አሜሪካ የተደበቀው ወንጀለኛ

September 9, 2012

ከኢየሩሳሌም አርአያ

የህወሃት አባል ነው ። ከትጥቅ ትግሉ ዘመን አንስቶ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ስልጣን እስከተቆናጠጠበት ጊዜ ድረስ ያለው የጀርባ ታሪክ በንጹሃን ደም የተጨማለቀ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህ ግለሰብ ተስፋዬ መረሳ ይባላል። ህወሃት ጫካ በነበረበት ጊዜ ተራው ታጋይ ከሴት ጋር የፍቅርም ሆነ የግብረ ስጋ ግኑኝነት ማድረግ እንደማይፈቀድለት አስገራሚው የፓርቲው ህግ ይደነግጋል። ይህ ህግ እስከ 1981 አ.ም የቆየ ሲሆን የበላይ አመራሩ ግን የፈለገውን የማድረግ መብት ነበረው። ፆታዊ ግንኙነት ሲያደርጉ የተገኙ ተራ ታጋዮች ይፈፀምባቸው የነበረው ቅጣት በጥይት ተደብድቦ መገደል ነበር። በሺህ የሚቆጠሩ የፓርቲው ተራ አባላት የዚህ ቅጣት ሰለባ ሆነዋል። እነዚህ ታጋዮች እንዲረሸኑ ሲወሰን ለመግደል ይጣደፉ ከነበሩት እና በርካታው የፓርቲ አባላት ከሚያስታዉሷቸው ገዳዮች አንዱ እና ቀንደኛው ተስፋዬ መረሳ ሲሆን ፣ ከእርሱ በተጨማሪ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ፣ ወ/ስላሴ ፣ሃይሉ (ሳንቲም) … በጭካኔ የግድያ ተግባራቸው ይጠቀሳሉ። ፊደል ያልቆጠሩት እነዚህ ወንጀለኞች የገዛ የትግል ጓዶቻቸውን ለመረሸን እጅ በማውጣት “እኔ… እኔ” እየተባባሉ ያሳዩ የነበረው ሰይጣናዊ ፉክክር እና ጥድፊያ ብዙ የፓርቲው አባላት አሁን ድረስ ያስታውሱታል።

አቶ መለስ እነዚህን ግለሰቦች በደህንነትና ፖሊስ ቁልፍ ቦታ ያስቀመጡአቸው የታዘዙትን እንደሚፈጽሙላቸው ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነበር ። እነ ተስፋዬ “ግደሉ “ሲባሉ “ስንት?” ነበር የሚሉት ።በገሃድም የታየው ይሄው ነበር ።

የክልል 14 ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት እና በህግ ዲግሪ የነበራቸው ሻለቃ በፍቃዱ ቶሌራ በ1996 አ.ም ያለ አንዳች ጥፋት እንዲነሱ ተደርጎ ፣በምትካቸው ወደ ስልጣን እንዲመጣ የተደረገው ተስፋዬ መረሳ በምርጫ 97 የአቶ መለስን ትእዛዝን በመቀበል የበርካታ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ደም እንዲፈስ አድርጓል ።በመቶዎች የሚቆጠሩ አካላቸው እንዲጎድል ፣በሺዎች የሚቆጠሩ እስር ቤት እንዲጋዙ ፣በርካቶች ከስራቸው እንዲባረሩ አድርጓል።ከአዲስ አበባ ፖሊስ 400 የሚጠጉ አባላትን በቅንጅት ደጋፊነት እና አባልነት በመፈረጅ እንዲባረሩ ወስኖአል።

በወቅቱ ለዚህ የወንጀል ተግባሩ ከአቶ መለስ ሙገሳ እና ውዳሴ ለማግኘት በቅቶአል። አስገራሚው ነገር ይህ ወንጀለኛ በዚህ የጭካኔ ተግባሩ የልብ ልብ ተሰምቶት ሸራተን ጎራ ማለት ይጀምራል። የተስፋዬ ሸራተን መጥቶ መለኪያ ማንሳት ያላስደሰታቸው ሽማግሌው ስብሃት ነጋ «አቅሙን፣ደረጃውን፣ልኩን አይቶ አይጠጣም?እዚህ መጥቶ ከእኛ እኩል መጠጣት እና መዝናናት ይፈልጋል ?የምን መዳፈር ነው ?» ሲሉ ንዴት የተሞላበት ተግሳፅ እንዲደርሰው ያደርጋሉ ።የስብሃት አደገኛነት የት እንደሚደርስ እና ምን አይነት የበቀል መዘዝ እንደሚያስከትል ጠንቅቆ የሚያውቀው ተስፋዬ አሳቻ ጊዜ ሲጠብቅ ይቆያል።

