ከኢትዮጵያ ተስፋ ወጣቶች ድርጅት የተሰጠ መግለጫ

September 19, 2012

አገራችን ኢትዮጵያ በየዘመኑ ተነስተው የወደቁ የአገዛዝ ስርአቶች አስተናግዳለች፤ሁሉም አገዛዞች በዘመናቸው ህዝቡን በተለያየ መልኩ ገዝተዋል። ህዝባችንም ላልተስማሙት ገዢዎቹEthiopian Tesfa Youth በየወቅቱ ተነስቶ አስፈላጊውን አመጽ በማካሄድ ለውጥ አምጥቷል ። ዛሬ በ፳፩ኛው ክፍለ ዘመን አለም በዲሞክራሲ እና በሰብአዊነት የተሻለ ደረጃ በደረሰበት ግዜ አገራችን ኢትዮጵያን እየገዙ ያሉት የባንዳውና ዘረኛ አንባገነን ወያኔ ገዢዎች እና ጭፍራዎቻቸው ህዝባችንን ከመቼውም ግዜ በላይ በከፋ መልኩ በጭካኔ እየገዙት ይገኛሉ።በአገራችንና በህዝባችን ላይ ዛሬ እየደረሰው ያለው መከራና ግፍ ብንዘረዝረው የማያልቅ ነው፤ ከብዙ በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል የፍትህ አልባነት ፣ዘረኝነት፣በየግዜው እያሻቀበ ያለው የኑሮ ውድነት ከአብዛኛው ማህበረሰብ አቅም በላይ ስለሆነ የእለት ጉርስ ለማግኘት የዘውትር ጭንቀትና ሃሳብ ነው የተማሪዎችም በትምህርት ገበታ ላይ እያሉ በርሀብ መውደቅ የዘውትር ትእይንት ነው።

ይህ አንባገነን ስርአት በየቤተ እምነቱ ውስጥ ጣልቃ እየገባ የአማኞቹን ሰላም እየነሳ ይገኛል።እንደሚታወቀው ክርስትያኑ ማህበረሰብ እውነተኛ ሰላምና የአእምሮ እረፍት የሚያገኝበትን ቤተ እምነቱን በማፍረስ፣ በማቃጠል ጥንታዊ ገዳማቱን በልማት ስም በማጥፋትና በማዋረድ እውነተኛ የሃይማኖቱ አገልጋይ የሆኑትን ካህናትን በማሰር፣በማንገላታትና በማሳደድ ላይ ይገኛል። እንዲሁም በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይም በሀይል አዲስ አስተምእሮት በመጫን፣ያልመረጧቸውንና የማይወክሏቸውን የእምነት መሪዎች በማስቀመጥ ህዝበ ሙስሊሙን ያሰቃያል።መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ለምን ጣልቃ ይገባል በማለት ሀይማኖታዊና ሰላማዊ ጥያቄ ያነሱትን አማኞች ለእስር፣ ለእንግልት፣ ለግድያና ለስደት ዳርጓቸዋል። ይህ ዘረኛ ስርአት ሀገሪቷን በዘር ከፋፍሎ አንዱን ብሄር ከሌላኛው ጋር በማጋጨት የህዝቡን የመኖር ህልውና አስጊ ደረጃ ላይ አድርሶታል። በአገዛዙ ቅጥረኞች የአማራውን ህዝብ ከደቡብ ክልል ማባረር፣የኦሮሞን፣የአፋርን፣ የጋንቤላን፣ የሱማሌን እንዲሁም ሌላውንም ኢትዮጵያዊ በልማት ስም ከቦታው ማፈናቀል፤ለም መሬታችንን ለባእዳን አሳልፎ መስጠት፤የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችን እና አባሎቻቸውን ማስፈራራት፣ማሰቃየት፣ማዋከብ፣ ማሰር እንዲሁም በነጻ ጋዜጠኞች ላይ እስር፣እንግልት፣ማሰደድ፣በማስፋራራት ከስራቸው እንዲርቁ ማድረግ እንዲሁም እንደነ እስክንድር ነጋ፣እርዮት አለሙ ያለ ጥፋታቸው በሼዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በማሰር ማንገላታት፣ማስፈራራት፣ማሰቃየትና መግደል በአጠቃላይ በወገኖቻችን እና አገራችን ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ፣ የመብት ረገጣ፣ኢፍትሃዊ አገዛዝ እያወገዝን አገዛዙ በአስቸኳይ ከዚህ ድርጊቱ ይቆጠብ ዘንድ እናሳስባለን።

በተጨማሪ ይሄንን እኩይ ተግባር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የምትፈጽሙም ሆነ የምታስፈጽሙ ድርጅቶች፣ግለሰቦች፣የአገዛዙ የፖሊስ፣የደህንነት፣የመከላከያ ሰራዊት፣የቀበሌና ወረዳ ባለስልጣን ሌሎቹም ጭምር ይህን እኩይ ተግባራችሁን ባስቸኳይ በማቆም ወደ ህዝብ ትግል በማንኛውም መንገድ በመቀላቀል ከህዝብ ጎን በመቆም የበደላችሁትን ህዝብና አገር ግዜው ሳያልፍ በመካስ ከታሪክ ተወቃሽነትና ከህዝብ ቁጣ እራሳችሁን ታድኑ ዘንድ እና ለማይቀረው ለውጥ አስተዋጽኦ ታደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን።

ከኢትዮጵያ ተስፋ ወጣቶች ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ኮሜቴ

አዳማ  ኢትዮጵያ

ድል ለኢትዮጵያ!!!

ኢትዮጵያ በነጻነት ከነክብሯ ትኖራለች!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>