Reported: Ethiopian media forum.
(ኢ.ኤም.ኤፍ) የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም መለየታቸው ኦገስት 21፣ 2012 ዓ.ም. ታወጀ። ከአንድ ቀን በፊት የአቶ መለስ ዜናዊ
አስከሬን፤ ከውጭ አገር እንዲገባ ተደርጎ በቦሌ ተርሚናል የሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ ተቀምጦ ነበር የቆየው። ሆኖም በኢቲቪ የዜና እወጃ ላይ፤ “በትላንቱ ምሽት በድንገት ህይወታቸው አልፏል።” የሚል ውሸት በድጋሚ ተሰምቷል።
በሌላ በኩል ለረዥም ጊዜያት እውነቱን ሲክድ የነበረው በረከት ስምኦን… “መለስ በቅርቡ ወደ ስራ ይመለሳሉ” በማለት፤ የሃሰት ቃል ሲያቀብል ከቆየ በኋላ ዛሬ ማለዳ ላይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን መሞት ለማርዳት በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ለማለት እንኳን ሳይደፍር ቀርቷል። የመለስ ዜናዊ ዜና እረፍት ከተሰማ በኋላ፤ ልጆቻቸውን በመለስ አስተዳደር
የመለስ ዜናዊ አስከሬን በቦሌ የሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ ተቀምጧል!!
የተነጠቁ ወላጆች፤ ፍትህ አጥተው በእስር እና በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ደስታቸውን ሲገልጹ፤ ቀኑ የጨለመባቸው የኢህአዴግ ወገኖች ደግሞ ሆድ ብሷቸው ሲያለቅሱ ውለዋል።
በአሁኑ ወቅት. የመለስ ዜናዊን ቦታ ተክተው እንዲሰሩ የተደረጉት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሲሆኑ፤ የጠቅላይ ሚንስትርነቱ ቦታ ወደ ሌላ ብሄር መሄዱ በዘረኝነት አጥር ውስጥ የሚገኙትን በተለይም፤ የህወሃት ከፍተኛ አመራር እና የጦር አዛዦችን ያስኮረፈ ይመስላል። በአሁኑ ወቅት ጄነራል የሳሞራ የኑስን ህመም ተከትሎ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት በመንታ መንገድ ላይ ይገኛል። በአጠቃላይ የአየር ኃይል እና የምድር ጦር ሰራዊቱ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መስመር ውጪ በህወሃት ከፍተኛ የጦር መኮንኖችም አመራር ስር መውደቁ ይታወቃል።
የአባ ጳውሎስ የቀብር ስነ ስር ዓት የፊታችን ሃሙስ በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሚከናወን ሲሆን፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር የቀብር ስነ ስር ዓት የት እና መቼ እንደሚከናወን አልታወቀም። ሁለቱም ሰዎች በጥቂት ቀናት ልዩነት መሞታቸውን የታዘቡ ሰዎችም፤ ክስተቱን “ፍቅር እስከ መቃብር።” ብለውታል።
ዛሬ በታወጀው የኢቲቪ ዜና ላይ መለስ ዜናዊ ትላንትና በድንገት ሞቱ ይበል እንጂ፤ የት እንደሞቱ አልገለጸም። እውነቱ ግን አሁንም የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አስከሬን፤ ከውጭ አገር ከገባ በኋላ በቦሌ ተርሚናል የሬሳ ማስቀመጫ ክፍል ውስጥ ይገኛል። ይህ ድርጊት ለመለስ ዜናዊ ክብር ሳይሆን ውርደት ነው። በበረዶ ቤት ስለተቀመጠው አስከሬን… አቶ በረከት ስምኦን በቅርቡ ምን ይነግሩን ይሆን?
© 2012, ↑ Ethiopian News in Amharic
Log in- Posts - Add New - Powered by WordPress - Designed by Gabfire Themes
alemu na hagos ,endihum Tolosa.
August 23, 2012 at 5:22 am
Zore bye sayew sataw melesin ,
Paulos siketel ferto bichawun ,
Minew mistu kerech yemusina nigst ,
Temamina yihonal behodam shumaminet ,
Ahunim tezegaje maneh balesaminet .
Hulum beshitagna behimem yaleku ,
Lager layasibu tesfakortew yalu.
Samorana seyum woyane bemulu ,
Nisha gibuna ken saychelim danu,
Hagerin mebedl dihochin mawared ,
Mechefichef makatel belayachew manded,
Yemibekel ale kesemay yemifered.
Ahun yayachihut bicha endaymesilachu,
Mot yitebikach hual kaltemelesachu.
meretework
August 21, 2012 at 4:58 pm
wow! feqr malet yehe new
sitamemu tamo simotu kalmotu
bemn ytaweqal sew wedajnetu
And when you spread out your palms”I hide my eyes from you “Even though you make many prayers”Iam not listening”with bloodshed your” very hands have become filled”…………..Isaiah 1-15….
zemenu lijaddis
August 21, 2012 at 4:02 pm
esachew 1 gze motewal. Le degafiwoch hazen lelelaw desta yehone yimeslal.be selam alekm bilu god be mot asenabetachew enji.
Teddy
August 21, 2012 at 2:40 pm
መለስና አቡኑ-ፍቅር እስከ መቃብር
አቡኑና መለስ፣ መለስና አቡኑ፤
ድርና ማግ ሆነው እንዲያ ሲፎንኑ፤
በወራት ልዩነት፣ ከአይናችን በነኑ።
ልክ እንደ ሹመቱ፤ እንደተመካከሩ፤
በመቅዘፍት ተይዘው፣ ሲደነባበሩ፤
ከሆስፒታል ገብተው፣ እንደተኙ ቀሩ።
ከ70 ዓመት በፊት፣ በሃዲስ ተደርሶ፤
ፍቅር እስከ መቃብር፣ በሚል ተደጉሶ፤
በልብ ወለድነት፤ ለሁሉም ተዳርሶ፤
በኢትዬጵያ ምድር፣ ሲኖር ተወድሶ፤
በገሃድ ታወጀ፤ ይኸው ቀኑ ደርሶ።
የእኒያን ፊውዳሎች፣ ግብራቸውን ወስደው፤
በወራት ልዩነት፣ ይሄው አየናቸው፤
መለስና አቡኑ፣ ገጸ ባህሪ ሆነው፤
በአስገራሚ ፍጥነት፣ ሄዱ ተመራርተው።
ቴዲ ፣ ነሐሴ 10 2004 ዓ.ም ተጻፈ
መታሰቢያነቱ በወራት ልዩነት ለተለዩን ለጠቅላይ ሚነስትር መለስ ዜናዊና ለፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