የጎዳና ልጆች ለቅሶ

August 29, 2012

Henoke Yeshetlla

በዚች ግጥም ልግባባችሁ…

“እንባ እንደ ጅረት ፈሰሰ
ደረት ኢንደ አፈር ፈረሰ
ምድረ ጭርንቁስ ድሃ
ተቃቀፈና አነባ
ግና ያለፈ እናዳላረፈ አረፈ
አየ አየና አለፈ”

አለ ገጣሚው…እውነት ነው ዛሬ ሃገራችን ደረት እንዳፈር ፈርሶዋል…እነባ እንደጅረት ፈሶዋል የዘመናት በደሉን የሚገልጽበት ነጻ መድረክ ተከፈተለት…”አያ ጅቦም አመካኝቶ በልቶዋል”:: ኢትዮጵያዊነት የሚያሳየን ብዙ ድራማዎችም አሉ…ይቀጥሉማል:: ለውሾቻቸው የታሸገ ምግብ መግዛት ከጀመሩት የቦሌ   የሃያት እና የገብርኤል ሰፈር  ሃብታሞች  ላስኪት ወጥረው የቆሻሻ ገንዳ ግርግዳ አድርገው እስከሚኖሩት ያገሬ የጎዳና ተዳዳሪዎች ሃዘናቸው እንዲገልጹ ተደርጎዋል እየገለጹም ነው:: የዛሬ ጸሁፌም የሚያተኩረው ሁለተኞቹ ላይ ነው:: አንባቢያን ኢንደምታውቁት middle class ወይም በኔ ድፍየና መሃል ሰፋሪ ስለተባሉት የህብረተሰብ ክፍሎች ጊዜ ካገኘሁ እመለስበታለሁ::  አሁን ግን “ሃሳቡ እንዲገባችሁ” እኔም እንደ አቤ ቶኪቻው በአዲስ መስመር እጀምራለሁ::

ያዲስ አበባ ጎዳና ተዳዳሪዎች በጠቅላይ ሚንስትሩ መሞት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ:: ሃዘናቸው ያተኮረባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች እንደሚከተለው ይቀርባል::

እኛ ባራት ኪሎና በአካባቢዋ የምንኖር የጎዳና ተዳዳሪዎች በጠቅላይ ሚንስትራችን መሞት የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን ስንገልጥ በብርድ የተሰነጠቀ በጸሃይ የጠቆረ  በቅማል ወንፊት የሆነ ፊታችንን ኢንደምታዩት በሃዘናቸው ከከፊል ደመናማነት ወደ ከል  ሰማይነት እንደተቀየረ ለማስገንዘብም እየሞከርን ነው:: ተቅላይ ሚንስትራችን በህይወት ባሉ ጊዜ… የሰው ልጅ በእውነትም ሊለምደው ይችላል የማይባለውን ነገር ያስለምዱን ታላቅ መሪ ናቸው:: ከበርሃ በቀሰሙት ልምዳቸው ያለምግብ ለሳምንታት ኢንዴት መኖር እንደሚቻል ብቻ ሳይሆን ባንድ ልብስ ላይውም በበከተና በተባይ በተወረረ ብጫቂ ጨርቅ ራስን ንቆ እንዴት መኖር እንደሚቻል አስተምረውናል::

