ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
የረፖርተር ድሕረ ገፅ ሲዘግብ:
በጎሳ ላይ የተመሰረተ ግጭት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል በመጸዳጃ ቤቶች፤ በቤተመጻህፍትና በመኝታ ቤት ግድግዳ ላይ፤የተጻፉ አስፀያፊ ክብረነክ ጸሁፎች ከስድስት በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ለከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ተጠቂ ዳርጓቸዋል:: በርካታዎችንም ለእስር አብቅቷል፡፡ ለላለፉት አሰርት ዓመታት፤በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል ግጭቶችን ሲያስነሱ ከርመዋል፡፡ ይህም መሰረታዊ ችግሩና መንስኤው አስተዳደራዊ ድክመት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተመሳሳይ ባለፈው በእለተ ዕረቡ ጃንዋሪ 2 2013 የተቀሰቀሰው ግጭትም በተለይ በሁለት ጎሳዎች በኦሮሞና በትግራይ ተማሪዎች መሃል የተከሰተ ነበር፡፡ ምስክሮች እንደሚሉት፤ግጭቱ የተቀሰቀሰው የትግራይ ተወላጅ የሆነው ተማሪ፤ በመጸዳጃ ቤት፤ በቤተመጻህፍትና በተማሪዎች መኝታ ቤቶች ግድግዳዎች ላይ የጎሳን ክብር የሚነካ ጽሁፍ በመጻፉ ነበር፡፡
እንደ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለስልጣን አባባል ‹‹ግጭቱ የተቀሰቀሰው ያንን የጎሣ ክብር የሚነካ ክብረነክ ጽሁፍ በተመለከቱት ተማሪዎች መሆኑን ነው::›› በዚህም የተነሳ 20
ተማሪዎች መቁሰላችውንና 3ቱ የጠናባቸው ወደ ሆስፒታ፤ል መወሰዳቸውን በተጨማሪ ሁለቱ የቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው ታውቋል፡፡ ሌሎች 20ዎችም በፖሊስ ባልለየለት ውንጀላ ለእስር ተዳርገዋል፡፡
ስለኢትዮጵያ ‹‹የብልሆች መፍለቂያ ከነበረው ዩኒቨርሲቲ›› ይህን ሁኔታ ሳነበው ያደረብኝ ግብታዊ አስተያየት፤ ማመን እስኪያቅተኝ ነበር፡፡ ሳስበዉም ‹‹ይህ ፈጽሞ ሊታመን የሚችል ጉዳይ አይደልም፡፡ ይህ ከኢትዮጵያ አነሮች ትውልድ (ወጣቱ ትውልድ) በዚህ ፈሪነትና የማያስፈራራ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ መግባት ተግባራቸው አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዚህ ቆሻሻ እና እጣቢ አተላ የጎሳ ፖለቲካ ውስጥ ከመንደፋደፍ የተሸለና የበለጠ ተግባር ማከናውን ይችላሉ›› አልኩኝ :: ይህን የመሰለ የረከሰ የጥላቻ ምግባር፤የወዲፊቶቹ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን፤የቀጣዩ ትውልድ መምህራን፤ ሳይንቲስቶች፤ እና የፈጠራ ሰዎች ምግባር እንዳልሆነ ነበር እራሴን ማሳመን የሞከርኩት፡፡
ነገሩን የበለጠ ሳጤነው አምአሮ የሚነካና የሚአስቀፍፍ ሆኖ አገኘሁት፡፡ እራሴንም ጠየቅሁ፡፡ ምናልባትስ ይህ የጎሳ ክብር የሚነካ ጽሁፍ በሌሎች የአ አ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተፈጠረ ቢሆንስ? ይህን የመሰለው ዝቃጭ፤ወኔቢስ፤ባለጌ ተግባር ስለነዚህ ተማሪዎች ምን ይላል? ስለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችስ? ስለአጠቃላዮቹ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችስ? ስለ መላው የኢትዮጵያ ወጣቶችስ?
ከዚህ ጥየቄ ጋር በመታገል ላይ እንዳለሁ፤ ሊገታ የማይችል ሃፍረትና ውርደት ሰሜት ወረረኝ፡፡ እራሴን ደጋግሜ መረመርኩት፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ምርጥና ብሩህ አእምሮ ያለቸው ተማሪዎች—- የኢዮጵያ አነሮች —- ይህን በመሰል ኋላ ቀር፤ አረመኔያዊ፤ ጨካኝና አሰቃቂ፤ ተናካሽ፤ ተንኮል የተመላበት፤ተግባር አንዴት ሊሰሩ ይችላሉ? በምን መንስኤ ነው፤ አንድ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ስብስብ ሌላውን ወገን ስብእና ለመድፈር፤ የጋኔን ተግባር ለመፈጸም፤ ዝቅ አድርጎ ለመመልከት፤ አውሬ በማስመሰል፤ አካሄድና ተግባር የሚሰማሩት? ለምን? እኮ ለምን? ለነዚህ ጥያቄዎች አንዳችም ምክንያታዊ ምላሽ ላገኝ አልቻልኩም፡፡
ይህ የ ጎሳ ጥላቻ ወንጀል የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ሰለ አትዮጴያ ወጣቶች ክብርና ወደፊት ላገራቸው ሰለምተበቀባቸው ግዴታ በመፅፈበት ወቅት ነበር :: ሆነ በተባለው የጎሳ ጥላቻ ወንጀል የበለጠ ግራ እየተጋባሁ ሄድኩ፡፡ ይህን አስጠያፊና አስፈሪ፤ ቀፋፊ ሁኔታ በምክንያታዊነት በጥልቀት ለመረዳትና በዚህ አስገራሚ ትርኢት ውስጥ አንዳንድ የኢትዮጵያ አነሮች እንደ ጉማሬዎቹ በመንቀሳቀስ እንደጅቦቹ ለመሆን መከጀላቸው አስገረመኝ፡፡ አሳፈረኝ፡፡ አሳዘነኝ፡፡
ያን ግልብ ስሜቴን ወደ ጎን አልኩና ረጋ ብዬ ማሰብ ጀመርኩ:: ከምር ጠንክሬ አሰብኩ፡፡ ይህ በዩኒቨርሲቲው የተከናወነው ‹‹በጎሳ ላይ የተመሰረተውን አልመግባባት›› ድርጊት ከጥሩ እምነት ካላቸው ሁነኛ መደበኛ ተማሪዎች ተጠንስሶ በስራ ላይ የዋለ ነው ለማለት ምን ማስረጃ ሊቀርብ ይችላል? በእውነትስ የተባለውና በዚህ በየግድግዳው ላይ የሰፈሩትን ክብረ ነክ ጽሁፎች የጻፈው ‹‹ተማሪ›› ማነው? በዚህ ዩኒቨርሲቲ የሙዚቃ ሸክላ አጫዋች መሰል የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ተቀምሞ የተበተነውን መሸንገያ አባባል ማመን አለብን? እንዴት ነው የዩኒቨርሲቲ አስተዳዳሪዎች ‹‹ለአሰርት ዓመታት በዩኒቨርሲቲዎች ሲከናወኑ የነበሩትን የጎሳ ግጭቶች” ያሳለፏቸውና አሁንም ሲቀጥሉ አጃቸዉን አጣጥፈው መመልከት የቻሉት? በዩኒቨርሲቲውስ ውስጥ ምራቃቸውን የዋጡና የበሰሉ፤ችግሮችን ለማክሸፍና ለማግባባት ፈቃደኛ የሆኑ አመራሮች የሉም?
