀማኖት ተከታይ በሆንን ኢትዮጵያውያን ላይ በአንድ መነኵሴ ነኝ ባይ የቀበሮ ባሕታዊ ግለሰብ አማካኝነትና በወያኔ ቀጠረኞች የደረሰብንን ይቅር የማይባል በደል ዕለት በዕለት እንደምትከታተሉና መጨረሻችንን ለማየት በጉጉት እንደምትጠባበቁ እዚህ ያሉት ወንድሞችና እህቶች በሚገባ ያውቁታል። ያመሰግናሉም። ታዲያ ከዚያች ቀውጢ የሁዳዴ ጾም መያዢያ ማግስት፣ ጀምሮ የተዘጋብን ቤተክርስትያን ጉድይ እስካሁን እልባት ሳያገኝ፣ ቀርቶ ሕጻናቱም፣ አይቆርቡም፣ አዛውንቱም፣ ወይዛዝርቱም እግዚአብሔርን ማምለኪያ ቦታ አላገኙም። ይኸ በደል ባንድ ካኽን ንኝ ባይ ሲፈጸም በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪአው መሆን አለበት። ብቻ በየሰንበቱ፣ “አንድ ሐሙስ የቀራችሁ፣ የእንጨት ሽበት፣ ሽሜ ጉጉ” እያተባሉ በወያኔ ሶልዲ በተገዙ ስድ ወጣቶች እየተሰደቡ፣ ሴቶችም ለጆሮ በሚቀፍ ስደብ እየተሸማቀቁ፣ ቤተክርስቲያኗ ቅጥር ገቢ እየገቡ ሕንጻዋን እየተሳለሙ፣ ከሕዝብ ጋር ከሚንከራተቱ አንድ ቄስ፣ አንድ መሪ ጌታ፣ እና በመምሕር ታሪኩን ጨምሮ በዛ ካሉ ዲያቆናት መሪነት ሜዳ ላይ እየጸለዩ፣ አራት ወራት አሳለፈዋል። ምን ላይ ደረሰ እያላችሁ የምትጠይቁ በዝታችኋል። ሁለቱ አዋጊ ጳጳሳትም፣ አቡነ ገብርኤልና አቡነ ቀውስቶስ፣ የትም ቦታ መንቀሳቀስ በማይገባቸው የሱባኤ ሰሞን አገረ ስብከታቸውን ጥለው ሕንጻውን ሊቀሙን ቢመጡም፣ በተደረገው ርብርብ ሳይሳካላቸው ቀርቶ “አባ” ተባዩን የቀበሮ ባህታዊ፣ “በርታ” ብለው ወደመጡበት ተመልሰዋል። “በመነኵሴ ነኝ” ባዩ አመጸኛ ግለሰብ አዝማችነት፣ ተዝቆ፣ ተዝቆ በማያልቀው የወያኔ ገነዘብ ኪራይ ከፋይነት ተደለለው፣ ቤተክርስቲያን አንድም ቀን ረግጠው በማያውቁ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ ጋጠ-ወጦች (ጋንግስተሮች) እስከመገፋት መገፍተር፣ደርሷል። እና አባ ተባዩም ንብረት እስከመስረቅና ማጋዝ ጀምረው ነበር። እንዲያም ሁኖ፣ እስካሁን ሕዝበ ክርስቲያኑ ቤተክስቲያኑን እየጠበቀና እየተከላከለ ይገኛል። ግፉ ግን በዝቷል። ሁለንተናው ዘቅጧል። ነገሩ ሁሉ ከድጡ ወደማጡ ተብሎ ቢደመደም ይበጃል። “አባባሱባት” ነበር ያልኳችሁ ባለፈው? እሱን እርሱት። ያሁኑ ይባስ።

የመዳን ንሰሐ ለጥቃት ሲያጋልጥ

ባለፈው ሳምንት የተፈጽመው አሳፋሪ ወንጀል፣ በታሪካችን ምንጊዜም “በምዕምን ላይ ደረሰ” ሲባል ተሰምቶም የማይታወቅ ጉድ ነው። ፈረንጆች “Abuse of Trust” ይሉታል።  ያመኑት ፈረስ በደንደስ እንደሚሉት ነው። በመጨረሻው ጽሑፌ ከአንባቢዎቼ የተልያየሁት “ብጹዐን አባቶች ለታስታርቁን ወይስ ልታዋጉን መጣችሁ?” በማለት በሞነጫጨርኩት መጣጥፍ ነበር። አባዛኛው መልዕክቱ ቢገባውም፣ ሌሎች ሰዎች ነገሩን እያባባስኩ እንጂ እየረዳሁ አለመሆኔን ስላሳሰቡኝ፣ ላልተወሰነ ጊዜ ምንም ላለመጻፍ አቅጄ ቆየሁ። የኔ ዝምታ ግን “ትሻልን ፈትቼ ትብስና አገባሁ” ቢጤ ሆኖብንና አሸንፈው ጭጭ ያሰኙኝ መሰላቸው። የኔ መተው ነገሩን አልከተተውም። ጳጳሳቱ ወደመጡበት በመመለሳቸው፣ የወያኔን ይሁንታ ተጨምሮበት፣ የቀበሮ ባህታዊው ባሰባቸው። በነጋ በጠባ ሕዝቡን “በምን ላቁስለው?” እያሉ ሲያልሙ የሚያድሩ ይመስላሉ። ፓትርያርኩ በሞቱላቸው ጊዜ፣ ይኸን ሕዝብ በምን ቆሽቱን ላድብን ብለው፣ ለታጋይ ጳውሎስ ፍትሀት አደርጋለሁ ብለው ተነስተው እንደአንጫጩን ይታወሳል። አሁን ደግሞ ሌላ አገኙ። የቤተክርስቲያናችንን መሠረት የናደ፣ እንኳን ከአንድ የአሀይምኖት አባት ነኝ ብሎ ከሚመጻደቅ ይቅርና፣ ከመርካቶ ዱሩየም የማይጠበቅ፣ በጣም የወረደ ተግባር ፈጸሙ። “ቤተክርስቲያናችንን ይጎዳል፣ ዝም በሉ” ለምትሉን፣ ዝምታ ለበጓም አልበጃት፣ ዝም አንልም። ዝም እማ ካልን ዲያብሎስ ይነግሳል። በዓለም ዙሪያ ያሉት ክርስቲያን ወንድሞችና እየቶቻችን የደረሰብንን በደል አውቀው፣ በጸሎታቸው እንዲተባበሩን፣ በደሉ ይታወቅ። የሎንደንማ ሕዝብ በተፈጽመው አስነዋሪ ነገር ተደናግጦ ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለበት ግራ ገብቶት ቁጭ ብሏል። አንዳንዱ፣ “ተው ከእግዚአብሔር ያግኙት”ይሉናል። ኤዲያ! እግዚአብሔር በአምሳያው የፈጠረን የምንችለውን አድርገን የማንችለውን ልንተውለት ነው። የምንችለውንም፣ የማንችለውንም ለሱ መተውማ ስንፍና ነው። የተጎዱት ያቃስታሉ። እንዴት ዝም እንላለን? ከመሀላችን አንዳችን ተጎዳን ማለት፣ ሁላችንም ተጎድተናል ማለት ነው። ነውሩን እራሱ ይደብቅ እንጂ እኔ ጫካ አይደለሁም የምደብቅለት። አልደብቅለትም። ያበጠው ይፈንዳ! ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

