ምን ማድረግ አልብን?

September 14, 2012

ደመቀ ታዬ

የአቶ መለስ  ዜናዊን ሞት ተከትሎ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ምን አናድርግ? የሚለው ሁኗል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ብዙ በሳል የሆኑ አስተያየቶች ከበሰሉ ኢትዮጵያውያን ቀርበዋል።በአንጻሩ ያው የተለመደው የጥላቻ ከበሮም ሲመታ ከርሟል።የአቶ መለስን  ሞት በተመለከት  ሁለት  የተለያዩ አስተያየቶች መድረኩን በይበልጥ የያዙት ይመስላል። አንዱ አስተያየት  ኢሓደግና ሕወሃት አስካሉ ድረስ  የመለስ ሞት  የሚያመጣው ለውጥ የለም የሚል ሲሆን፣ ሌላው አስተያየት ደግሞ የአቶ መለስ ሞት በኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣል  የአድል በር ይከፍታል የሚለው ነው። በበኪሌ ሁለተኛውን በጥንቃቄና በበሰለ መንገድ ከያዝነው ሁኔታዎችን  ሲሆን ለመለወጥ  አለበለዚያ ለማሻሻል አንችላለን  የሚል አስተያየት አለኝ።

በኔ አስተያየት አቶ መለስ በሥልጣን ለመቆየት ብሔረ-ሰቦችን ከብሔረ-ሰቦች፣ ግለሰቦችን ከግለሰቦች በማጋጨት የተካኑ ነበሩ።በተጨማሪም አይን  አውጣ በሆነ መንገድ ሰዎችን የመደለል ችሎታ የነበራቸው ሰው ነበሩ። አቶ መለስ ከቻይናና ከአሜሪካ ጋር የነበራቸው  የጠበቀ ግንኙነት ለዚህ ችሎታቸው አንዱ ምስክር ነ፣ሌሎች ምሳሌዎችንም መጥቀስ ይቻላል።

አቶ መለስ ለ17 ዓመት ከታገሉት መካከል አንድ ናቸው፣ ይሁን አንጂ ከረጅሙ ምላሳቸው  በቀር በሌላ ዘርፍ ይህን ያህል የታወቁ አልነበሩም። በዚህ ምክኒያት ሁል ጊዜ በስጋትና በጭንቀት ይኖሩ ነበር። ይህ ሁኔታ ደግሞ ባላቸው ሥልጣን ሁሉ የሚያሰጉዋቸውን  በሙሉ መምታትና ማስወገድ ነበረባቸው።በዚህም ምክኒያት ድርጂታቸውንም ሆነ  አብረዋቸው የታገሉትን በታትነዋል፣ አዳክመዋል።በዚህ አንጻር ካየናቸው አቶ መለስ ከኮረኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም ጋር  ይመሳሰላሉ። የኮረኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም መኮብለል ያስከተለውን ያህል ችግር ይፈጥራል ባይባልም የአቶ መለስ መሞት ሰፋ ያለ በር ሊከፍት ይችላል።ይህ ሁኔታ ደግሞ ለበጎም ይሁን ለመጥፎ ምክኒያት ሊሆን ይችላል።

