“የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ለውጥ እየጠበቀ ነው” አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

September 10, 2012

በፍሬው አበበ

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የቀድሞ የፓርላማ አባልና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) አማካሪ ምክርቤት ሰብሳቢ ናቸው። ከወቅታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ፍሬው አበበ አነጋግሮአቸዋል።

ሰንደቅ፡- ከጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት በኃላ አስተዳደሩን ከተረከበው አዲስ አመራር ምን ይጠበቃል?

አቶ ቡልቻ፡- አዲስ አመራር አለን’ንዴ?ይህን ከአንተ ነው የምሰማው። አንተ አዲስ አመራር ትላለህ። እኛ ግን አዲስ አመራር እያየን አይደለም። ማንነው የሚመራን?ቃለምልልስ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ለውጥ እየጠበቀ ነው” አቶ ቡልቻ ደመቅሳ
ይህ’ኮ የዘጠና ሚሊየን ሕዝብ ጉዳይ እኮ ነው። የዛሬ 30 እና 40 ዓመት የኢትዮጽያ ሕዝብ ቁጥሩ 50 ሚሊየን ገደማ ነበር። ዛሬ 90 ሚሊየን ደርሷል። ችግሩ ሰፍቷል፣ ፍላጎቱ አድጓል። የዚህ ትልቅ አገር፣ ትልቅ ሕዝብ አመራር እንዴት ተወሰነ? የኢትዮጽያ ፓርላማ የሚባል አለ።

ፓርላማው በእንዲህ ዓይነት ትልቅ ጉዳይ አያገባውም’ንዴ?

ሰንደቅ፡- በአሁኑ ሰዓት በግልጽ የሚታወቅ አዲስ አመራር የለም ነው እያሉኝ ነው?

አቶ ቡልቻ፡- አዎን!…መሪው ማን እንደሆነ ሕዝብ የማወቅ መብት አለው።

ሰንደቅ፡- በቀጣይ ተተኪ ከሚሆነው አመራር ምን ይጠበቃል?

አቶ ቡልቻ፡- መጀመሪያ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በአሁኑ ጊዜ አገሪትዋ ምን ዓይነት አመራር ያስፈልጋታል ብሎ መጠየቅ አለበት። እኔም እጠይቃለሁ። እስካሁን ድረስ አንድ ፓርቲ፣ ያውም ዝግት ያለ ፓርቲ… ሌላ ኀሳብ፣ አማራጭ የማይቀበል፣ የማያስተናግድ ፓርቲ ላለፉት 21 ዓመታት ሲመራን ቆይቷል። ከዛሬ 21 ዓመታት በፊት ይዞት የመጣውን የራሱን ኀሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ይሞክራል። ኀሳብ አይለወጥም’ንዴ? ታላቁ የአሜሪካ መንግስት እንኳን በየአራት ዓመቱ አመራሩን ይለውጣል። ፖሊሲ ባይለውጥ እንኳን አመራሩ መለወጡ ጥሩ ነገር ነው። 21 ዓመታት ሙሉ በአንድ አመራር ብቻ፣ በአንድ ፍልስፍና ብቻ፣ በትግል ላይ ተገናኘን በሚሉ ጥቂት ሰዎች ብቻ ኢትዮጵያን ያህል አገር እንዴት ትመራለች? በቀጣይ በኢትዮጵያ የተሸለ ነገር የሚመጣው የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ተገናኝተው፣ በክብ ጠረጼዛ ዙሪያ ተመካክረው መፍትሔ ማምጣት የሚችሉበት ዕድል ሲፈጠር ብቻ ነው።

ሰንደቅ፡- የአቶ መለስ ህልፈተ ሕይወት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አዲስ ነገር እንዲፈጠር ያደርጋል ብለው ያምናሉ?

አቶ ቡልቻ፡- አዎ…ትልቅ ለውጥ መምጣት አለበት። ኢህአዴግ እና አቶ መለስ አገሪቷን የመሩበት አቅጣጫ ብዙ ኢትዮጽያዊያንን ያረካና በቂ አልነበረም። ብዙ ኢትዮጽያዊያን ደስተኞች አይደሉም። ይህ ሁሉ በአቶ መለስ ቀብር ላይ የተገኙ የውጪ አገር ሰዎች ንግግርና ምስክርነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰምቶ በቃ ጥያቄዬ መልስ አግኝቷል ብሎ ቤቱ አርፎ የሚቀመጥ ይመስልሃል? የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ትልቅ ለውጥ እየጠበቀ ነው።

ሰንደቅ፡- ሰሞኑን ሐዘኑን ለመግለጽ የወጣው ሕዝብ ለኢህአዴግ እግረመንገድ ድጋፉን ሰጥቷል እየተባለ ነው?

