መለስ አዝማሪ አይደለም

September 17, 2012

በተስፋዬ ገብረአብ

በመለስ የሃዘን መድረክ ላይ አንዲት የህወሃት ደጋፊ የሆነች ሴት ያደረገችውን ንግግር ተከታትዬው ነበር። ለጆሮ በሚጥመው፣ “ለለ” በበዛበት ውብ የእንደርታ ትግርኛ እንዲህ አለች፣

“ቀዳሚዎቹ መሪዎች ለአባይ ምን አደረጉ? ከሃምሳ አመታት በላይ በማሲንቆ ዘፈን ሲዘፍኑለት ነበር። አዝማሪ አቁመው፣ ‘አባይ! አባይ!’ ሲሉ ሙሾ ሲያወርዱ ነው የኖሩት። መለስ ግን አዝማሪ አለመሆኑን ሊያውቁት ይገባል። (መለስ ዋጣ አይኮነን)፣ አዎ! መለስ ጀግና እንጂ አዝማሪ አይደለም። አባይ እንዴት እንደሚደፈር አሳይቶአቸዋል…”

ወይዘሮዋ እዚህ ላይ መናገር አቃታትና ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። መለስ አርባው ሳይወጣ ስሙን በአሉታዊ ማንሳት የሚመች አልነበረም። ስርአቱ ግን የመለስን መሞት ለፖለቲካ ፍጆታ እያዋለው ስለሆነ የግድ ስሙን ለማንሳት እንገደዳለን።መለስ አዝማሪ አይደለም

ከመነሻው፣ “አባይን መድፈር” ምን ማለት ነው?

አባይን ለመገደብ ሃይለስላሴም ደርግም ጥናት አድርገው ነበር። የአለማቀፉን ማህበረሰብ ድጋፍና የብድር ገንዘብ ስላላገኙ ሊጀምሩት ሳይችሉ ቀርተዋል። የመድፈር ያለ መድፈር ጉዳይ አልነበረም። በጀብደኛነት ኮሎኔል መንግስቱን ማን ይስተካከለዋል? ኤርትራን ጠምዝዘው በእጃቸው ያስገቡት አክሊሉ ሀብተወልድ አይደሉም እንዴ? ጃንሆይ ወሰን በማስፋት እንጂ፣ ወሰን በማጥበብ አይታወቁም። ሁለቱም መንግስታት ቢቻላቸው ኖሮ አባይን ከመገደብ ወደሁዋላ ባላሉ ነበር። የመድፈር ወኔ አጥተው ሳይሆን፣ ተጨባጩ አቅማቸው ስላልፈቀደ ይመስለኛል የአባይን ግድብ ያልገነቡት።

መለስ በወኔ ዘሎ ገባበት።

ግድቡን ለመገንባት የሚበቃ ገንዘብ ማግኘት አለማግኘቱን አላጠናም። ታሞ ስለነበር ሳይጨርሰው እንደሚያልፍ መቼም ተረድቶት ይሆናል። ተከታዮቹ (እነ በረከት፣ እነ ሃይለማርያም) የግድቡን ግንባታ ሊጨርሱት እንደሚችሉ ምን ዋስትና ነበረው? ከቦንድ ሽያጭ የተሰበሰበችው 5 ቢሊዮን ለሲሚንቶም አትበቃ። ሌላ ምን ትቶላቸው ሄደ? ድፍረት እና ወኔ?

