ዜና በጨዋታ፤ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ጥያቄ ዛሬ ቀጥሎ ዋለ

September 21, 2012

አቤ ቶኪቻው

ላለፈው አንድ ወር አካባቢ የጠቅላይ ሚኒስትሩ “ግባተ መሬት” እስኪፈፀም ድረስ እንዲሁም መንግስት ሀዘኑ በረድ እስኪልለት እና ለቀስተኛ እንግዶች እስኪሸኙ በሚል ጋብ ብሎ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ጥያቄ በዛሬው ዕለት በርካታ አማኞች በተገኙበት በአንዋር መስጊድ ተከናውኗል።

ሙስሊም ኢትዮጵያውያኖቹ በዛሬው የተቃውሞ ውሏቸው የታሰሩ በርካታ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እና ኡስታዞች እንዲፈቱ እንዲሁም በቀበሌዎች ሊደረግ የታሰበው የመጅሊስ ምርጫ ዕውቅና የማይሰጡት መሆኑን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ገልፀዋል።ዜና በጨዋታ፤ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ጥያቄ ዛሬ ቀጥሎ ዋለ

ልብ አድርጉልኝ 1

አነዚህን ወንድሞቻችንን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቅሶ ቀለል እኪል ብለው የወሰዱት የስክነት እርምጃ የሚደነቅ ነው። እነዚህን ወንድሞች ነው እንግዲህ መንግስት ባለፈው ግዜ “ሆን ብላችሁ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባን ለማወክ አስባችኋል” ብሎ በአስለቃሽ ጭስ እና በአስለቃሽ ዱላ እየዬ ሲያስብላቸው የነበረው። ታድያ ብዙ መራቂ አባቶች አሉን አይደል እንዴ “እንዳስለቀሳችሁን እርሱ ያስለቅሳችሁ” ብለው መንግስታቸውን መረቁ… አፍታም አልቆየ ወድያውኑ የመንግስት ዋና ዋና ሰዎች እየዬ አሉ።

ልብ አደርጉልኝ 2

አሁንም ብዙሃኑን ጥቂት ማለት አደጋው ብዙ ነው። እናም መስማት ይበጃል። አለበለዛ ማለቅስ ይመጣል… “ጥንቱን ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማለቀስ” ይል ነበር አባቴ… እናም የመንግሰት ዋና የስራ ሂደት ባለቤቶች ሆይ እባካችሁ መጥናችሁ ደቁሱ…!

የቃላት መፍቻ

በዚህ ወግ አግባብ “መደቆስ” ተብሎ የተገለፀው ችግሮችን ለመፍታት የሚደረግ የሰለጠነ ዘዴ ነው። እደግመዋለሁ መንግስታችን ሆይ አሁንም ባለችው ጊዜ እባክህ መጥነህ ደቁስ…!

ዘግይቶ በደረሰኝ ዜና ፖሊስ ዛሬም በደሴ ሙስሊም ምዕመኑን ሲደበድብ ውሏል። ይህ አይነቱ “መደቆስ” ይዳርጋል ለማልቀስ…! ተዉ ልብ ግዙ….! የልብ ገበያ የት እንደሆነ እንጠቁማለን…!

One Response to ዜና በጨዋታ፤ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ጥያቄ ዛሬ ቀጥሎ ዋለ

  1. belachew Reply

    September 21, 2012 at 7:49 pm

    Abe min godelebeih. Bicha le machester feremish aydel. Bilatbilt.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>