ጥርጣሬ ቀስ እያለ፤ድንጋጤዬንና ሃፍረቴ መተካት ስለጀመረ፤ የዚህ ‹‹በጎሳ ላይ የተመሰረተ ብጥብጥ›› በገዢው መንግስት ጀብደኛ ባለማዕረግ የተዋቀረና፤ የተተለመ እንደሆነስ የሚለው ጥያቄ አያፈጠጠ ያየኝ ጀመር፡፡ በኋላም የወንጀል መመርመርያ ማስረጃ ማፈላለጊያ “መነጽሬን” ሳደርገው፤ እንደገና በመሹለክለክ ድምጽዋን አጥፍታ ጨለማና ወቅትን መከለያ በማድረግ አንዲት መናጢና ቆሻሻ አይጥ ተንኮሏን ከፈጸመችና ተልእኮዋን ከፈጸመች በኋላ ሳትታይ ጥላው የሄደችውን የእጇንና የእግሯን አሸራ በግድገዳ ላይ ከተጻፈው አስጠያፊ ጥሁፍ አግርጌ ታትሞ አየሁት፡፡
በሜይ 2010 ጃዋር ሲራጅ ሞሃመድ ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ሐተታ ሰጪ እንዲሁም የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ እንደዘገበው በዩኒ ቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ከተማሪዎች ጋር በርካታ ውይይት ካካሄደ በኋላ እንዲሁም በሁለት ክፍል በሃራማያና፤በአዳማ ዩኒ ቨርሲቲ በ2006 የተከናወነውን ድርጊት ሰበቡን የአካዳሚክ ነጻነት ማጣትና በኢትዮጵያ የደህንነት ሚስጥራዊ ተቀጣሪዎች ተማሪ በመምሰል ሰርገው በመግባት የግጭቱ መሰሪ ጠንሳሾች መሆናቸውን ለማመን በቅቷል፡፡
ደግሞም በሴፕቴምበር 2011 ላይ በይፋ የዎጣው ማስረጃ አንዳሳየው በሴፕቴምበር 16 2006 “ የኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ 3 ፈንጂዎች መቅበራቸውንና በመፈንዳቱና፤ በወቅቱም የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ የሚካሄድበት ስለነበረ ከረር ያለ ጥያቄ ያስነሳውን ፍንዳታም ኤርትራንና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባርን ተጠያቂ እንዳደረጉ ነበር::” በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን መንግስት ኤምባሲ ባካሄደው ‹‹የሚስጢር ዘገባ›› በጉዳዩ ላይ የመርማሪዎቹ ጣት ወደ ኢትዮጵያ ገዢ መንግስት የደህንነት አባላትን በመጠቆም ለዚህ የወንጀል ድርጊት ተጠያቂ አድርጓቸዋል፡፡
በሌላም በኩል በ2006 የተገኘው ሚስጥራዊው ባለ 52 ገጽ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተዘጋጀው ሰነድ፤ የዲያስፖራው ዳይሬክቶሬት በዲያስፖራው ያሉትን የተቃዋሚ ሃይላትና አባሎቻቸውን የሚነዘንዝ፤ በሃይማኖት፤ በዘር፤ በፖለቲካ ጥላቻ የሚከፋፍልና ማንኛቸውንም ገዢውን ፓርቲ የሚቃወሙትን ለመከፋፈልና በመሃላቸው መግባባት እንዲጠፋ ያደረገው ጥረትና ዝግጅት ተጋልጦ ነበር ፡፡ ስለ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አጋጣሚ በይበልጥ ባሰብኩ ቁጥር፤የገዢው መንግስት ተቃዋሚዎችን ለማስጠላት ለመከፋፈል ለመበታተን ለማክሸፍ ብሎ የሚዘራውን ቆሻሻና የብልግና ባህሪ ያጋልጡት ጀምረዋል፡፡
በተጨባጭ ምርምሬ አንደተርዳሁት ‹‹በጎሳ ላይ ለተመሰረተው ግጭት›› ወንጀል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠያቂው ማን እንደሆነ ግልጽ የሆነው ማስረጃ የሚጠቆመው ወደ ተለመዱት ወንጀል ፈጻሚ የገዢው መንገስት ወንጀለኞች ነው፡፡
ሊታለፍ የማይችለው መደምደሚያም፤ (ሌላ ተቃራኒ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ) በጃንዋሪ 2 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለተፈጸመው ወንጀላዊ ተግባር ተጠያቂዎቹ፤ በግቢው ውስጥ በድብቅ የተቀመጡት መዘዝ ፈጣሪዎችና ምግባረ ብልሹ ሕሊና ቢስ ወኪል ተንኳሾችና ደባ ፈጻሚዎች እንጂ ጨርሶ ለጥሩ ዕምነት የተፈጠሩት ወጣት አቦሸማኔዎቹ የነገ የሃገር አለኝተ ዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡
የማጠቃለያው ግምገማም ይህንን መደምደሚያ የማያጠያይቅ ማስረጃ በመሆን ያረጋግጠዋል፡፡ ያለዉን ማስረጃ በጥቂቱ ብንመለከተው: በመጀመርያ እንድ ብቸኛ “ተማሪ”ብቻ ነው ድርጊቱን በመተንኮሱ የተወነጀለው፡፡ ይህ ደግሞ ተማሪዎች በአንድ ጎሳ ስር ተቧድነው ለዚህ ድርጊት መንቀሳቀሳቸውንና በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰላም ለማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም፤ መደራጀታቸውን ተአማኒነት ያሳጣዋል፡፡ ይህን እንቅሳቃሴ ለመጀመርና መነሻ ሆነ የተባለውም ብቸኛ “ተማሪ” የየት ጎሳ አባል እንደሆነ በግልጽ አልተረጋገጠም፡፡ የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት: ስምና መለያው ያልታወቀ፤ አንድ ተማሪ በማለት ወንጀለኛ ብለውታል፡፡ ይሁንና ይህ ‹‹ተማሪ›› ዓላማ ያለው እርገግጠኛ መደበኛ “ተማሪስ” ነው? ወይስ ተቀጣሪ ነገር ቆስቋሽ የስለላ ድርጅት ወኪል ግን እንደተማሪ ተመሳስሎ ተወሻቂ አባል (የቀበሮ መንኩሴ በግ መሃል ይጸለያል አንደሚባለው ሁሉ ) ነው? ይህስ ተማሪ በዘር ላይ የተመሰረተ የጥላቻ ባሕሪ ግለ ታሪክስ ያለው ነው?
ሶስተኛ፤ በሶስት ቦታዎች ማለትም በላይብረሪ፤ በመጻሕፍት ቤትና በተማሪ መኝታ ቤት ይህን መሰሉን የጎሳን ክብር የሚያዋርድና የሚያንቋሽሽ ጽሁፍ ለመጻፉ ምንም የተጠቀሰ ማስረጃ የለም፡፡ በጥላቻ ወንጀል ድርጊት፤ እንዲህ መሰሎች የጥላቻና የማዋረድ ተግባር ያለባቸው ጽሁፎች ሲጻፉ ዓላማቸው አንድን የጎሳ አባል የሚመለከቱ ሲሆኑ፤ ኢላማ የተደረጉት ግለሰብም ይሁን ቡድኖች ሊደርሱበትና ሊያዩት በሚችሉት ስፍራ ይሆናል እንጂ የግል ጥላቻውንና ብሶት ጣውን ከተለያዩ ብዙ ጎሳዎች የመጡ በሚገኙበት ግቢ ውስጥ የማይመለከታቸውም እንዲመለከቱት ለምን ይደረጋል?
