ሚጢጢ ዜና፤ ፍትህ ጋዜጣ ነገ ገበያ ላይ ልትውል እንደምትችል ተጠረጠረ!

August 9, 2012

አቤ ቶኪቻው

“ይቺ ናትና ዜና” ይበሉና ይከተሉኝ፤

ዘወትር በዕለተ አርብ ከአንባቢያኗ ጋር ስትገናኝ የቆየችው ፍትህ ጋዜጣ በነገው እለት ለንባብ ልትበቃ እንደምትችል ጭምጭምታ ከወደ አዲሳባ ሰምቻለሁ።ሚጢጢ ዜና፤ ፍትህ ጋዜጣ ነገ ገበያ ላይ ልትውል እንደምትችል ተጠረጠረ!

ከአንድ ወር በፊት “ለሀገር ደህንነት ስጋት” የሆነ ዘገባ ይዛለች ተብላ በፍትህ ሚኒስቴር የሶስት መስመር ደብዳቤ እገዳ የተጣለባት ተወዳጇ እና “ተሳዳጇ” ፍትህ ጋዜጣ ምንም እንኳ ፍትህ ሚኒስቴር ያገዳት ለአንድ ጊዜ እትም ብቻ ቢሆንም ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ደግሞ “ከዚህ በኋላ ቀፈፈኝ ፍትህን ማተም ውቃቤዬ አልወደደም እና ወግዱ!” ብሎ ከወዳጆቿ ጋር ተለያይታ ቆይታለች።

ነገር ግን ከቀናት በፊት ፍርድ ቤት “ለሀገር ደህንነት ስጋት” ሆኗል ያለውን ሰላሳ ሺህ ኮፒ ብዛት ያለው ጋዜጣ እንዲቃጠል ትዕዛዝ ሲያስተላልፍ እግረ መንገዱንም ለብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ደግሞ “ቆሌዬ ስላልወደዳችሁ አላትምም” ማለት እንደማይችሉ በደብዳቤ አዟል።

ስለሆነም ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፍርድ ቤቱን እግዜርን እና አንባቢውን ፈርቶ በዛሬው እለት ፍትህ ጋዜጣ እንድትታተም ይፈቅዳል ተብሎ ይጠረጠራል!

ዜናው በዚህ አበቃ… ሰላም እላችኋለሁ።

ሰሞኑን የጠፋሁት በቴክኒክ ችግር መሆኑንም እገልፃለሁ!

3 Responses to ሚጢጢ ዜና፤ ፍትህ ጋዜጣ ነገ ገበያ ላይ ልትውል እንደምትችል ተጠረጠረ!

  1. Mohammed Reply

    August 12, 2012 at 12:32 am

    Pleas join me naw

  2. ASCHALEW DAMTIE KEBEDE Reply

    August 10, 2012 at 11:07 am

    LETEKEBEREW YEETHIOPIA HZB YEMIYASFELGEW ANDNETEN NEW SLEZH BERTU ENBERTA

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>