9 Responses to ከድጡ ወደ ማጡ! የቀበሮ ባሕታዊ በሎንደን

 1. Sista Reply

  July 7, 2013 at 10:24 pm

  Wendemu Mekonnen thank you for such an enlightening article. I was crying and laughing about it all. Overall, it is terribly sad that these so called church people are cheapening our religion.

  It is shocking. people have to pay attention here. Girma so called aba and his young boys and girls want to make us think they are suprior to us. They call us menafek. And yet look at this picture. A papas, a girl chore and a bed? what a strange pic. and yet I feel terribly sorry for the two young girls.

  Maraki is the London weapon of Weyane aka Kidusan mahaber. Strange isn;t it? The daughter of ” Komcabaw” the derg that killed so many, now is eating with another knife. This benefit cheat supposedly goes to university, but she cheats the system, she is in Addis Ababa every other month, she was the first one to his of the rudeness in the church. Such a ring leader in violence and trouble making, she has found a platform in the sin machine of Aba Girma. She is the PR department of the long well organised distraction machine of Weyane. She does not know what is unfolding before her. watcdh this space.

 2. Ancient Ethiopia Reply

  July 5, 2013 at 10:10 pm

  አስቸኳይ የንስሃ ጥሪ ለሁሉም!!!
  (ከዲያቆን አሸናፊ መኮንን)
  repentance
  July 5, 2013 12:46 am By Editor 1 Comment

  ከዛሬ ሠላሣ ሁለት ዓመት በፊት በአንድ ገዳም ውስጥ ይኖሩ የነበሩና ለ40 ዓመት የዘጉ አንድ ባሕታዊ ከዘጉበት ቤተ ጸሎት ወጥተው ለሕዝቡ ታዩ፡፡ ታይተው የማያውቁ እኚህ አባት ዛሬ መውጣታቸው ሕዝቡን አስደንግጦታል፡፡ ለሰንበት ቅዳሴ ለተሰበሰበው ሕዝብ እንዲህ በማለት ተናገሩ፡- “በሕልሜ ቤበ- መኩ- እፍ- ጸጉ የሚሉ ቃላትን ያሳየኛል፡፡ ተጨንቄአለሁና እባካችሁ ፍቱልኝ” አሉ፡፡ ሕዝቡም፡- “አባታችን እኛ ምኑን እናውቀዋለን? ለእርስዎ እንዳሳየ ይፍታልዎ እንጂ” አሏቸው፡፡ እርሳቸውም ሕልሙን ሲተረጕሙ፡-

  ቤበ – ማለት ቤተ ክርስቲያን በረት ሆነች ማለት ነው፡፡

  መኩ – መሥዋዕት ኩበት ሆነ ማለት ነው

  እፍ – ዕጣን ፍግ ሆነ ማለት ነው፡፡

  ጸጉ – ጸሎት ጉባዔ/ ታይታ/ ሆነ ማለት ነው በማለት ተረጎሙ፡፡

  ሕልምም ሆነ ትንቢት በፍጻሜው ይታወቃል፡፡ እኝህ አባት ያሳያቸው እውነት እንደሆነ ዛሬ እያየነው ነው፡፡ በረት ቆሻሻ የበዛበት፣ ንጽሕና የጎደለው፣ ሥነ ሥርዓት የሌለበት፣ የሕያው ነፍስ ሳይሆን የደመ ነፍስ /የእንስሳት/ መከማቻ፣ ነጻነት የማይሰጥ፣ በውስጡ የሚኖሩት የሕሊና፣ የሰብአዊና የመንፈሳዊ ሕግ የማያዛቸው፣ ዙሪያው የሚበርድ ክፍት የሆነ ስፍራ ነው፡፡ እኝህ አባት ቤተ ክርስቲያን በረት ሆነች ይለኛል አሉ፡፡ ንስሐን የመሰለ የሕይወት ውኃ የሚነገርባት ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮቿ ያልታጠቡባት፣ ንስሐን ተሸክመው ንስሐ የሚቀበሉባት፣ በዓለም የሌለ ነውር በእርስዋ የሚሰማባት፣ ቅድስና የራቃት፣ ሁሉም በፊቱ ደስ ያለውን የሚያደርግባት፣ የደፈረ የሚኖርባት፣ እንኳን መንፈሳዊነት ሰብአዊነት የማይሰማቸው አገልጋዮች የተሰበሰቡባት፣ ትሩፋት የሚሠራ አይደለም የታዘዘውን የሚፈጽም የታጣባት፣ ለሚያያቸው ዕረፍት የማይሰጡ ያልተገሩ ሠራተኞች የሞሉባት፣ ለእግዚአብሔርና ለአገር ሕግ የማይገዙ የተከማቹባት፣ ሲያስቧቸው ብርድ ብርድ የሚሉ ሥርዓት አልበኞች የነገሡባት ስፍራ ሆናለች፡፡

  መንፈሳዊት ተቋም የሆነችው ቤተ ክርስቲያን ከመንፈሳዊነት አቋም ወጥታ ድርጅታዊ ሥርዓትን እንኳ አለማግኘቷ ያሳዝናል፡፡ የሥርዓት መገኛ ሥርዓት ስታጣ፣ የፍርድ ሰባኪ ፍርድ የለሽ ስትሆን፣ የነፍሶች ሰብሳቢ በታኝ ስትሆን፣ የራእይ መውጫ ራእይ ሲጨልምባት፣ የነገሥታት መካሪ በነገሥታት ስትመከር፣ ለገዛ ሕገ መንግሥቷ ለመጽሐፍ ቅዱስ አልገዛ ስትል፣ የኃጥአን መጠጊያ ሳትሆን የኃጢአት መለማመጃ ስትሆን፣ መሪዋን ክርስቶስን ለመስማት እምቢ ስትል እያየን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በረት ሆነች ያሉት እኒያ አባት የታያቸው እውነት መሆኑን እያየን ነው፡፡

