ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ “ዘመቻ ነፃነት” በሚል ሰላማዊ ጥያቄ ሊያነሳ ነው!

September 6, 2012

አቤ ቶኪቻው

እንደምን አደራችሁ ወሬ አስነበባለሁ በአዲስ መስመር እንገናኝ፤ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ “ዘመቻ ነፃነት” በሚል ሰላማዊ ጥያቄ ሊያነሳ ነው!

በሙስሊም ኢትዮጵያውያን የመብት ጥያቄ ሳቢያ ታዋቂው የሙስሊሞች ጉዳይ መፅሔት እና ሌሎች በርካታ የሀይማኖቱ ጋዜጦች፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ “ህውከተ ጤና” ወቅት ደግሞ ተወዳጇ ፍትህ ጋዜጣ እንዲሁም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ “ህልፈተ ህይወት” በኋላ ደግሞ አንድ ቀረች የተባለችው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከገበያው ላይ “ዴሊት” ተደርገው በአሁኑ ወቅት አንባቢው ህብረተሰብ ጋዜጣ ቢፈልግ የሚያገኘው ወይ አዲስ ዘመን ወይ አዲስ አድማስን ብቻ ሆኗል።

አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የሚያዘጋጀው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣም ይህንን ተከትሎ “ዘመቻ ነፃነት” የሚል ስያሜ ያለው አንድ ቡድን ማቋቋሙን ሰማሁኝ።

ይህ ቡድን በሰላማዊ እና ህጋዊ እንቅስቃሴዎች የሚመራ ሲሆን በሀገሪቱ ውስጥ “ልክ እንደ ቀይ ቀበሮ” ህልውናቸው አደጋ ላይ እየወደቀ የመጣውን የመናገር ነፃነት፣ የፕሬስ ነፃነት፣ የመደራጀት ነፃነት እንዲሁም የእምነት እና የአስተሳሰብ ነፃነቶች መቀበር ሳይሆን መከበር ይገባቸዋል! የሚል ጥያቄ ማንገቡን ወሬ አቀባዮቼ ነግረውኛል።

ሰላማዊ ጥያቄው በምን ተነስቶ በምን እንደሚቋጭ ለማጣራት ሙከራ አላደረኩም። ሙከራ አድርጌ ግን እነግራችሁ ዘንድ ግድ ይለኛል። ስራዬ ወሬ ማቀበል ነውና…!

ወሬዬን ስላነበባችሁ አመሰግናለሁ ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>