የሆነው ሆኖ፣ “መለስ አዝማሪ አይደለም” ወይም፣ “አባይን ደፈረ” ለማለት ቢያንስ ግድቡ ተገንብቶ እስኪያልቅ መጠበቅ ይገባል። የፋይናንስ ባለሙያ ቡልቻ ደመቅሳ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አባይን ለመገንባት የሚበቃ አቅም አንደሌለው ጠቁመው ነበር። ብርሃኑ ነጋም፣ የአባይ ግድብ ግንባታ ወሬ ለፖለቲካ ፍጆታ የመጣ መሆኑን አስረግጦ ተናግሮ ነበር። ቡልቻ የተናገሩትን በቅርቡ አይ፣ ኤም ኤፍ ደግሞታል። ግብፅ ግድቡ ከተገነባ በጦር ጄት እንደምትመታው መግለፅዋን ዊኪሊክስ ጠቁሞ ነበር። በርግጥ ግብፅ ይህን አስተባብላለች። ግብፅ አስተባብላለች ብሎ ማመን ግን አይቻልም። ግድቡ በግብፅ ጦር ከተደበደበ የኢትዮጵያ ምላሽ ምን ይሆናል? በአፀፋው አስዋን ግድብን በጦር ጄት መምታት ወይስ የሱዳንን መሬት በመጣስ ታንከኛ ጦር ወደ ግብፅ መላክ? የመቀሌው የኢትዮጵያ አየር ሃይል ግብፅን ለመደብደብ ብቃት አለው? ዝግጅት ተድርጎአል? መለስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ አልሰጠም። “ግብፅ አትደፍረንም፣ ማን እንደሆንን ታውቀናለች” አይነት የጎረምሳ ንግግር ነበር ያደረገው።

የአባይ ግድብ ዜና የኢትዮጵያን ህዝብ ስሜት በከፍተኛ ሁኔታ እንዳነቃቃ እሙን ነው። በመለስ ዜናዊ እረፍት ያዘኑ ወጣቶች ሲናገሩ የተሰሙትም፣ “መለስ የአባይ ወንዝ ተገንብቶ ሳያይ በመሞቱ…” የሚለውን ነበር። የአባይ ግድብ ግንባታ በአንድ ምክንያት ቢቋረጥ፣ “መለስ ባይሞት አይቋረጥም ነበር። ሞት ቀደመው እንጂ…” የሚል አባባል እንደሚመጣ ግልፅ ነው። አንድ የቆየ ቀልድ ታወሰኝ።

“…ዳቦ የለም እንጂ፣ ስኳር ቢኖር ኖር፣ ሻይ አፍልተን ቁርስ እንበላ ነበር።”

