ሁሌ መታለል አይቻልም

September 22, 2012

በይግዛው እያሱ

በመሰሪ ስልቱ የታወቀው ወያኔ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም በየጊዜው ራሱን እየቀያየረ በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በደልና ጭቆና ለመቀጠል በሞተው አባቱ እየማለ ለ 21 ዓመት በብቸኝነት ይዞት የነበረውን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ማእረግ ለሁላቸውም እንዲዳረስ በመሚስል በየአስር ዓመቱ እንዲቀየር ገደብ ጣልን ብለው አንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሁለት ተርም በላይ እናዳይቆይ ኢሕአዴግ ወስኗል ይሉናል::

ኢሕአዴግ የስልጣን ምደባ ለማድረግ ከመወሰን ባሻገር ስልጣን ለህዝብ እንዳይሆንና ሙጥኝ ያለበት ምክንያት በዴሞክራሲ ካለማመንም ሌላ ለህዝብ ጥያቄ መልስ ለመስጠት አለመፈለጉን ያሳያል:: በዓለም አቀፍ ህብረተሰብ ተቀባይነት ለማግኘት ብቻ በየስድስት ወሩ ሊቀይረው የሚችለውን የወያኔ የጋራ ስምምነት በኢትዮጵያ ቴሌቨዥን መስኮት ወጥቶ ይተርክልናል::ይህ ውሳኔ ቢያንስ ትክክል ይሆናል ብሎ ህዝብ ለጊዜውም ቢሆን እንዲታለል እንኳ ህገ መንግስቱን አሻሽሎ የጠቅላይ ሚኒስትሩንም ሆን የሚኒስትሮችን የቆይታ ጊዜ ከ 2 ተርም በላይ እንደማይሆን የሚያሳይ ቢያሰፍር የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም ከመፈለጉ የተነሳ ቢያንስ ከ 10 ዓመት በኋላ የሚመጣው  የኢሕአዴግ ቡችላ ጥሩ ሊሆን ይችላል ብሎ ስለሚገምት ጊዜ ወስዶ ሊጠብቅ ይችል ነበር::

ይህ ባልሆነበት ሁኔታ የድሮው ጠቅላይ ሚኒስትር የቀኝ እጅ እንደነበር የሚነገርለት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚንስትሩ አቶ በረከት ሰምኦን የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ሚኒስትሮች የስልጣን ዘመናቸው ከሁለት ጊዜ በላይ እንዳይሆንና እድሜያቸውም ከ 60 እንደማይበልጥ ተወስኗል  ብለው ይደሰኩራሉ::

አቶ መለስም በህይወት ቢቆዩ ኖሮ ከ 60 ዓመት በላይ ስለሚሆናቸው መቀጠል እንደማይችሉ በህይወት እያሉ ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር ይገልጻል::  መቸም አይሰሙኝ ብሎ::

ውድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሌ መታለል አይቻልም አንዴ ወይም ሁለቴ ሊሆን ይችላል::ስለዚህ ይህን መሰሪ ተግባራቸውን በውል አጢነንና መርምረን በመቃወም ሌላ 21 ዓመት የመከራ ዘመን እንዳይጫንብን የየበኩላችንን ሃላፊነት መወጣት አለብን:: ሓላፊነት ሲባል ከስር ሌላ ለመምራት ብቻ ሳይሆን ራስንም ለመምራት የተስተካከለና የጠራ መስመር ለመያዝ እንዲያስችል ሁኔታወችን ቀድሞ ጠንቅቆ ማወቅ ማለት ነውና ምን እየተፈጸመብን እንደሆነ ለማንም የተሰወረ ስላልሆነ:- ድምጻችንን የሚያሰማው ጋዜጠኛ አሸባሪ ተብሎ ለእስር ሲዳረግና በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መደራጀት መብት ነው ተብሎ የተደራጀው የተፎካካሪ ፓርቲ አመራር አሸባሪ ተብሎ ሲዋከብና ሲታሰር በእምነቱ ዙሪያ ስለመብቱ የጠየቀ አልቃይዳ ተብሎ ሲጨፈጨፍና ሲገደል ከ 10 እና 15 ዓመት በላይ በኖሩበትና ሀብትና ንብረት አፍርተው ከኖሩበት አገር ያለምንም ጥሪት ንብረቱ ተወርሶና ቤቱ ፈርሶ ወደ ምትሔድበት ሂድ ተብሎ ከ 20,000 በላይ የሚገመት የአማራ ተወላጅ ከደቡብ ሲፈናቀል በሶስቱም ማእዘናት መሬቱን ለውጭ ባለሀብት ለመቸብቸብና የግል ካዝናቸውን ለማድለብ ገበሬውን ከማሳውና ከቅየው ሲያፈናቅሉ መሬትን በሊዝ እየሸጡ ለባለስልጣን ሀብት ማፍሪያ ለማድረግ ከተሜውን በመልሶ ግንባታ ሽፋን ቤቱን በዶዘር እያፈራረሱ ከሚኖርበት ሲያፈናቅሉና ሲያሳድዱ ስናይ ኖረን አሁንም ይህንኑ ሊገፉበት ሲሰናዱ አሜን ብለን የምንቀብልበት ጊዜ ማብቃት አለበት::

ይህም ሊሆን የሚችለው የአምባገነኑ አገዛዝ እያሳደረብን ያለውን ጫና በመቋቋም ሙስሊሙ ህብረተሰብ የጀመረውን የመብት ጥያቄ በመደገፍ እንደዜጋ የሃይማኖት ነጻነት ይከበር በሚል ሁሉም ድጋፉን መግለጽና የኦርቶዶክሱንም ፓትሪያርክ ከፖለቲካ ነጻ የሆነ ምርጫ እንዲያደርግና እየተሳደዱ ያሉት የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ስቃይ ይቁም ገዳሙም እንደተከበረ ይቆይ የጭቁን አርሶ አደሩ መሬት ለውጭ ባለሀብት መሸጥ ይቁም በመጨረሻም አላግባብ የታሰሩ ጋዜጠኞች እነ እስክንድር ነጋ ና ሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ ህዝባዊ የሽሽግር መንግስት ይቋቋም በማለት በየተሰማራንበት ድምጻችንን ከፍ አድርገን እናሰማ:: አንድ ሆነንም እንታገል::

2 Responses to ሁሌ መታለል አይቻልም

 1. Abel Reply

  September 24, 2012 at 2:31 am

  Mr. Yigzaw, it is w awonderful write up. Yes I agree with you what you said about as “the name change doesn’t help to answer the question of the people”. We all demand, or, Ethiopians’ demand more than a change of names. We all demand the change in Constitution and policies that EPRDF is following on Ethiopia. Freedom of Expression, equal justice, independent Policy and Military institutions, and also independent election board. Gov’t should allow plain field to play freely, and let the people to elect its own leader. If not this happens, Ethiopians will never sleep. We expect this from the new Prime Minester as soon as possible. He should use his Constitutional right to enforce his power on each policies and made Ethioipieans satisfied with new leadership.
  I like your argument and advice to the people of Ethiopia to know how EPRDF is trying to cheat the people.