አራተኛ፤ ከዚህ አስቀያሚ የግድግዳ ጽሁፍ ሌላ ማስረጃ ሊሆን የሚችል አንዳችም ነገር ከዚህ የችግሩ ጠንሳሽ በተባለው ‹‹ተማሪ›› ላይ አልተገኘም፡፡
አምስተኛ፤ በጃንዋሪ 2 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጸመው ደባ የተለየ ሁኔታ ሆኖ ሊታይ አይችልም፡፡ ላለፉት በርካታ አሰርት ዓመታት ይህን መሰል በጎሳ ላይ ተመሰረተ አምባጓሮ ይነሳ እንደነበር የማያጠያይቅ ነው፡፡ ለምንስ የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት ጉዳዩ ሲያቆጠቁጥ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ለዚህ ከመብቃቱ ቀደም ብለው አላከሸፉትም፡፡ ድርጊቱ በአስከፊና ሊቀለበስ ወደማይችልበት ሁኔታ ከደረሰና አዳገው ሁሉ ከተከናወነም በኋላ በሌሎች ተማሪዎች ላይ አመጹ ተስፋፍቶ እንዳይቀጥልም ባለስላጣናቱ የወሰዱት እርምጃ የለም፡፡
ስድስተኛ፤ በነጻ አካላት ጉዳዩ ሙሉ በሙሉ ከመጣራቱስ አስቀድመው የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት “አመጹ የተጀመረው በግድግዳዎች ላይ የተጻፈውን ምግባረ ብልሹና ጎሳን የሚያንኳስስ ጥሁፍ ያዩት ተማሪዎች ነው በማለት ለምነስ መግለጫ አወጡ? ጉዳዩን ከመሰረቱ አንስተው የሚያጣሩ ገለልተኛ ወገኖች በማዋቀርና በመመርመር ለወዲቱ ይህን መሰል ድርጊት በድጋሚ እንዳይከሰት ማድረግ የሚቻልበትን ዘዴ ለምን አልቀያሱም? የዩኒቬርሲቲው ባለስልጣናት ጉዳዩን እራሳቸውን ከተጠያቂነትና ከሃላፊነት በማግለል ለፖሊስ ሙሉ በሙሉ ለምን አስረከቡት? ምናልባት በዩኒቨርሲቲው የሚከሰተውን የጎሳ ጥላቻ ወንጀል ቸል ያሉት አይታችሁ እንዳላየ ሁኑ የሚል መመርያ ስለተሰጣቸው ይሆን?
ሰባተኛ፤ የዚህ የጥላቻ ብጥብጥ ወንጀል ተጠቂ የሆኑትስ በፖሊስ ለመደብደብ ለመያዝና ለመታሰር ለጉዳት ለምን ተዳረጉ?
በአጭሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጸመው የጥላቻ ወንጀል የቀረበው ሁኔታና ማስረጃ ጨርሶ ወደ ተከሳሾቹ ተማሪዎች ጣት አያመላክትም፡፡ ይልቁንስ ያአመልካች ጣት በወንጀለከኝነት የሚጠቁመው ወደ ከሳሾቹ ነው፡፡ የዚህን የጥላቻ ወንጀል ፈጻሚዎች ለማጣራትና ለመያዝ የሚያስፈልገው፤ ያንን የግድግዳ ላይ ጽሁፍ የከተቡትን የማይታዩ ጣቶች ብቻ ሳይሆን እነዚያን ተማሪዎቹን እስኪጠወልጉ ድረስ የቀጠቀጡና ያሰቃዩ፤ ከዚያም በረጩት የአመጽ ነዳጅ ላይ እንዳይጠፋና የበለጥ እንዲቀጣጠል ንዳድ የረጩበትንና የጎሳ ግጭቱን ያቀጣጠሉትን፤በተማሪዎች መሃል ጥላቻ ንትረክና ዉዝግብ አንድፈጠር የሚዶልቱ ወንጀል ጠንሳሶች ነው፡፡
ያም እንዳለ ሆኖ፤አሁን ወቅቱ ነው፤ አስፈላጊው ወቅት ነው፤ትክክለኛው ጊዜ ……..
የማገገሚያጊዜ፤የመቀበያውየመተቃቀፊያ የእርቀሠላምጊዜ አሁን ነው
በክዱስ ጽሁፍ እንደሰፈረው፤ ‹‹ለማንኛውም ሁኔታ ወቅት አለው፤ከሰማይ በታች ላሉት ነገሮች ሁሉ ለየምክንያቱ ጊዜ አለው::›› ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለሃዘንም ወቅት አለው፤ ድንጋይ ለመወርወርም ጊዜ አለው፡፡ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፡፡ እንዲሁም ለመተቃቀፍም ጊዜ አለው ለሠላምና ለማገገምም ጊዜ አለው፡፡ ለእርቀሰላምም የራሱ ጊዜ አለው፡፡
አሁን ነው ጊዜው፤ — ትክለኛው ጊዜ– ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች በትምህርት ቤቶች፤ በዩኒቬርስቲዎች፤ በስራ ቦታዎች፤ በአጎራባች መንደሮችና በመንገድም ላይ የማገገሚያው ወቅት፡፡ ጊዜው—– ትክክለኛው ጊዜ—- የኢትዮጵያ ወጣቶች በወንድማማችነት በአህትማማችነት ስሜት መተቃቀፍ መተሳሰብ እጅ ለእጅ በመያያዝና አንድ በመሆን ብዛታቸውን ለቅድመአያቶቻቸው ክብርና ለታሪካቸው መከበርያ ማድረግ የሚገባቸው፡፡
ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የጎሳ ጥላቻን የብጥብጥን አዙሪት የመበጠሻ ጊዜው አሁንነው:: አላስፈላጊውን የቅሬታ ልምድ የማክተሚያ፤ የፍርሃትን ባህል፤ ጥላቻን፤ አውልቆ የመጣያው ትክክለኛው ጊዜው አሁን ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች ጣቶቻቸውን በማቆላለፍ እጅ ለእጅ በመያያዝ የፍርሃትን እከክ ማራገፊያቸው፤ ጥላቻን፤ግጭትን፤ከልባቸው ፤ ከሕሊናቸው፤ ከመንፈሳቸው አውጥተው መጣያ ጊዜያቸው አሁን ነው፡፡ ጓደኞቻቸውንና የትምህርት ባልደረቦቻቸውን እንደጠላትና ባላጋራ መመልከትን ማቆሚያቸው ጊዜ አሁን ነው፡፡
ሰላም ፈጥረው እርስ በርሳቸው እንደወንድምና እህት የሚተቃቀፉበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብልህና ምርጦች አንድ ላይ በመስራትና በመተጋገዝ የተሸለን ነገ ለመፍጠር የሚችሉበት፤በረጋና ጠንካራ በሆነ የሕግ የበላይነት ላይ፤ ሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ የተከበሩበት አማራጭ ሂደቶች ያሉበት መትለሚያው ጊዜ አሁን ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እንዳስተማሩት ‹‹ከጠላት ጋር ሠላምን መፍጠር ካስፈለገህ፤ከጠላትህ ጋር ተጓድነህ መስራት አለብህ፤ ያን ጊዜ ጠላትህ ወዳጅህ ይሆናል::›› እነዚያን ጠላት የምንላቸውን ወንድምና አህት አብሮ ተማሪዎች ና ወዳጅ ማድረጊያ ጊዜው አሁን ነው፡፡
በዩኒቨርሲቲ ግቢያችን ውስጥና ከግቢያችንም ውጪ ጥላቻንና የጥላቻ ወንጀልን ለማጥፋት መተባበርያው ጊዜ አሁን ነው፡፡
ከሕሊናችንና ከመንፈሳችን ውስጥ የጥላቻ ቋጠሯችንን ማጥፊያው፤ የፍርሃትን ሰንሰለትና ካቴና መበጠሸውጊዜ አሁን ነው፡፡ የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ካለፈው ጫና እራሳቸውን ለማላቀቅና ነጻ ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው፡፡
ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ቆንጨራውን በመቅበር ለአንድዬና ለመጨረሻው ጊዜ ‹‹አሻፈረን! አንዳችን ሌላውን የዚህ ወይም የዚያ ጎሳ ስለሆንን ለመጠላላት አሻፈረን፤ እምቢ! መባያችን ጊዜው አሁን ነው፡፡ አሻፈረን! ምክንያቱም ሁላችንም በተለያየ ስም በምንጠራው የጋራችን በሆነው አምላክ ስር አለያም የሁላችን በሆነችው ሀጋራችን የተለያየ ማእዘን ነዋሪዎች ነንና፡፡ እምቢ! በምንም መልኩ ለመጠቀሚያነትና እንደ አሻንጉሊትነት ሆነን በሚጠቀሙብን ለጥላቻ ለእርስ በርስ መቆራቆስ መጠቀሚያ አንሆንም፤ እምቢኝ! የሠለጠንን ነንና ለጥላቻ አንሰለፍም፡፡ አዳኝ እንደሚያሳድደው የሚታደን አውሬ ለመሆን እምቢኝ!
