ጎ… ሽ መለስን መለስን መሰሉኝ!

October 2, 2012

አቤ ቶኪቻው

 

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ሳምንት ሆናቸው መሰለኝ። ይሁናቸው ገና ድርጅታቸው ከፈቀደ ሃያ አንድ አመት ይሆናቸው የለ…!? ዋናው የእርሳቸው ፀባይ ማሳመር ነው።ጎ… ሽ መለስን መለስን መሰሉኝ!

የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ  ከትላንት በፊት ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ድርጅት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አዳምጬ ነበር። እኔ የምለው አቶ መለስ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም እንዲህ ይመሳሰሉ ኖሯል እንዴ!? የቃላት አጠቃቀማቸው ራሱ ከሟቹ ጋር አንድ አይደል እንዴ…!? ግራ ገባን እኮ የሞተው ማነው…?

አቶ ሃይለማሪያም ደጋግመው እንደነገሩን የመለስን ራዕይ ለማስቀጠል የመጡ አንዳች አካል እንጂ ራሳቸውን የቻሉ ግለሰብ አይደሉም። እኛ “የለም እርሶማ የለውጥ ሃዋርያ ኖት” ብንላቸውም ነጠላ ሰረዝ “የለም እርሶማ የገንፎ ምንቸት ኖት” ብንላቸውም ነጠላ ሰረዝ “የለም እርስዎማ ኃይለማርያም ኖት” ብንላቸውም ድርብ ሰረዝ እርሳቸው ግን “እኔ መለስ ነኝ” እያሉን ነው። አሁን ትምህርተ ስላቅ ትምጣ¡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ “እነ እስክንድር ነጋን ባለ ሁለት ቆብ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ ሁለት ቆብ ማጥለቅ አይቻልም” ብለዋል። “ቀዩን መስመር ማለፍ ክልክል ነው” ሲሉም አስጠንቅቀዋል። “ብሎግ እና ዌብ ሳይት ዕገዳውም እንደሚቀጥል…” አርድተውናል፤ እርሳቸው መለስ እንጂ ኃይለማሪያም እንዳልሆኑ እያረጋገጡልን ነው።

እኛ  “ጎ…ሽ  መለስን መለስን መሰሉኝ!” ብለን ስናደንቅ ተስፋ ጥለውባቸው የነበሩ ሰዎች ደግሞ “እስከዚህም ፊት” በሚባል ደረጃ ዝቅ አድርገዋቸዋል።

በመጨረሻም፤

ጋሽ ደበበ ሰይፉ ጠብቋት፣ ጠብቋት፣ ጠብቋት ለቀረችው ልጅ የፃፋት ግጥም እንደሚከተለው ትነበባለች!

ጠብቄሽ ነበረ

መንፈሴን አጽድቼ

ገላዩን አጥርቼ

አበባ አሳብቤ

አዱኛ ሰብስቤ

ጠብቄሽ ነበረ

ብትቀሪ ጊዜ

መንፈሴን አሳደፍኩ

ገላዩን አጎደፍኩ

አበባው ደረቀ

አዱኛው አለቀ

ብትቀሪ ጊዜ የጣልኩብሽ ተስፋ

እኔን ይዞ ጠፋ

ደበበ ሠይፉ (1962)

2 Responses to ጎ… ሽ መለስን መለስን መሰሉኝ!

 1. opps Reply

  October 3, 2012 at 12:39 pm

  Hailemariam desalegn said meles was ”a great leader, africa’s father, brought prosperity to ethiopia, tireless leader who burned himself like a candle to make light to others”” bla bla bla.

  AS a starter, meles one of the worst fascist dictators who incited inter ethnic and racial, relegious violence and could not be described as the father of africa. he was a genocidal divisive, bigotted, hateful dictator. Hate ran through the blood of the fascist zenawi. That was his personality.

  HD said he is a christian. But we see him lying to the world by describing the genocidal dictator zenawi in the way he did.

  HD also said he is a carbon copy of zenawi. that means HD is describing himself as genocidal fascist who will continue to jail, torture and murder political opponents, journalists and innocent citizens who refuse to take his fascist orders. That means HD will continue to sell Ethiopian land to Arabs, indian, pakistani and other bidders by uprooting the poor Ethiopians from their ancestral lands and exposing them to hunger and death. Most will end up as farm labourers working for 50cents a day for pakistani and arab landlords.

  The struggle should continue to free ethiopia from the domination of ethno-fascist woyane.

