የወ/ሮ አዜብ ሥላቅ

September 8, 2012

(ወገ ሹኩቻ እና የአዜቧ አቛም ፡-  ወ/ሮ አዜብ የቱ ጋ ናቸው?… ለሁሉም ግን ተዘባበቱብን)

( ተፃፈ በወፉ 9/5/2012)

ወ/ሮ አዜብ ከሁለት ልጆቻቸው ጋር በህዝብ ፊት ቆመው ያደረጉት ንግግር ስሜት የሚነካ መሆኑን ባይካድም ተራ የፖለቲካ ሸፍጥ የሚመስልም እንደነበረ ሁሉ ይገነዘበዋል የሚል ፅኑAzeb Mesfin, the wife of Meles Zenawi ዕምነት አለኝ፡፡ ወ/ሮ አዜብ ስሜት በጎዳው ንግግራቸው እና አስበው ያፈለቁት ሃሳብ እጅግ የሚያሳዝን ቢሆንም ንግግራቸው ውስጥ ግን ሸፍጥ፤ ክደት፤ የተራከሰና በስክነት ያልታሰበ ፖለቲካ ጣል አድርገዋል፡፡ ሙት ወቃሽ አያድርገኝና ባለቤታቸው የተዘባበቱበትን የህዝብ ዳኝነት ጉዳይ ወ/ሮዋም አንስተው ተሳልቀውብናል፡፡

በመጀመሪያ የወ/ሮ አዜብ ስብዕና ወይንም የአማራ ትግሬነት ደም ቅየራ እንዴት እንደተከናወነና በማን ተንኮል ተበርዞ እንደተሰራ ከወ/ሮ አዜብ ከ30 ዓመት በላይ ቆይታ በኋላ ተገልፆልናል፡፡ ብዙዎች እንደሚሉት እና ወ/ሮ አዜብ እራሳቸው እንደመሰከሩት ወደ ትግል ሜዳ የገቡት ትንሽ ልጅ ሆነው ነው፡፡ ወጣት ሳልሆን ገና ትንሽ ልጅ እያለሁ መለስን አወቅሁት ይሉናል፡፡ የዘረኝነት ኮብራ ወ/ሮ አዜብን የነደፋቸው በዚያን ጊዜ ነው፡፡ ለሁሉም እኩልነት የሚታገሉት መለስ የትግሬን የበላይነት የከተቧቸውና ጎንደሬነታቸውን አስወልቀው ትግሬ ያደረጓቸው ያኔ ነበር፡፡ የወ/ሮ አዜብ ስብዕና ተጠፍጥፎ የተሰራው በመለስ መሆኑን ለመገንዘብ ጥቂት ሃሳብ ላንሳ፡፡ መለስ በፍቅር ፍቅረኛቸው ነበር፡፡ ስለዚህም መለስ ልባቸውን በፍቅር ሰልቦታል፡፡ ሁለተኛው አስተማሪየ ነበር አሉ፡፡ መለስ የአዜብን ጭንቅላት (አዕምሮ)በከባዱ አቅጣጫውን አስቶታል፡፡ በተምታታው ቅጥ አንባሩን በጠፋው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፤ሌኒንዝም፤ ልማታዊ ዲሞክራሲ፤ ጥገኛ ፤ትምክህተኛ እያለ በጭንቅላታቸው ላይ ተጫውቷል፡፡ ወ/ሮ አዜብ አስተማሪየ ነው ከማለታቸው በላይ የመለስ ጭንቅላት ገቢያ ያወጣልም ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ ስለዚህም አዜብ መስፍን ስብዕናም ስሜትም ጭንቅላትም ከመለስ ተቀብለዋል፡፡ አለቃየ ነበር ብለውናል፡፡ በአዜብ ላይ ስልጣን ነበረው ማለት ስለሆነ ሃይላቸውን ሁሉ የሚቆጣጠረው መለስ ነበር ማለት ነው፡፡ መለስ በመጨረሻም የአዜብ ሁሉ ነገራቸውና ሁለንተናቸው በመሆኑም በፍፁም ነፍሳቸው ሃይላቸው እና ሃሳባቸው የመለስ እስረኛ መሆናቸውን መስክረዋል፡፡ በመሆኑም ከ30 ዓመት በላይ የአንድ ሰው ሁለንተናዊ እስረኛ የነበሩ ሴት ሃዘን ተጨምሮባቸው የሚናገሩትን ማመን ቢከብድም ንግግራቸው ማጤን ግን ተገቢ ነው፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጲያ ህዝብ በአንድ ቦታ በአንድ አይነት እባብ ሊነደፍ ስለማይገባው ነው፡፡