ከአንድጉማሬጥቂትቃላትለበርካታዎቹአቦሸማኔዎች
በርካታ አቦሸማኔዎች ምናልባትም ጉማሬውን ትውልድ ማዳመጡ ያስገርማቸው ይሆናል፡፡
እኛ ጉማሬዎች ‹‹በዕውቀት የተጋረድን›› ‹‹ራዕይ የጎደለን›› ‹‹የራሳችን ምንጭ እስካልደረቀብን ድረስ ጠቅላላው ሃገር ቢደረማመስ ደንታ የሌለን ›› ነን ተበለን አነታወቃለን:: ያም ሆኖ ወጣቱን ትውልድ በአክብሮት እባካችሁ ጆሯችሁን አውሱኝና ለመደመጥ እድል ስጡኝ እላለሁ፡፡
ጀግኑ!
የመጀመርያው የኢትዮጵያ ትውልድ በመሆን፤ እራሳችሁን ከሰንሰለቱ ነጻ በማድረግ ካለፈው የጫና ሰቆቃ እኛንም አራሳችህሁንም ለማላቀቅ ብቁ፡፡
የመጀመርያው የኢትዮጵያ ትውልድ በመሆን፤ ታሪካዊ ጥላቻን፤ ቅሬታን በማጥፋት፤ መግባባትንና መቻቻልን በማምጣት አዲስ እርቀሰላም በኢትዮጵያ ታሪክ ጀምሩ፡፡
የጥላቻን ቁስል ለማዳን የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን ለዘመናት ያመረቀዘውን በማጥፋት ለመጪው ትውልድ ያለፈው ትውልድ ስህተትና ጥፋት እስረኞች እንደማይሆኑ አረጋግጡላቸው፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን ሁላችንም በእኩልነት የሰው ዘር አባላት በመሆናችን ይህንንም በጎሰኝነት ለማቀደም ብለን አዘቅት አንውረድ ::
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን አንደኛችን ለሌላው ይቅርታን በመቸር ለአንድዬና ለመጨረሻ ጊዜ ቆንጨራውን በመቅበር፤ ጣቶቻችንም የጠመንጃ ቃታና ምላጭ ለመሳብ፤ጣቶቻችን የጥላቻ መነሾ የሆኑ ቃላትን በየግድግዳው ላይ ለመለቅለቅ ሳይሆን እጆቻችን የሚዘረጉት የመግባባት የመተሳሰብ ሰላምታ ለመለዋወጥና ለችግርም ይሁን ለደስታ እጅ ለመዋዋስ ብቻ አንድሆን ማረግ ያሻል፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን የተለያዩት እምነቶቻችን መለኮታዊነታቸውን ማረጋገጥ እንቻል::
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን አሻፈረኝ! አምቢ! በማለት ውስጥ ውስጡን ከሚበላን የጎሳ የሃይሞነት የጻታ ልዩነት በተቃርኖ እንቁም::
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን በመኝታ ቤቶች፤ በቤተመጻህፍት፤በመጸዳጃ ቤቶችም ያሉትን አስነዋሪና በታታኝ፤ ጎሰኝነትን የሚያቅራሩ ቃላታን በእርቀሰላም፤ በመግባባት፤ በውህደት፤ በፍቅር አሰባሳቢ ቃላቶች እንሸፍናቸው፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን የወደፊቷ ሃገራችን መሪ ሻምበሎች እናንት ኩሩ አቦሸማኔዎችእንጂ፤ የደከሙት፤ሙሰኞቹ፤ ምግባረብልሹዎቹ፤ እራሳቸውን የሚያስተናግዱ ጉማሬዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን ለመሆን የምትመኘውን ሁሉ በመሆን፤ለመሆንም ለማሰብ ቀደምት አንሁን፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን የትላንቱን የመረረ ስሜት በዛሬውና በነገው ጣፋጭ እርቀሰላም፤ መግባባት፤ አንድነት፤ መሰረት ላይ መልሳችሁ አዋቅሩት፡፡
የሃቅ ወቅቱ ደርሷል፡ አቦሸማኔዎቹ እራሳቸውን በማዳን ለእኛም መድህን ይሆኑን ይሆን ?
ለኢትዮጵያ ምርጡና ብሩሁ የሃቅ ወቅት ደርሷል!
የኢትዮጵያ ምርጥና ብሩህ አቦሸማኔዎች ካለፈው ጫናና መከራ እራሳቸውን በማዳንና የጎሳ መጎጃጃ፤ የሃይሞነት አክራሪነትን የጨቋኝ ስጦታ በመጣል እራሳቸውን ማዳን ይችሉ ይሆን?
እነዚህ አቦሸማኔዎች ተጠራጣሪዎቹን፤ የመሸጉትን ምስኪን ጉማሬዎች ከራሳቸው ነጻ ያወጧቸው ይሆን?
ከጎሳ መቆራቆስ ወደ ጎሳ ፍቅር፤መቻቻል አንድነት፤ መግባባትን ያበቁን ይሆን?
አቦሸማኔዎቹ ስብእናችንን ከጎግፍ ማነቆና ከአውሬ አስተሳሰብ ያላቅቁን ይሆን?
አቦሸማኔዎች የእርቀ ሰላምን ጥበብ ያስተምሩን ይሆን? በእርቀሰላም ቋንቋ ያናግሩን ይሆን?
የኢትዮጵያ ብልህና ብሩሆች አንድ የወጣት ግብረሃይል በመሆን 2013ን የአቦሸማኔዎች ዓመት ያደርጉት ይሆን? አንድ ላይ በመቆም የጎሳ ጥላቻን ቆንጨራ በመስበር የወገንተኛነትን ጎራዴ በማቅለጥ የእርቀሰላምን ሙሉነት ያስመርቱን ይሆን?
የአላንዳች ጥርጥር አዎን ይቻላቸዋል!