ጠቅላይ ሚንስትራችን በህየውት በነበሩ ጊዜ  “ክርስቶስ በሓጣንና በጻድቃን ላይ ለመፍረድ በድጋሚ ወደዚች ምድር ይመጣል” የሚለውን አባባል ” በቀን ሶስቴ ትበላላችሁ” በሚለው ተክተን እንድናምን ያደረጉን ታላቅ ሰው ነበሩ:: ጥቅላይ ሚንስትራችንን በይበልጥም ክረምት ሲመጣ “አይዞአችሁ በሃምሌ ዝናብ ተደብደቡ ..ታዛ መጠለያ አይኑራችሁ…ፌደራል ፖሊስም ሌባ እያለ ይደብድባችሁ” ብለው የመከሩንን አንረሳውም:: ጠቅላይ ሚንስትራችን በህይወት በነበሩ ጊዜ አርቆ አሳቢነታቸውን ካሳዩበት መንገዶች ወስጥ እኛ የጎዳና ተዳዳሪዎች እየበዛን በመጣንበት ሰአት “አይዞአችሁ  አዲስ ቀለበት መንገድ እሰራላሁ  ” ባሉት መሰረት  ቃላቸውን ሳያጥፉ ከሚቆረቁረውና ከገረጋንቲው ጎዳና አውጥተውን ፎቅና ምድር የቀለበት መንገድ የሰሩልንን በፍጹም ከህሊናችን የሚጠፋ አይደለም:: ከኛ ከጎዳና ታዳዳሪዎችም መሃል ተቅላይ ሚኒስትሩን በሙሉ አይኖቻችን ያየናቸው ብዙ ነን:: ይሄ ደሞ አብዛኛው ኢትይኦጵያዊ በተኛበት ሰአት ለሽርሽር ወደ ውጭ በሚወጡበት ጊዜ ሲሆን…ምን ያህል ንቁና የማይተኙ ሰው መሆናቸው ደሞ ከኛ ጋ በፍጹም ያመሳስላቸዋል:: በይበልጥ አንዳንዴ… ተቅላይ ሚንስተር መለስ ዜናዊ ሰውነታችን ላይ ትልቅ ቅማል ሲያዩ “ይሄ ቅማል እኔ በርሃ እያለሁ አብሮኝ የነበረውን ይመስላል ምናልባትም የኔ ቅማል ለናንተ ቅማል ቅድመ አያቱ ሳይሆን አይቀርም” እያሉ አንድ መሆናችንን ይነግሩናል:: ባለፈ ጊዜ ለሚሊኒየም ሸራተን አዲስ ዝግጅት በነበረ ጊዜ…ከሰው የተረፈው ከሚደፋ ከሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ጋ በመነጋገር እኛ እንድንበላው ያደረጉት በፍጹም አይረሳንም:: አልፎም ተርፎም  በሃገር ውስጥም ይሁን ወውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሉጢዎች  በየመኖሪያ ቤቶቻችን እያስገደዱ እንዲደፍሩን … ሃገራችንን ሃገር ሳይሆን ቡና ቤት ኢንድትሆን ስላደረጉአት ሃዘናችን ጥልቅ ነው:: ከዚህ ሁሉ በላይ ግን ሃዘናችንን ያበረታብን  “የጎዳና ተዳዳሪዎች እኩልነት” የሚለውን ረቂቅ አዋጅ ከመጽደቁ በፊት እንድንመለከተው ሰጥተውን ማስተካከያው ቸርሰን ለመመለስ በምንዘጋጅበት ሰአት ማለፋቸው ሃዘናችንን አበርክቶብናል::

ለቂቅ አዋጁ እንዲ ይል ነበር….
የጎዳና ተዳዳሪዎች የእኩልነት አዋጅ

የሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ እንደሚያሳየው በአሁኑ ሰአት የኢትዮጵያ ህዝብ ቤት ውስጥ ከመኖር ወደ ጎዳና መውጣትን መርጦዋል…ነገሩ ይበል የሚያስብል ነው:: ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ በሚቀጥሉት 10 አመታት ውስጥ 40 ከ 100 የሚሆነው የሃገራችን ህዝብ ወደ ጎዳና ይወጣል ተብሎ ይገመታል የተቀረው 60% ደግሞ በጎዳና አቁዋርጦ ወደ ሌሎች ሃገርኦች ይሄዳል…ስለዚህ “አዎ ስለዚህ ይላል አዋጁ” …ስለዚህ ከዚህ ቀደም ያልነበረ  አሁን ግን የሚያስፈልገንን ይሄን አዋጅ ስናጸድቅ የጎዳና ተዳዳሪዎች ምክር ቤት ረቂቅ አዋጁን ከተመለከት በሁዋላ በድምጽ ብልጫ ያጸድቀዋል::

