ተጋዳላይ ማትያስ ሹመት ያዳብር!

March 2, 2013

Click here for PDF

እንዳይነቀሳቀስ አጁን በስንሰለት ጠፍረህ አሰረኸው፡
ሽጉጥክን ደግነህ ተናዘዝ ብትለው፡
በእምነቴ አትምጣ ከፈለክ ያውልህ ደረቴን ለጥይት፡
ከቶ አልበገርም በባዶ ድራማ አድማጭ የለሽ ተረት፡
ሞቴን ከነምነቴ ብሎ በመጽናቱ ግራ የተጋባህ፡
ደንባራ ወያኔ ፊልም መቆራረጥ መቀጣጠል ገባህ፡፡

አንተ አቡ በከር አንድ ጎኔን ሞቀው በጣም አኮራኸኝ ፡
አኩል አልሞቅ አለኝ አንዱ ጎኔ ሳስቶ ክፉኛ በረደኝ ።

እንኳንስ ተከታይ፤ አስተማሪው ካህን መነኩሴው ጳጳሱ፡
ለምነት አልቆም አለ አሳሳችው ነፍሱ።

ኦርቶዶክስ ሃይማኖት መሆኗ ቀረና የእምነት ማህደር፡
ታጋይ ተፈራርቆ ይሾምባት ጀመር።

የሃይማኖት መሪ በግዜር ይመረጣል ተብይ አድጌ፡
አገር በጾም ጸሎት ትጸናለች ሲባል ተምሬ አድጌ፤
ታጋይ ጳጳስ ሲሆን ስተቱ የማን ነው? መልስ አጣሁ ፈልጌ።

በመርዝ በጥይት ወገኑን ጨርሶ የመጣ ሹመኛ ደብሩን ቢረከበው፡
እግዜር የሾመው ነው በሚል አጉል ባህል መስቀል ልሳለም ነው?

ወይስ

አንተ እርኩስ መንፈስ ተጣልቼሃለሁ፡
መስቀልህ ይቅርብኝ ቤቴ ጸልያለሁ፡
ገንዘቤም በኪሴ ለምን ጦርሃለሁ፡
ብዬ ላሳርፈው?

ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን የምትሆነው ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው የሃይማኖት መሪ ሲኖራት እንጂ የፖለቲካ ስልጣን በተቆጣጠሩ ባለስልጣናት የሚሾም ካድሬ ቁጥጥር ስር ሆና አደለም ፡ ስለዚህ ለተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች ሁሉ ማስተላለፍ የምፈልገው ምልእክት፡ ስርዓት እሰኪከበር ድረስ ጸሎታችሁን በቤታችሁ ገንዘባችሁን በኪሳችሁ እንድታረጉት እንዲሆን ነው፡ በገዛ ገንዘባችሁ ወያኔን የምታዳብሩበት ምክንያት አይኖርም፡፡

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ

እስከ ነጻነት

12 Responses to ተጋዳላይ ማትያስ ሹመት ያዳብር!

 1. DASSENNECH Reply

  March 4, 2013 at 2:07 pm

  BEN
  ላስተያየትህ አመሰግናለሁ፡
  እዚህ ላይ ሁለት ነገሮችን ላስታውስህ፡ እግዚአብሄር አዳምን ሲፈጥር ሶሶት ጸጋ ሰቶት ነው፡ ከሶሰት አንዱ ነጻ ህሊና ነው፡ የፈለገውን እንዲያስብ እና ተግባራዊም እንዲያረግ መብት ማለት ነው፡ ስለዚህ “ማሰብ ካልቻላችሁ መተው ይቻላል” ብለህ ከወያኔ አትናገሩ የባሰ ማዕቀብ መጣልህ ብቻ ሳይሆን ያንተ ሃሳብ መለኮታዊ የሌላው ተነቃፊ ሊሆን የሚችልበትን እነኳ ያገናዘብክ አልመሰለኝም
  ሁለተኛ
  እንደኔ በድንግዝግዝ ውስጥ ላሉት ያሰተላለፍከው መልዕክት ነው፡ ቅዱስ ገብርኤል ባላችሁበት ቁሙ ያላቸው ሳጥናኤል እነዳያሳስታቸው መሰለኝ ካልተሳሳትኩ፡ እና ሳጥናኤል በማትያስ ተመስሎ ስለመጣ ባላችሁበት ቁሙ ማለት ምኑ ላይ ነው ድንግዝግዙ? ነው ወይስ ቅዱስ አባታችን ናቸው ጸጥ ለጥ ብላችሁ ተቀበቸው የሚል ሰም ለበስ ድጋፍ እየሰጠህ ነው?
  እግዚአብሄር ይርዳን አሜን