አቶ ቡልቻ፡- በእኔ ግምት ሐዘንን መግለጽ ድጋፍን አያሳይም። እርግጥ ነው፤ አቶ መለስ እንደማናችንም ዘመዶች አሏቸው፤ የሚወዷቸውም፣ የሚደግፏቸውም ሰዎች አሉዋቸው። ከዚህ አንጻር ለሐዘን ሰው መውጣቱ አያስገርምም። ግን ኢትዮጽያ ሕዝብ ወጥቶ አላለቀሰም። ለምን ብትል ብዙ ቁስል ያለበት ህዝብ አለ። የዛሬ አራት ዓመት በአንድ ቀን ከቀትር በኋላ ብቻ በኦሮሚያ 200 ሰዎች የተገደሉበት ሁኔታ ተረሳ? በ1997 ዓ.ም የወለጋ ሕዝብ ጦርነት ተከፈተበት፤ መዓት ሰዎች አለቁ፤ ማሳቸው ተቃጠለ፤ የተቀሩት ተሰደዱ፤ ይህ ይረሳስ ቢባል እንዴትይረሳል? ለአቶ መለስ የሚያለቅስላቸው ቢኖርም እጅግ የበዛው የማያለቅስላቸው፣ ያዘነባቸው ሕዝብ ነው። ባለፉት ዓመታት በዚህ ሥርዓት ብዙ ሰዎች ታስረዋል፣ ተደብድበዋል፣ ተገርፈዋል፣ ተንገላተዋል፣ ተሰደዋል። ብዙ ቤተሰቦች ተበትነዋል። ይህንን እውነታ ማንም ሊክደው አይችልም። ሰዎች ለአቶ መለስ ስላለቀሱ፣ ስላዘኑ ብቻ ለኢህአዴግ ድጋፍ ሰጡ ማለት የማይቻለው ከዚህ አንጻር ነው። ለነገሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ለአቶ መለስ ቢያለቅስ እንኳን ለኢህአዴግ ድጋፍ ሰጠ ማለት አይቻልም።

ሰንደቅ፡- ተጠባባቂ ጠ/ሚኒስትሩ የአቶ መለስን ጅምሮች ይዘው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል። ይህ ምን ትርጉም ይሰጥዎታል?

አቶ ቡልቻ፡- አስቀድሜ ተናገርኩ እኮ!… ኢህአዴግ በሕግና በፖለቲካ ተደግፎ በሕዝብ ላይ ትልቅ ግፍ ሲሰራ ነበር። በዚህ መንገድ ሊቀጥል ነው? ይህን ዓይነት አካሄድማ ማንም ኢትዮጵያዊ አይደግፈውም። ለምንድነው ሰዎች ያለህግ የሚታሰሩት? ለምንድነው ሰዎች ከታሰሩ በኃላ በዘመዶቻቸውና በወዳጆቻቸው እንዳይጎበኙ የሚከለከሉት? ለምንድነው ሰዎች ሃሳባቸውን በነጻ በመግለጻቸው፣ በመጻፋቸው የሚታሰሩት? ሕገመንግስቱ የኀሳብ ነጻነት አለ ይላል። ማንም ሰው ኀሳቡን በነጻነት መግለጽ ይችላል። የተሰጠውን ኀሳብ ሰዎች ሊቀበሉት ይችላሉ ወይም አይችሉም ሌላ ጉዳይ ነው። ለምን ተናገርክ፣ ለምን ጻፍክ ብሎ ማሰር፣ ፍርድቤት ማመላለስ ምን ዓይነት የህግ ሥርዓት ነው?እርግጥ ነው አባይ ይገደባል ሲባል በግሌ ደስ ይለኛል። ልማትን የሚጠላ የለምና። ግን ስንትና ስንት ጉድፎችን ተሸክሜ እሄዳለሁ ብሎ ማለት ምን ማለት ነው? በእኔ ግምት በቀድሞ አገዛዝ እቀጥላለሁ ማለት ሕዝብን ተስፋ ማስቆረጥ ነው።

5 Responses to “የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ለውጥ እየጠበቀ ነው” አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

 1. Wontafa Reply

  November 6, 2012 at 2:19 pm

  BETAM AMESEGINALEHU ATO BULCHA BEWOTATINET YALSERUTIN AHUN JAGTEW MAWURATACHEW YAW YAW NEW ENA DEKMEWAL YIREFU.

