የሃይለማርያም አንገት (ከተስፋዬ ገብረአብ)

September 20, 2012

(ከተስፋዬ ገብረአብ)

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ፕሬዚዳንት ሆነው በተመረጡ ጊዜ በመከላከያና በሲቪል የህወሃት አባላት ዘንድ አቧራው ጨሶ እንደነበር አስታውሳለሁ። አባላቱ የፖለቲካውን ጨዋታHailemariam Desalegn new Ethiopian PM አልተረዱትም ነበር። በወቅቱ የነጋሶ ሹመት የይስሙላ መሆኑን ማስረዳት፣ ለህወሃት መሪዎች ፈተና ሆኖባቸው ነበር። ህወሃት አሁንም ተመሳሳይ ችግር ገጥሞታል። ምናልባትም በቀጣዩ የሃይል አሰላለፍ የህወሃት የበላይነት እንደተጠበቀ መሆኑን ማሳመን ካልቻሉ መፈንቅለ መንግስት ሊያጋጥም ይችላል።

የህወሃት ሲቪልና የመከላከያ አባላት በአብዛኛው፣ “የኢትዮጵያ ስልጣን ሙሉ በሙሉ ለኛ ይገባል” ብለው ያምናሉ። ለሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የሚሰጡ ሹመቶችን በቀና አይመለከቱም። “አቅም የላቸውም፣ ሰነፎች ናቸው፣ ሌቦች ናቸው” ይሏቸዋል።

እዚህ ላይ እውነት አላቸው።

ህወሃት በአብዛኛው ወደ ስልጣን የሚያመጣቸው፣ ደካሞችን እየመረጠ ነው። አባተ ኪሾን ራስህ ሾመህ፣ አባተ ኪሾን መክሰስ ግን ስላቅ ነው። እያወቅህ ለምን ከአቅሙ በላይ ስልጣን ትሰጠዋለህ?

ከሰሞኑ በተፈጠረው ሁኔታም በህወሃት ካምፖች አካባቢ አለመረጋጋት መስፈኑ እውነት ነው። በአመራሩ ደረጃ፣ “መከላከያ፣ ደህንነት፣ ውጭጉዳይ እና ኢኮኖሚውን ከያዝን ያለችግር መቀጠል እንችላለን” የሚል እምነታቸውን ማሰማን ስለመቻላቸው ግን ከወዲሁ ርግጠኛ መሆን አይቻልም። በሂደት የሃይል ሚዛኑ ሊቀለበስ ይችላል። ከህወሃት ባሻገር ያሉት አባል ድርጅቶች፣ በራሳቸው ጭንቅላት መመራቱን ሊለማመዱ ይችላሉ። መለስ አለመኖሩ ድፍረታቸውን ሊጨምርላቸው ይችላል። የህዝብ እና የአለማቀፉ ህብረተሰብ ግፊት በራሳቸው ማሰብ እንዲጀምሩ ሊያግዛቸው ይችል ይሆናል።

ሃይለማርያም ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን የበቃው በመለስ ስለተመረጠ ብቻ ነው። ሃይሌ የውሃ ባለሙያ ነው። በአንድ ውሱን ሙያ መሰልጠኑ ለሃገር መሪነት ብቁ አያደርገውም። ፖለቲካም ሙያ ነው። ሙያ ብቻ ሳይሆን ተሰጥኦም ነው። ሃይሌ የህክምና ባለሙያ እንዳልሆነው ሁሉ፣ ለፖለቲካው ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል። ፕሮፌሰር አስራት ያልተሳካላቸው በወያኔ አፈና ብቻ አይደለም፤ የፖለቲካ ጨዋታውን አሻጥር አላወቁበትም። እየተንደረደሩ ከግንቡ ይጋጩ ነበር። ከባድ ነፋስ ሲመጣ ማጎንበስ ይገባ ይሆናል። መለስ በጣም ጮሌ ነበር። ማጎንበስ ይችልበት ነበር። ምርጫ 97 ጠርጎት ሊሄድ ጫፉ ላይ ሲደርስ፣ አንገቱን ዝቅ አድርጎ አሳለፈው። በርግጥም ተቃዋሚዎችን ለድርድር በመጥራት፣ ከባዱን ማእበል ማሳለፍ ችሎአል። ማእበሉ ካለፈ በሁዋላ፣ ቅንጅቶቹን ሰብስቦ አሰረ።

