ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!

February 26, 2013

በመቅደስ አበራ (ከጀርመን)

ትላንት የተናገሩትን ዛሬ፤ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር  የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው  ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡የገንዛ ሀገሩን ቆርሶ ለሱዳን የሚሰጥ፣የባህርበር አያስፈልገኝም የአሰብን ወደብ ውሰዱት፣ኤርትራ እንድትገነጠል ፈቅጃለሁና እውቅና ስጡልኝ እባካችሁ እያለ የአለም መንግትታትን  የተማጸነ፣የገንዛ ዞጎቹን አፈናቅሎ ለውጭ ባለ ሀብቶች መሬታቸውን የሚሰጥ፤የሀገሪቱን ሀብት ለተደራጁ ወንበዴወች የሚያስዘርፍና የሚዘርፍ፤ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አጥፍቼ  ታላቋን ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ አንባገነን እንዴት ያለ ሀገራዊ ራዕይ ነው የሚኖረው፡፡

ዘረኛው መንግስት በተለያዩ ጊዜያት እንዱን ብሄር በሌላው ብሄር ላይ በማነሳሳት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሀብትና ንብረታቸውን ተዘርፈው ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእልፈት ተዳርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችን  በሽብር ስም እያሰረ ንጹሀንን ሲያሸብር ቆይቷል፡፡በርካታ ፓርቲዎች በሰርጎ ገብ ሰላዮች የተነሳ ይዘውት የተነሱትን አላማ እና  የህዝብ አደራ እዳር ሳያደርሱ በጅምር ቀርተዋል፡፡በወያኔ መሰሪ ተንኮል በተቀነባበረ ሴራ ጦርነት ውስጥ ያልገባ ክልልና ብሄር ባይገኝም ውጤቱ እንደሚፈልጉት ስላልሆነላቸው እና የኢትዮጵያ ህዝቦችም ባላቸው አርቆ አስተዋይነትና ረጅም ጊዜ በሰላም አብሮ የመኖር ባህሉ በመታገዝ  የፕሮፖጋንዳቸው ሰለባ ባለመሆናቸው ለወያኔዎች ትልቅ ራስ ምታት ጥሮባቸዋል፡፡እስካሁን ሲጫወትበት የነበረውን ካርድም እንዲቀይርም ተገዷል፡፡ አዲሱ የመጫወቻ ካርድም ከብሄር ግጭት ወደ ሐይማኖታዊ ግጭት ለማሸጋገርም የሚያስችለውን “ጀሀዳዊ ሀረካት”የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ከ1500 አመት በላይ አብረው የኖሩትን ሁለቱን ታላላቅ እምነቶች ማለቂያ ወደሌለው ጦረነት በመማገድ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ቢምክርም እናንተ ከመጣችሁት ገና 21 ዓመታችሁ ነው እኛ ደግም ለረጅም ጊዜ  በፍቅር አብረን ኑረናል፤  የጋራ ጠላታችን ዘረኛው ወያኔ ነው፡፡እኛ ከእነሱ እንሻላለን አንለያይም እያሉ በየአደባባዮ አንገት ላንገት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቁጭታቸውን ሲገልጹ መመልከት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ሰሞኑን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም ሙኒክ ላይ የታየውም ህብረት የዚሁ አካል ነው፡፡

እንዴት እንደ  ኢትዮጵያ ያለች ታላቅ ሀገር እና እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ቀደምት ህዝቦች እንደ ወያኔ ባሉ ትንሽ ሰዎች ይገዛሉ?እንዴት የአለም ማህበረሰብ በሀሰት የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ሲታለል ይኖራል?እስከመቼ ብቻቸውን በምርጫ ተወዳድረው አሸነፍን እያሉ ሲያላግጡ ይኖራሉ? ወያኔዎችስ በቀጣይ ምን የማደናገሪያ ስልት ያመጡ ይሆን? እኔ በበኩሌ በቃ ብያለሁ፡፡ ወያኔ ራዕይ የለውም ኑሮትም አያውቅም፤ ወደፊትም አይኖረውም፡፡የወያኔ  ሀገር እና ህዝብ የማውደም ቅዠት እንጂ ሀገራዊ ራዕይ ብሎ ነገር አያውቅም፡፡በጋራ ጠላታችን ላይ በጋራ እንነሳ!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

2 Responses to ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!

  1. andnet berhane Reply

    March 1, 2013 at 12:28 am

    ወያነ ራእይ የለውም ይህ ጸሐይ የሞቀው አገር ያወቀው በመሰረቱ ከአባቱ ከዛእብያ የተወራረሠ ስራአት ያለው በግፍ የተጠመቀ አረመኔ ቡድን መሆኑን የማይረዳው ካለ ለሆድ ያደረ እሱነቱን የዘነጋ መሆን አለበት እንድግዲህ የዚህን መርዝ ማርከሻ ምን ይሆን በጽሑፍ ባደባባይ በመጮህ ገበናውን አስምተናል ያደመጡንም ከኛ የሚጠብቁት እርስ በርስ ተላልቀን ሃገራችን ባድማ ለማድረግ የተጠነሰሰ ሴራ ስላለ በበኩላችን ማድረግ የሚገባን ምንድነው ብለን ራሳችንን እንጠይቅ ፡ እውነት ነው በመቅደስ አበራ ያስቀመትቀው ምንም ከመረት የማይወድቅ ማስረጃነቱ ቁልጭ ያለ ሃቅ ነው፡
    በሃገራችን ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ አንገት የሚያስደፋ የነበረንን ክብርና ልእልና ያዋረደ ከመሆኑ ባሻገር በገዛ ሃገራችን ባይታወር መሆን ከዛም አልፈን እንድፈረስ ሲጋልቡብን እንደአህያ ሲጭኑን ወጊድ ያላልን ለሃያአንድ ዓመታት በትግስት መቆየት ለምን ይሆን? ለዚህ መልስ ያስፈልገዋል መወለድ ላንድ ጊዘ በመሆኑም ሞትም አንድጊዜ እንጂ ሁለተኛ የለውም፡ በህይወት እያሉ ከመሞት የከፋ ነገር የለም ስለዚህ በቁርጠኝነት መነሳትና ይህንን የከፋ አገዛዝ ወደድንም አልወደድንም ባለን ሃይልና አቅም እምቢ በማለት የዜግነት መብታችንን ለማስጠበቅ ያለ ልዩነት ከእስላም እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን ጎን የለውጥ ችቦ በመለኮስ ለ እምነታችን ለመብታችን መጠበቅ ክርስቲያናዊ ኃላፊነት በመሸከም የድምጻችን ይሰማ ትግል በቀጣይነት መልስ እስኪያገኝ ያለ መሰልቸት ጎን ለጎን ቆመን የሃገር ባለቤትነትነታችንን በጽናት ማሳየት የያንዳድችን ኢትዮጳውያንነን የምንል ሁሉ ተጠያቂና ተካፋይነትን ይጠይቃል ፡
    በጽሑፍ ጦርንነት አብቅቶ በአካል ግብራዊነት ለመተርጎም ሁሉም የትግል ተቃዋሚዎች ሁሉም በአንድነት ለዚህ ሃገራዊ መብታዊ ጥሪ በመተባበር ወደአንድ ግምባር እንዲገቡ የሕዝብ ጥሪ በመሆኑ ተቀብለው እንዲመጡ በያለንበት እናሳማ፡ ትግል በትብብር በአንድነት ያለ ስብጥር ሲሆን ድልን ያመጣል፡እባካችሁ ተባበሩ ተባበሩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>