 2. በለው ! Reply

  September 13, 2012 at 10:10 am

  የተከበሩ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የዕድሜ ባለፀጋ በትምህርታቸው እና ባላቸው ረጅም የሥራ ልምድ በተለይ በሀገራችን የኢኮኖሚው ዘርፍ ብቃት በሌላቸው እና በአድሎአዊ የሀገሪቱ የክክል ባጀት አመዳደብ ላይ እንዲሁም ሀገሪቱ አስመዘገበች ተብሎ በሚፎከርበት ፲፩ ከመቶ (ሁለት አሀዝ) ዕድገት ወሬው ከተግባሩ ያለመጣጣሙን በፓርላማ ውስጥ በነበራቸው ፭ ደቂቃ ጊዜን ቆጥበውም ይሁን አጋጣሚውን ባገኙት የጋዜጣ እና የሬዲዮ ቃለምልልሶች ሁሉ ያስተምራሉ።ሀገራቸውን በጣም የሚወዱ በፖለቲካው ዘርፍ በአብሮ መሥራት በሀገራዊ እርቅ…ሀገር የጋራ ነው!ሁላችንም ያገባናል!ብለው የሚያምኑ ታላቅ ሰው ናቸው።
  አሁንም እንደተለመደው ባሉበት የከበረ አድናቆቴን ምስጋናዬን አቀርባለሁ። *ይህን ነበር እንግዲህ አቶ መለስ ያጡት!? ችሎታ ያለውን አማካሪ ማፈላለግ ማግኝትና መምከር ጋጠ -ወጥነትን ማቆም! ሌላውም ዜጋ ለሀገሩ እንደሚያገባው መረዳት! ያልተዋጋ፣ በፓርቲ ያልታቀፈ፤ ከጎናቸው ሆኖ ያላዳነቀ እና ያላጨበጨበ ጠላት አድርጎ መፈረጅን ማስቀረት! በጦርነት አሸንፌ ሥልጣን ያዝኩ የሚል ፺፮ ከመቶ የሕዘብ ፍቅር አለኝ የሚል መሪ ‘መፃፍን፣ መተቸትን፣ መወያየትን ለምን ይፈራል? ?በግልፅነትና በተጠያቂነት ላይ ለምን ያፍራል? ? በሕገመንግስቱ አንድ ገፅ ተኩል የተለጠጠ ሥልጣንን አንድ ግለሰብ ለምን ጠቀለለ? ? ታዲያ መጨረሻው ባንቋሸሸው ሰንደቅ በሦስት ክንድ መሬት መጠቅለል አልቀርም!። በጣም አሳፋሪው እና ዘግናኙ ግን ያዙኝ ልቀቁኝ የውሸት ለቅሶ ‘ማላገጥ’ ይባላል። አደግመዋለሁ አላጋጭ ሆዳም ሌባ በዝቷል።አራት ነጥብ። በግለሰብ እሬሳ የሕዘብን ድጋፍ ለፖለቲካው ቁማር ተጫውተውበታል ።አራት ነጥብ። አሁን የሥልጣን ሽግግሩ “ሳይበከል እና ሳይበረዝ” የት ሄደ? ? አማካሪዎቻቸው እና ድሮ የፓርላማ ወንበር የሚቆጥሩት ዛሬ ቂጣቸውን ለማኖር የሚለካኩት ሁሉ… ሠውዬውንም, ራዕያቸውንም፣ፓሪቲያቸውንም፣ ሕዝቡንም ፣ሀገርንም፣ሲገሉ እና ሲያስገድሉ የኖሩ ጥቅመኖች አስመሳዮች ናቸው ። አቶ መለስም ፓርቲያቸውም, ጓዶቻቸውም ሞት ማንንም እንደማይፈራ! ዘረቢስ እንደሆነ! ገንዘብ እና ሥልጣን እንደማይገድበው! በሕገ መንግስታቸው ላይ ስላልተጠቀሰ መኖሩን ዘንግተውት ነበር ሞት ግን አልረሳቸውም …ይህም አጉል ዕንባ በከፍተኛ ዝናብና ጎርፍ ጀምሯል…ሽንኩርት በሰልፍ…አንድ እንቁላል ሦስት ብር ! ፬ ሚሊየን ሕዘብ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልገዋል….. የዕርዳታ ስንዴ ለዕዝን ከማቅረብ ሠርቶ እራስን መመገብ… ዕራዩን ቀስ እያልክ ብላ!ተጠንቀቅ አጥንትም አለው!!