የሃይለማርያም የግል ባህሪ የኢትዮጵያን ውስብስብ ፖለቲካ ለማስተናገድ አቅሙ ያጥረው ይሆናል። ኢትዮጵያ መሰረቱ በተደላደለ ህግ የምትመራ ሃገር ብትሆን ኖሮ፣ እንኳን ሃይለማርያም፣ ሃይሌ ገብረስላሴም ሊመራት በቻለ ነበር። በዚህ ወቅት ህግ እያነበብክ ብቻ ኢትዮጵያን መምራት አይቻልም።

ሃይለማርያም የመለስን ቢሮ ተረክቦ ስራውን ሲጀምር፣ ከመለስ ጠረጴዛ ላይ ተቆልለው የሚጠብቁት በርካታ ስራዎች አሉ። ተቃዋሚዎች እርቅ እየጠየቁ ነው። የፖለቲካ እስረኞች ጉዳይ አለ። ቀጣዩ ምርጫ እየመጣ ነው። የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ጥያቄ ገና አልተፈታም። የኑሮ ውድነቱ እያሻቀበ ነው። ሙስናው ጣራ ነክቶአል። አበዳሪዎችና ለጋሾች እጅ የመጠምዘዝ ልማዳቸውን አጠናክረው እየመጡ ነው። መለስ አቅዶት የሄደው የግንባታ ስራ ጥናት የጎደለው ቅዠት ይመስላል። የምእራባውያን መሪዎች እና የስለላ ድርጅቶች ስልክ እየደወሉና ቢሮው እየመጡ ጥያቄዎች ያቀርቡለታል። ሃይሌ እንዴት ያስተናግዳቸው ይሆን?

“አንድ ጊዜ ይጠብቁኝ፣ ነገ ይደውሉ እባክዎ?፣ ተመካክሬ ልንገርዎ!” እያለ እስከመቼ ይሸኛቸዋል?

ኤታማዦር ሹሙ እና የደህንነት ዳይሬክተሩ አንዳንድ አስደንጋጭ ድርጊት ሊፈፅሙ ይችላሉ። ስለተፈፀመው ድርጊት ማብራሪያ የሚጠየቀው ግን ሃይለማርያም ይሆናል።

“ትናንት አስር ሰላማዊ ኦጋዴንያን ተገደሉ። ማብራሪያ?” የሚል ጥያቄ?

ሃይለማርያም፣ “ጌታቸው አሰፋን ያነጋግሩ” ማለት አይችልም።

ነገ አንዱ አበዳሪ መጥቶ፣

“የፕሬስ ህጉን ካላሻሻላችሁ፣ ይህን ብድር አንለቀውም” ሊለው ይችላል።

“እስኪ ከበረከት ጋር ተነጋገሩበት” ይሆናል የሃይሌ ምላሽ።

የመለስ ሞት ከተጠበቀው ጊዜ በጣም ቀድሞ በመምጣቱ፣ ተደነጋግረዋል። መለስ ቢሞት ሊያደርጉ ስለሚችሉት ነገር ቀደም ብለው አላሰቡበትም፣ አልተዘጋጁበትም። መለስ ሲሞት ከያቅጣጫው ግፊቱ በረታባቸው። ስለዚህ በዚህ መልኩ ሸፋፍነው አገር እንዳይተራመስባቸው ሞካክረዋል። በሚፈልጉት መልኩ ስልጣናቸውን እስኪያደላድሉ፣ አገሪቱን በኮሚቴ ሊመሩ ወስነዋል። የኮሚቴ ስራ የተሳካ የሚሆነው የኮሚቴው ሰብሳቢ ጠንካራ፣ ተፅእኖ የመፍጠርና የማዳመጥ አቅም  ካለው ብቻ ነው። 44 መርፌዎች፣ አንድ ማረሻ አይወጣቸውም።

