በቫንኩቨር ከተማ ኢትዮጵያውያን የተሰጠ መግለጫ

August 31, 2012

ነሀሴ 24 ቀን 2004 ዓም

በቅርቡ ሕይወቱ አለፈ ስለተባለው የውያኔው ቁንጮ መለሰ (ለገሰ) ዜናዊ “የቫንኩቨር ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሀዘን መግለጫ አስተላለፉ” በማለት Vancouver Ethiopian Community press releaseበሕወሓት ወያኔ ቁጥጥር ሥር የሚገኘው ኢ.ቲቪ የተለመደ የሃሰት ፈጠራ ዜና ነሀሴ 23/2004 ዓም በማስተላለፉ ሐሰት መሆኑን ለማሳወቅ ይህንን መግለጫ ለማውጣት ተገደናል።

ምንም እንኳን በባህላችን ሕይወቱ ያለፈን ሰው ምንም ክፉ ቢሆን ለቤተሰቡና ለዘመድ ወዳጅ ጓደኛ ሞራል ሲባል ክፉ ነገር ላለመናገር ዝምታን ብንመርጥም በስማችን ለዚህ በንጹሐን ደም የተበከለና በክህደት ለሚታወቀው ሰው የተሠራው የሀዘን ድራማ አስቆጥቶናል።

በቫንኩቨር ካናዳ ነዋሪ የየሆንን ኢትዮጵያውያን በዘረኛውና እብሪተኛው ሕውሓት/ወያነ በፈጸመብን ግፍና ሥቃይ ሕይወታችንን ለማትረፍ ተሰደን ወደ ካናዳ የመጣንና ቀደም ሲልም በወታደራዊ ደርግ የተሰደዱት ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ለመግባት የሚያስችል መግቢያ ቅዳዳ በማጣት ቤተሰባቸውን፤ ያደጉበትን ቀዬ፤ ባህልና፤ ሕዝብ…ወዘተ እየናፈቁ የተቀመጡ መሆኑ እየታወቀ እንዲህ ያለ ቅጥፈት መፈብረኩ “በሬው ወለደ” ሳይሆን በሬው መንታ ወለደ የውሸት ውሸት ነው።

ለገሰ (መለስ) ዜናዊ እና ቡድኑ የትግሬ ነፃ አውጭ ግምባር በአገራችን ላይ ያደረሰው ጥፋት በዚህ አጭር ጽሑፍ ለማውጣት ባይቻልም ከዘበኛ እስከ ፕሮፌሰር ዘር እየመረጠ ከሥራ ያባረረ፤ ከመኖሪያ ቀዬ እያፈናቀለ መሬቱን ለባዕድ የሸጠ፤ አገር የገነጠለ፤ ምሬት ለሱዳን የሰጠ፤ ኀይማኖት የደፈረ፤ በጅምላ ጭፍጨፋ ወንጀል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት የተከሰሰ ወንጀለኛ ሞት በቫንኮቨር የምንገኝ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ይህ ሰው በህይወት ዘመኑ በሰራው ወንጀል ለፍርድ ቀርቦ እንደ ሳዳም ሁሴን መቀጣጫ መሆን የሚገባው መሆኑን ብናምንም በዚህ መልክ መሞቱ አስገርሞናል፤ ጥርጣሬም ገብቶናል እንጂ አላሳዘነንም። ሕዝባችን እፎይታ ሲሰማው የዋልድባ አባቶችና የሙስሊሙ ማኅበረሰብ ጸሎትም ሰምሯል እንላለን።

በመሆኑም እኛ በቫንኩቨር ካናዳ ነዋሪ የሆንን አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ነሃሴ 23/2004 በስማችን የተላለፈው ሃሰተኛ የወያኔ ድራማ መሆኑን በመላው ዓለምና በአገር ውስጥ  ለሚገኙ ወገኖቻችን እየገለጽን የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል።

1.  በዚህ ሰው ሞት ሕወሓት ዜናውን ከመደበቅ ጀምሮ በግድ አልቅሱ እያለ በታጣቂዎቹና ካድሬዎቹ በሕዝብ ላይ የሚፋጽሙትን ማሰቃየት እንዲያቆም።

2.  ለገሰ (መለሰ) ዜናዊ አገር የሸጠ፤ ያስገነጠል፤ ህዝብ የጨፈጨፈ ያስጨፈጨፈ ጨካኝ አረመኔ ከሃዲ ባንዳ በመሆኑ በአርበኞችና የሀገር ባለውለታዎች መካነ መቃብር እንዳይቀበር እንጠይቃለን።

3.  በስሙ የተመዘገበ ማናቸውም በአገር ውስጥና በውጭ ያለ በሚስቱ፤ በዘመዱ፤ በልጆቹና በሚስቱ ዘመዶች የተመዘገበ ንብረት ሁሉ ከአገርና ሕዝብ የተዘረፈ በመሆኑ እንዲታገድ።

4.  ከዚህ ዘረኛ ሥርዓት ጋር በዘር፤ በጥቅም ወይም ባለማወቅ የተሰለፋችሁ ሥርዓቱ ያለቀለት መሆኑን ተገንዝባችሁ የአንድነት ኃይሎችን በመቀላቀል የነፃነቱን ቀን እንድናፋጥንና ለብሔራዊ ዕርቅ እንድንዘጋጅ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለ።

ነሀሴ 24 ቀን 2004 ዓም

ካናዳ ቫንኩቨር

2 Responses to በቫንኩቨር ከተማ ኢትዮጵያውያን የተሰጠ መግለጫ

 1. addis007 Reply

  September 1, 2012 at 3:59 am

  ምን ያስደንቃል ይሄ የተለመደ ፕሮፓጋንዳ አይደለም እንዴ? አገር ቤት እኮ በሽተኞች፤ጎዳና ተዳዳሪዎች፤ሴቶች፤ወንዶች፤ትልቅ ትንሽ
  ሳይሉ ሀዘናችውን ገለጡ እየተባለ ነው።

 2. tarekegn kecanada Reply

  September 1, 2012 at 3:01 am

  ሰላም ለኢሳት እየተመኘሁ ህውሃት ይህን ያህል ጊዜ ማስለቀሱ ለወደፊቲ ያለው ኣመራር ብቃት ዋጋ እንደሌለው በቂ ማረጋገጫ ነው ሰለዚ ????

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>