ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በማዕከላዊ ቃሉን ሰጠ!

August 1, 2012

አቤ ቶኪቻው

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እና “የመለስ አምልኮ” መፅሐፍ ደራሲ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በማዕከላዊ ምርመራ ጣቢያ ቃሉን መስጠቱን በፌስ ቡክ ግድግዳው ላይ ለጥፏል። እንደሚከተለው ይነበባል።ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በማዕከላዊ ቃሉን ሰጠ!

“የታገደቸው ጋዜጣ ትለቀቅና ለንባብ ትውላለች ብዬ ሳስብ፣ እኛ ባልነበርንበትና ባልተከራከርንበት ችሎት ቀርባ ‹‹ትውረስ›› የሚል ወሳኔ አሳለፉ፡፡ እኛም ካዛስ ተወርሳ መንግስት ሸጦ ገቢውን ይወስዳልን? ብለን ስንጠይቅ ‹‹አይ ለሽያጭ አትቀርብም፤ ትቃጠላለች እንጂ›› አሉና ጋዜጣዋ ዕለተ ቃጠሎዋን እየጠበቀች እንደሆነ ውሳኔውን ያሳለፉ ዳኛ ትላንት አረዱኝ፡፡

ዛሬ ደግሞ ማዕከላዊ ምርመራ ጣቢያ በፌደራል ፖሊስ ተጠርቼ ‹‹ፍትህ ሚንስቴር ክስ አቅርቦብሃልና ቃል ስጥ›› ተባልኩ፡፡ መቼስ ምን እላለሁ ክሱ ምንድር ነው? ከማለት ውጪ በሚል ቃል ለመስጠት ተዘጋጀሁ፡፡ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ትሁት ሆነው የቀረቡት መርማሪዎቼም ሰባት የፍትህ እትሞችን ፊት ለፊቴ ዘርግተው ስምንት ክስ አቀረቡብኝ፡፡ ለሁለት ሰዓት ከግማሽ ያህል ለስምንቱም መልስ ስሰጥ ቆየሁ፡፡ የሚገርመው ግን የቀረበብኝ ክስ የዛሬ ዓመት በታታሙ የፍትህ ዕትሞች በወጡ ፅሁፎች መሆኑ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ማዕከላዊ ከቀድሞ አሰራሩ ለውጥ አሳይቷል፡፡ ምክንያቱም እስከዛሬ ድረስ ተከስሼ ቃል ከሰጠው በኋላ በዋስ ነበር የምወጣው፤ በአሁኑ ክስ ግን ቃል ከሰጠው በኋላ ‹‹ምን አይነት ዋስ ላቅርብ?›› ብዬ ስጠይቅ ‹‹ዝም ብለህ ሂድ፤ ዋስ አያስፈልግም፡፡ እዛው ፍርድ ቤት ከዐቃቤ ህግ ጋር ትገናኛላችሁ›› አለኝ፡፡ እኔም አመስግኜ ማዕከላዊ ድረስ ተከትለውኝ በመጡ አራት ባልደረቦቼ ታጅቤ ከግማሽ ሰዓት በፊት ወጣሁ፡፡”

ተሜ ስለ ፍትህ ጋዜጣ ቀጣይ እታ ፈንታ እንዲሁም ከአቃቢ ህጉ ጋር ፍርድ ቤት የሚገናኙበትን ግዜ አልነገረንም። ኢሳት በትላንት ዘገባው “ተመስገን ደሳለኝ በሀገር መክዳት ወንጀል ሊከሰስ እንደሆነ ለማስረጃም  “የመለስ አምልኮ” መፅሐፉ ሳይቀር ሊቀርብበት እንደታሰበ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር።

ወዳጃችን ተሜ  የላይኛው ይጠብቀው እንላለን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>