አዋጅ…ከዛሬ ከ ጥቅምት ገለመኔ ጀምሮ ሁሉም የጎዳና ተዳዳሪዎች በመረጡት ጎዳና ላይ የመኖር መብታቸው በህግ የተጠበቀ ነው:: ማንኛውም የጎዳና ተዳዳሪ በሚገባው ቁዋንቁ መነጋገር ይችላል :: ከንዚህም ውስጥ የልመና ቁዋንቁዋ የጥግረራ ቁውንቁዋ ያራዳ ቁዋንቁዋ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ:: ማልቀስ ብሄራዊ ቁዋንቁዋቸው እንዲሆን ወስነናል:: ምክር ቤት ቀደምት የጎዳና ተዳዳሪዎችና አድሃሪ የቆሎ ተማሪዎችን ለመቆጣተር ሲል በጎዳና ተዳዳሪዎች መሃከል ቅኔ የሚናገር…ወደ በቱ ተመልሶ የሚገባ እና ወዘተን በ 15 አመት ጽኑ እስራት የቀጣል:: እስራቱም የሚፈጸመው መንገድ ፈጽሞ ካልገባባቸው አካባቢዎች ሄዶ አዲስ ኑሮ እንዲጀምሩ በማድረግ ይሆናል:: ይላል!

በመጨረሻም የጠቅላይ ሚኒስትሩ መሞት  በተመለከተ የተሰማንን ልባዊ  ኢየገለጥን እኛ የጎዳና ተዳዳሪዎች ብቻዎትን እንዳማይተኙ አብረንዎ ከበን እሳት እየሞቅን እንደምንተኛ ቃል ኢንገባሎታለን:: በመጨረሻም በቅርቡ እኛን ለተቀላቀሉት ጠቅላይ ሚንስትራችን ቤተሰቦች መጽናናቱን እየተመኘን…የተቅላይ ሚንስትራችንን መሞት ተከትሎ በሚደረገው ሃገራዊ የድንኩዋን ሰበራ ላይ እየተሳተፉ ያሉትን በጎዳናና በቤት መሃከል የሚኖሩ ወገኖቻችንን..እንኩዋን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለ መለስ ዜናዊ በአለ ሞት አደረሳችሁ አደረሰን እያልን…እኛም በ-አምስት አመት መርሃ ግብራቸው ውስጥ ካካተቱት የዘኬ ለቀማችን እንሄዳለን:: ድል ለችግርና ረሃብ! ያዲሳባ ጎዳና ተዳዳሪዎች…ነሃሴ ምንትስ ሺ አርት መቶ አራት!

