የከፋፈሉንን መሪ አንድ ሆነን ቀበርናቸው!

September 14, 2012

Click here for PDF

ከተወልደ በየነ (ተቦርነ) ነሃሴ 2004

በቅርቡ የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በሀገራችን የተፈጠረውን ሁኔታ ሳይ አንድ የቆየ የስለላ ታሪክ ትዝ አለኝ::

ባንድ ወቅት አንድ አሜሪካዊ የስለላ ድርጅት አባል ወደ ቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት እንዲሄድ ይታዘዛል በዚህም መሰረት በሶቭየት ህብረት በሚኖረው ቆይታ ምስጢራዊ መረጃወችን Meles Zenawi with Chines presidentለመላክ ቀይና ሰማያዊ ቀለም ያላቸው ብዕሮችን እንዲጠቀም በጥብቅ ይታዘዛል ይህም የሆነበት ምክንያት በወቅቱ የነበረው የሩሲያ ስለላ ድርጅት ከሀገሩ ይወጡ ለነበሩ ማናቸውም ጽሁፎች መነበብ አለባችው የሚል ህግ ስለነበረው ነው በዚህም መሰረት ቀዩ ብዕር ትክክለኛ መረጃን ለመላክ የሚጠቀምበት ሲሆን መረጃው ሀሰተኛ መሆኑን ለመጠቆም ሰሚያዊውን ብዕር እንዲጠቀም በጥብቅ ተነግሮት ወደ ሩሲያ ያቀናል::

የሶቭየት ህብረት ቆይታውን በተመለከተም ሪፖርት ሲያደርግ ታላቋ ሩሲያ የነፃነት፣ የፍትህ፣ የዲሞክራሲ፣ የዕኩልነት ሁሉም ነገር ተሟልቶ ያለባት ምቹ ሀገር እንደሆነች ገልጾ በሩሲያ ፈልጌ ያጣሁት ነገር ቢኖር ቀይ ብዕር ብቻ ነው ብሎ ረፖርቱን አጠቃለለ::

ወደ እኛ ሀገር ስንመለስ እውነት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአመራር ብቃት፣ ጀግንነት፣ ብልህነት፣ አርቆ አሳቢነት ሰሞኑን እየተባለ ያለው ብቻ ነው ከተበለ ትክክል አይመስለኝም ምክንያቱም እውነቱን ለመፃፍ እንደ አሜሪካዊው ሰላይ ቀይ ብዕር ካላጣን በስተቀር ወይም በነበረው ፕሮገራም መጣበብ ምክንያት ተዘሎ ካልሆነ በቀር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ 21 ዓመት ያመራር ዘመናቸው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆነውን የኢትዩጵያን ሠራዊት የበተኑ፣ ኤርትራን ያስገነጠሉ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የወደብ አላስፈላጊነትን በልበሙሉነትና በብልህ ያመራር ብስለት ያስረዱ ታላቅ የማይተኩ መሪ ናቸው::

በተሳሳተ የትምርት ፖሊሲ ዓንድ ትውልድ ያመከኑ ባለ ራዕይ መሪ ነበሩ::

በኢትዩ-ኤርትራ ጦርነት 80ሺህ ኢትዩጲያዊያን ወታደሮችን ያስፈጁ እና ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ እደራደራለሁ ያሉ መለኪያም መተኪያም የማይገኝላቸው ታላቅ የሀገር ሀብትም ነበሩ::

በ1997 ምርጫ በሰላማዊ መንገድ በካርዱ ያሸነፋቸው ህዝብ ላይ አነጣጥሮ ገዳይ ያዘመቱ ልበ-ሙሉ ጀግናም ነበሩ:: ታድያ ይሄ ሁሉ ታላላቅ የጀግንነት የብልህነት ያስተዋይነት ብቃታቸው ታሪክ ተዘሎ መታለፍ አግባብ አይደለም ምክንያቱም በነዚህ ምክንያቶች የፈሰሰው እንባና ደም ለቀብራቸው ከፈሰሰው እንባ በተሻለ የሳቸውን ብቃት ያሳያል የሚል እምነት ነበረኝ::

ለማንኛውም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የከፋፈሉት ህዝብ አንድ ሆኖ በናቁት ሰንደቅ ዓላማ ጠቅልሎ ባዋረዱአት ቤተከርስቴያን ቀብሯቸዋል:: ወርቅ ከሆነው የትግራይ ህዘብ የተፈጠሩት ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ አሁን የሉም በዘር በሀይማኖት እንዲከፋፈል የደከሙለት ህዝብም አንድ ሆኖ እሳቸውን ቀበረ ስለዚህ ሟች በከንቱ ደከሙ:: ነፍስ ይማር!

