ይድረስ ለወየናችሁ ሁሉ

August 20, 2012

ይድረስ በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የዘረኝነት በሽታ ለተለከፋችሁና ወያኔም ሳትሆኑ የቫይረሱ ተሸካሚ ሆናችሁ ሆዳችሁን በማምለክ ለምትሰቃዩ ሁሉ፡-

‹‹ከእኛ በላይ ማንም የለም›› በሚል ከንቱ ትዕቢት ተወጥራችሁ አገር ገነጠላችሁ፤ አስገነጠላችሁ፡፡ ኢትዮጵያንና ህዝቧን በዘር፣ በቋንቋ፣ በጎሣ፣ በኃይማኖት፣ ወዘተርፈ እየከፋፍላችሁ አናቆራችሁ፡፡ ለአቅመ አዳምም ሆነ ሔዋን ያልደረሱ ህጻናትን ጨምሮ የንፁሃን ደምን ያለርህረሄ በየአደባባዩም ሆነ በየጉራንጉሩ በግፍ አፈሰሳችሁ፤ ደፋችሁ፡፡ ከጥይታችሁ የተረፈውን ደግሞ ከቀየው በማፈናቀልና በሠፈራ ስም እንደ እንስሳ በበረት በማጎር ድምፅ አልባ ገዳይ በሆኑት ረሃብ እና በሽታ ዘርን መርጣችሁ በማነጣጠር ጨረሳችሁ፡፡ ዕብሪታችሁም ገደብና ቅጥ አጣ፡፡ የማያጠረቃችሁን የፍቅረ-ንዋይ ጥማችሁን ለማርካት ስትሉ መሬቷን ለባዕድ በጅምላ ቸበቸባችሁ፡፡ ቀጣይ ትውልድንና የአገርን ህልውና  ለማጥፋት በተለያየ መንገድ ሌት ከቀን በርትታችሁ መስራታችሁ በከፊልም ቢሆን ተሳክቶላችሁ ዛሬ የህዝቡ ስቃይና ግፍ ሞልቶ በመፍሰስ ላይ ይገኛል፡፡

ይህም አልበቃ ቢላችሁ እግዚአብሔር የቀደሳትን ቤተ-ክርስቲያን አረከሳችሁ፣ አላህ የሚመሰገንበትን መስጊድ ደፈራችሁ፡፡ እግዚአብሔርንና ህዝብንም አስከፋችሁ፡፡ አስቆጣችሁ፡፡ በመሆኑም ህዝበ ክርስቲያኑ ‹‹አንመካም በጉልበታችን፤ እግዚአብሄር ነው የእኛ ኃይላችን››ን ሲዘምር ህዝበ ሙሰሊሙም ‹‹አላሁ ወአክበር፡፡›› እያለ እንደ እናንተ በጠብ-መንጃ ሳይመካ ከሚችለው በላይ ቢሆንበትም ጀርባው እየቆሰለና ልቡ እየደማ በትዕግስት እስከዛሬ ድረስ ተሸክሟችሁ ኑሯል፡፡

ይሁን እንጂ ዛሬ ግን ከሲቢል ሰርቪስ በገፍ ያመረታችኋቸው ደንጋዮች የማይዳኙትና በሽብርተኛነት፣ በቀድሞው ሥርዓት ናፋቂነት፣ በነጭ-ለባሽነት፣ በሻዕቢያ ተላላኪነትነት፣ በፀረ ልማትና በዘር ማጥፋት ወንጀል ከስሳችሁ ቀጠሮ የማትጠይቁበትና ዘብጥያ ልታወርዱት ፈፅሞ የማይቻላችሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ህዝቡን የመታደግ ሥራውን ጀምሯል፡፡

ፋሽስቱ መለስ ፀጥ አለ፤ ዲያቢሎሱ አባ ገብረ መድኅን ተከተለ፤ ወደፊት የሚቀጥለውም ሁሉ እንደርሱ ፈቃድ ነውና ክብር ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን፡፡ አላሁ ወአክበር፡፡  (ስለነብሳቸው እያንዳንዳቸውን ሥራቸው ያውጣቸው፡፡)