  ታዋቂው,አዋቂው,ድንቀኛው,ፈላስፋው,ጠበብቱ,መሐንዲሱ ባለዕራዪ ቅንድባሙ የአፍሪካ መሪ,ለሱዳን እና ለሱማሌ ስላም ተወርዋሪ በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነዋሪ…ድንገት ታመሙ,መነመኑ,ታከሙ,ገገሙ አገገሙ,ተንጋለሉ,ጠፉ, ተሰወሩ,መነኑ, ደከሙ አረፉ,ሲባል መጨረሻው ናፍቆን ከረመ! አብዛኛው ሕገመንግስቱ በአንድ ገጽ ተኩል ባሸከማቸው ሥልጣን ደክሞአቸው ከጠቅላይነት መጠቅለል ይሻላል ብለው እንደቆረጡ አስቀድመው ተናግርዋል… ሳናይ አናምንም አልን!ላለፉት ሁለት ወር ከተለያዪ ሀገራት የቀብር ሥነ ሥርዓት ልምድ ሲኮርጁ ተከረመ,ደጋፊዎቻቸውን እያሰለጠኑ ነው ተባለ::ሰውዬውን አድዋ የጣለው አውሮፐላን መጣ አሥራ አምስት ቀን እሬሳ ቋንጣ ነው??ሰውዬው በቁማቸው ብቻ ሳይሆን ሞተውም የሥራ ዕድል ፈጠሩ ፎቶግራፍና ካኒቴራ በራሱ በኢህአዴግ ኢንቨስትመንት ከተማየቱን አጨናነቃት! ታጋይ መለስ ምን አለ ቀና ማለት ቢችሉ ነበር እንኳንም ለወያኔ ሊቀመንበር አድዋም ለጠላት እንዲህ ነበር የሸለሉት! የፎከሩት! የዘመቱት! የተዋጉት! ያሸነፉት! የማረኩት የገደሉት የቀበሩት ሐውልትም ያቆሙት ያውላቸሁ!! እናንተ ታሪክን ስታጠፉት ስትለውጡት ስትበርዙ ስትከልሱት የኢትዮጵያ ሕዝብ በራሳቸሁ ላይ ታሪክን ሠርተው በአደባባይ እራሳችሁን አስመሰከሯችሁ! ለልጆቻችሁ አወረሱላችሁ በእርግጥ ወደውን በፍቅር ነው ካላቸሁ እውነትም ደደቦች ናችሁ!ይልቁንም ሳትውሉ ሳታድሩ ሀገርን ለመታደግ ሁሉንም አሳትፋችሁ ለመሥረትና ለማደግ ,,, ሰላም; አንድነት; እኩልነትን; ሰብካችሁ; አሰብካችሁ; ሽማግሌ ቆጥራችሁ ለእርቅ ተነሱ ::ይህ ኩሩ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል ሊከበር ሊወደስ ሊደመጥ ቃሉ ሊተገበርለት ይገባል።አለበለዚያ በዚች የፉገራ ዕንባ ነገር ይመጣል በለው! ከሀገረ ካናዳ

 3. ሰላም Reply

  September 12, 2012 at 7:48 pm

  ትክክለኛውን እና ያለውን እውነታ ነው በትክክል ያስቀመጡት እግዚአብሄር ይባርክዎት

 4. What about others? Reply

  September 12, 2012 at 11:07 am

  We deeply thank you Obo Bulcha for raising our common questions.

 5. metertolemariam Reply

  September 11, 2012 at 12:22 am

  betame amesegnalhu Ato Bulcha- lelochum ye parlama abaloche, le ehadege magonbse titwe, leandem lemechereshawem – ye ethiopia hizebe mebete yikebke, ke ditu wede matu eygebane ametate mequtere yikere malete yijemeru.

  Endegena amsegnalu Ato Bulcha. Geta yibarkote yetebkotem

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>