  በጸጋ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን በሕግ የምትከራከርና የምትካሰስ ስትሆን፣ ሁሉን ትተናል መስቀል ተሸክመናል የሚሉት አገልጋዮችዋ ሁሉን ይዘናል፣ መስቀል ጥለናል የሚሉ ቅምጥሎች ሲሆኑባት እያየን ነው፡፡ ዓለምን ሰልችተው የሚመጡ ምእመናን ዓለምን በቤተ ክርስቲያን ሲያገኙ፣ ቤተ ክርስቲያንም የዓለምን መመሪያ የምትፈልግ ስትሆን፣ እንደ ቃሉ ሳይሆን እንደ ዘመኑ ለመኖር ስታቅድ ማየት፣ የተጣሉትን የምታስታርቀው በገላጋይ ስትኖር፣ ዓለምን በቅድስና ውበቷ የምትማርከው በዓለም ስትማረክ ማየት ያሳዝናል፡፡ የትዕግሥት አምላክ በትዕግሥቱ ቤተ ክርስቲያንን እየጠበቃት ነው፡፡ ትዕግሥቱ ካልገባት በዓለም ፊት የምትቀጣበትና የውስጥ ልብስዋ ተገልጦ የምትገረፍበት ዘመን ቅርብ ነው፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በታላቅ ትዕግሥቱ እያያት ነው፡፡ እርሱ በፍርድ የተነሣ ቀን ግን በትሩ እስኪያልቅ ይቀጣታል፡፡uturn

  “የወፍ ዘፈን አውራጁ አይታወቅም” እንደሚባለው መደማመጥ የሌለባት፣ ሁሉም በየአቅጣጫው የሚዘፍንባት፣ ሕዝቡን እንደ ቅርጫ ከፋፍሎ የሚበላባት የጠላት ቤት ሆናለች፡፡ እኒያ ጭምት ልጆችዋ ከአደባባይዋ ርቀው፣ አመንዝሮችና ቀማኞች አለሁ አለሁ የሚሉባት፣ አንድ ሐሰተኛ ሲነቀል ሁለት የሚበቅልባት፣ በእውነት ቃል ሳይሆን በአፈ ጮሌነት የሚኖርባት … የእውነትን ሚዛን የጣለች ቤት ሆናለች፡፡ ለዚህ ሁሉ የሚቆጭ የለም፡፡ በክፋት ከመወዳደር በቀር የእግዚአብሔር ቤት ንጹሕ ይሁን ብሎ የሚቆረቆር ቢጠፋም ቤቱን የማይተው ጌታ ግን ይነሣል፡፡ ያልገመትነውንና ጆሮአችን ያልጠበቀውን ቍጣ እናያለን፣ እንሰማለን፡፡ ይህ ጊዜ የእግዚአብሔር የትዕግሥቱ ጥላ የተዘረጋበት ነው፡፡ የታጠፈ ቀን ግን የመዓቱን እሳት፣ የቍጣውን በረዶ አንችለውም፡፡ እግዚአብሔር መቀጣጫ እንድንሆን አድርጎ ይቀጣናል፡፡ እርሱ ከታሪካችን ርዝመት ጋር ጉዳይ የለውም፡፡ የዛሬን መታዘዛችንን ያያል፡፡ የማያምኑትን ከቀጣ አውቀው የሚያጠፉትንማ በደንብ ይቀጣል፡፡ ዛሬ የኮራንበት ካባ አልሠራንበትም ነገ እናፍርበታለን፡፡ እግዚአብሔር ከጣለን የሚያነሣን የለምና ዛሬ የምናከማቸው ሀብት አይረባንም፡፡ እግዚአብሔር ምንም ቢሆን ጥሎ አይጥለንም ብለን በባዶ የኮራንበት ቃልም አይጠልለንም፡፡ እርሱ እግዚአብሔር የሚያከብሩትን የሚያከብር፣ የናቁትን የሚንቅ ነው /1ሳሙ. 2፡30/፡፡ እንኳን እኛን እስራኤልን የጣላቸው ባለመታዘዝ ነው፡፡ ኃጢአት ትንቢት የተነገረለትን፣ ሱባዔ የተቆጠረለትን የሰሎሞንን መቅደስ አፍርሷል፡፡

  ታዲያ ጥሎ አይጥለንም እንዴት ማለት እንችላለን? የኮራንበት የጦር መሣሪያም አያድነንም፡፡ እንኳን የእኛ መሣሪያ ኒውክለር የታጠቁም ከቍጣ አያመልጡም፡፡ ታላቅ ሕዝብ ነህ እያልን አመንዝራውንና ነፍሰ ገዳዩን ተከታያችንን አድንቀናል፡፡ ያው ሕዝብ ግን ይበላናል፡፡ ያላስተማርነው ሕዝብ ጠላት መሆኑን የምናይበት ዘመን ቀርቦአል፡፡ የማይሞላው ከረጢታችን ዘላለማዊ እሳት ይበላዋል፡፡ የመበለቶችን ቤት የዘረፍንበት፣ ወጣቶችን ያስነወርንበት፣ የድሆች ልጆችን ጉሮሮ የዘጋንበት፣ በመማፀኛ ዘመን ወገናችንን አውጥተን የጣልንበት፣ በወገናችን ሞት የተሠረግንበት፣ በጭንቁ የሳቅንበት፣ ትዳርን ያፋታንበት፣ እስቲ ይህን ሕዝብ ልጩህበት ያልንበት፣ እንደ አማልክት ውዳሴና ስግደት የተቀበልንበት፣ እግዚአብሔር ካለ ይህን ያድርግ ያልንበት፣ ወገንና ወገን ሲተላለቅ እንደሌለ ሆነን የተቀመጥንበት፣ ንጹሐንን የገደልንበት፣ ወንጌልን የገፋንበት፣ እውነትን የቀበርንበት … ያ የእርም ጽዋችን ሞልቷልና እግዚአብሔር ይነቅለናል፡፡ ቍጥቋጦ ሳይቀረን ከሥራችን ይፈነቅለናል፡፡ ያን ቀን የቀድሞ ወዳጆቻችንን እንፈልጋለን፡፡ እነርሱ ግን ከጠላት ይልቅ ይከፉብናል፡፡ ያን ቀን ያጠራቀምነውን ገንዘብ እንፈልጋለን፡፡ ለአንድ ቀን መታከሚያም አይሆነንም፡፡ ያን ቀን ወንጌል የቱ ነው? አሁንም ሰብከን እንብላ እንላለን፣ ጆሮ ግን ይከዳናል፡፡ ያን ቀን መንግሥት እንኳ ጥግ ይሁነን እንላለን፣ እንደ አጸያፊ ቆሻሻም እንጣላለን፡፡ ያን ቀን ሠርጋችንን አጅቡት እንላለን፣ የልቅሶ ያህል አይደምቅም፡፡ ያን ቀን ማዘዝ እንፈልጋለን ቃላችን ግን ይቀላል፡፡ ዛሬ ያለነው የመጨረሻው መጀመሪያ ላይ ነን፡፡ አስማት ጥንቆላችን፣ ብዙዎችን ያሳበድንበት መተታችን ያለ ያዢ አብደን በአደባባይ ያሽከረክረናል፡፡ የሚያዝንልን አጥተን ያለ ታዛቢ እንቀራለን፡፡ ይህ አገልጋዮች ነን ለሚሉ ሁሉ የተደገሰ ድግስ ነው፡፡ ንስሐ በማይገቡት ላይ እግዚአብሔር ይህን መዓት ያፈስሳል፡፡ ትዕግሥቱ ይህ ሁሉ እንዳይመጣ ነበር፡፡ የትዕግሥቱ ምሥጢር ካልገባን የመዓቱን ሰይፍ እንጎርሳለን፡፡ እፈራለሁ ከቀድሞ ይልቅ ዛሬ እፈራለሁ፡፡ እግዚአብሔር ትዕግሥቱን ሲያሰፋ ይበልጥ እፈራለሁ፡፡ ካልተመለስን ጥበብ፣ ጉልበትና ሀብት የማያልፋት ብርቱ ቀን መጥታብናለች፡፡