አገር እንዲህ ሊመራ አይችልምና በዚህ መንገድ ብዙም ሊቀጥሉ አይችሉም። እና ታዲያ የሃይለማርያም እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? ክፉ አልመኝለትም። በተፈጥሮው ጥሩ ሰው ስለሆነ እንዲጎዳ አልሻም። ሆኖም ሃይለማርያም ጭንቀታም እንደመሆኑ፣ ደግና ቀና የሚያስብ እንደመሆኑ፣ በታወቁት ጭንቀት ወለድ በሽታዎች ሊጠቃ ይችላል። እና ሁለት እድሎች ይገጥሙታል። የህወሃት ሰዎች ዳግም አንሰራርተው ራሳቸውን በአዲስ መልክ ማደራጀት ከቻሉ፣ “የአቅም እጥረት” በሚል ሃይሌን ያሰናብቱታል። ካልሆነ እሱ ራሱ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለማስገባት ይገደዳል። መጪውን  ስምንት አመታት በኮሎኔል መንግስቱ ቢሮ ውስጥ ይቆያል ብዬ ግን አልጠብቅም።

ይህ ኢትዮጵያ ነው። የምኒልክ ዙፋን ቀለሙ ቀይ ነው። አማን ሚካኤል አንዶም፣ ተፈሪ በንቲ፣ ተፈሪ መኮንን፣ እያሱ ሚካኤል፣ አጥናፉ አባተ፣ በዚህ ቀይ አውሬ ተበልተዋል። ሃይለማርያም ብዙም ሳያስብበት እንደ በግ እየተጎተተ አንገቱን ጊሎቲኑ ስር አስገብቶአል። “ጌታን የተቀበለ ሰው ስለሆነ፣ የእየሱስ ክርስቶስ መንፈስ በላዩ ላይ አድሮ ሃይል ይሆነዋል” ብለው የነገሩኝ ሰዎች አሉ። እውነት ያድርገው! ምናልባት የዚህች አገር የዝንተአለም ችግር በሃይለማርያም በኩል ይወገድ ይሆናል። እግዚአብሄር ሰጠ፣ እግዚአብሄር ነሳ። እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን። አሜን!

11 Responses to የሃይለማርያም አንገት (ከተስፋዬ ገብረአብ)

 1. gudu Reply

  September 28, 2012 at 5:55 am

  ወያኔ የኮክብ ልማታዊ አልቃሾችና ልማታዊ አስለቃሾች ሽልማት እያዘጋጀች መሆኑ ተሰማ:: የኮክብ ሽልማቱ በብሂራዊ ደረጃ የሚደረግ ሲሆን ሽልማቱም ለአሸናፊ ግለሰቦች በአነስተናና ቲቃቀን ለተደራጁ የአስለቃሾች ማህበራት አሸናፊዎች ለአሸናፊ ወረዳዎችና ክልሎች እንደሚሰት ይነገራል:: በግለሰብ ደረጃ ህይሌ ገ/ስላሰ በወረዳ አድዋ በክልል እንደተለመደዉ ትግራይ ተሸላሚዎች ይሆናሉ ተብሎ ይተበቃል:: በአነስተናና ቲቃቀን ክተደራጁት የአስለቃሽ ማሀበራት መካከል ደግሞ አንድ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ተክለ ሃየማኖት የምባለዉ ሰፈር ያለ የአስለቃሾች ማህበር ሳይሆን እንደማይቀር ተገምቶአል:: የልማታዊ አልቃሾችና ልማታዊ አስለቃሾች ኮከብ ተሸላሚዎች የሽልማት ስነ ስሪአትም የመለስ የሃዉልት ምረቃዉ ዕለት አብሮ እንደምከናወን አንዳንድ ዘገባዎች ያመለክታሉ::

 2. abe nebro Reply

  September 24, 2012 at 10:09 am

  yhe sew sile Ethiopia and tiro neger tsifo ayawkim..eski liteykh lemehono hagerachin yhen yahel bedilah neber ?ende home less

 3. A. Reply

  September 21, 2012 at 2:48 pm

  When H/M came to federal government from south religion president position, the reason given was that he was suffering from severe hypertension and he was unable to do his job in stressful and pressing conditions. I wish someone would investigate this further and tell us about his health conditions. If indeed he has a serious blood pressure problem, I am wondering how he would be able to run the PM office which probably is more demanding than his older post…Is there something that Bereket is cooking?