በ2000 አ.ም ከቢጤዎቹ ጋር አንድ ፕላን ይነድፋል። ከደህንነት ሹሞች ከነኢሳያስ ጋር የመከረው ጉዳይ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ተፈጻሚ ለማድረግ ተንቀሳቀሱ ።የምክክሩ ምስጢር ይህ ነበር ። በአዲስ አበባ በተለይ ፒያሳ፣አራት ኪሎ ፣ከጊዮን_- ፍልዉሃ እስከ ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ ፣አሜሪካ ግቢ፣ መርካቶ ፣ቦሌ፣22 ማዞሪያ፣መገናኛ እና በመሳሰሉት አካባቢዎች ከፍተኛ የዶላር ጥቁር ገበያ ይካሄዳል። ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ሲቪል የለበሡ በሺህ የሚቆጠሩ የደህንነት አባሎች በሁሉም መደብሮች በር ላይ በተመሳሳይ ሰአት እንዲገኙ ከተደረገ በኋላ በዚያው ቅጽበት ከተስፋዬ “ጀምሩ”የሚል ትእዛዝ ሲተላለፍ… መሳሪያ እየደቀኑ ዶላሩን ጠራርገው ከየመደብሩ በሃይል ወሰዱ ። ከአሜሪካ ግቢ ብቻ ከስምንት መቶ ሺህ ዶላር በላይ ሲገኝ በአጠቃላይ 4.5ሚልዮን ዶላር ገደማ በጉልበት ተወረሰ ። ከዶላር በተጨማሪ ከመርካቶ እና ፒያሳ ከ2 ሚሊዮን የበለጠ ጥሬ ገንዘብ(የኢትዮጵያ ብር) ተወስዶአል። በ1984-85 አ.ም በወቅቱ የሃገሪቱ ፕረዚዳንት የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ የዶላር ጥቁር ገበያን አስመልክተው ሲናገሩ “ምንዛሬውን ከወቅቱ ገበያ ጋር እኩል እናካሂደዋለን እንጂ የጥቁር ገበያውን ቁጥጥር አናደርግበትም ፣አንነካውም “በማለት ተናግረው እንደነበር ብዙዎች ያስታውሱታል። ሆኖም ግን በቃሉ የማይገኘው የኢህአዴግ መንግስት በጠራራ ፀሃይ የለየለት የአደባባይ ዝርፊያ ሲያከናውን በርካቶች ኑሮአቸው ተናግቶአል፤ አንዳንዶችም ህይወታቸውን እስከማጥፋት ደርሰዋል።

ይህ ገንዘብ በቀጥታ ገቢ የተደረገው ወይም የተረከበው ተስፋዬ መረሳ ነበር ።በወቅቱ በመንግስት ሚዲያ ህገወጥ የዶላር አዘዋዋሪዎች እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ እና ገንዘቡ ለመንግስት ገቢ መደረጉን የገለጸው ተስፋዬ፣ይህንን በተናገረ በሳምንት ልዩነት የተዘረፈውን ገንዘብ በሳምሶናይት ይዞ በቦሌ ወደ ኬንያ አመራ ።ከዚያም ወደ አሜሪካን አቀና ።ይህ በንጹሃን ደም የታጠበ ወንጀለኛ እና ዘራፊ አሜሪካን እንደመሸገ የተረጋገጠ ቢሆንም፣የት ከተማ እንዳለ እና እንደሚኖር ማወቅ አልተቻለም።

11 Responses to አሜሪካ የተደበቀው ወንጀለኛ

 1. samsson Dechassa Reply

  September 15, 2012 at 3:39 am

  It would be great if any one who has his picture could share it with the Ethiopian community in the US. If he is in this country he would not be able to hide forever– sooner or later the rat has to come out of its hole!

 2. lebaw Reply

  September 11, 2012 at 12:06 am

  i think his family won the dv lottery and i know that they were first living in atlanta ga and i believe his wife and kids are still there but i’m not sure about him i saw him in dc when he first arrived in usa

 3. anteneh Reply

  September 10, 2012 at 7:01 am

  tesfaye is in Addis now. why dont get tamrat Layne to justice who massacred thousands of ethiopians and who lives in colorado now?

 4. dee Reply

  September 9, 2012 at 7:07 pm

  ERI-TV Amharic News (May 10, 2008). check on ተስፋዬ መረሳ pic

 5. cucu Reply

  September 9, 2012 at 2:14 pm

  የተስፋዬ መረሳ ፎቶው ካለ እና ቢወጣ በቀላሉ መለየት ይቻላል። ትልቅ ሃላፊነት የነበረው ሰው ከሆነ ፎቶውን ማግኘት አይከብድም። ፎቶው ያላቸው ሰዎች እንዲተባበሩ ማድረግ እና ለFBI እንዲላክ ማድረግ ነው። እየሩሳሌም አርአያን በጣም አመሰግናለሁ።

 6. Ewnet Aymotim Reply

  September 9, 2012 at 1:47 pm

  Eyerusalem, may you post his pictures and we all can hunt him?
  thank you and great job.

 7. loly Reply

  September 9, 2012 at 1:36 pm

  please our fellow ethopian in U.S give information for FBI about this idot and others! the crimes he did is not easy also.

 8. Abesha Reply

  September 9, 2012 at 11:51 am

  Let such crimes reveal and let the hunting begin. Everyone, mark these names and pass them on to the FBI or state departments. Justice is so close to us and it wouldn’t cost a penny to report a misdeed.

 9. Walelgne Mekonnen Reply

  September 9, 2012 at 7:50 am

  እጅግ በጣም ጥሩ አካሄድ ነው!! ብዙ የወያኔ ወንጀለኞች (በነብስ ማጥፋት በማሰቃየት በሰብአዊ መብቶች ጥሰትና የሃገርና የህዝብ ሀብት የዘረፉ ወንጀል የፈፅሙ) በምዕራቡ ዐለም ተደብቀው እየኖሩ ይገኛሉ: እነዚህን ወንጀለኞች ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመተባበር ለፍርድ እንዲቀርቡ መደረግ አለበት::

 10. Eyasu Reply

  September 9, 2012 at 4:51 am

  Tesfaye Meresa used to live in Macon Georgia. Some Ethiopian Patriot in Atlanta were on the fianal stage of exposing this criminal to US authority when he disappeared from Macon. According to our finding he is in Adis abeba Now

 11. Natnael Haile Reply

  September 9, 2012 at 4:35 am

  Please any body who has his picture or vivid description sent to the media, so we can find him and he can have his place for the rest of his life.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>