  የጠፋው እረኛ ብቻ አይደለም በግም ጠፍቷል፡፡ የምንመራው በአብዛኛው በግ መሳይ ነው፡፡ ሲሰክር አድሮ ጠዋት ጠበል የሚጠጣ፣ ሲያመነዝር አንግቶ ማለዳ ቅዳሴ የሚገኝ፣ ለሃይማኖቴ እገድላለሁ የሚል ለሃይማኖቱ ግን የማይሞት፣ ለእምነቱ የማይኖርላት ግን ሲሳደብላት የሚወል፣ ቅበላና ፋሲካን በኃጢአት የሚፈጽም ጾመኛ መሳይ፣ በመድረክ ሳይሆን በሕይወቱ ድራማ የሚሠራ፣ ከዘረፈው ላይ ዓሥራት የሚያወጣ፣ ቆርቦ የሚያብድ፣ አምኖ የማያምን፣ ሠራተኞቹን እያስጨነቀ ቀሳውስትን የሚቀልብ፣ ድንበር እየገፋ አቤት አቤት እያለ የሚጸልይ፣ ጋራ ጋራውን ጠንቋይ ፍለጋ ሲያስስ አድሮ ጠዋት ለኪዳን የሚደርስ፣ እጁ በደም ተጨማልቆ ቤተ ክርስቲያን የሚያንፅ፣ የንስሐ ስብከት የሚወድ ንስሐን ግን የማይወድ፣ ሰባኪ ቀላቢ ወንጌል ተቃዋሚ፣ ለስድብ አጨብጫቢ ለእውነት አጉረምራሚ፣ ሕይወት ሲነገር የሚያንቀላፋ የሰው ነውር ሲወራ የሚነቃ፣ በለው የሚል ድምፅ የሚፈልግ ጦረኛ፣ ማንበብ የማይወድ የነገሩትን ብቻ የሚሰማ፣ እስኪሞላለት የቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ከሞላለት በኋላ ኵሩ፣ ዛሬን ለመርካት ስበኩኝ የሚል ዘላቂ ሕይወትን የማይሻ፣ ከእግዚአብሔር ርቆ አገልጋይ በመወዳጀት እድናለሁ የሚል፣ የመንገዱን ካርታ ጥሎ የሚንከራተት፣ ተረኛ ብልጥ እንደ ዘረፈው የሚኖር፣ ታላቅ ሕዝብ እያሉ የሚያሳንሱትን አወዳሾች የሚሸልም፣ ተመለስ ያለውን የሚወግር፣ እውነተኞችን ጥላሸት የሚቀባ፣ የአሉ ተከታይ የወሬ አንጋሽ፣ ከነሕመሙ ቤተ ክርስቲያን መጥቶ ከነሕመሙ የሚመለስ፣ የዋህ ሳይሆን ሞኝ የሆነ አማኒ ይዘናል፡፡ ይህ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በየአብያተ ክርስቲያናቱ እየፈላ ያለ ሞገደኛ ወገን ነው፡፡ ንስሐ ካልገባ ይህ ወገን ብርቱ ቅጣት ይጠብቀዋል፡፡ መከራን እንደተለማመደ የሚኖር፣ አሁን ያለው መከራ ሳይደንቀው የሚመጣውን መከራ የሚናፍቅ ደንዳና ሕዝብ ይዘናል፡፡ የትዕግሥት አምላክ ዝም ያለን ሥራችን ተስማምቶት አይደለም፡፡ ለንስሐ ጊዜ እየሰጠን ነው፡፡ ራሳችንን የምናይበት ቍርጥ ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡ ስለዚህ ንስሐ እንግባ፡፡

  በዓመት ውስጥ ባሉት ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀናት ጸሎት፣ አገልግሎት እንፈጽማለን፡፡ ይህ በሌላው ዓለም የሌለ የታደልነው ሀብት ነው፡፡ ነገር ግን ፍቅር የሌለው ጸሎት፣ ቅድስና የሌለበት ቅዳሴ፣ መታዘዝ የሌለበት አገልግሎት ስለሆነ ይሄው አልተባረክንም፡፡ ተገልጋዩ ግዳጅን ለመፈጸም ያህል ወደ ቤተ ክርስቲያን ይመጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የናፍቆት ፍቅር የለውም፡፡ አገልጋዩ ለእንጀራ ይጮኻል፡፡ ከሚሰማው አምላክ ጋር አይነጋገርም፡፡ ልማድ እንዳይቀር ስለምናደርገው ጸልየን ለምን መልስ አጣን? ጾመን ለምን አልተባረክንም? ቀድሰን ለምን ጸጋ አልፈሰሰልንም? አገልግለን ለምን አላፈራንም? ብለን ራሳችንን ለመጠየቅ ጊዜ የለንም፡፡ ግን የተለመደው እንዳይቋረጥ ሕይወት የሌለውን ሥነ ሥርዓት፣ ቅዱስ ፍርሃት የሌለበትን ጸሎት፣ ተመስጦ የሌለበትን ዜማ፣ መገዛት የሌለበትን ቅኔ እናቀርባለን፡፡ ከሚሰማን አምላክ ጋር እየተነጋገርን መልስ አጥተን ዘመናት አልፈዋል፡፡