 4. Sergute Selassie Reply

  September 21, 2012 at 9:19 am

  ከዬት እንደምጀምር አላውቀውም። ዝንቅቅ የሆነ ስሜት ያለብኝ ይመስለኛል። መከፋትም። የተከበሩ ፕ/አስራት ወ/ዬስ የመጀመሪያውን እሳተ ጎመራ ፊት ለፊት የተጋደሉ። በጣም ግልጽ፣ ቀጥተኛና እውነተኛ ሰው ነበሩ። ሞታቸውን በወቅቱ የሰሙቱ የወቅቱ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ተጠሪም ሰፊ የሆነ ሀተታ ሰጥተውበታል። ትውልድ የማይተካቸው ድንቅ መሪ ነበሩ። በሙያቸውም እጅግ ተወዳጅ ነበሩ። በሙያቸው ካገኙት ተደመጭነት በላይ በላይ ደግሞ በፖለቲካ ሰውነታቸው የወገን ህዝብ ዕንባ ሰቀቀን ያገባኛል ብለው የተሰለፉበት የፖለቲካ ዘርፍ መጠን የለሽን የህዝብ ፍቅር በገፍ አፍሰውበታል። እኔ በአእምሮ ጋዜጣ „እንኳንም ታሰሩ“ ብዬ የጻፍኩት ነበር (በሥርጉት እርቂሁን – ዬብዕር ስም) አበድሽ እስክባል ድረስ። ስለምን በእኔ እድሜ ያን ያህል የህዝብ ፍቅር ዕውን ሆኖ በተጨባጭ ያየሁበት የመጀመሪያ ገጠመኝ ስለነበር። በፍርድ ቤቶች አካባቢ የነበረው ህዝብም ተቀስቅሶ የወጣ አልነበረም ከሞት ጋር ፊት ለፊት የተጋፈጠ ነበር። ሞትን አውቆ የተመመ ዬነፃነት ራህብተኛ ህዝብ ነበር። ክቡርነታቸው ሲያልፉም አጋጣሚ አድሎኝ በፍትኃተ ጸሎት ሥርዓታቸው ላይ ተገኝቼ ስለነበር ትውልድ ከቶውንም ሊተካቸው የማይችል በሚል አንድ ዘገባ በዓለምዓቀፍ ሚዲያ ማቅረቤን አስታውሳለሁ። ክቡርነታቸው … ሰማዕት፤ አርበኛና የዕውነት ሐዋርያ ነበሩ።
  ሌላው ቀኑን አላስተውሰውም „ኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ሰው የላትም“ የሚል እርእስ ያለው አንድ የግጥም መጸሐፍ እንደ ወጣም ያነበብኩ ይመስለኛል በቅርቡ። ይህ እርእስ ለእኔ ፈጽሞ ያልተመቸኝ ነበር። ሌላው ይቅርና እስር ቤት ያሉ ወገኖች ሰዎች አይደሉንም። ሕዝብ ማለት እኮ የሰዎች ስብስብ ማለት ነው። የሰዎች ማህበር ማለት ነው። ዬአንድ ሐገር ሕዝብ ማለትም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እውቅና ባለው የመሬት ክልል የሚኖር ማለት ነው። በቃ። ሰው ከሌለ ሕዝብ የለም። አንዳንድ ጊዜ ከእውነት ጋር እንላተማለን መላ ሕይዎታቸውን ሁሉ ለህዝብ ዕንባ ተቆርቋሪነት የሚደክሙ፤ ሌት ተቀን የሚሰሩ ልጆች አሏት ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ ዛሬም። አንድ ነገር ፕ/ባራክ ኦባማን ከስልጣን ያወጣው ብቃታቸው ብቻውን፤ እእ! ዲታነታቸው እእ! ፤ ጥቁርነታቸው አይታሰበም~ ሥርዓቱ ስለተዘረጋ ብቻ ነው። ሥርዓቱ ይዘርጋና ኢትዮጵያ ሰው ስታጣ እናያለን። ኢትዮጵያ ሰው አላት … አራትዓይናማ!