6 Responses to መለስ አዝማሪ አይደለም

 1. በለው ! Reply

  September 19, 2012 at 7:22 pm

  “አባይን መድፈር” ምን ማለት ነው?የአፄውም ሆነ የኮነሬል መንግስቱ ሥርዓት ቢቻላቸው ኖሮ አባይን ከመገደብ ወደሁዋላ ባላሉ ነበር። የመድፈር ወኔ አጥተው ሳይሆን፣ ተጨባጩ አቅማቸው ስላልፈቀደ ነው። መለስ በወኔ ዘሎ ገባበት…! መለስ አርባው ሳይወጣ ስሙን በአሉታዊ ማንሳት የሚመች አልነበረም። ስርአቱ ግን የመለስን መሞት ለፖለቲካ ፍጆታ እያዋለው ስለሆነ የግድ ስሙን ለማንሳት እንገደዳለን!!!! ይህንን ሁሉ ሥራ ብቻቸውን ከሠሩ በእርግጥ ሎላው ሲሞላፈጥ ነበር።!!
  አዎን ከማንቆላጰስ ወደ መሟዘዝ ተሸጋግረዋል አንዲህማ በምላስና በመፈክር ሆኖ ቢሆን በሁሉም መስክ የት በደረስን አሁንም እዛው ነን።”አንዳንዶች እንደሚሉት አቶ መልስ አባይን በህዝብ ገንዘብ እሳቸው በምላሳቸው ደፍረውት ይሆናል አዲሱ (ተተኪው) ትውልድ ግን በራሱ ወጪ ይሸፍነዋል እየተባለ ይፎገራል!።ለዛውም ፣በሥብሰባ አዳራሽም ይሁን በስታዲየም በአደባባይም ይሁን በገዳም በልመና፣በፆም በፀሎት እግዝሐብሔርም ዝናብ እንዲያዋጣ እንማፀናለን!!ግድቡ እንደተተነበየው በ፯ ዓመት ሊጠናቀቅ ከታሰበው በፊት ይደረሳል የሚባለው በ፳፻፲፪ ዓ.ም(፳፻፲፰) በአውሮፓውያን.አቆ ቢያልቅ ፳፻፳ ከድሕነት ወጣን ማለት ይሆን? ለመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ሕዝቡ ይሸፍነዋል ተብሎ ከተጠበቀው ፳ ከመቶ ፲ ከመቶ ብቻ አደለም ተሰበሰበው? “ገና ሳይወጠወጥ ወስከባው ቁጢጢጥ” መጀመሪያም ለግብፅ እና ለሱዳን ቦንድ ባይሸጡ ኖሮ አንድ ደንጋይ አያስቀመጥም ነበር። ላልገባችሁ… በመጀመሪያ ህገ መንግስታችሁ የግለሰብ ሉዓላዊነት ይላል እንጂ የሀገር ሉዓላዊነት አይልም!! ባለ ዕራዩ መሪህ የተጠቀለለበት ባንዲራ የትኛውንም ዳር ድንበር አይወክልም!ስለዚህም ነው ትግራይ ሁመራን ጠቅልሎ ሰሜን ሱዳን እና ትግራይ ጎረቤታሞች ሆነው ስሞኑን በእረሻ መሬት የተጣሉት? ?።በህገ መንግስቱ አፃፃፍ በዚህ ግድብ አንድ ኮሽታ ቢፈጠር የመጀመሪያው ተጠያቂ ባለ ዕዳ የዚያ ክልል አስተዳደር ሆኖ…አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የፌዴራሉ ጣልቃ ይገባል!!! ለዚህ ነው ትምህርት ሚ/ር ባሕል እና እስፖርት የጤና ሚ/ር ለብሔር ብሔረሰቦች ተሰጥቶ ኢኮኖሚው እና መከላከያውን አታገኙም ሲያምራችሁ ይቅር !!እደግመዋለሁ!!አታገኙትም!።(የህዘቦች)ነው።አራት ነጥብ።(የህወአት እና የኢንቨስተሩ) ብቻ። በዚህ አጋጣሚ ራዕይን በማስፈፀም ከሚቀሳፍቱት ሙዚቃ እና የግጥም የድርሰት የድራማ ችሎታቸውን ለማሳየት ሲቆሉብን የከረሙት ለካሜራ ጥቁር ልብስ(ከል) ለብሰው ጫማቸውን አስጠርገው ተንቀሳቃሽ ቴሌፎናቸው በቲቪ እንደሚታዩ የሚያወሳቸው ጥቁር መነፅር ድንኳን ውስጥ አድርገው ያስተዛዘኑ የአርቲስቶችን አቅም ለመለካት ያህል… የየትኛውም የሃይመኖት ተከታይ ቢሆኑ “መጀመሪያ ባልጀራህን እንደ እራስህ ውደድ አጠገብህ ያለውን ሳታውቅና ሳትወድ… ያላየኽኝን የማታውቀኝን እንዴት ልታከብረኝና ልታምነኝ ትችላለህ? ብሏል ስለሆነም አቶ መለስ አውርተው ሄደዋል ብዙ ሽረጉድ በዝቷል ተፎክሯል ተሸልሏል ለመሆኑ ይህንን ቪዲዮ ስትመለከቱ ምን? ማን? መሆናችሁ ይታወቃችሁ ይሆን? አጅግም ተሞላፈጣችሁ!መሌ አመለጠች!!
  http://www.diretube.com/diretube-exclusive/a-abreham-asmelash-needs-your-help-video_51f920c4f.html

 2. Tazabiew Reply

  September 18, 2012 at 10:17 pm

  Admins do you notice what Tesfaye Gebreabe said about Aklilu Habteweld ? That was the main message of the whole articles, James Bond Shabia special agent.