  እግዚአብሔር ከመሥዋዕት በፊት መታዘዝን ይፈልጋል፡፡ የእኛ የሆነውን ከመስጠታችን በፊት ራሳችንን እንድንሰጠው፣ ከአገልግሎት በፊት እንድናውቀው ይሻል፡፡ እኛ ግን ኑሮአችን ይዞታ ማስከበር እንጂ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ መናኘት አይደለም፡፡ ሕዝቡን ባለማወቅ መጋረጃ ጋርደን መፍረድ የምንፈልግ ቃልቻዎች እንጂ ሰብከን የምንለውጥ አገልጋዮች አልሆንም፡፡ ሕዝቡም ጧፍና ዕጣኑን አምጥቷል እርሱ ግን አልመጣም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ደጃፍም ያዘነውንና የተከፋውን ለመቀበል ሳይሆን ብርና ወርቅ ለመቀበል ተከፍተዋል፡፡ ጴጥሮስ ብርና ወርቅ የለኝም ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ ብሎ ሽባውን ፈወሰ /የሐዋ. 3፡6/፡፡ ዛሬ ግን ቤተ ክርስቲያን ብርና ወርቅ የለኝም አትልም፡፡ ግን የሥጋና የነፍስ በሽተኞች አይፈወሱም፡፡

  እየዘመርን እንሰዳደባለን፣ ተጣልተን እንቆርባለን፣ ለወንድማችን ጉድጓድ እየቆፈርን አቤት አቤት እንላለን፡፡ እግዚአብሔር አዝኖብናል፡፡ እርሱን የሰው ያህል እንኳ ስላላከበርነው፣ ቤቱንም የቤታችንን ያህል እንኳ ስላላከበርን እግዚአብሔር ተቀይሞናል፡፡ ዛሬ የመዓቱን ሰይፍ በቁጣው ሰገባ ስለተያዘልን እንዝናናለን፡፡ ሰይፉ የተመዘዘ ቀን ግን የደሙ ምልክት እንጂ ገንዘባችን አያድነንም፡፡ እያደረግን ያለነው እግዚአብሔር ከቻለ ይፍረድብን የሚል ድፍረት ነው፡፡ ግን መከራውን ባንጎትተውም ሊወርድ ነው፡፡

  እምነታችንን የያዝነው ለፉክክር እንጂ ለሕይወት አይደለም፡፡ ሌሎች ሲሰብኩ እንሰብካለን፣ ካልነኩን በእንቅልፋችን ራሳችን እንሞታለን፡፡ ሲነኩን በወንድነት ሃይማኖትን ለማስከበር እንነሣለን፡፡ “የእንጦጦ መምህር ቢናገር ባመት፣ ያውም እሬት” እንዲሉ፡፡ በንጹሕ ልብ መጸለይ አልሆነልንም፡፡ አገር ለአገር በመዞር እግዚአብሔርን የምናገኘው ይመስለናል፡፡ እርሱ ግን በንጹሕ ልብ እንጂ በፈጣን እግሮች የሚገኝ አይደለም፡፡ ጸሎታችንም ጉባዔ ወይም ለታይታ እንጂ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት አይደለም፡፡ ድንጋይ ውርወራ ስንጀምር፡- “ኃይል የእግዚአብሔር ነው” በሚል ዝማሬ በመሆኑ ምን ያህል እንደማናስተውል ይታያል፡፡ በእውነት የምናምነው ኃይል የእግዚአብሔር ነው ብለን ነው? ታዲያ ዓመፁ ከየት መጣ? “የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል” /2ጢሞ. 3፡5/ የሚለው ቃል ደርሶብናል፡፡ ስብከቱ፣ ዝማሬው ቢበዛም የእኛ ደንዳናነት ግን አልተፈረካከሰም፡፡ እዩኝ እዩኝ የሚል ክርስትና እንጂ የሚታይ ክርስትና የለንም፡፡ በሕይወታችን ነውር የሸሹንን በስብከታችን ለመመለስ የምንጥር ሞኞች ነን፡፡ ስብከት ሲጠፋን እንሳደባለን፡፡ የተጨነቀውን ሕዝብ በማስፈራራት እንዘርፋለን፡፡ የጠላነውን ሰው ታርጋ ሰጥተን ቅንዓታችንን የሃይማኖት ካባ እናለብሰዋለን፡፡ ቁመናችንን እንጂ የክርስቶስን መልክ ልናሳይ አልቻልንም፡፡ የልብሳችን ሽቱ እንጂ የሕይወታችን መዓዛ ሊያውድ አልቻለም፡፡ አጥንተን እንጂ ኖረን መናገር አልሆነልንም፡፡ ለምንዝርናችን ድንበር ብናሳጣውም የእግዚአብሔር ቁጣ ግን ሊገድበው ነውና ፈጥነን ንስሐ እንግባ፡፡ በዘርፋፋው ቀሚሳችን ሳይሆን በተትረፈረፈው ክርስትናችን፣ በነጭ ነጠላችን ሳይሆን በነጭ ልባችን የትዕግሥትን አምላክ ደስ እናሰኘው፡፡ ቃሉ፡- “እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ ነው ኃይለኛም ታጋሽም ነው፤ ሁልጊዜም አይቆጣም፡፡ ባትመለሱ ግን ሰይፉን ይስላል” /መዝ. 7፡11-12/ ይለናል፡፡ ትዕግሥቱ ለንስሐ ነው፡፡ ንስሐ መግባት እስከ ዛሬ ለታገሠው ትዕግሥቱ ክብር መስጠት ነው፡፡

  እግዚአብሔር የንስሐና የፍቅርን መንፈስ ያድለን!

 3. Gobeze Reply

  July 5, 2013 at 5:52 pm

  It is very uplifting the letter posted on this cite ,most people who stand behind the truth they don’t right the fact just like you did.I will thank you wondemu mekonen this is the kind of truth should be out quite often we give this corrupted pappas(archbishop )and priest so much trust and respect they start to count them self like almighty god. what make the situation worse the those who can read understand the truth and challenge them they will accuse those who demand there members right as politician,in case you don’t know where you are this is G.B. where peoples right respected god given us our right not aba Girma(Girum) or Abune Entose.