 2. በለው ! Reply

  October 2, 2012 at 1:35 am

  “ልጁ ፍንጭቱ ነው ምልክቱ.ያዝ ያዝ ጠበቅ አርጉት.. ፈረሱ ላይ ስታወጡት… ብቻውን አይወጣም ይመከራል! ይደገፋል !ይቃኛል!ተባለ እርሳቸውም እንዳረጋገጡት ለመስዋትነት ወደ መሰዊያው ወስነው(ቆርጠው) እንደተቀመጡ ተናግረዋል።ስለ ዕራይ ማስፈፀም ሲናገሩም “ሳይበረዝ” ይቀጥላል ብለዋል እኔ የምለው ይህ ቃል በኑዛዜው ደብዳቤ ላይ ሰፍሮ ከታጋይ አዜብ ጋር ነው ያነበባችሁት? ? በእረግጥ አማኝም ታማኝም ነዎት ብዙ ነገር ከአቶ መልስ ጋር ሰርቼአለሁ ብዙ ነገር ተምሬአለሁ ብለዋል ። የሚመሩት በየትኛው ዲግሪና ማስተርስ ነው? ? አቶ መልስ መፅሐፍ ናቸው ያለው ማን ነበር? ? ከዚህ በፊት የመጀመሪያው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ሹመትና ህንድ ሀገር ሄደው ለጋዜጠኛ የሰጡት መልስ አስደንጋጭ እንደነበር ፅፌአለሁ።…የድሃ ቤተሰብ አርሶ አደሮችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በተመለከተ ሲጠየቁ “አሁን ባለው ትላልቅ ባለሀብት መሬቱን ገዝቶ ምርት ሲትረፈረፍ ትናንሽ ገበሬዎች ቀስ በቀስ ይጠፋሉ” ብለው ነበር። እኔም እንዲብራራ ጠየኩ “ይጠፋሉ ሲሉ ምን ማለት ነው? በመሳሪያ ይገደላሉ? ይፈናቀላሉ? በመርዝ ልትገሏቸው ነው? ወይንስ ልታቃጥሏቸው ?ጥያቄዬ በጠቅላይ ሚ/ርነት ማዕረግዎ ብቻ ሳይሆን የምህንድስና ትምህርትዎን አይመጥንም !! ከዘመኑ ማስትሬት በሀገራችን ማሰሮ የተሸከመች ጉብል በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የበለጠ ዕውቀት እንዳላት በቦታው ተገኝተን አረጋግጠናል። !! እባክዎ የሳቸው ዕራይ የሚለውን “በሕዝብ ፍላጎት እና ጠንካራ ተሳትፎ”! ሕዝብን አገለግላለሁ እያሉ ያሻሽሉት ።አራት ነጥብ።ብድር በምድር እንዳይሆን ለምክትል ጠሚኒስትርዎ (ድንብሹ) በሕገ ወያኔ አንቀፅ ፸፭(፩)(ሀ) እና ፪ የተጠቀሰውን ተግባራዊ ያደርጋሉ ማለት ነው? ?መቼም ሰውዬው ባይደይሙ ኖሮ ይቺን ቦታ በመተካካት አያገኟትም ነበር።በዚህ ሞልቶ በተረፈው ከደፋሪው በወረሱት ትምህርትዎ ይሁን እና ለመሆኑ “የሥልጣን መተካካት፣ የሥልጣን ሽግግር፣የሥልጣን ዝውውር(ሽግሽግ) (እርክክብ) አንድ ናቸው?? ሰላማዊ ሽግግር ስትሉ እርስ በእርስ ስትናጩ ከርማችሗል አሁን ተረጋጋችሁ ማለት ነበር?? ፪ወር ከ፳፭ ቀን እራሱን ያስተዳደረ ህዝብ ሊመሰገን፣ ሊከበር፣ ሊወደስ፣ ሊደመጥ፣ ይገባል።ከወዲሁ እሳቸው የሚለውን ስላቅ ተወት አድርገው እኛ ሁላችንም የኢትዮጵያ ሕዝቦች በጋራ ሆነን ሳንቧደን በህብረት ልንሰራ ልናድግ ይገባል በሳል አማካሪዎችን የህዝብ አመኔታና ድጋፍ ያላቸውን ያሰባስቡ ዕውቀታቸው በምላሳቸው የተለካ ግን ወደ መሰዊያው እንጂ ወደ ህዘብ ፍቅር አያደርስዎትም በዚች አጭር ቀን ለማማረር ሳይሆን የጎደለውን ለመሙላት ክፍተት እና ክፍት አፍ እንዳይበዛ ለማስታወስ ነው።ቀጥሎ የሚያዩትም ቪዲዮ በቤትዎ በሥራ ጓደኖችዎ እና በፀሎት ቤትዎ እንዳይደገም ከአደራ ጋር ነው።ይህ አምልኮት በኦርቶዶክስ እምነት በቃለ አዋዲም ይሁን በሕገ መንግስቱ አይጠበቀም የዘመነኞች የዘር ስብከትና “የአብዮታዊ ዴሞክራሲ”የፖለቲካ ክፍለ ጊዜ ቤተክርስቲያኑን ተከራይቶ ነው። ለመሆኑ የህ ሁሉ የተንደላቀቀውን ዲሞክራሲ ጥሎ እንዴት? ለምን?ከሀገረሩ ወጣ!!የኢህአዴግ ዲሞክራሲው ጨው በዝቶት? ወይንስ በጣም የተለጠጠ ሆኖ ነው እንዲህ ከል አልብሶ የሚያነፋርቃቸው? ? ? http://www.zehabesha.com/?p=10870

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *