የህማማት ማሰታወሻ ‹‹ህዝቤን ልቀቅ!›› እስክንድር ነጋን ልቀቅ!…

April 30, 2013

ተመስገን ደሳለኝ

ይህ ሳምንት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ‹‹ሰሞነ ህማማት›› ተብሎ በፀሎትና በስግደት ይከበራል፡፡ ይህ የሆነው ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ በሀሰት ተወንጅሎ ለስቅላት ተላልፎ የተሰጠበት፣ በሰው ልጅ ከሚደርስ ስቃይ፣ መከራና ግርፋት ሁሉ የከፋውን የተቀበለበት ሳምንት በመሆኑ ነው፡፡

…የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የኦርቶዶክስ ክርስትና ሀይማኖት ጥብቅ አማኝ ነው፤ የሀይማኖቱን ትእዛዛቶች በጥብቅ ያከብራል፤ ሁሉንም አፅዋማትም ይፆማል፡፡ ዛሬ በግፍ ታስሮ በሚገኝበት የቃሊቲ ወህኒም ሆኖ እንኳ የኩዳዴን ፆም ከመፆም አልሰነፈም (በነገራችን ላይ እስክንድር የሚገኝበት ‹‹ዞን ሶስት›› ፈርሶ እንደገና ሊሰራ ስለሆነ እስረኞቹ ወደሌላ ቦታ ሊዘዋወሩ እንደሆነ ተነግሯቸዋል)
እስክንድር የተወለደው ጥቅምት 27 ነው፡፡ ይህ ዕለት ደግሞ ለእምነቱ ተከታዮች የ‹‹መድሐኒያለም ዕለት›› እየተባለ የሚከበረበት ቀን ነው፡፡ እርሱም ቢሆን ምንጊዜም ጠዋት ወይም ማታ ከስድስት ኪሎ ዩንቨርስቲ ከፍ ብሎ በሚገኘው ‹‹ምስኪያዙና መድሐኒያለም ቤተ-ክርስቲያ››ን የፈለገ አያጣውም፡፡የህማማት ማሰታወሻ ‹‹ህዝቤን ልቀቅ!›› እስክንድር ነጋን ልቀቅ!...

…የፊታችን ሀሙስ (ሚያዚያ 24 ቀን 2005 ዓ.ም) የእስክንድር ነጋ ይግባኝ ‹‹ለመጨረሻ ጊዜ›› ተብሎ ተቀጥሯል፡፡ ዕለቱ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ‹‹ፀሎተ ሀሙስ›› ታስቦ የሚውልበት ቀን ነው (አይሁዳውያን ኢየሱስ ክርስቶስን አሳልፈው ሰጥተው ሲያበቁ ስለሁከት፣ ስለመግደል በወሀኒ ታስሮ የነበረውን በርባንን ‹‹ፍታልን!›› ያሉበትን እና የሐዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በትህትና ያጠበበትን ለማስታወስ ነው ቀኑ ‹‹ፀሎተ-ሀሙስ›› ተብሎ የተሰየመው)

…በድህረ ምርጫ 97 ለእስር ከተዳረጉ ጋዜጠኞች መካከል እስክንድር ነጋ አንዱ ነበር፡፡ የተፈታውም በ‹‹ይቅርታ›› ሳይሆን ፍርድ ቤቱ ‹‹ነፃ ነህ!›› ብሎ አሰናብቶት ነው፡፡ ቀኑም የ‹‹ፀሎተ-ሀሙስ›› ዕለት ነበር፡፡ …የከነገ በስቲያ ሚያዚያ 24 ግጥምጥሞሽስ ምን ያሰማን ይሆን?
የሆነ ሆኖ የመፅሀፍ ቅዱስ ቃል ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት እግዚአብሄር ሙሴን እንዲህ እንዳለው ይነግረናል፡-
‹‹እኔ እግዚአብሄር ነኝ፤ ከባርነት አወጣችኋላሁ፤ ከተገዥነታቸውም አድናችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋቸኋለሁ፤ አምላክም እሆናቸኋለሁ፡፡›› (ኦሪት ዘጸአት ም.6 ቁ.6-7)
በወቅቱ ብዙ ሺህ ንፁሃን፣ ፈርኦን በተባለ ጨካኝ ንጉስ ስር ይሰቃዩ ነበር፡፡ እናም ከዕለታት አንድ ቀን እግዚአብሄር ሙሴን ወደ ፈርኦን ላከው፡፡ ሙሴም ቤተ-መንግስቱ ውስጥ ድረስ ዘልቆ በዙፋኑ ለተቀመጠው ፈርኦን እንዲህ ሲል የአምላኩን መልዕክት ነገረው፡-
‹‹እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡- በፊቴ ለመዋረድ እስከመቼ እምቢ ትላለህ? ያገለግለኝ ዘንድ ህዝቤን ልቀቅ!››
…በምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያም እስከዛሬ ድረስ ያየነው ስርዓቱና ምንደኞቹ ንፁሃንን በሀሰት ከሰው፣ በሀሰት ምስክርና በሀሰት ማስረጃ ወደ ጨለማ (ወህኒ) ሲወረውሩ ነው፡፡