ከዚህ በመነሳት  ̋የመለስ ራዕይ እስካልተበረዘ ድረስ” ይሰመርበት ከኢትዮጲያ ህዝብ ጎን ቆሜ የበኩሌን አስተዋፅኦ አደርጋለሁ ብለዋል፡፡ ከዚህ ንግግር የመጀመሪያው ጥያቄ አዜብ ከኢህዴግ ጎን የቆሙት በመለስ ራዕይ ብቻ ነው ወይንም ኢህአዴግ ራዕይ የለውም ማለት ነው የሚል ነው፡፡ አሊያም የመለስ ራዕይ ወይም ማንነት እንጂ ኢህአዴግ የለም ማለት ነው፡፡ ድሮ ድሮ ኢህአዴግ የለም ወያኔ እንጂ ይባል ነበር አሁን ደግሞ መለስ እንጂ ወያኔም ኢህአዴግም እንደሌለ ነው የምንረዳው፡፡ ወ/ሮዋ ሌላ የነገሩን ሁለተኛው ነገር  ኢህአዴግ ራዕይ እንደሌለው ሲሆን ሶስተኛው ኢህአዴግ የመለስን ራዕይ እምቢ ሊል ይችላል የሚለውን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ይህ ንግግር የሚያሳየን ኢህአዴግ መለስን ፈርቶ የመለስን ራዕይ አቤት ወዴት እያለ ይፈፅም እንደነበር ነው፡፡ አዜብ ስጋታቸውን እና ምርጫቸውን አካፍለውናል፡፡ የዚህ አስደናቂ ጎን የመለስ ራዕይ ካልተበረዘ ከኢትዮጲያ ህዝብ ጋር እቆማለሁ ማለታቸው ነው፡፡ ተመልከቱ እኒህ ሴት የሚቆሙት ከማን ጋር ነው? ከኢህአዴግ ጋር ወይስ ከኢትዮጲያ ህዝብ ጋር?  ከኢህአዴግ ጋር ወይስ ከመለስ ራዕይ ጋር ወይስ ከወያኔ ጋር? እንደግል ወይስ እንደወያኔ?  እንደ ኢህአዴግ ወይስ እንደ ወያኔ?  በአጭሩ ወ/ሮ አዜብ እያሳበቁት ያሉት መለስ ስለሌለ የባለቤቴን ራዕይና እኔን እንዳያባርሩኝ ጠበቃ ቁሙ የምትል ቅስቀሳ መሰለችኝ፡፡ ወ/ሮዋ በሃዘን ውስጥ ቢሆኑም እያወጉን ያሉት ወግ  ̋ወገ ሹኩቻ ነው፡፡”

ወ/ሮ አዜብ አቛምዎትን እንደግልም ሆነ እንደ  ፓርቲ ፖሊት  አባልነትዎ ሊለዋወጡ (እንደ ባለቤተዎ ሊገለባበጡ) ይችላሉ፡፡ ከአህያ ጋር የዋለች ላም እንዲሉ የተገለባባጩ መለስ ሚስት በመሆነዎ አልፈርድቦዎትም፡፡ ግና ማሳሰቢያው በኢትዮጲያ ህዝብ ላይ አይሳለቁበት የሚል ነው፡፡ ስላቀዎን ላሳየዎ፡-

ስላቅ 1፡-  ህዝቡ ዳኛ ነው ብሎ መለስ ያምን ነበር አሉን፡፡ ይህ ስላቅ ነው፡፡ ለ21 ዓመት አንድም ቀን የህዝቡን ሃሳብ ሲፈፅም ታይቶ አይታወቅም (በመሬት ፖሊሲ፤ በምርጫ፤ በአሰብ ወደብ፤ በፌደራሊዝም አወቃቀር፤ በትምህርት ፖሊሲ ሁሉ ጭፍን አምባገነን መሆኑን ለ21 ዓመት በህዝቡ ላይ ተፈናጦ አስመስክሮአል)