 4. Senayet Kasa Reply

  July 5, 2013 at 3:28 pm

  ዶ/ር ወንድሙ መኮንን ድሮም እውነተኛና ለእውነት ሲል ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለ ሃቀኛ የኢትዮጵያ ልጅ ነው።

  ራሱን Tom Kebede ብሎ የጠራው ሰው “ወጣቶቹ የወያኔ የሚል ታቤላ ተሰጣቸው” የሚል አስተያየት ሰጥቷል።

  1. አባ ግርማ ከነተከታዮቻቸው ቤተ ክርስቲያኗን ከስደተኛው ሕዝብ ነጥቀው ለወያኔ ለማስረከብና በባለውለታነት ለመሾምና ለመሸለም ሲሉ በጠራራ ፀሐይ ሰው እያያቸው ነው ወያኔ ኤምባሲ የሄዱት።

  2. ቀጥሎም ኤምባሲው ተቀብሎ ወያኔ ከራሱ ጎሳ መርጦ በሾማቸው ሰዎች ወደሚመራው የአውሮፓ ሃገረ ስብከት ላካቸው።

  3. አባ ግርማ እና ተከታዮቻቸው የትግራይ ተወላጆች ከሌሎች ኢትዮጵያኖች ተገንጥለው ባቋቋሙት ከሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አመራሮች ጋር በመተባበር በዚሁ በሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌላውን ስደተኛ የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረጽዮን ቤተ ክርስቲያን አባላት በማግለል ደጋፊዎቻቸውንና የወያኔ ሥርት ደጋፊ የሆኑ የሌላ ቤተ ክርስቲያን አባለትን በመሰብሰብ ለዚሁ ተግባር ተብሎ ከኢትዮጵያ በመጡት በሁለት ሊቃነ ጳጳሳት ፊት ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረጽዮን ከአሁን በኋላ ወያኔ በአቋቋመው ሃገረ ስብከት ስር መሆኗን ካህናቱ ሁሉ በፊርማቸው ስላረጋገጡ በማለት የተገኘውን ሕዝብ በማስጨብጨብ ቤተ ክርስቲያኗን በጓዳ በር ለወያኔ አስረከቡ።

  4. ከዚህ በመቀጠልም ከአሁን በፊት ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በአባ ጳውሎስ ላይ እና በመንበረ ፓትርያርኩ ላይ የወሰደችውን አቋምና እንደ ቤተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን በመቆም ለሰው ልጆች መብት መከበርና ለፍትሕ ያደረገችውን ጩከት በሙሉ እንደ ጥፋት በመቁጠር አባ ግርማ ከበደ የማይወክሉትን ስደተኛውን የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እባላት እወክለዋለሁ በማለት በወያኔዎቹ መሪዎች ፊት ይቅርታ ጠየቁ።

  5. ይህንን ሁሉ ካደረጉ በኋላ የአገልግሎት ዘመናቸው ካለቀ 4 ዓመት ቢሞላቸውም የምእመናኑ ተመራጮች በገዛ ፍቃዳቸው ሥራቸውን ሲለቁ አባ ግርማ ከበደ፤ ቄስ ዳዊት አበበና ቄስ አባተ ጎበና የተባሉት ግን ካልሞትን በስተቀር የተመረጥንበትን የአስተዳደር ሥልጣን አለቅም ብለው የሙጥኝ በማለት ሥራቸውን በፍቃዳቸው በለቀቁት 4 ምዕመናን ምትክ 4 የነሱ ደጋፊዎች የሆኑ ሌሎች ምእማናንን በምርጫ ሳይሆን የወያኔው ሹማምንቶች እንዲሾሙላቸው በማድረግ በያዙት የአስተዳደር ሥልጣን ላይ እስከመጨረሻው ለመቆየት ሞከሩ።

  6. ይህ ደባና ተንኮል የሚፈጸምበት በሺህ የሚቆጠርውና ለወያኔ ባለማደር መብቴን ይከበርልኝ የሚለው ስደተኛው ኢትዮጵያዊ የቤተ ክርስቲያኗ አባል፤ በቁጣ በመነሳት በጎን በሸጡትና በተደራደሩበት ላይ በቁጣ በመነሳት ቁጣውን በሰላማዊ መንገድ ገለጸ።

  ተበዳዩ አዛውንት፤ ወጣት ጎልማሳ፤ ወንድና ሴት የማይል እንጂ አዛውንትን የሚመለከትና ወጣቶችን የሚያገል አይደለም።

  7. ይህ የሕዝብ ቁጣ በተነሳ በሳምንቱ አባ ግርማ ከበደ ከወያኔ ሃገረስብከትና ከወያኔ ልዩ ልዩ ተቋሞች ጋር በማበር በከተማ ውስጥ ያሉ ወጣቶችን በጎሳ ፓለቲካ የተመለመሉ ሰዎች እንዲያደራጇቸው በማድረግ፤ የዕለት የውሎ አበል በመክፈልና፤ አበሻ ምግብ ቤት ወስዶ በመጋበዝ አንዳንዶቹን ደግሞ ፍጹም ሃሰት በሆነ ወሬ በመቀስቀስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ መጥተው ተበዳዩን ስደተኛ እንዲያጠቁ አሰለፏቸው።
  የቤተ ክርስቲያኗ አባላት የሆኑ ለወያኔ ያላደሩና እውነተኛ ስደተኛ የሆኑ ኢትዮጵያን ወጣቶች በቁጥርም ሆነ በማንኛቸውም ረገድ የወያኔ ቅጥረኛ ሆነው ከመጡት ወጣቶች የሚበልጡና የላቁ ስለነበሩ በአባ ግርማ ዕቅድ መሠረት እነዚህ የቤተ ክርስቲያንን ደጃፍ ረግጠው የማያውቁና ኢትዮጵያዊም ሆነ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር የጎደላቸው ሰዎች በስደት ሃገር ሃይማኖታቸውንና ቤተ ክርስቲያናቸውን ለ40 ዓመታት ጠብቀው ያኖሩ ክርስቲያኖችን ከጸሎታቸው ሊያስተጓጉሏቸውም ሆነ ሊተናኮሏቸው ሳይችሉ ቀርተዋል።