በመላ ሀገሪቷ የነገሰውም የህግ የበላይነት አይደለም፤ የፈርኦን የበላይነት እንጂ፡፡ ፈርኦኖች ደግሞ ምን ጊዜም ከመከራ እንጂ ከታሪክ ተምረው አያውቁም፡፡ መልካሚቷን ምክርም ሊሰሙ አይወዱም፡፡ ስለዚህም ብቸኛው አማራጭ በአደባባይ ተሰባስበን፡-
‹‹በፊታችን ለመዋረድ እስከመቼ እምቢ ትላለችሁ? ሀገራቸውን ያገለግሉ ዘንድ ወንድምና እህቶቻችንን ልቀቅ!››
‹‹እስክንድር ነጋን ልቀቅ!
በቀለ ገርባን ልቀቅ!
አንዱአለም አራጌን ልቀቅ!
ርዕዮት አለሙን ልቀቅ!
ውብሸት ታዬን ልቀቅ!
የሱፍ ጌታቸውን ልቀቅ!
አቡበክር አህመድን ልቀቅ!
ብዙ… ብዙ ሺህ ንፁሃንን ልቀቅ!››
እያሉ መጮኹ ኢያሪኮን ለማፍረስ ያልተመለሰው የጭቁኖች ጩኸት መነቃነቅ የጀመረውን ስርዓት ለመፈረካከስ ብቸኛው ምርጫችን እንደሆነ ዛሬም ደግሜ እናገራለሁ፡፡
‹‹ልቀቅ! ልቀቅ! ልቀቅ!››

6 Responses to የህማማት ማሰታወሻ ‹‹ህዝቤን ልቀቅ!›› እስክንድር ነጋን ልቀቅ!…

 1. YALEMGENET Reply

  May 6, 2013 at 1:10 pm

  I Admire Temesgen, You are very strong man,you are my enrgey to fight Weyane Apartide regime. God Bless you! UNITY IS STRENGTH!

 2. Biniam teshome Reply

  May 6, 2013 at 9:11 am

  “1st ende brhan shema yemanedewn yehager fkrhn ladnklh.yethiopian yetnsae birhan fentaki ljochua bekaliti yechelema beret wst metagorachew basebku gize yegresat yihonbgnal.slehager maseb tsdku kunenae huno bebrhan alem chelema eyedasesu menor…abet gaeta yepetrosn yenetsa debdabae yadlachhu”tasrachhu ltasfetun yemtchlu ntsuhan meswat hoy yenantem tnsae kenatachhu tnsae ga yhonal”amen zemen ywleden.”

 3. Teshale Reply

  May 3, 2013 at 5:36 pm

  I am ashamed of myself for keeping silent while this regime is doing so much harm to my country. I am even more ashamed of myself and consider my life worthless, when I keep silent while my heroes like Eskinder, Andualem, Abubeker and many more suffer in jail. Temesgen, you are yet another one justifying how worthless and disgusting my life is. I must make my life worth something or die in honor than live in shame.

 4. Truneh Yirga Reply

  May 2, 2013 at 12:27 am

  Dear brother Temesgen, I always admire your courage for challenging the cruel Weyane regime and fighting for justice without fear. May God give you enough wisdom and grace to mobilize all peace loving Ethiopians to speak the truth and stand firm with you for justice may God protect you from all evils.
  ውድ ወንድሜ ተመስገን በእርግጥ አንተም እንደተረዳሃው፥ የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ በፈርዖንና በኣማልክቱ ፊት ሕዝቤን ልቀቅ ብሎ እንደተናገረ፥ ዛሬም በኢትዮጵያ ሕዝቤን ልቀቅ የሚል በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን፣ በሕዝቡ መሃከል ፍቅርና አመኔታን የተላበሰ አንድ የእምነት አርበኛ ያስፈለገበት ሰዓት ደርሰናል::
  ለዚህም በአገራችን እየተቀጣጠለ ባላው ፈርጀ ብዙ የነጻነትና የፍትሕ ትግል እያደረግኽው ላለው ተጋድሎህ አክብሮቴ ከፍ ያለ ነው፥ ጽናትህንም በጣም ዓደንቀዋለሁ፥ ሆኖም ግን ሕዝቡን የምታስተባብርበት ጥበብ፥ በጨካኙ ወያኔ ፊት ግንባርህን እንደ ባልጩት፣ እግሮችህን እንደብረት የሚያጸና የእግዚአብሔር ጸጋ ይብዛልህ ለማለት እወዳለሁ።
  ምክንያቱም ወያኔ ሕዝቡን አስፈራርቶና አስደንግጦ ለማጨናገፍ የለመደውን ዘዴ ሁሉ መሞከሩ አይቀሬ ነውና።

 5. keduse Reply

  May 1, 2013 at 6:12 pm

  Bewnet besemu min ale mechays new yaserutin yekerta teyk kemalet beka yeker belenae yemluit bemindenew yemaymelkuit? mechay new sewoch sayaleksu sayerabu yemnoruit be Ethiopia? egzeabher ethiopian YEMELKETATENA YEFRED.

 6. Asegid Wegayehu Reply

  May 1, 2013 at 5:20 pm

  All in all i apreciate all ur news and I am with u upto weyane removed {{FROM MAM}}

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>