One Response to የጎዳና ልጆች ለቅሶ

 1. wefudelu Reply

  August 30, 2012 at 2:13 am

  መለስ፤ ቆሞ ያስለቀሰን ሞቶም አስለቀሰን!
  ቅዠት እየመሰለኝ ከተቸገርኩበት የሰሞኑ ክስተት ውስጥ የመለስ ሞትና የለቀስተኛው ውዥንብር ነው፡፡ “መለስ ሲስቅ ያናድዳል ሲናደድ ያስቃል” የሚል መጣጥፍ ከሶስት ወር በፊት ፖስት አድርጌ ነበር፡፡ የዚህ ተቃራኒ መጣጥፍ በህይወቱና በሞቱ ያስለቀሰን መሪ መለስ ነው በማለት ማሰብ ጀመረኩኝ፡፡ በመጀመሪያ የወያኔ የ21 አመታት አገዛዝ መራር ተቃዋሚ መሆኔን ላርዳችሁ አሊያም ላብስራችሁ፡፡ የአቶ መለስ ስራቸውም ትንፋሻቸውም አይጥመኝም፡፡
  ሰሞኑን ላምነው የከበደኝ ነገር የሞትና የእንባ ምህታታዊ ግንኙነት ነው፡፡ የጠቅላይ ሚንስተሩ ሬሳ ( ሬሳ መለስ) ወደ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) የገባ ጊዜ ያለቅሳሉ ብየ የማልገምታቸው ሰዎች ሁሉ በእንባ ሲራጩ ሳይ ተገረምኩ፡፡ የበረከት እና የአዜብ ለቅሶ የውሸት( የቁጩ) አይደለም፡፡ የምር ነበር፡፡ የአዜብ እብደት እጅግ አሳዘነኝ ስለዚህም አለቀስኩ፡፡ ያለቀስኩት ሳላስበው ነው፡፡ በአዕምሮየ እየሳቅሁኝ በልቤ አለቀስኩኝ፡፡ የልቤ አሸንፎ እንባ ከአይኖቼ ፈሰሱ፡፡ በተለይ ተቀጣሁ የምትለዋ የወ/ሮ አዜብ ንግግር ሰረሰረችኝ፡፡
  በነገራችን ላይ የኢትዮጲያ ህዝብ በመንገደኛ ሬሳም ቢሆን ያለቅሳል፡፡ በማያውቀው ሰው የሬሳ ድንኳን ገብቶ ያስነካዋል፡፡ ሽንኩርት ወይንም ድንች ለመግዛት ወደ ገቢያ የሄዱ እናት አያጋጥማቸው እንጂ ለቅሶና የለቅሶ ድንኳን ካጋጠማቸው ሁሉንም ረስተው የሞተ ዘመዳችውን እያሰቡ ሊያስነኩት ይችላሉ፡፡ኧረ እንዲያውም ለልጆቻቸው ምሳ መስራቱን ረስተው ልጆቻቸውን እያስራቡ ሊውሉ ይችላሉ፡፡ የእትዮጵያውያን የለቅሶ ባህል ውል ካላለላችሁ ይች እውነተኛ ታሪክ በሚገባ ታስረዳችኋለች፡፡
  እነሆ ታሪኳ ፡- አንድ የቅርብ ዘመዳችን ሴት ወ/ሮ በ96 ዓመታቸው ያርፉና ዘመድ አዝማድ ተሰባስቦ ለቀብር ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለሃገር (ርቀቱ 180 ኪሎሜትር ይሆናል) ይሄዳል፡፡ አራት የምንሆን ሰዎች ግን በስራ ምክንያት በማግስቱ ተነስተን ከመካከላችን ካለ በእንዱ ሰው የግል መኪና ጉዞችንን ጀመርን፡፡ እኔ በሃዘን ተውጨ ነበርና አልፎ አልፎ ሃሳብ ከመስጠት ውጭ እምብዛም አበርውኝ የሚሄዱቱን ሰዎች ወሬ (ወጋቸውን) አልተቀላቀለኩትም ነበር፡፡ በጨዋታቸው መካከል ስለᎂች እድሜ ተነሳና ሁሉም ከ96 ዓመት በላይ መቆየት እንደሌለባቸው እንዲያውም መለቀስ እንደሌለበት ከዚያ በላይ ቢቆዮ ሸክም እንደሆነ አውግተው ተግባቡ፡፡ እንዳይደረስ የለም ለቅሶ ቤት ስንደርስ እነዚያ እድሜ ጠግበዋል ለᎂች መለቀስ የለበትም ያሉት “እናቴ እናቴ ምነው ምነው ቶሎ ሄድሽብን ሳታማክሪን” እያሉ እንባ የለሽ ጩኸት ስሰማ አንድም የሰዎች ግብዝነት ሌላም ድራማው ለቛሚዎች የሚሰጥ አምልኳዊ ድራማ አናዶኝ ድርቅ ብየ ቀረኹኝ፡፡ምን