One Response to የከፋፈሉንን መሪ አንድ ሆነን ቀበርናቸው!

 1. በለው ! Reply

  September 16, 2012 at 2:45 am

  ***ሰውዬውን አድዋ የጣለው አውሮፕላን አዲስ አበባ ለቀስተኞችን ይዞ መጣ አሥራ ሁለት ቀን እሬሳ ቋንጣ ነው??ምን አለ ቀና ማለት ቢችሉ ነበር እንኳንም ለወያኔ ሊቀመንበር አድዋም ላይ ለፋሽሽት ጣሊያን እንዲህ ነበር በክተት አዋጅ የወጡት፣ የሸለሉት፣ የፎከሩት፣ የሰነቁት!፣(ንፍሮ የቀቀሉት) ፣የዘመቱት የተዋጉት ፣ የማረኩት፣ የገደሉት፣ የቀበሩት ያሸነፉት፣ሐውልትም ያቆሙት! ያውላቸሁ!! እናንተ ታሪክን ስታጠፉት ስትለውጡት ስትበርዙ ስትከልሱት በራሳቸሁ ላይ ታሪክን ሠርተው ደገሙ ለልጆቻችሁም የጠፋውን ታሪክ በአይናቸው አስመስክረው በልባቸው አወረሱላችሁ!!! ይህ ሃያል ጨዋ ጅግና ሳይማር ያስተማራችሁ ጥበቡን አሳያችሁ።አራት ነጥብ።የገደላቸው “የስራ ጫና እና ረጅም ግዜ የቆየ የስራ ኃላፊነት ነው።”የሚሉት ዛሬ ግን እኛ እንሠራዋለን ግድ የለም ለእኛ ይተውት! እርስዎ ብቻ እረፉ! ደህና ግቡ! እያሉ የሚቀሳፍቱት በእርግጥ መለስ ብለው የማያዩ ታዛቢ የሌላቸው ብቸኛው ሁለግብ ታጋይ መሆናቸው ይገረማል!።ያስተዛዝባል!እኔ ምለው መለስ ለዚህ ሁሉ ሥራ ፷፻፪፻ ብር እየተከፈላቸው አውራ ባለቤት ከሆኑ ይህ ፓርላማ ተጎልቶ የሚገለፍጠው… በእየመሥሪያ ቤቱ የተኮለኮለው ሁሉ ምን ሠርቶ ይከፈለዋል? እሳቸው የወጠኑትን ሁሉ ሲያፈርስ ነበር ማለት ይሆን ? ?በእየ መንገዱ ሲወጡ ሲገቡ ሕዝቡን ፊታችሁን አዙሩ እያሉ በመሸማቅ ኖረው ዛሬ በኩራት በዘጠኙም ክልል መቀበርና ሥልጣንን ለ፹ሚሊየን ሕዝብ ማካፈል እኮ…! ክርስቶስ ስንት ዳቦ ? ስንት ዓሳ ? ለስንቶች ? ነበር ያበላው(ቁጥሩ ተዘነጋኝ ወይ ቁርጥ) አሉ..ወ/ሮ መመሳሰል፡ለማናቸውም ምንም እንኳ ሕገ መንግስቱ ከሰጣቸው አንድ ገፅ ተኩል ሥልጣን በላይ የተጋነነ ከአምስት ዓመቱም የእብደት እና ትራንስፎርሜሽን የተለጠጠ ዕቅድ በልጦ በጣም የተሞላቀቀ ያሸኛኘት ሥርዓት መሆኑ ፎግሮ ማስፎገር እና መፎገር ቢሆንም እሰይ አበጃችሁ ሌላው ለመቅበር እማ ማን ብሎ !ተረኛው ማነው? ላደረጋችሁት የብሔር አስተዋፆአዊ ለቀሶ, ረገዳ, ሽላሎ,የገንዘብ እና ዕንባ ከልብ እናመሰግናለን። ሕብረታችሁ ልጦናል ይመቻችሁ በለው!!!!!!
  “ክበር ተመስገን የእኛ ጌታ ፤
  ከጠዋት አንስተህ እስከ ማታ ፤
  ለጠራኸው ሁሉ ያለህ ቦታ! ፤
  መራሃቸው አሉ ሁለቱን ፤
  የአብዮትም የፖለቲካ ጠበብትን ፤፤
  በእውነቱ በጠራ ሀገር ፤በጠራ ሰማይ
  በጠራ አመራር፣ጥይት ቢቆላ ሲታይ
  የሀገር ባህል ወግ አደለም ወይ …
  የሰማዩም ባለቤት ሁሉ በእሱ ነው ጣይ
  ለሀገር ከሆነ ራዕዩ ይገለጥ አንሰጋም
  ከቶ፤በፍፁም! በጭራሽ !”መለስ አንልም!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>