የወቅቱ አማራጭ ወይም አቋራጭ የሌለው ጉዳይ ምን አናድርግ? ወይም ምን ማድረግ አንችላለን? የሚለው ነው። ይህን ወሳኝ ጥያቄ በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሠነዘሩ ሰንብትዋል። አንዱ አስተያየት የገዢው ፓርቲና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተሰብስበው በመነጋገር የወደፊቱን መንገድ መጥረግ አለባቸው የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛ ደግም አቶ መለስን የሚተኩትን  ባለሥልጣናት በመቅረብና በማነጋገር አስቸኳይ የሆኑትን ጉዳዮች አንድ ባንድ መቅረፍ አና ለዘላቂው መፍትሄ መንገድ መጥረግ ይመረጣል የሚል ይመስለኛል። አጣዳፊና ጊዜ የማይሰጡ ችግሮች የሚባሉት አስረኞች፣ አፋኝ ሕጎች፣ የፍርድ ቤቶች ነጻነት፣ የጦር ኃይሎች ግለለልተኛነት፣ የደሞክራቲክ መብቶች፣ የምርጫ ቦርድ ገለልተኛነት፣ የመናገርና የመጻፍ መብቶች፣ የፓርቲዎች በነጻ መንቀሳቀስ፣ ወዘት ናቸው።በኔ ግምት  አነመለስ ሥልጣን ሲይዙ ያደረጉትን ዓይነት ስብሰባ ለማካሄድ የሚቻል አይመስለኝም።ለዚህም ምክኒያቴን ልግለጽ።ኢሓዴግ ወይም ሕወሃት በሥልጣን ላይ ነው፣ የታጠቀና የተደራጀ  ሠራዊት  አለው። የስለላ ድርጂቶች በቁጥጥሩ ስር ናቸው፣ ሌሎችም። ይህን ሥልጣን ይዞ  ከሌሎች ከ80 በላይ ከሆኑ  የተቃዋሚ ድርጂቶች ጋር  ስብሰባ በመቀመጥ በአሁኑ ወቅት ሥልጣን ይካፈላል ማለት  የሚቻል አይመስለኝም።ይህ ሰብሰባ አንዲካሄድ ሊረዱ የሚችሉ ጉዳዮች ይጠቀሳሉ። አንዱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ነው፣ ሌላው የአሜሪካና የአውሮፓ ግፊት ነው።የመጀመሪያው ምን ያህል ጊዜ አንደሚወስድ ለማወቅ አይቻልም፣ ሁለተኛ  ጥቅማቸው አስከተጠበቀ ድረስ ሊገፉበት አይፈልጉ ይሆናል። ያም ሆነ ይህ የተፈለገውን ያህል ተጻኖ ለማድረግ አረዘም ያለ ጉዞ ያስፈልግ ይሆናል።

በአሁኑ ጊዜ ማን ምን  ቦታ ወይም ሥልጣን አንደሚይዝ አይታወቅም። ይህም ቢታወቅ በርቀት ሆኖ ማን ምን አንደሆነ በርግጠኛነት ለመናገር የሚቻል አይመስለኝም። ጥሩ ጥሩውን በመመኘትና በማሰብ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ለውይይትና  አንዳንድ ነገሮችን ለማሻሻል ፈቃደኛ ናቸው ብለን አንነሳ፣ ሌሎችም አርሳቸውን የመሰሉ አሉ ብለንም አንመኝ።ስለሆነም አቀራረባችንን ለዘብ አድርገን፣ ውግዘታችንን ቀንሰን፣ የተጀመረውን  ለመጨረስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎች ለማከናወን፣ አገራችንን ከውጭም ከውስጥም ጠላቶች ለማዳን ውይይትን መርጠን መሞከርና ውጤቱን ማየት አልብን የሚል አምነት አለኝ።

ኢትዮጵያውያን በጣም አገራቸውን ከሚወዱ ሕዝቦች መካከል የሚገኙ ናቸው የሚል አምነት አለኝ። ግን አስከአሁን ሊላቀቀን ያልቻል ችግርም ተሸክመን አንጓዛለን።  አንደማስቲካ  የምናኝከው ግን ደግሞ የማንተፋው ወይም የማንውጠው ችግር አለ፣ ያለፈውን አያነሳን መነታረክ፣ መናቆር፣ መበታተን። ይህ ሁኔታ አልጠቀመንም፣ ሊጠቅመንም አይችልም። መሳደብ የሐሳብ ድህነትን ወይም ማካንነትን አንደሚያመለክት ሁሉ ያለውፈውን  ማኘት፣ ግራ-ቀኙን ጥላ አሸት መቅርባት ከሐሳብ ድህነት ተለይቶ የሚታይ አይደለም።ፖለቲካ የሚቻለውን  ከማይቻለው አየለዩ የሚከናወን  ከፍተኛ  ሥራ ነው።ደሞክራሲም የዚህ ጥበብ መገለጫ አንዱ መንገድ ነው።ለግል ክብርና ዝና ከመሯሯጥ ለወገንና ለአገር መሥራት ያስከብራል፣ ያረካል።

One Response to ምን ማድረግ አልብን?

  1. Abraham Reply

    September 14, 2012 at 2:04 pm

    በጣም አሪፍ ሃሳብ። መቼም እንደ መለስ መጪዉ ፖለቲካዉን በብልጠት ( with out sincerity) ማስኬድ የሚፈልግ ላይመጣ ይችላል፤ ስለዚህ የሚመጣዉን አለሳልሶ መቅረብ አይከፍም። መምከር ፣ማስመክር ማለፊያ ሃሳብ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>