 2. Ben Reply

  March 4, 2013 at 4:06 am

  ዳሰነች፡፡DASSENNECH
  እኔስ፡የኢትዮጵያ፡ፈርስት፡ቤን፡አይደለሁም፡ማወቅ፡ካስፈለገህ፡የእርሱ፡ተቃዋሚ፡ነኝ፡ምክንያት፡ወደ፡አንድ፡በኩል፡ያጋደለ፡ስራ፡ስለሚሰራ፡ዛሬ፡ዛሬ፡ደግሞ፡የለየለት፡ወያኔ፡ሆኖ፡የህዝቤ፡ስቃይ፡እንዲበዛ፡አጥብቆ፡እየሰራ፡ስለሆነ፡ነው፡፡
  እንዳንተ፡ላሉ፡በድንግዝግዝ፡ውስጥ፡ለሚገኙ፡ወገኖቼ፡የማስተላልፈው፡መልዕክት፡በነበራችሁበት፡ቁሙ፡ “ቅዱስ፡ገብርዔል፡መላዕክትን፡እንዳሳሰባቸው”
  አሜን፡ቸሩ፡እግዚዓብሄር፡ይርዳን፡፡

 3. GEREMBA Reply

  March 4, 2013 at 12:27 am

  I BETTER PRAY AT MY HOME. WHY DO I GO TO CHURH WHEN THE CHURHS ARE LED BY CADRES.

 4. torry Reply

  March 3, 2013 at 8:30 pm

  the new woyane patriarch who is a former ‘tegadalay’ of the fascist Tigre people liberation front has blood on his hands and is not fit for such a position.

 5. Orthodox Reply

  March 3, 2013 at 4:24 am

  Ewunet newu manen lemesmatena lemayet newu betekrstiyan yemikedewu beselam arefo bet mekemet yeshalal sewu bemogenet ega enesunfelega ayedelem yemnehedewu sel betam newu yemigermewu tadeya manewu yemitayewuna yemisemawu sedek felega hedo mergem yezo kememelese beselam bota bebet meseleyeu yebeletal Egzeabher amlak behulum bota alehu neww yalewu.

 6. Gidey Reply

  March 3, 2013 at 3:22 am

  Betam tekkele belehal, begnaw genzeb engnaw lay aruben, ahun ahun sasebew gizew yederese yemeslegnal, alem beka yalu sewoch endezi lehodachew siyaderu sitay betam new yemiyaseferew, sihon mengest benesu mehal sigeba erasu ayehonm enagn yewist chegerachn erasachn enefetale malet sinorebachew endegena kegna lesegaw kemirote sew belay hodam honubegn, asafari new

 7. DASSENNECH Reply

  March 3, 2013 at 2:41 am

  BEN:
  የትኛው ቤን ነህ ባክህ? የወያኔው Ethiopianfirs neh?

  ድንቄም አሳቢ

 8. Ben Reply

  March 3, 2013 at 2:12 am

  ሰው፡ምነው፡ረከሰ?

  የዋጋ፡ውጣ፡ውረድ፡ያለው፡በሸቀጥ፡ላይ፡እንጂ፡በሰዎች፡ላይ፡አልነበረም፡፡

  የአንዳንዱ፡ሰው፡አስተያየት፡ግን፡ፍጹም፡ጥላቻ፡የተሞላ፡ነው፡፡

  ወያኖን፡ጥላቻ፡ሌላ፡ኅይማኖት፡ሌላ:

  እባካችሁ፡ማሰብ፡ካልቻላችሁ፡ዝም፡ማለት፡ይቻላል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>