 5. Wondimu Mekonnen Reply

  July 5, 2013 at 12:32 pm

  zienamarqos and DASSENNECH

  በመጀመሪያ ደረጃ EDADFን ከልቤ ማመስገን እወዳለሁ። ጽሑፉን፣ ጊዜ ወስደው፣ ትምህርት ሰጪነቱን ተረድተው በማውጣታቸው።
  ቀጥሎ፣ ሁለታችሁን ስለበጎው አስተያየታችሁ፣ አመሰግናለሁ። አንድ ዘመዴ DASSENNECH ለማስረዳት የምሞክረው፣ እኛ ዩኬ ውስጥ የምንኖረው ኢትዮጵያውያን የምንሻኮተው እርስ-በርስ ስለሚመስላቸው፣ አንዳንዴ መሀል ገብተው ከመከላከል ባሻገር ብዙ አያደርጉም። ከኛ የበለጠ፣ “ተበደልን” እያሉ የሚጮኹ እነሱ ስለሆኑ፣ በቁጥርም አነስ ስለሚሉ፣ ተንኰላቸውን ሊረዳልን አልቻለም። እርግጥ ውሪ ጋንግስተሮቹ ነገር ፍለጋ እንደሚመጡ ፖሊሶች ተረድተዋል። በሕግ መብታችንን ለማስከበር የማናደርገው ነገር የለም። ሕግ ግን ጊዜ እየፈጀ ነው። እነሱ በወያኔ ሶልዲ ይኖራሉ፣ እኛ ግን ጥረን፣ ግረን ስለሆነ፣ የግንዘብም ዕጦት ስላለብን፣ በሕጉ በኵል እየተጓተተብን ነው። ግን ግፍን በማይወድ ብእግዚአብሔር ኃይል እንደምናሸንፍ፣ ለደቂቃ እንኳን አንጠራጠርም። እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነው። ባላችሁበት ግን፣ ስለኛ ስለወንድሞቻችሁን እህቶቻችሁ ከመጸለይ አትቦዝኑ። እግዚአብሔርን ፍርዱን ቶሎ እንዲሰጠን ተማጠኑልን። ተገፍተናል። ተገፍተረናል። ከቤተክርስቲያናችን ወጥተን ሜዳ ላይ ተጥለናል። ጸልዩልን።

  Tom Kebede

  ወዳጄ ልቤ። እዚያ ጽሑፍ ውስጥ፣ ቁም-ነገር ሞልቶበት እንዳለ ሁሉ፣ ብዙ ቀልዶች አሉበት። ጽሑፉ ረዥም ነው። እንዲያስተምርም ነው። አልተማሪ መሆኔ ሪሰርች አድርገህ ለዓለም አጋልጠኻል። ታዲያ እንዴት እንደማስተምር ማወቅ ከፈለግክ፣ ናና አንድ ቀን ሌክቸሬን ተካፈል። ተማሪዎቼን ጠጣር ጭብጥ ካሳየሁአቸው በኋላ፣ ትንሽ ዕርፍት እንዲያገኙ፣ ነገሮችን ዞር አድርጌ በሳቅ አፈነዳቸዋለሁ። ድካማቸው ያልፍና እንደገና ወደ ቁም-ነገሩ እወስዳቸዋለሁ። በዚህ ዘዴዬ የመጨረሻው ደካም መጥቶ ከጎበዞቹ ጋር ይስተካከላል። ይኸ የኔ ከባድ ጽንሰ-ሀሳቦችን ወደቤት መሰብሰቢያ ዘዴ ነው። አሁን አንተ ያንን እንደ ማረፊያ መዝናኛ አድረግህ መውሰድ ነበረብህ። የተንኰለኛው ግሩም ከበደ ተከታይ ከሆንክ፣ ነገሩን አትቀበለውም። አየህ፣ አንተ ስታነበው፣ ከመጀመሪያውም ስህተት ፍለጋ ስለሆነ፣ ስትማር እንዲሁ እንደተዳፈነብህ ትቀራለህ። እኔ ልምከርህ። እኔ የጻፍኩትን ድባቅ ለመምታት ከፈለግክ፣ ይኸን “ነፍስ አባቱ ነበርኩ። ቤቱ ሂጄ ጸብል ረጭቼ ነበር” እያሉ ግሩም የሚያሞኙሕን ነገር እርግፍ አድርገህ ተወውና፣ መጽሐፉ የሚለውን የት ጋ እንዳጣመምኩ፣ ዕውነትን የት ጋር እንደሸውድኳት ለማስረዳት አንገትህን መጻሕፍት ውስጥ ቅበርና አንብብህ ተረዳ። “ይኸ ጸበል ረጨኹ፣ ስለዚህ የኔን ከሴቶች ጋር መዳራትን መናገር አልነበረበትም” የሚሉህን ተወው። እሱ አለፈ። “አባባሱባት” በሚልው ጽሑፌ የሚገባቸውን ክብር ሰጥቼአቸዋለሁ። ያኔ አውቀው ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነበረባቸው። አልሰሙም። ዕድሜ ላንተ፣ “ንጉሱን የገደሉ፣ ፓትርያርኩን የገደሉ …” እያሉ ሲያላዝኑ ቀድተህ አሰማኸን። በዕውነቱ ውለታ ውለኽልናል። ስም ብትቀይርም፣ ሰዎች ደውለው “Endexiye“ ቶም በሚለው ስሙ ጽፏል ብለው ስለነገሩኝ ነው፣ ላመሰግንኽ የመጣኹት። አብዛኛውን የገኘኹትን ካንተው ይ-ትዩብና ከፌስ ቡክ ነው። በመጀመሪያ ገመናችሁን ደብቁና ከዚያ በኋላ፣ “ሌባ ማለት” ይቀላችሁአል።

  You seem to be very angry. Calm down Tom Kebede. May I invite you to listen to the following Girum’s spiritual song.

  http://www.youtube.com/watch?v=7u0x0rMksXQ

  አመሰግናለሁ

 6. zienamarqos Reply

  July 5, 2013 at 5:18 am

  ወንድሙ፡መኮንን፡የሚያውቁትን፡እና፡እያዩት፡ያልለውን፡ጽፈው፡እንድናውቀው፡በማድረግ፡ላይ፡ናቸው።
  ሁኔታውን፡አገናዝበን፡በመረዳት፡ፈንታ፣አትጻፍ፡ብለን፡የምናወግዛቸው፡ሰወች፡መጠንቀቅ፡ይኖርብብናል።
  ”ቆማጣን፡ቆማጣ፡ካላሉት፡ከመሃል፡ገብቶ፡ይፈተፍታል”፡ነውና፡ለሃያ፡ሁለት፡ዓመታት፡ገብረ፡መድኅንም፡
  አበሻቅጠውት፡እግዚአብሔር፡ገላገለን።ገብረ፡መድኅንም፡የወጣላቸው፡አመንዝራ፡ስለ፡ነበሩ፡ካናዳ፡ልጅ፡አልላቸው።
  ስለዚህ፣የሚጻፍልንን፡እየተከታተልን፡የእግዚአብሔርን፡ፍርድ፡በመጠበቅ፡ከማጋለጥ፡የማይቆጠቡትን፡ወገኖች፡እናመስግን።
  አለበለዚያ፡አትጻፍ፡የምትሉት፡የከዳተኞች፡አረመኔ፡ወያኔዎች፡ሰላይና፡አጫፋሮዎች፡መሆናችሁን፡ታስመሰክራላችሁ።

