ለመሆኑ አላሙዲን የት ጠፍቶ ከረመ? በህይወት አለ? ወይስ የለም?

August 29, 2012

የ ”ኢትዮጵያን ሪቪው” ድረ-ገጽ የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ ወዳጅ (አረቡ ቱጃር) ሼክ ሙሃመድ አላሙዲ ሞተዋል! ሲል የዘገበ ሲሆን ማምሻውን ደግሞ “ኢ ኤም ኤፍ” ድረ-ገጽ የለምSheikh Mohammed Hussen Alamudi a friend of Meles Zenawi ሰውየው አልሞቱም ይልቁንም ለመለስ ዜናዊ ቀብር አዲስ አበባ ገብተዋል ባይ ነው።

ለመሆኑ አላሙዲን የት ጠፍቶ ከረመ? በህይወት አለ የለም?

(ኢ.ኤም.ኤፍ.) የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የቅርብ ወዳጅ የነበሩት ሼኽ መሃመድ አል አሙዲ ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል። “ሼኽ አላሙዲ ሞተዋል” የሚል ዜና በሰፊው ተሰራጭቶ የቆየ ቢሆንም፤ ከአገር ቤት የደረሰን ዜና እንዳረጋገጠው ከሆነ ሼኩ በህይወት መኖራቸውን ለማወቅ ችለናል። የቅርብ ምንጮች ለኢ.ኤም.ኤፍ. እንደገለጹት ከሆነ፤ ሼኽ መሃመድ አላሙዲ አዲስ አበባ የገቡት በመጪ እሁድ በሚደረገው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በህክምና ላይ በነበሩበት ወቅት፤ ሼኽ አላሙዲ ወጪውን ሸፍነው ለማሳከም ጥያቄ ቢያቀርቡም የቀድሞዋ ቀዳማዊ ሴት አዜብ መስፍን ፈቃደኛ ሳትሆን በመቅረቷ፤ አስፈላጊውን ወጪ በማድረግ በሼኹ በኩል ሊደረግ የነበረ ህክምና ሳይደረግ ቀርቷል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ እና ሼኽ መሃመድ አላሙዲ ወዳጅ የመሆናቸውን ያህል፤ የቀድሞዋ ቀዳሚዋ ሴትዮ ከሼኽ አላሙዲን ጋር አግባብ የላቸውም። ወደፊት በሚኖረው የስልጣን ሽግሽግ እና ሽግግር ወቅት አዜብ መስፍን ወደ ስልጣን የምትመጣ ከሆነች በሼኽ አላሙዲ የንግድ ድርጅቶች ላይ ግልጽ የሆነ ጥቃት እንደምትፈጽም ይጠበቃል። በዚህም ምክንያት በህወሃት አማካኝነት፤ አዜብ መስፍን እንደገና ወደ ስልጣን መውጣቷን እንደስጋት የሚቆጥሩ ውስጥ አዋቂዎች በርካታ ናቸው። እነዚሁ ውስጥ አዋቂዎች እንደገለጹልን ከሆነ፤ “ከእሁዱ ቀብር በኋላ፤ ሼኽ አላሙዲን እንደቀድሞው ወደ ኢትዮጵያ የመመላለሳቸው ጉዳይ ሊቀንስ ይችላል።” ብለዋል በሃዘን።

3 Responses to ለመሆኑ አላሙዲን የት ጠፍቶ ከረመ? በህይወት አለ? ወይስ የለም?

 1. ojulu lero Reply

  August 29, 2012 at 6:23 pm

  who cares for the dead fish, except the the fisher man. i don’t even know why ppl worry about ppls death when your time is up it does’t matter how rich or poor you are you have to go anyway. peace in Ethiopia and god bless Ethiopian ppl.

 2. Abesha Reply

  August 29, 2012 at 4:28 pm

  Alamoudin is affected by two deaths. A manager in his company and an alliance-friend in Ethiopia. Other than that, he’s fine and he’s been taking care of himself. His greatest threat is only the emergence of Azeb as a power holder in the Ethiopian climate. As she seem to underestimate his competency and she dreams of being the one and only. So long as she’s out of the picture, he’ll be fine and continue living with Ato Abinet by his side all the time, everywhere.

 3. Gebre Reply

  August 29, 2012 at 12:45 pm

  It is not true, he is alive. Currently he is in Sweden. Rather, the general manager of his petroleum company in Sweden is dead. His recent travel to Sweden is related to the death of his general manager.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>