ባለፈው ሳምንት 2013 የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ዓመት ብዬ ስተነብይ፤ የኢትዮጵያን ወጣቶች ለማስተማር፤ ለማዳረስ፤ለማሳመን ቃል ገብቼ ነበር፡፡ አኛ ጉማሬዎች አቦሸማነዎችን አናስተመራለን የሚል አምነትም ነበረኝ:: ጉማሬዎችን አቦሸማኔዎችን ያስተምራሉ ብዬ አልገመትኩም ነበር:: ለዚህ ነው እኛ ጉማሬዎች ግራ የተጋባ ሸውራራ (የተዛባ አመለካከት) ቅርብ አዳሪነት፤ጠባብ አስተሳሰብ፤ የምያጠቃን:: ለአቦሸማኔዎች የማስተማርያ ወቅት ሊኖር ስለመቻሉ ጥርጣሬዬ የመጣው::
ስለዚህም የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎችና ጉማሬዎች በርካታ ግብግቦች የሚገጥሟቸው፡፡ የአቦሸማኔዎቹ ፈታና ጉማሬዎቹን የእርቀሰላምን ጥበብ ማስተማሩ ላይ ነው፡፡ የጉማሬዎቹ ፈተና ደግሞ ከአቦሸማኔዎች የእርቀሰላምን ጥበብ መማሩ ላይ ነው፡፡
አቦሸማኔዎች ታሪካዊ ገድል የመፈጸም እድል ቀርቦላቸዋል፡- ይሄዉም በምሳሌነት ማስተማር፡፡
በአዲስ አበባው ዩኒቨርሲቲ አጋጣሚ የተሳተፉትን፤ ወዳዳጆቻቸውንና ሌሎቹም ጭምር በግቢያቸው የተፈጸመውን አስጸያፊ የግጭት ሁኔታና ሁከት አስመልክቼ የማቀርበው ጥሪ ሁኔታውን ወደ ውብና ያማረ ፍቅርና ሰላም የሞላበት ፍሬያማ ውጤት ለማምጣት የአንድነት አውድማ ላይ እንዲሰባሰቡ ነው፡፡ እያንዳንዳቸው ወደ ሌላው በመቅረብ ይቅርታን እንዲጠይቁና እንዲቀባበሉ እጠይቃለሁ፡፡ አንዲት በጣም ትንሽ የሆነችውን ‹‹ይቅርታ›› የምትለውን ቃል ለመተንፈስ ወኔ ይጠይቃል፡፡
በራሳቸው ውህደት እንዲፈጥሩ እጠይቃለሁ—-አንድ ለአንድ፤ በትንሹና በበርካታው ስብስብ—–ልዩነታቸውን ይወያዩበት ይነጋገሩበት ይምከሩበት፡፡ አንደኛቸው የሌላው ጉዳትና ግፍ ይሰማው፡፡ አንዱ የሌላው ፍርሃትና ጥርጣሬ ይሰማው:: አንዱ ለሌላው እንባ ንቀት አይኑረው፡፡
በብሩህ ህሊና፤ በንጹህ ልቦና፤ አእምሮና መንፈስ ሊነጋገሩ ግድ ነውና ይህንንም እጠይቃለሁ፡፡
እያንዳንዳቸው የሌላውን ስሜትና ጥርጣሬ እንዲረዱ እጠይቃለሁ፡፡ በጓደኞቻቸው ጫማ ውስጥ ሆነው ለኪሎሜትር እንዲራመዱ እጠይቃለሁ:: በመጫሚያም ይሁን በባዶ እግራቸው ፈገግ ሊያሰኛቸው የሚችል ሁኔታ ያጋጥማቸዋል፡፡
የኢትጵያ አቦሸማኔዎችን 2013ን የእርቀሰላምና የሰላም ዓመት እንዲያደርጉት እጠይቃለሁ፡፡
ጃንዋሪ 2 1013 በታሪክ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጎሳ ጥላቻን ቆንጨራ፤የሃይሞነት ወገንተኝነት፤ የጾታ ልዩነት የተቀበሩበት ዕለት ሆኖ ዘወትር አንድታሰብ ይሁን፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተው አስጸያፊ ሁኔታ ለሕዝብ ማስተማሪያነት ያገልግል፡፡
ጥንካሬን ከችግር ወልዳችሁ፤ አንድነትን ከከፋፋይ ተምራችሁ፤ ከጓደኞቻችሁ ተማሪዎች ጋር ለመደማመጥና የመግባባትን፤ የመቻቻልን፤ የውህደትን ዘር ለማፈስ እንድትበቁ እማጸናችኋለሁ፡፡
የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ጉማሬዎችን እንደመሩ እጠይቃለሁ፡፡ እኛን አትከተሉን፤መሄጃችንን አናውቀውምና፡፡እኛ የጠፋው የጉማሬ ትውልዶች ነን፡፡
ይህን ግብግብ በመቀበል፤ትክክለኛውን እንደትክክል፤ስህተቱንም ወደ ትክክለኛነት ካልለወጣችሁት፤ አቦሸማኔዎች በስልጠና ላይ ያሉ ደካማ ጉማሬዎች ናቸው የሚል ትችት ላይ መውደቅ ይመጣል::
ለሁሉም ጊዜ አለው:: ለኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች፤ ለማገገምና ለእርቀሰላም ሰዓቱ አሁን ነው፡፡
የኔ ጥያቄ ለእዮጵያ ወጣቶች ይህ ነው:- አሁን ስንት ሰአት ነው!?!
የተባበሩት የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ፈጽሞ ለውድቀትና ለሽንፈት አይዳረጉም!
*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from)
(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::
© 2013, ↑ Ethiopian News in Amharic
Log in- Posts - Add New - Powered by WordPress - Designed by Gabfire Themes
Save-Ethiopia
January 16, 2013 at 10:19 am
ጥሩ ፅሁፍ ነው፡፡ፍቅርን ተስፋንና እምነትን በአዲሱ ትውልድ የሚዘራ ነው፡፡ነገር ግን እውነት የሚባለው ነገር ትንሽ ይጎለዋል፡፡ማለትም በታሪክና በተጨባጭ ያለውን ነባራዊውን የኢትዮጵያ እውነታ በትክክል ያለመረዳትና ያለማስቀመጥ፡፡አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ እንዲባል እኔ ያለውን ታሪካዊና ተጨባጭ እውነትንና ችግርን እንዳለ በመጋፈጥና በመቀበል የማምነው፡፡አሁን ላለው ለኢትዮጵያችን ስር የሠደደና ዘርፈ ብዙ ችግርም ዋናው መፍትሄ በሰከነ መንገድ ቆም ብሎ ምን እየሆነ ነው ብሎ በመጠየቅ እውነታውን መጋፈጥና መቀበል ከዚያም ይህ በራሱ አንድ እርምጃ ስለሆነ ቀጥሎ ደግሞ ወደ መፍትሄው ማምራት እነደሆነ ይሰማኛል፡፡በሽታውና የበሽታው መንስኤ በቅጡ ሳይታወቅ እኮ ወደ መድሃኒቱና መፍትሄው ለመሄድ አይቻልም፡፡
የእኛ የኢትዮጵያውያን ችግር በዋናነት እንደተረዳሁት ከሆነ እንደ ልባም ሰው ንቃተ-ህሊናችንንና የማሰብ ሃይላችንን ተጠቅመን በሰከነ መንገድ ማሰብ ካለመቻላችን የመነጨ ነው፡፡ዋናው ጠላታችንና ችግራችን ከድህነትም በላይ ይህ ይመስለኛል፡፡በዓለም ላይ ዛሬ የሰው ልጅ የሚጠቀምባቸው ብዙ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሁሉ የሰው ልጅ ጭንቅላቱን በሃይለኛቸው አስጭንቆ አስጠብቦ በታታሪነት የሰራቸው ነገሮች ናቸው፡፡እነ ቶማስ ኤዲሰን እኮ የኤሌክትሪክ ሃይልን ለማግኘትና ትቅም ላይ ለማዋል 24 ሰዓት እየደከሙና እልህ አስጨራሽና አድካሚ ጥርት ከማድረጋቸው የተነሳ እዚያው በቤተ-ሙከራቸው ውስጥ ሳይቀር እንቅልፍ ይወስዳቸው እንደነበር ነው የሚታወቀው፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም በፖለቲካው ምህዳር ውስጥ ላመኑበት ነገር በትጋት አእምሮን አስጨንቆ የመንቀሳቀስ ነገር አይታይም ፡፡ኢትዮጵያውያን ባብዛኛው በጭንቅላታችን የማሰብ ሃይል ሳይሆን በስሜታችን ደመ-ነፍሳዊ አካሄድ የምንመራና ባብዛኛው በቀላሉ የሚረበሽ የህፃንነት ባህሪ የሚታይብን ነን፡፡ፖለቲካው እራሱ በቅጡ ያልሰከነና የህፃናት የእቃ እቃ ጨዋታ ነው የሚመስለው፡፡በአንድ ሀገር ውስጥ 70 ያህል የፖለቲካ ፓርቲ መመስረት ለእኛ የዲሞክራሲ ደረጃችን መገለጫ እንደሆነ ጭምር የሚሰማን ህዝቦች ነን፡፡70 የፖለቲካ ፓርቲ ያለበት ሀገር በአለም ላይ እስካሁን አልሰማሁም፡፡መፍትሄው ደግሞ ፕሮፌሰር አለማየሁ በስሜታዊነት እየተመሩ አንዱን ትውልድ አቦሸማኔ(Cheetah) ሌላውን ደግሞ ጉማሬ(Hippopotamus) እያሉ ከታሪክና ከነባራዊው እውነታ ጋር የማይጣጣም ገፅታ መፍጠር አይደለም፡፡እውነቴን ነው የምለው ይህ አካሄድ እራሳቸው ፕሮፌሰሩ ከሚናገሩትና አሁን እራሱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም ሆነ በሌላው የትምህርት ተቋም ተፈጠረ ከሚባለው ሁኔታ ጋር እርስ በርስ የሚጋጭ ነገር ነው የሚሆነው፡፡አንድ ወቅት ላይ አንድ ጥራዝ-ነጠቅ ፀኃፊ የድሮው ኋላቀር ትውልድ መሬት በጋሻ የሚለካ ሲሆን የአሁኑ ዘመነኛ ትውልድ ድግሞ መረጃን(Data) በጊጋ ባይትና በቴራ ባይት የሚለካ የተለየ ትውልድ ነው ብሎ መፃፉን ሳስታውስ ምን ያህል አጠቃላይ የትውልድ ዝቅጠት(Generational Systemic Crisis) ውስጥ እንዳለን ይሰማኛል፡፡እንደዚህ ፀኃፊ ከሆነ የአሁኑ ትውልድ መረጃን(Data) እንደ ዳቦ እየቆረጠመ ወይንም ህብስተ-መና ከሰማይ እየወረደለት በዚህ ለመኖር የሚችል ስለሆነ ቤት የሚሰራበትና እህል የሚዘራበት መሬት ስለማያስፈልገው መሬታችን ሁሉ ለባእዳን ሲቸበቸብ ዝም ብሎ ማየት አለበት ማለት ነው፡፡ይህ አንዱን ትውልድ አቦሸማኔ(Cheetah) ሌላውን ደግሞ ጉማሬ(Hippopotamus) እያለ በመለያየት የሚያገናኝ ድልድይ ሳይሆን የሚለያይ የበርሊን ግንብ በመገንባት የሚቀነቀን እሳቤ አንድ ወቅት ደ/ር ተኮላ ወ/ሃጎስ Juvenile Fantasy ካለው ጋር እየተመሳሰለብኝ ነው፡፡የእኛ የኢትዮያውያን ሌላው ችግር በጊዜና በቦታ የተለጠጡ ለሁሉም ስር የሠደዱና የተስፋፉ ዘርፈ ብዙ ችግሮቻችን ሁሉ አንድ ወጥ የሆነ ጥቅል መፍትሄ በአንድ ጊዜ ለማግኘት መፍገምገማችን ነው፡፡በቃ ሶሻሊዝም ከተባለ ሶሻሊዝም ለሁሉም ችግራችን ሁሉ መፍትሄ እንደሚሰጠን ተደርጎ ይቀርብልናል፡፡ካፒታሊዝም ወይንም የእነ መለስ ልመታዊ ምንገስት ወይንም እድገትና ትራንስፎርሜሽን ወይንም ህዳሴ/ሬኔሳንስ ወዘተ ከተባለ ያንንም በተመሳሳይ መንገድ ነው የምናየው፡፡ዛሬ ደግሞ እነ ፕሮፌሰር አለማየሁ አንዱን ትውልድ አቦሸማኔ(Cheetah) ሌላውን ደግሞ ጉማሬ(Hippopotamus) እያሉ ከታሪክና ከነባራዊው እውነታ ጋር የማይጣጣም ገፅታ በመፍጠር አዲስ መፍትሄ ይዘው የመጡ እንዳይመስለን መጠንቀቁ የሚበጅ ነው፡፡ይህ አይነት እንደ ፔንዱለም ከአንዱ ጫፍ ወደ አንዱ ጫፍ የሚዘል ያልሰከነ እይታ ለዘመናት ችግር ውስጥ እየከተተን ነው ያለው፡፡የሰው ልጅ አጠቃላይ ታሪክና ትውልድ ከአንድ ወቅያኖስ ወይንም ባህር መንጭቶ የሚቀዳና የሚፈስ ተመልሶም ወደ ተመሳሳይ ወቅያኖስ ወይንም ባህር የሚገባ እንደ ወራጅ ወንዝ የሚመሰል ነው፡፡ንጉስ ሰለሞን ከፀሃይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም ሁሉም ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነፋስን እንደመከተል ነው እንዳለው መሆኑ ቀርቶ በተቃራኒው ግን ፕሮፌሰር አለማየሁ አንዱን ትውልድ አቦሸማኔ(Cheetah) ሌላውን ደግሞ ጉማሬ(Hippopotamus) እያሉ ከታሪክና ከነባራዊው እውነታ ጋር የማይጣጣም ገፅታ መፍጠር ብዙ እርቀት የማያስኬድ ብቻ ሳይሆን ውሎ አድሮ ሌላ ችግርም ጭምር የሚፈጥር ነገር ነው የሚሆነው፡፡ይልቁንስ የሚጠቅመን ነገር ይህ አይነት የበርሊን ግንብ መገንባት ሳይሆን ያሁን ትውልድም ይሁን የድሮው ትውልድ እንዴት በመከባበር በመተማመንና በመግባባት እርስ በርሱ ሊማማርና ሀገርን በጋራ ግንዛቤ ሊገነባና የታሪክንና የትውልድን የማያቋርጥ ፈሳሽ ወንዝ ሊያስቀጥል ይችላል የሚለው ነው መሆን ያለበት፡፡አቦሸማኔ(Cheetah) ያያውን ለማደንና ለመያዝ ፈጣን እንደሆነ ይታወቃል ነገር ግን የሚታደነው የት እንዳለና ወደየት አቅጣጫ መሄድና መሮጥ እንዳለበት ግን አቅጣጫ የሚጠቁመው ያስፈልገዋል፡፡የቱንም ያህል የስለጣኔ ልዩነት ቢኖር እናት ለሴት ልጇ ምጥ ለማስተማር ብዙ ይከብዳታል እንዴ?አባትስ ለወንድ ልጁ ተመሳሳይ የወንድነት ባህሪንና ተግባርን ለማስተማር ያን ያህል ይከብደዋልን?