  ሁለተኛው ነገር ከተቃዋሚ የፖለቲካ መሪዎች ሀገር ውስጥ የፖለቲካ ሳይንስ ሙሑር ረ/ፕ መራራ ጉዲና ብቻ መሰሉኝ። ሌሎችም በጣም ጥቂት ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል… እኔ የማላውቃቸው … የሆነ ሆኖ ቀደም ባለው ጊዜ አፄ ቴወድሮሰ፤ አፄ ሚኒሊክ፤ እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ዘውዲቱ … አሉላ አባ ነጋ በላይ ዘለቀ … አጼ ዮኋንስ … ዘመነ መሳፍነትንም በምልሰት ቃኙት የትኛው ጀግና መሪ ነው በፖለቲካ ሳይንስ የተመረቀው ….
  ሌላ ደግሞ … ካነበብኩት … መላ እያጣን ተቸገርን። ስለ ሰባዕዊነት ተቃዋሚ ኃይሎች መሪዎች አስተያዬት ሲሰጡ የሰባዕዊ መብት ተሟጋች እንጂ ለመሪነት እንላላን፤ እንደ ፖለቲካ ሙሁር ማብራሪያ ሲሰጡም በመሰሉ እንፈርጃለን፤ እንደ ፖለቲካ ሰውነት የቅራኔ አያያዞችን ሲተነትኑ እና ሲያብራሩ ደግሞ የፖለቲካ ሙሁር ተንተኛ እንጂ እንደ መሪ አልነበረም ትንተነው እንላላን። እኛ አዎን እኛ ለሰውም ለእግዚአብሄርም የማንመች ስለሆንን ነው በሙጃ 21 ዓመት የተገዛን … አንድ መሪ የህዝብ መብት ገፋፋ የሚያንገበግበው ፍጹም ሰባዕዊ ፤ ሙሁር፤ የፖለቲካ ተንታኝ ቢሆን ያስደስታል እንጂ ምን ያሰከፋል? ብንታደልማ እንደነዚህ ያሉ ወገኖች ሥርዓቱ ቢዘረጋ ካለምንም እንክን ቦታው ቢይዙ ማን እንደኛ ጌታ …
  … ሌላው የወያኔ ሥርዓት ሁለንትናው የዛቀጠ ነው። በሁሉም ዘርፍ ጎሳ ላይ ያለ ስለሆነ ኋለቀርነት የሰፈነበት ነው። ኋላቀርነት ማለት በሁሉም ዘርፍ ያልጠመጣጠነ እድገት ያለበት ማለት ነው፤ ስለዚህ ለኢትዮጵያ የሚያሰፈልጋት የሰለጠነ ሥርዓት ለማምጣት ከጎሳ የዘለለ ሥርነቀል ለውጥ … ብቻ!
  እንደ ማጠቃለያ … „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል“ (ምሳሌ 16 ቁጥር 9) እግዚአብሄር እራሱ ባለበት ታዕምር ላይ ስለወያኔ የስልጣን ሹኩቻ፤ ትርምስ ምንም ትንተና አያሰፈልግም። ጊዜም ማባከን። ይልቅ ሊሰሩ በሚገባቸው ህዝበ ጠቀም ተግባራት ላይ ማተኮሩ ይበጃል። ዛሬ ጸጥ ለጥ ብሎ የሚሰራው የወያኔ ህግ አንድ ቀን ይጣሳል“ እንደ እኔ ወያኔ በመሪው ሞት ተዝካሩን ያወጣ ይመስለኛል። ነገ ዕድል የለውማ … ! ሰባት ዓመት? እንዴት ነው ነገሩ …. በፍጹም! … ረሃብ ቀድሞ መትረዬሱን ያፈነዳዋል … አትጠራጠር ጋዜጠኛው … ለሀገር ተቆርቋሪነት ለደም ዕንባ አጋርነት፤ ሀገርን ከጥፋት ለመታደግ ደግሞ የፖለቲካ ዲፕሎማ አያስፈልግም ….
  ጨረስኩ ለዛሬ !

 5. Tejo Reply

  September 21, 2012 at 4:32 am

  As most notice even from the elected PM brief, He said the “collective leadership” to be planted among the EPRDF clones. Does that mean, I am not by myself, why we cannot listen to him? Respecting his personality, belief, and political experience the diaspora community or the local has to give this golden opportunity to lead the country. Are we not responsible to show, direct and sometimes from the distance to teach him. We heard he was a good student, He should learn it by now how to manipulate those sharks.

 6. Askale Dama Reply

  September 21, 2012 at 3:24 am

  The 4 ethnic parties of EPRDF are trying to create a different type of regime, post Meles. Meles created one-man rule tyranny or dictatorial type of regime. He became the law and the procedural regime. He became the purpose of the state, the vision of the state. These are 2 elements of any regime – its institution or procedures and its substantive purpose. These are gone. The folks now needs to structure a regime (form of rule) – who has what office, how and for how long. This is going to be a Junta type regime. They call it collective leadership. It simply means a committe with a weak figure head HM. The state purpose will slowly change. Development is going to slow down or stop. The regime is going to be in confusion, slow, uncertain and full of distrust. All of these are intensified by the pressure of the opposition from below. The most likely development is some kind of mass driven reform of the system or a military coup leading to a messy civil war and chaos. No single bandit is the boss. Group of bandits cannot loot peacefully for long. This is the law of social dynamics. Intelligent elements within EDRDF will begin to plan things with the opposition and stay ahead of the game. The intelligent political practice resides in the department of regime change and soft landing, not a new authoritarian growth. Authritarian growth has come to an end. We are soft landing.

 7. Walelgne Mekonnen Reply

  September 20, 2012 at 5:11 pm

  Thank you Mr. Tesfaye for briefing us in 3D way. In my opinion you should not criticize the TPLF/EPRDF or woyane because you have been working all bad and good with them for long time, but you wake up out of anesthesia with unpublicized and unclear conflict between them, just like Tamirat Layine (the formerly beast later became priest).

 8. Anonymous Reply

  September 20, 2012 at 3:18 pm

  ተስፋዬ የፖለቲካ ትንታኔህ ጥሩ ነው:: ባለፈው የጻፍከው የስራ ድልድሉ ሰምሮልሃል:: ነገር ግን አሁን የሰጠኽው ፍንጭ ግን አስፈሪ ነው:: አስፈሪነቱ ለአቶ ሃይለማሪያም ብቻ አይደለም:: ለኢትዮጵያም ጭምር ነው:: እስኪ ግዜ እንስጠው የሚሉትን ተቃዋሚ ሃይሎችንም የሚያሳስብ ነው:: በርግጥ እንዳልከው ፈተናው ቀላል አይሆንም:: ነገር ግን ጥበበኛ መሆን ይጠበቅበታል:: የርሱ ሹመት ደግሞ የዶ/ር ነጋሶ አይነት የወያኔ ሺወዳ አለመሆኑን ለህዝቡ ማሳየት አለበት:: የመንግስት ግልበጣ እንዳይኖር መዘጋት ያለባቸው Loop holes መዘጋት ያለባቸው ይመስለኛል:: ያልጠረጠረ መመንጠሩ አይቀርምና:: የሚኒሊክ ወንበር ግን ሁሉንም አትበላም:: መንግስቱ ለ17ዓመታት ተቀምጦባት ይኽው የሰላም አየር ይተነፍሳል:: ወንበሯ ላይ በጉልበታቸው ሳይሆን ከህዝብ የወጡ በህዝብ የተመረጡ ለህዝብ የሚሰሩ መሪዎች የሚቀመጡባት እንድትሆን ትግላችን ለአፍታ እንኳን መቆም የለበትም::

 9. Henoke Yeshetlla Reply

  September 20, 2012 at 2:58 pm

  You are mini melese! another monster!!!!
  henoke Y

 10. Abesha Reply

  September 20, 2012 at 2:53 pm

  @ Ygermal
  ኅ/ማሪያም የውሃ ባለሞያ ነው መለስ የምን ባለ ሞያ ነበር?
  መለስ በጣም ጮሌ ነበር። ማጎንበስ ይችልበት ነበር።
  Please read between the lines before blaming the writer!!

 11. ygermal Reply

  September 20, 2012 at 12:44 pm

  በእውነቱ በጣም ጥሩ ጽሁፍ ነ ው ተስፋዬ የጻፍከው ነገር ግን እንዳንዴ ቅብጥር ጥር ምታደርገው ነገር ስለኢትዮጵያ ያለክን እመለካከት በጥርጣሬ እንዳይ ያደርገኛል ቢያንስ ትንቢትህ በመልካም ይሁን:: / ኅ/ማሪያም የውሃ ባለሞያ ነው መለስ የምን ባለ ሞያ ነበር? ፖለቲካን በእናቱ ማህጸን ተለማምዶስ የወጣስ ማነው? የወደፊቱን ደግሞ ለማሳየት ይቅርና እራቅ እድርገህ ማሰብ እንኳን የቻልክ እይመስለኝም ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>