ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች

September 7, 2012

ሰሞኑን የዜና ማሰራጫዎችን ያጨናነቀው የአምባገነኑ የመለሰ ዜናዊ ህልፈት ነው።ይህንንም አስመልክቶ አገር ቤት ህዝባችን ወጥተህ ድንኳን ጥለህ አልቅስ እየተባለ ቁምስቅሉን እያየ ነው።የጎዳና ተዳዳሪና ሆስፒታል የተኙ ድኩማኖች ሳይቀሩ በዊል ቼርና በክራንች እየተጎተቱ የዎያኔ ካድሬዎች ሲያስለቅሱ ሲያዋክቡ አይተን ተደምመናል፡ድርጊቱም የሰሜን ኮሪያውን አምባገነን ሞት አስታውሶናል።ይቺን ማሳሰቢያ ለመጻፍ የተገደድነውም ሰሞኑን በከተማችን በዊኒፔግ ወጣችሁ ለመለስ አልቅሱ የምትል በራሪ ወረቀት በማየታችን ነው።”ግዛኝ ብለው ለመሸጥ አሰበኝ”ይሉዋል ይኸ ነው።ሃገር በሃራጅ ሲቸበቸብ፤ህዝባች በረሃብ ሲረገፍ ዝም ብለን በማየታችን እንደከብት ቆጥረውን ይሆን?

ለመሆኑ መለስ ማን ነበር?

ከታሪክ እንደምንረዳው፤በአባቱ በጣሊያን ወረራ ጊዜ ለጣሊያን ሎሌ ሆነው የኢትዮጵያ አርበኞችን ያሳድዱ የነበሩ የትግራይ ተወላጅ የአቶ አስረስ የልጅ ልጅ መሆኑን ስንረዳ፣በናቱ ኤርትራዊ መሆኑን እናውቃለን።ስለሆነም በስድሳዎቹ ገደማ ኢትዮጵያን አፈራርሶ ኤርትራንና ትግራይን ለማስገንጠል ቁጭትና በቀል አርግዞ ከመሰል ጓዶቹ ጋር  ጫካ ገባ፤በለስ ቀናቸውና ሃገሪቷንም ተቆጣጠሩ።

