ለ13 ዓመታት ገለልተኛ ሆና የቆየችው የኖርዝ ካሎራይና ቤተ ክርስቲያን ህጋዊውን ሲኖዶስ ተቀላቀለች

February 27, 2013

Click here for PDF

… በእኛ ዘመንም ቤተ ክርስቲያን በሶስት ጎራ የተመደበችበት ዘመን ነው። ይህን ክፍፍል ወደ አንድነት ለማምጣት የመካነብርሃን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የራሷን ድርሻ ተወጥታለች፣ ለቤተEthiopian-Orthodox-Church-Holy-Synod ክርስቲያናችን ሕግና ስርዓትም መጠበቅ ቅድሚያ ትሰጥታለች። ስለዚህም ስላሴን እናመሰግናለን። በሻርለት ኖርዝ ካሎራይና የምትገኘው መካነ ብርሃን ቅድስት ስላሴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 13 ዓመታት በገለልተኛነት መኖሯዋ የታወሳል። በገለልተኝነት እንድትቆይ ያስገደዳትም ዋናው ምክንያት ለአለፉት ሃያ አመታት ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ማዕከል በማድረግ የተፈጠረው ልዩነት ተወግዶ በተዋህዶ ይመለሳል በማለት ነበር። በተለይ ደግሞ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ ታላቅ ተስፋ የተጣለበትና ለአለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ሲካሄድ የቆዬው የሰላም ድርድር ከፍጻሜ ደርሶ ለማየት ምኞታችን ፍጹም ነበር። ሆኖም ከዛሬ 21 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን የተቆጣጠረው አካል በቤተክርስቲያናችን ላይ ያስገባውን እጅ መሰብሰብ ባለመቻሉና ለፍላጎቱም መጠቀሚያ የሚሆኑ ለግል ጥቅምና ስልጣን እንጂ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት ደንታ የሌላቸውን አንዳንድ አባቶች ከጎኑ በማሰለፍ ብዙ የተደከመበትና ተስፋ የተጣለበት የሰላም ድርድር ያለውጤት እንዲቋጭ አድርጓል። ስለዚህ የመካነ ብርሃን ቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያናችን በገለልተኛነት መቆየት የታሰበውን አንድነት የሚያመጣ ሳይሆን ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሳተ አካሄድ በማጠናከር ዕምነታችንንና የቤተ ክርስቲያን ስርዓታችን የሚያፋልስ በመሆኑ ለማስተካከል ተገዳለች። ይቀጥላል…

4 Responses to ለ13 ዓመታት ገለልተኛ ሆና የቆየችው የኖርዝ ካሎራይና ቤተ ክርስቲያን ህጋዊውን ሲኖዶስ ተቀላቀለች

 1. Ben Reply

  March 4, 2013 at 3:51 am

  ወትሮም፡የማይሆን፡መንገድ፡ነበር፡የተከተላችሁት፡፡ “ከነዚህ፡ከታናናሾቹ፡አንዱን፡ከሚያስት፡በአንገቱ፡ላይ፡የወፍጮ፡ድንጋይ፡ታስሮ፡ወደ፡ባህር፡ቢጣል፡ይሻለዋል”
  እናም፡በድጋሚ፡ለምን፡ሁለተኛ፡ስህተት፡ትሰራላችሁ?
  አሁንም፡ጊዜው፡አልረፈደምና፡ንስሃ፡ግቡ!!!

 2. mequ Reply

  February 28, 2013 at 12:43 am

  Yes, “silus qidus wordolachihual” congratulations!!! Hope fully the holy spirit of yours will reach others who they think only humanely. It is just, right and timely move by you and if others follow your foot step we as a people will be blessed. As we are getting most information from addis is grim, we should put our prayers and humanly power together so that we can reach to the Holy land, Ethiopia in time to resurrect our church from the ashes weyane throw in.

  God bless you all North Carolina !!!

  mequ

 3. mequ Reply

  February 28, 2013 at 12:41 am

  Yes, “silus qidus wordolachihual” congratulations!!! Hope fully the holy spirit of yours will reach others who they think only humanely. It is just, right and timely move by you and if others follow your foot step we as a people will be blessed. As we are getting most information from addis is grim, we should put our prayers and humanly power together so that we can reach to the Holy land, Ethiopia in time to resurrect our church from the ashes weyane throw it.

  God bless you all North Carolina !!!

  mequ

 4. Abei Reply

  February 27, 2013 at 8:06 pm

  Wise move. Hope others will follow.
  God bless

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>