ወያኔዎች ሆይ! ዐይን አላችሁ የህዝቡን ለቅሶ አታዩም፡፡ ጆሮ አላችሁ እሮሮውን ግን አትሰሙም፡፡ እግርም እያላችሁ ከቆማችሁበት እሳተ-ገሞራ ላይም ፈቀቅ ትሉ ዘንድ አልተቻላችሁም፤ ለሰላም ትዘረጉት ዘንድ በተሰጣችሁ እጅም ደምን ከማፍሰስ አልታገሳችሁምና በዚህ ተግባራችሁ ህያው እግዚአብሔርን እጅግ አሳዝናችኋል፤ አስቆጥታችኋልም፡፡

እግዚአብሔርም ቁጣውን ሲገለፅላችሁ ከመፀፀት፣ ከመማርና ከጥፋት ተግባራችሁ ከመታቀብ ይልቅ የፍርፋሪ አለቆቻችሁን ታስደስቱ ዘንድ አምላካችሁን ይህ ነጭ ለባሽ፣ የድሮውን ሥርዓት ናፋቂ፣ በትግርኛ ተናጋሪ ላይ ጥላቻ ያለበት ትምክህተኛ እስከማለት ድረስ (ከጥጋቧ የተነሳ ሰማይን በእርግጫ ተራግጣ ለመራቁ ምክንያት መሆኗ እንደሚነገርላት እንስሳ) ርቃችሁ ልትሄዱ የምትችሉ ፍጡራን መሆናችሁን ባለፉት ሃያ አንድ የጥጋባችሁ ዓመታት ራሳችሁን በሚገባ አስተዋውቃችኋል፤ በተግባርም አሳይታችኋል፡፡

ዕውነት ዕውነት እላችኋለሁ! እግዚአብሔር የፈጠራትን ነብስ እየቀጠፋችሁ ለዘለዓለም ትዘልቁ ዘንድ አይቻላችሁምና ወዮላችሁ፤ ተጠንቀቁ፡፡ እጃችሁንም ከዚህ ህዝብና ከዕምነት ተቋማቱ ላይ አሁኑኑ አንሱ ፡፡ አድልዎን፣ ጥላቻን፣ ተንኮልንና ምቀኝነትን ከውስጣችሁ አስወግዳችሁ እንደአለቆቻችሁ ሳይመሽባችሁ ወደ ህሊናችሁ ዛሬውኑ ተመለሱ፡፡ ኢምንት ናችሁና ነፃነቱንና ሥልጣኑን ባለቤቱ ለሆነው ለኢትዮጵያ ህዝብ በአስቸኳይ መልሳችሁ ሳትፈሩና ሳታፍሩ ህዝብንና እግዚአብሄርን ይቅርታ ጠይቁ፡፡ ሁለቱም ይቅር ባይ ናቸውና አይነፍጓችሁም፡፡ እግዚአብሔር ተዓምሩን አሳይቷችኋልና ከጥፋት ትድኑ ዘንድ አሁኑኑ ፍጠኑ፡፡ አሸናፊው አልፋና ኦሜጋ የሆነው ልዑል እግዚአብሔር እንጂ በድን የሆኑት ጎይታዮቻችሁ መለስ ዘራዊ ወታጋይ ጳውሎስ አይደሉምና፡፡

በመጨረሻም፡- እረኛችን እግዚአብሔር ሆይ! እኛን በጎችህን ከዲያቢሎስና ተኩላዎቹ ለመጠበቅ ስለዋልክልንና ስለምትውልልን ውለታ ሁሉ ክበር ተመስገን፡፡ አላሁ ወአክበር፡፡

ዘለቀ ጀምበሩ ከቶሮንቶ (ካናዳ)

[email protected]

2 Responses to ይድረስ ለወየናችሁ ሁሉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>