ከዚያስ መለስ ምን አደረገ?ከዚያማ ምን ያላደረገው ነገር አለ፤በመጀመሪያ ሃገሪቷን በዘር በቋንቋ ክልል ሸንሽኖ አንዱን ብሄር በሌላው ላይ በማነሳሳት ህዝብን ካጨፋጨፈና እርስ በርስ የጎሪጥ እንዲተያይ ካደረገ በኋላ ኤርትራን ለማስገንጠል የተባበሩት መንግስታትን ተማጸኖ ህልሙን እውን አደረገ፤ጌቶቹ አሜሪካና እንግሊዞች በአሰብ ጉዳይ ላይ እንዲደራደር ቢጠይቁትም መለስ ግን ወደብ አያስፈልገንም በማለት ሃገራችንን ወደብ አልባ አደረጋት።የኢትዮጵያም ህዝብ አገራችን በጠላት እጅ እነደወደቀች ያን ጊዜ ተረዳ። የኢሳያስና የመለስ ፍቅር ብዙም አልቆየም የኢትዮጵያ አምላክ ምንቅርቅራቸውን አወታጣውና “እብድ ቢጨምት እስከ እኩለ ቀን”እነዲሉ ጦር ተማዘዙና ከሁለቱም ወገን ከ120 ሺ ያላነሱ ወጣቶች ከሁለቱም ወገን በጦርነቱ ሰለባ ሆኑ፤ከዚያም የአባይን ወንዝ ለግብጽ አሳልፎ በመስጠት ብቸኛ ተጠቃሚነቷን በፊርማ አረጋገጠላት፤ይህ ግለሰብ ነው አባይን የደፈረ ጀግና እየተባለ የሚለፈፍለት፤ድፍረቱ የኢትዮጵያንም፡ሆነ የአባይ ተፋሰስ አገሮችን ሳያማክር አሳለፎ በመሰጠት ከሆነ እንስማማለን።በዚህም አላቆመም ጀግናው መለስ፣ርዝመቱ ወደ 1600 ኪሎ ሜትር ወደ ጎን ደግሞ 60 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ለም መሬታችንን ነዋሪዎቹን በማፈናቀል ለኢትዮጵያ መሰረታዊ ጠላት ለሱዳን በማን አለበኝነት አሳለፎ ሰጣቸው።መለስ ሃገሩንና ከሱ ጎሳ ውጪ የሆነን ሁሉ እየጠላ ለ21 አመት ገዛ፤ስለሆነም ኢትዮጵያን ለጨረታና ለሽያጭ በማቅረብ የገጠሩንም ሆነ የከተማ ህዝባችንን እያፈናቀለና የጎዳና ተዳዳሪ በማድረግ በሃገርና በወገን ፍዳና ስቃይ ተሳለቀ፤ህዝብ በገዛ አገሩ ስደተኛ የሆነባት አገር ሆና እያለች ይህን ሰው ለልማት የተጋ መሪ እያሉ ህዝቡን ተሳለቁበት፤ዛሬ ደሃው ገበሬ መሬቱን ተነጥቆ ከቀየው ተባሮና መላው ቤተሰቡን በትኖ ለልመና ለጎዳና ተዳዳሪነት ተዳርጓል።ሃቁ ይኸ ሆኖ ሳለ ኢትዮጵያ ለማች ይሉናል፤ዛሬ ቻይና ህንድ አረቦች ሌሎቹም ሃገራችንን ተቀራምተው መሬታችንን አርሰው ያፈሱትን ምርት አንድ ማንኪያ ሳያስቀሩ ወደ ሃገራቸው ሲልኩ ህዝባችን በረሃብ እየረገፈ ነው፤ሰራተኛውም ልጆቹን በቀን ሶስት ጊዜ መመገብ አቅቶታል፤ህጻናት ዛሬ ባዲስ አበባ ጎዳናዎች ቆሻሻ መጣያ ላይ ለፍርፋሪ ከውሾች ጋር እየተጋፉ ነው። ምኑ ጋ ነው ኢትዮጵያ የበለጸገችው?ብልጽግናው በነማን ቤት ነው የሚታየው?ሃቁ ዛሬ ወጣቱ በገዛ አገሩ የበይ ተመልካች በመሆኑና ተሰፋ በመቁረጡ በስደት እየነጎደ በጉዞም ላይ በአውሬ እየተበላና ባህርም ውስጥ እየሰመጠ ማለቁን የመረጠበት ተሰፋ አስቆራጭ ጊዜ ላይ እያለን ወያኔዎች የነሱ ቀፈትና ኪስ ስለሞላ ብቻ ሃገር ቤት ጥጋብ ነው እያሉ በህዝባችን እየተሳለቁ ነው።ይህ አይነት ቅጥ ያጣ ግፍ ከንግዲህ እንደማይቀጥል ሊረዱት ይገባል፤ይህ ሁሉ አምባገነኑ መለስ የዘረጋው የከረፋና የገለማ የዘረኛ አስተዳደር ላንዴና ለመጨረሻ ከአገራችን ተመንግሎ ከመለስ ጋር ላይመለስ መቃብር ሊወርድ ይገባል።