ልላችሁ ነው ከዚያን ቀኝ ጀምሮ የለቅሶ ድራማ ተገልፆልኛል፡፡ ለመለስም የተለቀሰው ከዚህ አይለይም፡፡ እንዲያውም በታመመ ጊዜ እንዲሻለውና ወደ ስራ እንዲመለስ የፀለዮ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችም ገጥመውኛል፡፡ ምን ማለት ነው? ከተሻለው እንደገና ተነስቶ ይግዛን ይጮቁነን ያንገላታን ማለት አይደለምን? እነዚህ የሚፀልዩትን የማያውቁ አማኝ ኢአማኝ ናቸው፡፡
  ለማንኛውም ወደ ለቅሶው ታሪክ ልመለስና አዲስ አበባ እያለሁ ያየሁትን ትዝብት ልንገራችሁ፡፡ በነገራችን ላይ ይሄ በዐይኔ በብሌኑ ያየሁት ነው፡፡ ትዝበት ብየዋለሁ
  ትዝበት 1፡- ለቅሶ በትዕዛዝ
  የመለስ አስክሬን ወደ አዲስ አበባ ሲገባ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰዎች ጥቁር ለብሰው እንዲወጡና ሃዘናቸውን እንዲገልፁ ትዕዛዝ ተላልፎ ነበር፡፡ ለዚህም የትራንሰፖርት መኪና ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዚያን ቀን ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ኤርፖርት የገባሁት በእግሬ ነበር ምክንያቱም መንገዱን ለመንግስት ሰራተኞች መመላለሻ መኪኖች ክፍት ለማድረግ ትራፊኮች ስለከለከሉን፡፡
  ትዝብት 2፡- ፍርሃት የወለደው ለቅሶ
  ወላጅ እናቴ ለመለስ እየየ ብላ አልቅሳለች፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ ለመለስ እምብዛም ነበረች፡፡ እኔም እናቴ ለምን እንዳለቀሰች ስጠይቃት እንዲህ ነበር ያለችኝ “መለስ እልኸኛ ዘረኛ አልጠቃም ባይና ስራት የለሽ ነው፡፡ ከሁሉም ጥመቱን አልወድለትም፡፡ ቢሆንም እኔ የወንድ ልጆች እናት ነኝና ወንድ ልጅ በወጣበት ሲቀር ያሳዝናል” ብላኛለች፡፡ ስለዚህም እናቴን የመሰሉ በፍርሃት የሚያለቅሱ አሉ፡፡ አስታውሱ እናቴ ያለቀሰችው ለኔ ነው እንጂ ለመለስ አይደለም፡፡ ብዙ አይነት ፍርሃታዊ ለቅሶዎች አሉ፡፡
  ትዝብት 3፡- ለቅሶ በይሉኝታ
  መለስ ብዙ ጊዜ እንዲሁ በከንቱ አስሮ የፈታት አንድ የታወቀች ነጋዴ ለመለስ እንዳለቀሰች ነገረችኝ፡፡ ደግማ ደጋግማ መለስ ያሳዝናል ስትለኝ እኔ በአምለክ ስራ አልገባም ደግሞም አላዝንም ስላት ነፃ ወጣችና “ …ለነገሩ ምን ያሳዝናል ይኼ አገር አጥፊ እኔም ከሰው ላለመለየት ይሉኝታ ይዞኝ እንጂ ለሱ መለቀስ የለበትም” ብላኛለች፡፡ባለ ስልጣነትን ጋዜጦኞችን እንዲሁም ነጋዴዎችን ይጨምራል፡፡
  ትዝብት4፡- ለቅሶ በውሎ አበል
  ተከፍሎአቸው የሚያለቅሱ ቡታጅራ ውስጥ እንዳሉ ከነሱ ውስጥ አንዷ ሴት እንደተከፈላት ስትናገር ሰምቻለሁ፡፡
  ትዝብት 5፡-ለቅሶ በአስለቃሽ (ፉንራል ዲጄ)
  የሞተባቸውን ዘመድ እያሰቡ የሚያለቅሱ አሊያም የለቅሶ አማልክትን ቀስቃሽ ልማታዊ አልቃሾች የሚያስለቅሷቸው፡፡
  ትዝብት 6፡-ለቅሶ በጎሳ ( የአባላት ለቅሶ) የተጠቃሚዎች እንባ ወይንም ልማታዊ አልቃሽ
  የበሉ ያባሉ ጥቅም ይቀርብናል ብለው የሰጉ ውሽዋሾች