አጠቃላዩ ትውልድ እንደ ሸረሪት ድር እርስ በርሱ የተወሳሰበና የተያያዘ መሆኑን ማመን አለብን እንጂ አንዱን ትውልድ አቦሸማኔ(Cheetah) ሌላውን ደግሞ ጉማሬ(Hippopotamus) ማለትና አለመተማመንና መለያየትን መፍጠር ተገቢ አይደለም፡፡ከፖለቲካውም በላይ አጠቃላዩን ተፈጥሮንና ህይወትን ስናይ ይህንን የሚደግፍ አይደለም፡፡የጥንቱ ዘመነ ቅኝ ግዛት በቀጥታ የሃይል ወረራ ነበር ሲተገበር የኖረው ያሁኑ ደግሞ መልኩን ቀይሮ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ በዲሞክራሲና በሰብዓዊ መብት ሽፋን የሚደረግ እየሆነ ነው፡፡መሬት በጋሻ ይለካል የተባለው ጉማሬ የተባለው ትውልድ መረጃን(Data) በጊጋ ባይትና በቴራ ባይት ይለካል ለተባለው አቦሸማኔ ለተባለው ትውልድ ይህንን እውነታ የማስረዳት የታሪክ ግዴታ አለበት፡፡ያለበለዚያ ይህ እንቁላል እኮ በሎጂክ ይህን ያህል ነው ያለው ተማሪ እናት ሎጂክህን ብላ እንዳሉት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ቀጣዩ ትውልድ ዳቦ ተራብኩ ሲል በጊጋ ባይትና በቴራ ባይት የምትለካውን መረጃህን(Data) ብላ ማለት የሚያስከትል ነው የሚሆነው፡፡
ድግሞስ አሁን ያለው ትውልድ በሸቀጥ መልክ ከውጪ በገንዘባችን እየገዛን ከመጠቀም ውጪ የትኛውን የተለየ የሳይነስና የቴክኖጂ ፈጠራ አደረጋና ነው ይህንን ያህል የሌለ አሳሳች ምስል የሚፈጠረው?85 ፐርሰንት የሚሆነው የኢትዮጵያ ገበሬ እንደሆነ ዛሬም አብዛኛው በበሬ ከማረስ አልወጣም፡፡የሞትንም እኛ የነገስንም እኛ እንደተባለው ስኬታችንም ሆነ ውድቀታችን እርስ በርስ የተያያዘ እንደሆነ ማመን አለብን፡፡አባትና እናት አስቀድሞ ያልዘራውን መልካም ፍሬ ልጅ ከየት አምጥቶ ነው በተአምር የሚሰበስበው? በእርግጥ አዎ ነገሮችን በሂደት በሰከነ መንገድ ወደ ጥሩ ሁኔታ መቀየር ይቻላል፡፡ነገር ግን መነሻ እርሾ ያስፈልጋል፡፡አዎ አቦሸማኔ ለተባለው የትውልዱ መነሻ እርሾ ደግሞ ጉማሬ የተባለው ያለፈው ትውልድ ያስቀመጠለት ኢትዮጵያዊ ታሪኩና ማንነቱ ነው፡፡ከዚህ ውጪ ግን ፕሮፌሰር አለማየሁ የሚያቀነቅኑት ሰብዓዊ መብት ህገ-መንግስት ዲሞክራሲ ወዘተ የሚባሉት የምእራቡ አለም ፅንሰ ሃሳቦች ዝም ብለው በሌለ ሌላ አይነት አዲስ የሆነ መጤና ባእድ ማንነት ላይ በተአምር ሊገነቡ አይችሉም፡፡If there is no old me then there is no new me አይነት ነው የሚሆነው ነገሩ፡፡ብዙ ጊዜ ፕሮፌሰር አለማየሁ በሚፅፉት ፅኁፍ ላይ ያለኝ ትልቅ ቅሬታ በቃላት ብቻ ያሸበረቁ ለውጦችን በመሬት ላይ ካለው ከታሪክና ከተጨባጭ ሁኔታ ጋር በቅጡ ሳያገናዝቡ ዝም ብለው በተአምር እንደሚመጡ አድርገው በማቅረባቸው ነው፡፡ይህ የፕሮፌሰር አለማየሁ እይታ አዲሱን ትውልድ በቅጡ ካለማወቅ የመነጨ እንደሆነ አድርጌ ልረዳውና ነገር ግን በሌላው ጎን ደግሞ ምናልባትም ደግሞ ሆነኝ ብለው ይህንን አይነት የትውልድ ማያያዣ ድልድይ ሳይሆን የሚለያያይ የበርሊን ግንብ የሚገነቡት አንዳንድ ግለሰቦችም ሆኑ ሃይሎች ሌላ የተደበቀ እኩይ አጀንዳ ሊያራምዱ እንደሚችሉ መጠራጠር አለብን፡፡ይህም ከላይ እንዳስቀመጥኩት ዛሬ ዘመናዊ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት በታዳጊው አለም በተለይም በአፍሪካ ተግባራዊ እየሆነ ያለው በቀጥታ ወረራ ሳይሆን በቅጡ ያልሰከኑና ጥራዝ ነጠቅ የሆኑትን የአዲሱን ትውልድ ፖለቲከኞችና ምሁራን ዲሞክራሲ ሰብዓዊ መብት ወዘተ በሚባሉ አዲስ መጥ እሳቤዎች በማማለል እንደሆነ ነው፡፡ስለዚህም ዛሬ የምእራቡ አለም መንግስታትና የሚያራምዱት የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራልና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ፕሮጀክት ተግባራዊ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ተግበራዊ እንዲሆን በአፍሪካና ታዳገው አለም ዘመናዊ ቅኝ ግዛትን እያስፋፉት ያለው በዲሞክራሲና በሰብዓዊ መብት ሽፋን ነው፡፡በቅርቡ በሊቢያ በሶርያ በአይቮሪኮስት በኮንጎ በማሊ ወዘተ እየተቀሰቀሱ ላሉ ውስጣዊ ግጭቶች የተሰጠው ምላሽና መፍትሄ ዲሞክራሲንና ሰብዓዊ መብትን ሽፋን አድርጎ ውጪያዊ የባእዳን ወረራን ማስተናገድ ነው፡፡ስለዚህም እንደ ፕሮፌሰሩ እይታ ከሆነ በአቦሸማኔ የተመሰለው አዲስ ያልሰከነ ዘመነኛ ትውልድ በልኩ በባእዳን ሃይሎች የተሰፋለትን ዘመነኛ ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብትን እንደ በቀቀን ይዞ እንዲያቀነቅን እየተደረገ ከበስተጀርባ በረቀቀና በተቀባበረ መንገድ ዘመናዊ ቅኝ ግዛትን እንዲያስተናግድ እንዳይሆን በእጅጉ ያስፈራል፡፡ይህንን የቅኝ-ግዛት ጉዳይ በተወሰነ የሚያብራራ አንድ የድሮ ተረት የማውቀውን ያህል ላስታውስ እፈልጋለሁኝ፡፡አንድ ቀን ከዚህ በፊት ፈፅሞ የማይተዋወቁ የጦጣና የነብር ጨቅላ ልጆች አብረው መጫወት ይጀምራሉ፡፡በሁለቱም በኩል ይህ አዲስና ከዚህ በፊት ያልገጠማቸው ግንኙነታቸውና ጨዋታቸው በሁለቱም ዘንድ አዲስ የተለየ ደስ የሚል ሰሜትን የፈጠረ ነበር፡፡በዚህም የተነሳም ሁለቱም ጨቅላዎች ለየቤተሰቦቻቸው ገጠመኛቸውን ደስ እንደሚል ይናገራሉ፡፡በዚህ ጊዜ ጦጣ እናት በሆነው ደንግጣ በይ የእኔ ልጅ ከዚህ በፊት ስላልነገርኩሽ ነው እንጂ አብረሽ የተጫወትሻቸው የእኛ ዋና አዳኝ ጠላቶች ናቸውና ከዚህ በኋላ ዳግም ፈፅሞ አብረሽ እንዳትውይ ብላ አጥብቃ ታስጠነቅቃለች፡፡የጨቅላ ነብር እናት ደግሞ በተቃራኒው በመገረምና በመደሰት የአብራኬ ክፋይ ልጄ ሆይ አብረሽ የተጫወትሻቸው ለእኛ ጥሩ ምግብ የሚሆኑ ናቸውና ከዚህ በኋላ ስታገኛቸው ፈፅሞ እንዳትምሪያቸው ብላ ታስጠነቅቃለች፡፡በሌላ ጊዜ ሁለቱ ጨቅላዎች በሩቁ ሲገናኙ የነብር ልጅ የጦጣን ልጅ እንደበፊቱ እንዲጫወቱ በደስታ ትጋብዛለች፡፡በዚህ ጊዜ የጦጣ ልጅ ማን ሞኝ አለ እኛም ነቄ ብለናል እንደሚባለው አይነት እናንተ ጋር የተመከረው እኛም ቤት ተመክሯል አለቻት፡፡ፕሮፌሰር አለማየሁ እኛን ታዳጊውን አለምና አፍሪካን አቦሸማኔ እና ጉማሬ ብለው የከፋፈሉንን ያህል የሰለጠነውን የምእራቡን አለም ሁኔታ ግን ፈፅሞ ያስታወሱት ወይንም ያሰቡበት አይመስለኝም፡፡ማለትም የምእራቡ አለም ዛሬም ያንን የጥንቱን የመስፋፋት የኮሎኒያሊዝም ባህሪውን ፈፅሞ እንዳልረሳውና እንዳልተወው መዘንጋት የለብንም፡፡የነብር እናት ለነብር ልጅ እደነገረቻት ሁሉ ይህንን አውቀን እኛም የጦጣዋ እናት ለጦጣዋ ልጅ እንደነገረቻት ሁሉ እኛም ለቀጣዩ በአቦሸማኔ ለተሰየመው አዲስ ትውልድ አቅጣጫውንና እውነቱን መንገርና የሚያገናኝ ድልድይ መስራት አለብን እንጂ ጉማሬ እና አቦሸማኔ እያልን የማይሆን የሚለያይ ግንብ መገንባት የለብንም፡፡በሰለጠነው አለም ይህ አይነት አላስፈላጊ የሚለያይ ግንብ ሳይሆን የሚያገናኝ ድልድይ ነው የሚሰራውና በዚህ የተነሳም እናት ነብር ለልጅ ነብር ስልጦጣዎች ምንነት ትናገራለች፡፡እኛ ጋር ስንመጣ ግን እናት ጦጣ በታሪኩ እንዳደረገችው ሳይሆን በተቃራኒው ሁሉም ነገር ሰላም እንደሆነና እንዲያውም ምእራቡ አለምና ነጮች እንደ ቅዱስ መልአክ እየተሳሉ ነው የሚቀርበው፡፡ሰለ ሰብዓዊነጽም ሆነ ስለዲሞክራሲ እነሱ ነጮቹ የሚነግሩንን መልስን እንደ በቀቀን ማስተጋባት እንጂ የራሳችንን የዘመናት ታሪክና ማንነታችንን ለመመርመርና ለመረዳት ፈፅሞ አንፈልግም፡፡ለዘመናት በክርስትናውም ሆነ በእስልምናው አርስ በርስ ተግባብተን ተከባብረንና ተፈቃቅረን የኖርን የሃይማኖት ሀገርና ህዝብ ሆነን ሳለ በተቃራኒው ግን ሰብኣዊነትንና መፈቃቀርን ግን የመርዝ ጋዝ ከረጩብን ጣሊያኖች ዘንድ እንድንማር ነው የምንፈልገው፡፡የሀገርና የኢትዮጵያዊነት ጥልቅ ትርጉምና ፋይዳ ለተራና ዘላቂነት ለሌለው አላፊ ኢኮኖሚያዊ ጥቅምና ብልጭልጭ ነገር የተለወጠበት ዘመን የአሁኑ የአቦሸማኔ ዘመን አይደለምን?
ነው ወይንስ ትውልዱ ሰለጠነ እንዲባል ብቻ አንድ ላፕቶፕ ወይንም አይፖድና ሞባይል ከውጪ በተቀበለ ቁጥር በልዋጭ አርባ ጋሻ መሬት በልዋጭ እንዲሰጥ ነው የሚፈለገው?
ስለዚህም ፕሮፌሰር የተናገሩት ሌላው ነገር በቅርቡ ተግባራዊ ቢሆንም ባይሆንም ቅሉ ግን ጥሩና መልካም ተስፋ ሰጪ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ይህ አቦሸማኔ ትውልድ (Cheetah Generation) እና ጉማሬ ትውልድ (Hippopotamus Generation) በሚል የሚያቀነቅኑት የመከፋፈል አካሄድ የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን አደገኛ እንደሆነ ይሰማኛልና ባለማወቅ ከሆነ አሁኑኑ ያቁሙት፡፡የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አይነት እንዳይሆን ዘለቄታዊ መፍትሄው ደግሞ ከሁሉም በላይ የማሰብ ሃይላችንን ተጠቅመን በሰከነ መንገድ ማሰብና የበሽታዎችን አንድ ሺህ አንድ ምልክቶች ሳይሆን ዋና መንስኤዎች መረዳት ነው፡፡
ስለዚህም ይህች ሀገር ላለፉት 21 ዓመታትና አሁንም በቀጣይነት የግሎባል ካፒታሊዘም ኒዎ-ሊበራልና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክቶች በዚህች ሀገር ላይ ለዘመናት ጥረስ ነክሰው በነበሩት የባእዳን ሃይሎች ቅጥረኛ በሆኑት በመለስ/ወያኔ እና በኢሳያስ/ሻእብያ አማካኝነት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ተግባራዊ እየሆነባት ያለች ምስኪን ሀገር ናት፡፡ይህንን ትልቅ ስእል ለማየት ስንችል ብቻ ነው ለባእዳን ሃይሎችና ሀገር በቀል ቅጥረኛዎቻቸው ስውር አላማና ፍላጎት ሲባል አርተፊሻል በሆነ መንገድ እየተቀነባበረብን ያለውና ይህንንም ለማሳካት እንዲረዳ በከፋፍለህ ግዛው ስልት ተግባራዊ እየተደረገብን ያለው የብሄር የሃይማኖት የፆታ ወዘተ ግጭቱና ቀውሱ ዋና መንስኤና በተከታይም መወሰድ የሚገባው የመፍትሄ እርምጃ በግልፅ ሊታየን የሚችለው፡፡እጅግ የሚገርመው ይህንን የከፋፍለህ ግዛው ስልት ልባሙ አፄ ምኒልክ ከአድዋ ድል መልስ በጃንሜዳ ለኢትዮጵያ ህዝብ አስጠንቅቀው ነበር ይባላል፡፡ማለትም ባእዳን ሃይሎች እኛን የሚያጠቁን ባብዛኛው የውስጥ የእርስ በርስ አለመተማመናችንና መከፋፈላችንን መሰረት አድርገው እንደሆነ አስረግጠው ተናግረው ነበር፡፡ታዲያ ዛሬ ይህ በአቦሸማኔ የተመሰለው ዘመነኛ ልብ ያልገዛ ትውልድ ጭምር ከበስተጀርባ የተደገሰለትን የጥፋት ድግስ በቅጡ ሳይረዳ በቅጠረኞች አማካኝነት ዘመናዊ ቅኝ ግዛት ውስጥ ተዘፍቀን ሳለ ከ70 በላይ የፖለቲካ ፓርቲ እንደ እቁብና እድር መስርቶ ለዲሞክራሲ እታገላለሁኝ ሲል የታሪክ ምፀት ይመሰለኛል፡፡ቅድሚያ የመቀመጫየን እንዳለችው ዝንጀሮ ቅድሚያ ለምን እንደምንታገል እንኳን በቅጡ ያልገባን በመሆናችን “ልብ እንደሌለው እንስሳ ሆነ” የተባለው አባባል በእኛ የተፈፀመብን ይመስለኛል፡፡
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!