 3. Ancient Ethiopia Reply

  September 18, 2012 at 8:49 pm

  What she said is expected from backward people.
  meles mighty not be “azemari” but he was well known beggar that was why he milked over 50 billion dollars from westren countries. Meles had used abbay damn construction to devert the publice attention from politics and to milk those hodams like cow.
  By the way what did serawit fiker , aster awoke and other pro TPLF azemaris say when that ignorant used the word ” azemari”. Azemarinet is a proffession.. so azemarinet is far better than beggarizim.

 4. Ethiopiawi Reply

  September 18, 2012 at 7:33 pm

  Mr. Tesfaye
  A big lie , ”Akililu Habtewolde had forced ertrea to be part of Ethiopia´´
  Tesfesh As every body knows, you are a pro shabya x-weyane and x -derg leutenant. Since you prefer to be an Ethiopian, I choose to you to be a derge officer bcz a derge officer would never compromise with Ethiopian history and he believes that ertreans are Ethiopians, at the same time ertrea is Ethiopia

  I am writing here about Akililu Habtewolde, you wrote that ”he had forced ertrea to be part of Ethiopia” It is a big lie.Akililu habtewolde with out the will of ertreans he would have not been successful to unite ertrea to Ethiopia
  The Ertreans have struggled to return back to their mother land Ethiopia, at that time there was a referendum which had taken in Ertrea, Most of the Ertrean ppl with its delegation had voted to be part of the unitary Ethiopia but United nations had accepted it partially, and federation had been adapted .
  During the italian colonial rule The ertrean movments for united Ethiopia such as mahbere andenet, and agere fikiri were the famous parties who had done their best to be united with their mother land Ethiopia ,
  Do not forget that , Zeray deres a hero, colonel debesay geberekal, betweded asfiha,Lorenzo tezaz blata efrem teweldemedhin, dimitros …, amanuel amdemichael…, etc and at large the ertrean ppl had done the miracle, again the ertreans came back to Ethiopia.
  Do not distort history!!

 5. Gudfela Reply

  September 18, 2012 at 3:45 pm

  What this “Alqash” and her followers need to understand is that development is incremental. When she compared TPLF government with past governments, she revealed how ignorant and backward she is. Is this the type of thinking Ethiopia needs now???

 6. tulu Reply

  September 18, 2012 at 6:51 am

  Epitaph on a Tyrant
  by W. H. Auden

  Perfection, of a kind, was what he was after,
  And the poetry he invented was easy to understand;
  He knew human folly like the back of his hand,
  And was greatly interested in armies and fleets;
  When he laughed, respectable senators burst with laughter,
  And when he cried the little children died in the streets.

  አኮቴት ለአንድ አምባገነን
  (ትርጉም በቱሉ ፎርሳ ከነምሳ)
  የሰው አመል የገባው
  ማን እንደሱ ጮሌ?
  ለመሳሪያ ወ ሰራዊት ጋጋታም
  የተጋ ባተሌ።
  ደግሞም እንደጥበብ ፋና ወጊ
  ነበር ፍጽምናን ፈላጊ፤
  የዘረፈው ቅኔም ሚስጥር
  (የእንባ እና ሳቅ ህብር)
  የማይፈታ ዕንቆቅልሽ
  አልነበረም ከቶ ድድር፤
  እሱ ሲስቅ ሲፍለቀለቅ…
  የተከበሩ እንደራሴዎች
  ሳቁን ተቀብለው ያሽካካሉ፡
  እሱ ከፍቶት ደግሞ ሲያለቅስ…
  በየመንገዱ ልጆች ይደፋሉ
  እንባውን ተቀብለው
  በህይወታቸው ይከፍላሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>