  Abel Tsium

 2. Anonymous Reply

  September 23, 2012 at 2:42 am

  የወያኔ አጨብጫቢዎች አለቃቸው ከዚህ አለም በሞት ሲለይ “ጀግናው: የጀግኖቹ ጀግና: ታላቁ መሪያችን” እያሉ ልክ እንደሰሜን ኮሪያው መሪ እያሞገሱት ሲሸኙት ምን ቢያደርግላቸው ነው እንዲህ ያሉት? ያሰኛል:: በታሪክ እንደሚታወቀው ሃገራችን ከአጼ ምኒሊክ በኋላ ለሃገር እድገት ራእይ የሌላቸው መሪዎች ለአንድ ምእተ አመታት መርተዋታል:: ከሁሉ የሚያስደንቀው ግን የወያኔ ቁንጮ የነበረው መለስ ነው:: የሰራው ስራ ሁሉ ሃገርንና ህዝብን የሚያፈራርስ ጥቂቶች ተጠቃሚ የሆኑበት ለአንዱ እናት ለሌላው እንጀራ እናት የሆነች ሃገር የፈጠረ ስው ነበር:: ሕዝቡ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ህዝብ በመሆኑ ጥዋት ወጥቶ ማታ ወደደሳሳ ጎጆው በሰላም የሚገባ: መብቱ ሲገፈፍ አቅም አጥቶ “እግዚአብሔር ያውቃል ግድየለም” የሚል ሕዝብ ነው:: አመራር የሚያስጨንቀውና የሚያሳስበው መንግስትማ ለመብቱ የሚከራከር ሕዝብ በሰላማዊ ሰልፍ: በሬድዮና: በጋዜጦች ብሶቱን እያሰማ ሌላውን ሲቀሰቅስ “እንዴት አድርጌ መፍትሔ ላምጣ?” እያለ የተለያዩ የመፍትሔ ሃሳቦችን ማውጣትና ማውረድ ይጀምራል:: ዲሞክራሲ በሰፈነባቸው ሃገራት መሪዎች ስልጣን ላይ የሚወጡት ሊመቻቸው ሳይሆን እንደሻማ እየቀለጡ ለሌላው ሊያበሩ ሕዝባቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በቅንነት ሊያገለግሉ ነው:: የኛዎቹ ግን ለመብቱ የሚነሳን ሕዝብ በጥይት እየገደሉና ህዝቡን በችጋር እየጠበሱ ቤተመንግስታቸው ውስጥ ተከትተው የምቾት ህይወትን ይኮመኩማሉ:: እነርሱ አይደሉም: ልጆቻቸው ብሎም; ስማቸውን ከፍ እያደረገ የዘፈነ አዝማሪም ከምቾት ህይወት መቋደሱ አይቀርም:: ሲሞቱ ደግሞ የሌለ ቅጽል ስም እየወጣላቸው ያላደረጉትን አደረጉ እየተባለ ይዘፈንላቸዋል:: ከጥቂት ህሊና ካላቸው ሰዎች በስተቀር አብዛኛው እየተግደረደረም ቢሆን የጥቅማቸው ተቋዳሽ መሆኑ አይቀሬ ነው:: በውሸታሞች መሃከል እውነተኛ ሰው እንደእብድ እንደሚታየው አልፈልግም ያለውን ሰው ከሌላ አለም እንደመጣ ፍጡር በማየት ግራና ቀኙን ገልመጥ ብለው ወደፓርቲያቸው ጎራ ለጥቅማቸው ሲሉ የተቀላቀሉ ወይም ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲል የወገኑ ቤታቸው ይቁጠረው:: እንደነእስክንድርና አራጌ ያሉ ብዙ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን ደግሞ እንዲህስ አድርጌ ህሊናዬን ሼጬ ከምኖር ለእውነት ቆሜ መከራን ብቀበል ይሻላል ብለው ቃሊቲ እስር ቤት ተወርውረዋል:: እነርሱ ምንም የሚከሳቸው የህሊና ወቀሳ በውስጣቸው የለም:: ይልቅስ በነጋ በጠባ ህሊናቸው እየወቀሳቸው በመለኪያ ሃይል ያሉ ሰላማቸውን ያጡ እንደአሸን ናቸው:: እውነት ትዘገያለች እንጂ አሸናፊ መሆኗ አይቀርም:: ምክኒያቱም የእውነት አምላክ ውሎ አድሮ ትክክለኛውን ፍርድ መስጠቱ አይቀርም እየሰጠም ነው ያለው:: ያኔ ለእውነትና ለውሸት የቆሙት ማንነታቸው መለየቱ የማይቀር ነው:: እስከዚያው ድረስ ባለጊዜውም ይፈንጭ: ባለጊዜ ያልሆነውም ባይተዋር ይሁን::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>