  በስተመጨረሻ ቤተመንግስት ውስጥ ገብቼ የታዘብኩትን ላጫውታችሁና ልሰናበት፡፡ በግምት ወደ 1500 አካባቢ የሚሆን ሰው ተሰብስቧል፡፡ ቤተመንግስት በመሄድ ሃዘን ሊደርስ የተሰባሰበ ሰው ነው፡፡ እኔና ሁለት ገደኞቼ ወደዚያ ያመራነው ሁኔታውን ለመታዘብ ነው፡፡ የምንታዘበው መለስ የት ሆኖ ነው ያሰቃየን የሚለውንና ሃዘን የሚደርሰው ሰውን ምንነት ለማወቅ ነው፡፡ ወደ ቤተመንግስት ስንደርስ ዝናቡና የሰው ግፊያ ጨምሮ ባለበት ሰዓት አንድ ድምፅ ሰመሁና ዘወር አልሁ፡፡ እስከዚያ ድረስ የትኛው ጎሳ እንደሚበዛ አልተገነዘብኩም ነበር፡፡ ሸምገል ያሉ ሰው ናቸው ትናንት ስንመጣ ብዙ ህዝብ አልነበረም አሉ በትግረኛ አክሰንት፡፡ ሁለት ነገር ወደ አዕምሮየ መጣ 1)ለሁለተኛ ጊዜ ለቅሶ እንደሚደረሱ (ደጋግማችሁ ተገኙ ተብለውም ሊሆን ይችላል 2) ትግረኛ ተናጋሪ መሆናቸውን፡፡ እነዚህ ምልከታዎች አካባበውን እንዳጤን እረዳኝና ከተሰበሰበው መሃል አንድ እጅ እንኳ ሌላ ብሄር መኖሩን ተጠራጠርኩ፡፡ ላታምኑኝ ትችላላችሁ ብትኖሩ ትግራይ ክልል ያላቸሁ ይመስላችሁ ነበር፡፡ ወታደሩ ትግሬ ለቅሶው በትግረኛ ጠባቂው ትግሬ የሞተው ትግሬ መሆኑን ስታዮ ትገረማላችሁ፡፡ በጉዛችን ውስጥ ሌላ ትግሪኛ አክስንት ያለው ወታደር ተናገረ፡፡ “እያንዳንድሽ እንደሆንሽ መግባትሽ አይቀርልሽም አትገፋፉ” አለ እኔማ መሞታችሁ አይቀርም ያለ መስሎኝ “ከሞትን ሰነበትን” አልኩኝ በልቤ፡፡ ሳላጋንን ፊቴን ሃዘንተኛ አስመስየ ካለሳየሁ የምደበደብ ሁሉ መስሎኝ ተኮሳትሬ ዋልኩ ልላችሁ ነው፡፡ ወታደሮች ወጣቶች እና ሴቶች በሙሉ ትግሬዎች ናቸው፡፡ እያለቀሱ በትግሪኛ ለቅሶ አይሉት ቀረርቶ እየተንከባለሉ ሲያስነኩት ስመለከት ከቆየሁ በኋላ እኔ የያዝኩት ሰልፍ ሊደርስ አንድ ሁለት መስመር ሊቀረው ሲል ለቀስተኛው ምን እያደረገ እንደሆነ ተመለከትኩ፡፡ ሳላጋንን ለመለስ ፎቶ ሲሰገድ አየሁ፡፡ ለቅሶ ላይ የተቀመጡት የመለስ የሚያነክሰው ወንዱሙና ሌላው ውንድሙ እንዲሁም እህቱ ትመስላለች ቁጭ ብለዋል፡፡ እነ አዜብ የተቀመጡት በአጥር በተከበበ ሌላ ቦታ ነው፡፡ የሚገረማችሁ በባህላቸው ይህ ይደረግ አይደረግ አላውቅም ለቀስተኛው በትግርኛ እየተናገሩ ወታደሩን ይጨምራል እፊታቸው እየተንበረከኩ እና እየሰገዱ ሲያለቅሱ አየሁ፡፡ ብታምኑም ባትምኑም ሁሉም ትግሪኛ ተናጋሪዎች ነበሩ፡፡ ወይንም እንዲህ ብየ ላሻሽለው የትግራይ ክልል ለቅሶ መድረሻ ቀን ስለተገኘሁ ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ትግሬዎች አማልክት የሞተባቸው ይመስሉ ነበር፡፡ መለስ ኢትዮጲያን በቁሙም በሬሳውም አስለቀሳት፡፡ የሲቃ እና የደስታ መሆኑን ግን ተገንዝቢያለሁ፡፡
  ወሲባዊ አምልኮ
  አይ ኢትዮጲያ ጅልነትሽ
  ስላልገባሽ መፈታትሽ
  ሂጂ ተብለሽ መለቀቅሽ
  ስትፈች በንጉሱ በአምላክሽ
  በደስታ ቀን እጅግ አዝነሽ
  እንዳትሮጪ እንዳትሆኝ እንዳሻሽ
  መለስ ብለሽ ማምለክሽ!
  ተፃፈ በወፉ (8/29/2012)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>