ስላቅ 2፡-  መለስ ከውስጡ ዲሞክራት ነበር አሉን ይህም ስላቅ ነው፡፡ መለስ አመባገነናዊ ገዥ ነበር፡፡

ስላቅ3፡-  ልጆቹን ለኢትዮጲያ ህዝብ ሲል አያውቃቸውም አሉን ይህም ስላቅ ነው፡፡ምክንያቱም ከቤተሰቡ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እና ምቾት እንደነበረው ከንግግረው ነቅሼ ላውጣ

-የመለስ ሞት ለእኔ መራር ጨለማ ነው፡፡ ፍቅረኛየን አስተማሪየን አለቃየንና ሁለንተናየን አጣሁ ብለዋል፡፡ ጥብቅ ግንኙነት፡፡

-ልጆቼ መካሪ አፍቃሪና ተንሰፍሳፊ አባታቸውን ስላጡ አዝነዋል ብለዋል፡፡ ልጅን ያለ አባት ያስቀረው መለስ ታምራት ላይኔን ለ12 ዓመት አስሮ ልጆቻቻውን ያለአባት አስቀርተዋቸዋል፡፡ እሱ ግን በቤተመንግስት ከልጆቹ ጋር ሲዝናና ኖሯል፡፡ ይህም ጥብቅ ግንኙነት እንደነበረው ያሳያል፡፡

ስላቅ 4፡- የእናትነት ፈተናን ብቻየን የምወጣበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ በፊት ከማን ጋር ልጆቾዎን አሳደጉ ጊዜ ከሌለው መለስ ጋር አልነበርም? ለኢትዮጲያ ህዝብ ሲል ጊዜ ለልጆቹ አልነበረውም ካሉን እና ያሉን እውነት ከሆነ እስከዛሬ ብቻዎትን ነበር ያሳደጓቸው ማለት ነው፡፡  ስለዚህ ምንም አዲስ ነገር የለም ከቤተመንግስት ግቢ ከመውጣቶዎ በስተቀር፡፡ ከኢትዮጲያ ህዝብ ጋር ከሆኑክ እወጣዋለሁ ያሉንማ ከባድ ስላቅ ነው፡፡ ምንድን ነው ከኢትዮጲያ ህዝብ የሚጠብቁት ስለ ልጆቾዎ? እናንተ የማንን ልጅ አሳድጋችሁ ነው የኢትዮጲያ ህዝብ ልጅ የማሳደግ ሃላፊነት የሚሰጠው? ይህ አገራዊ ጉዲፊቻ (ልጅን ለሃገር ሙሉ መስጠት)ከምን የመጣ ነው ሞትን ፈሩ እንዴ? ይህም ስላቅ ነው፡፡ ወ/ሮ ሙሉ የታምራት ላይኔ ባለቤት ብቻቸውን ባላቸውን አምባገነኑ ባለቤትዎ በግፍ አስሮ እያሰቃያቸው እነ ብሌንን ሲያሳድጉ የኢትዮጲያ ህዝብ አብሮ እንዲቆሙ ንግግር አላደረጉም፡፡ እውነቱን ልንገረዎት ይህን የምናገረው ልቤ እየደማ ነው ከልቤ አዝንለዎታለሁ ግን ንግግርዎ ልቦዎን አሳየኝና ይህንን አፃፈኝ፡፡ እኛን አላወቁንም፡፡ ኢትዮጲያውያን ሩሁሩሁ ነን ግና ሸፍጥ አንወድም፡፡ ሃዘኑን ፖለቲካ ሲያደርጉት የአርባ ጉጉ ሕፃናት እልቂት የ97 ምርጫ እልቂት ሌላም ጥፋት ትውስ ይለናል ፡፡

ስላቅ 5፡- መለስ ቢል ቦርድ ላይ እንዲለጠፍ አይፈልግም ነበር አሉን፡፡ ይህ ስላቅ ነው፡፡ የመለስ የስልጣን ማዕረግ ብዛት የትየሌሌ ነበር፡፡ ለ21 ዓመት በህዝቡ ላይ ተፈናጦ ገዝቷል፡፡ ከዚህ በላይ ምን ቢል ቦርድ አለ?