 7. zienamarqos Reply

  July 5, 2013 at 5:01 am

  ወንድሙ፡መኮንን፡የሚውቁትን፡እና፡እያዩት፡ያልለውን፡ጽፈው፡እንድናውቀው፡በማድረግ፡ላይ፡ናቸው።ሁኔታውን፡አገናዝበን፡በመረዳት፡ፈንታ፣አትጻፍ፡ብለን፡የምናወግዛቸው፡ሰወች፡መጠንቀቅ፡ይኖርብብናል።”ቆማጣን፡ቆማጣ፡ካላሉት፡ከመሃል፡ገብቶ፡ይፈተፍታል”፡ነውና፡ለሃያ፡ሁለት፡ዓመታት፡ገብረ፡መድኅንም፡አበሻቅጠውት፡እግዚአብሔር፡ገላገለን።ገብረ፡መድኅንም፡የወጣላቸው፡አመንዝራ፡ስለ፡ነበሩ፡ካናዳ፡ልጅ፡አልላቸው።ስለዚህ፣የሚጻፍልንን፡እየተከታተልን፡የእግዚአብሔርን፡ፍርድ፡በመጠበቅ፡ከማጋለጥ፡የማይቆጠቡትን፡ወገኖች፡እናመስግን።አለበለዚያ፡አትጻፍ፡የምትሉት፡የከዳተኞች፡አረመኔ፡ወያኔዎች፡ሰላይና፡አጫፋሮዎች፡መሆናችሁን፡ታስመሰክራላችሁ።

 8. Tom Kebede Reply

  July 4, 2013 at 10:02 pm

  ውድ አንባቢያን እንደው በዚህ ዘመን አንደርቢ አባ ግርማ ላይ እንቁላል ወረወረ እንጂ እኛ አልወረወርንም ብሎ የሚጽፍ ለዛውም አቶ ወንድሙ መኮንን ተምሪያለው የሚል ዩንቨርስቲ የሚያስተምር ግለሰብ ይህን ሲል ምን ያክል ስሜታዊ እንደሆነና እኚ ከፍ ዝቅ እያደረገ የሚሰድባቸው አባት ላለፈው 12ዓመታት የነፍስ አባቱ የነበሩ ቤቱንና ቤተስብን በጸበል ሲባርኩና በጸሎታቸው ሲያስቡት የነበሩ አባት ናቸው፤ መቼም ከንደዚህ ያለ ጥላቻ እንደዚሁም የፈለኩት ካልሆነ ማንም ምንም ይባል ስም ከማጥፋት አልቆጠብም ብሎ ታጥቆ መነሳት ለአገር አሳቢነት ሳይሆን አገርን ማጥፋት ለወደፊቱ የጻአፊውን ታማኝነት ማሳጣት ነው፤ እስቲ ስለድግምት የተዋሸውን ውሸት ላስነብባችው “የእግዚአብሔር ቁጣ ነደደባቸው። ከየት እንደመጣ፣ ማን እንደሚወረውረው የማይታወⷅ (አንደረቢ-poltergeist የሚሉት ነገር ይሆን?) የዕንቁላል መዓት አባ ተባዩ አጭበርባሪ ግለሰብ አናት ላይ ይፈጠፍጥ ገባ። አሁንም ቢሆን
  አንድም እኔ ወረወርኩ የሚል ሰው አልተገኘም። እንቁላሉ ብቻ ዥው እያለ ሂዶ እራሳቸው ላይ ቷ ሲል ይታያል፣ ይሰማል! ቆባቸው ከላያቸው ላይ በረረችና ሂዳ ግንብ ሥር ተወተፈች! ይግርማል! ያ ሁሉ እንቁላል ሲወረወር አንድ እንኳን ስቶ ሊያተርፏቸው የሚሯሯጡትን ፖሊሶች አልነካም፣ “አባ” ተባዩን አሽትቶ ሂዶ ብቻ “ዷ!”። በሪሞት ኮንትሮል ከላይ የሚመራው(ጋይድ የሚያደርገው ሚሳየል) ተቀምጧል መሰለኝ። ተአምር ነው። ከየትም ትወርወረ ከየት፣ “አባ” ተባዩን እራስ የሳተ የለም ።

 9. DASSENNECH Reply

  July 4, 2013 at 2:20 pm

  ዶ/ር ወንድሙ፡

  ስለዚህ ነገር እንኳ አስተያየት መስጠት አልፈለኩም ነበር ግን ነገሩ በዛ፤ ተደጋገመ፤ መጠንም አለፈ፡
  ግራ የገባኝ ነገር ግን ይህ ሁሉ ምዕመን ያውም ህግና ስርዓት ባለበት አገር እንዴት እንደዚህ ሊጉላላ ቻለ? ቤተክርስቲያን ረግጠው የማያውቁ ጋንግስተሮችሽ ህዝቡን ሲገፈትሩና ሲያጎሳቁሉ እንዴት ዝም ተባሉ? ህጉም ጉልበቱም የወያኔ ነው ማለት ነው?
  ያህያ ባል ከጅብ አያስጥል እንዳይሆን እሰጋለሁ፡
  “ሃይልን በሚሰጠኝ በእግዚአብሄር ሁሉን እችላለሁ” የሚለው መለኮታዊ ቃል፡ በእግዚአብሄር እርዳታ ጠላቴንም አሸንፋለሁ፤ ችግሬንም ሁሉ ባሸናፊነት እወጣለሁ ማለት እንጂ፤ የሚደርስብኝን መከራ፡ የሚደርስብኝን መዋረድ፤ በገረፍ፤ መበደል፤ መጎሳቆል፤ መገፍተር፤ መንገላታት ሁሉ እሸከማለሁ፤ እታገሳለሁ ወይም እችላለሁ ማለት አደለም፤ ለንደኖች ግን ይህን የመረጣችሁ ይመስላል፡
  Freedom comes with a price including right to practice religion

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>