አንበሳው መለስ እብደቱን በመቀጠል፤ለጌቶቹም ታማኝነቱን ለማረጋገጥ ሶማሊያን ወሮ ኢትዮጵያን በእስልምና አማኝ አገሮች በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እነዲሉ የበለጠ እንድትጠላ አደረገ፤ይህንንም ሆን ብሎ ያደረገው ነው፤ህልሙ ኢትዮጵያን በዘር ከፋፍሎ አተረማምሶ ከጎረቤቶቿም ካናከሰ በሁዋላ ታላቂቱ ትግራይን ለመገንባት ነበር። ይህን ህልም የትግራይ ህዝብ ይጋራው አይጋራው በሂደት የምናየው ጉዳይ ይሆናል(ይህንን ያልንበት ምክንያት ወያኔ አሁንም ራሱን የትግራይ ነጻ አውጭ ሰለሚል ነው)።በመጨረሻም ይህ ሰው እብደት ይሁን ቅብጠት አናውቅም እገዚአብሄርን መፈታተን ጀመረ ሁለቱን ታላላቅ የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ለማጋጨት ብዙ ሞክሮ አልሆን ቢለው፤ለእሰልምናው አዲስ መጤ ሃይማኖት ከሊባኖስ አምጥቶ ሊጭንባቸው ሞክሮ እነሱም አሻፈረን በማለታቸው በጥይት ተደበደቡ ለእስርና ለእንግልትም ቢዳርጋቸው ትግላቸውን አላቆሙም ።እነ መለስ ጫካ ከነበሩበት ጊዜ ጀመሮ እስከ አሁኗ እለት ድረስ የሚያሳድዷትን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻ የእምነታችንን አሻራ ለማጥፋት በአሰቦትና በዝቋላ ገዳማት ደኖች ላይ እሳት በመልቀቅ ዋልድባንም በሳውዲ አረቢያ ተላላኪ በአላሙዴ በማሳረስ የሁለቱንም ሃይማኖት በመዳፈራቸው የግፍ ጽዋው ሞልቶ ስለፈሰሰ፤እግዜርም መኖሩን ለማሳወቅ የተገፋውንም ህዝብ ለመታደግ በእብሪተኞች ላይ ቁጣውን አወረደ፤” ፍቅር እስከ መቃብር” እነዲሉ አባትና ልጁን ይግባኝ የሌለውን ፍርዱን የሰራዊት ጌታ ስጣቸው። እግዜር አያየንም ብለው በሚስጥር በእግዚአብሄር ቤት የሚመላለሱ ነዋይ ያነሆለላቸው አባቶችም ገለጦ የሚወጋ ጌታ ቁጣውን እያወረደ ነውና ወደህሊናቸው ተመልሰው ንስሃ ገብተው ቤተክርስቲያናችንን በቅንነት ያገልግሉ፡ፍታት የተደረገላቸውም አባ ፓውሎስ ውግዝ እንደ አርዮስ የተባሉ መናፍቅ ነበሩና ቤተክርስቲያኑዋንና ፈጣሪን ይቅርታ ይጠይቁ።በዋልድባ የቅዱሳን አባቶች መቃብር በእብሪተኞች ሲፈነቃቀል መነኮሳት በጥይት ሲደበደቡ፤ሲሳደዱ ያልተቃወመች ቤተክርስቲያን ምን አይነት ቤተ ክርስቲያን ነች?አማኙስ ለምን አይጠይቅም?ለሃይማኖቱ የማይቆረቆር አማኝ ለምን ቤትክርስቲያን ይሄዳል?ማንን ነው የምናሞኘው?እንደ እስልምና አማኝ ወገኖቻችን ለሃይማኖታችን ቀናዊ የማንሆነው ለምንድን ነው? ዳቦ እየበሉ መምጣት ነው እንዴ ክርስትና? ክርስትና እኮ ፈተና ነው።ከንግዲህ ዘረኞች በሃይማኖታችን በሃገራችን እንዲሳለቁ መፍቀድ የለብንም፤እሰላሙ ሲነካ ኦርቶዶክሱ፤ኦርቶዶክሱ ሲነካ እስላሙ ለምን ማለት አለበት። አማራ ኦሮሞ ወላይታ ሲዳማ አፋርና ኢሳ፤ እስላምና ክርስቲያን እያልን መባላቱን አቁመን የጋራ ቤታችንን እናት ኢትዮጵያን ከቀን ጅቦች ነቅተን እንጠብቅ፤እስከዛሬ ያሞኙን ይበቃል፤ሃገር ሳትጠፋ አሁኑኑ በጋራ እንነሳ፤ለዚሁም እግዚአብሄር ይርዳን፤አሜን!!!

“እግዜአብሄር ይመስገን፤አላህ ዋክበር” አሜን!!!

“ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር”

ከዊኒፔግ ካናዳ

3 Responses to ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች

 1. [email protected] Reply

  September 9, 2012 at 4:42 am

  ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች?….ተስፋዬ ገ አብ ” …ኢትይዮጵያ እጅ የላትም…. ጊንዲሽ ናት” አይነት ጽሁፉን አደንቅለታለሁ። ኢትዮጵያ ማለት አንተ ነህ፡፤ እጅህን ዘርጋውና ወያኔዎችን ገፍትረህ ማስወጣት ነው ያለብህ..

 2. Manlibel Getatchew Reply

  September 8, 2012 at 11:46 am

  “ጌቶቹ አሜሪካና እንግሊዞች በአሰብ ጉዳይ ላይ እንዲደራደር ቢጠይቁትም መለስ ግን ወደብ አያስፈልገንም በማለት ሃገራችንን ወደብ አልባ አደረጋት።” ውሸት! የጌቶቹን ፈቃድ ነው የፈጸመ።

 3. Degu Habte Reply

  September 7, 2012 at 9:44 pm

  Please becareful the weyane group begin write like against the weyane to divide the Ethiopian people.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>