ስላቅ 6፡- መለስ ለእኩልነት ነው የታገለው ያሉትማ ታላቅ ስላቅ ነው፡፡ መለስን የሚያክል በዘረኛነት የሰከረ ሰው ታይቶ አይታወቅም፡፡ ፎቁ የማነው? መሬቱ የማነው? የጦር ሃይሉ ፤ ሰራዊቱ እና ዘራፊው ማነው? ጎንዴሬዋን አዜብን ትግሬ ነኝ እስኪሉ ያሳታቸው ማነው?

ስላቅ 7፡- እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ መለስ በየቤቱ ምን እንዳደረገለት ያውቃል ብለዋል፡፡ አቤት ስላቅ! ስላቅ ያደረገውን ልንገረዎት መለስ ያደረገው ሞት ውርደት ስድብና ጥፋት ነው፡፡

የእኔ ጥያቄ አሁን የኢትዮጲያ ህዝብ እንዲያውቅልዎት የፈለጉት ምንድን ነው? የሚለው ነው፡፡ ፍላጎትዎ፡-

 1. ኢህአዴግ የመለስን ራዕይ ሊያስፈፅመው ካልቻለ ህዝቡ ከጎኔ ሆኖ ያምጽ ለማለት ነው?
 2. ኢህአዴግ ራዕይ የለውም ወይንም ሌላው የፓርቲው አባል ማሰብ አይችልም ብለው እየቀሰቀሱን ነው?
 3. የመለስ የጥፋት ራዕይ እንዳይበረዝ ማለትም ሰው ይታሰር ፤ዴሞክራሲ ይጥፋ፤ አማራ እና ኦሮሞ በዘሩ ምክንያት ይንገላታ፤ ትግሬ በዘሩ ምክንያት ይጠቀም ለዚህም እንታገል እያሉን ነው?
 4. የመለስ ደካማ ጎኑ ሳይበረዝ (ሳይታረም) ይቀጥል ለማለት ነው?

ወ/ሮ አዜብ ያሉት ምንድን ነው? መለስ ያሰበው እና ያለው ካለተፈፀመ አልታገልም ነው፡፡ የመለስ ራዕይ ካልተበረዘ አስተወጽኦ አደርጋለሁ ያ ካልሆነ አላደርግም ነው፡፡ ይተውታ፡፡ እንዲያውም ይረፉ፡፡ አገሪቱን መለስ መለስ እያሉ አያላዝኑባት፡፡ የእርስዎ አስተወፅኦ ለሃገሬ ኢምንት ነው፡፡ ደግሞስ እስከዛሬ ምንም ሳያደርጉ  ቆይተው ዛሬ ምን መጣና ነው የኢትዮጲያ ህዝብ ያሉን? የትግራይ ህዝብ አይሉንም? ውሸት አይደልም ሃዘንዎ ሃዘናችን ነው፡፡መለስ ለፍርድ ሳይቀርብ መሞቱ ያሳዝናል፡፡ ሰውም ስለሆንንና ስለሆነ በመሞቱ አዝነናል፡፡ ሞትንና ሃዘንን ማየታችሁ ትምህርት ቢሆንም አስከፍቶናል፡፡ እኔ ፃሃፊው በግሌ ያዘንኩት ለእርስዎ ነው፡፡ ያለቀስኩትም ተቀጣሁ እያሉ ሲያለቅሱ ባየሁ ጊዜ ነው፡፡ ሳላጋንን እየየ ብየ አልቅሻለሁ ቢሆንም ግን ወ/ሮ አዜብ ልንገረዎት በሃዘን ላይ ሃዘን ካልጨመርኩበዎት ለኢትዮጲያ ህዝብ የሚያደርጉት ብቸኛው አስተዋፅኦ (ለሃገሬ የሚያደርጉት ) እራሶዎንና ᎂች ባለቤትዎን ወክለው (ይዘው) አውቀው ባጠፉትና ሳያውቁ በሰሩት በደል ንስሃ መግባት ብቻ ነው፡፡ቸር እንሰንብት፡፡ አዜብ ሆይ  ይቆዩልንም ይረፉልንም፡፡ ( ተፃፈ በወፉ 9/5/2012)

10 Responses to የወ/ሮ አዜብ ሥላቅ

 1. aytal Reply

  September 16, 2012 at 7:39 pm

  Fascist Azeb what do you want from the Ethiopian people – from Armachiho to Gambela to Gura Ferda who were killed and terrorized by your fascist Meles. I was expected that you and your fascist Meles be dragged out of Menelik palace by angry/hungry Ethiopians like the last communist dictators of Romania. Fascist Meles is lucky to be buried as a “normal” human being. He was worse than Mussoloni as regards to what he did to Ethiopia and the Ethiopian people. You and the fascists were enjoying 21 years of “SELAM” as told by killer SEYE

 2. meretework Reply

  September 10, 2012 at 12:57 am

  God have mercy on EMYE ETHIOPIA!! we have to be really serious for our land!she is the mother of corruptin , and evil” she is reflect her hasband, beqrebu wede esuga higelen AMEN!!

  DELE LE EWNET LE ETHIOPIA!!!

 3. ashebr Reply

  September 9, 2012 at 11:08 pm

  the comment and the analysis are wonderful and educational. it is also initiating for fighting for freedom. Let us get struggle for freedom and make Ethiopian proud and it good governance.

 4. Abebe Reply

  September 9, 2012 at 8:23 pm

  This article writer why you mentchion only Tamirat Layene(Lebaw)?There are somany ethiopian killed and in presion in Ethiopia>You know only Tamirat Layne(Lebaw and Geday Weyane)?

 5. Zeg Fanta Reply

  September 9, 2012 at 4:48 am

  Wofu, you said it all. Your writing skills and perceptions are scholar of first rate. You have described what Azeb said and what was in her mind accurately. You helped the other reader who commented after you what he did not want to read and understand. He offered no tangible argument other than an expression of rejection, which a sign of low spirit, perhaps more of realizing the reality. I thank you for making Azeb and people like her understand what it means to be on a rocky boat. The sky is coming down in turn to those who lived high and glittering in the mist of agonies and total desperations the Ethiopians felt for two decades. Meles saw what it meant to be hopeless and powerless, I am sure during his final minutes of his life. Azeb never knew the Ethiopian people, if she did what roles she played when young people unprotected like her children were mowned down by machine guns and mothers lost their savings, retirement funds, their children in a split of seconds! She did not raise her voice or even act she knew about it. As Wofu said, she was oblivious to all the sufferings of Ethiopian people and I am not sure what Ethiopian people she was referring to. Any way, this is to express to you my appreciations to your perceptive and accurate analysis and telling it as it is. Keep it up brother/Sister! We have lots of things ahead of us, and let us sit tight and watch and also do things that we can while the dust settles down. Happy New Year!

 6. Freedom le hulu Reply

  September 9, 2012 at 4:36 am

  Mr. Truth do you really think it is a waste. Do not make a mistake Mr.Wofu is telling the truth. She need (Azeb) to think twise her time is over this is not the right time to ask the Ethiopian peoples help. The will pay the price any way.

 7. Anonymous Reply

  September 9, 2012 at 2:43 am

  በርግጥም አዜብ ተስፋ የቆረጠችበት ጊዜ ላይ መሆንዋን ለማወቅ አያዳግትም;; ጸሃፊው እንዳለው እርዱኝ የምትለው ስትፎክርበት የነበረችውን ደሃውን የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ወይስ ትግራይን ነው? የሚለው አጠያያቂ ነው;; እንደኔ አስተያየት ግን አዜብ ታለቅስ የነበረው በከፊል ስለርስዋና ስለልጆችዋ የወደፊት እጣ ፈንታ እንዲሁም ከቤተመንግስት መውጣቱና ተራ ሰው መሆኑ ሲታሰባት እንጂ በመለስ ሞት ብቻ እርር ድብን ብላ አዝና አይመስለኝም;; “የጀነራል ሚስት ጀነራል የሆነች ይመስላታል” እንደሚባለው መለስ ቀጥቅጦ ይገዛ እንደነበረው እኔስ በምን አንሼ! ሳትል የቀረች አይመስለኝም:: አፍሪካን ምስጋና ይግባትና ደንቆሮውና ትምህርት የሰለቸው ሁሉ ጫካ ሸፍቶ አሸንፎ ሲመጣ ምደረ ምሁራንን ሰብስቦ የራሱን ፍልስፍና በድፍረት በማስተማርና ሰውን በማስፈራራትና በመግደል የሚፈልገውን ማድረግ የተለመደ ትእይንት ነው:: በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብን በመናቅ የሚፈልጉትን ነገር እያደረጉና እየደነፉ ላለፉት 21 አመታት ኖረዋል አሁንም እስከመቼ እንደሚቆዩ አይታወቅም:: ወይዘሮዋም ከስልጣን እርካብ ላይ ላለመውረድ መዘላበድዋ የተለመደ ነገር ስለሆነ አያስደንቅም:: የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ በመሆኑ “ይሁን እስቲ የፈለግሽውን በይ!” በአፉም ባይሆን በሆዱ ማለቱ አይቀርም:; የመሪነት ችሎታ ያለው ሰው የታጣባት ሀገር ይመስል ዝንጀሮው ሁሉ በጠመንጃ አፈሙዝ አስፈራርቶ ስልጣን ላይ እየወጣ የፈለገውን ሲያስር: ሲገድል: ከሃገር ሲያባርር ወዘተ አፉ የተሸበበው ህዝብ እህህ እያለ ወደአምላኩ ያለቅሳል:: የምድር ሲኦል የሆነች ሃገር እስክትመስል ዜጎችዋ በረሃብና በእርዛት የሚደርስላቸው ጠፍቶ ሲሰቃዩ ሌላው በጥላቻ ተሞልቶ “ጎሽ! ይበላችሁ” እያለ ጮማውን ሲቆርጥ ማየት ያሳዝናል:: ከጸሃፊው ጋር አንድ የማልስማማበት ነገር ቢኖር ከመለስ ጋር እጅና ግዋንት ሆኖ ይሰራ የነበረውን ታምራት የተባለውን ሰው እንደምሳሌ መሰንቀሩ ሌላ ኢትዮጵያዊ ለምሳሌ ጠፍቶ ነው? ያስብላል:: በኔ ግምት እርሱም ልክ እንደሌሎች ግዋዶቹ ከተጠያቂነት አይድንም:: የነዚያ ምንም ሳያጠፉ ወደገደል ውስጥ እየጮሁ የተፈጠፈጡት ኢትዮጵያውያን አምላክ አንድ ቀን መፍረዱ አይቀርም::

 8. truth Reply

  September 8, 2012 at 8:55 pm

  Waste of time Mr Wofu.

  She is the wife and mother of his children. Do you expect her to curse her husband? Please, focus on something else. No one really cares what a wife says about her husband…

  • cucu Reply

   September 9, 2012 at 2:27 pm

   we do buddy!

 9. Tulu Reply

  September 8, 2012 at 9:36 am

  ከቀብር መልስ
  (ለ”ቀዳማዊት” እመቤት አዜብ መስፍን)
  ከቀብር መልስ…
  ፀሀይም አድማስን ስማ ጠለቀች
  ጨረቃም በእፍርታም ፈገግታ ደመቀች፤
  “ፈራጅ ህዝብ” ወደየኑሮው ዘለቀ
  ያ በአንተ ክናድ የደቀቀ!
  እኔና እኔ ብቻ ቀረን
  በነበር ጽልመት ተውጠን።
  ከቀብር መልስ…
  “ብቸኝነት ብቻ ሲቀር”
  ሃዘኑም ሲሆን የግሌ
  የምሸከመው መስቀሌ፤
  ያን “ፈራጅ ህዝብ” ተጣራሁ በኦና
  ሐዘኑን ሳይሆን ይቅርታውን ልመና።

  ቱሉ ፎርሳ (ከነምሳ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>