ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ ተገለፀ

July 31, 2012

Ethiopia Hot blog

ኢሳት ቤልጄም ብራስልስ ዉስጥ መቀመጫዉን ያደረገዉን የግጭት ተንታኝ ቡድን ወይም በእንግሊዝኛዉ International Crisis Group (ICG) በመጥቀስMeles Zenawi's sprit እንደዘገበዉ የደርግን አገዛዝ በማስወገድ ኢትዮጵያን ላለፉት 21 አመታት በሐይል የገዙት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ57 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ የተለያዩ ዲፕሎማቶች የመሞታቸዉን እዉነት ይፋ እያደረጉ እንደሆነም አያይዞ ጠቅሷል፡፡

በዚህ የኢሳት ዘገባ እንደተገለፀዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ተከትሎ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ ብዙ ሚዲያወች በጠቅላይ ሚኒስትሩ የህይወት ጉዞ ላይ የሚያትቱ ፕሮግራሞችን እያዘጋጁ ይገኛል፡፡

እንደሚታወቀዉ ግንቦት 10/2004 በዋሽንግተን ሬገን ሕንፃ ከባድ የሚባል ተቃዉሞ ከገጠማቸዉ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት 72 ቀናቶች ከአይን ተሰዉረዉ የነበር ሲሆን ፤ ይህንን ተከትሎ የተለያዩ ሚዲያዎች ፣ ተቋማት እና ግለሰቦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጠና ታመዉ በሞት አፋፍ ላይ እንደሆኑና በህክምና ላይ እንደሚገኙ ሲጠቀሱ ነበር፡፡

ለረጅም ግዜ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መታመም ሲያስተባብል የቆየዉና በቅርቡ መታመማቸዉ በለሆሳስ ይፋ ያደረገዉ የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህና ናቸዉ… በቅርቡ ወደ ስራቸዉ ይመለሳሉ እያለ ሲሆን ፤ ይህም አንዳንድ ኢትዮጵያዉያንን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህንነት ግራ እንዲጋቡ አድርጓል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙተዋል የሚለዉን ዜና ተከትሎ ብዙ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ተንታኞች በስልጣን ላይ ያለዉ ፓርቲ የሚፈጠረዉን ክፍተት ለመሙላት አቅም እንደሌለዉ እየጠቆሙ ሲሆን ፤ በርግጥም በፓርቲዉ መንደር መደናገጥና ዉዥንብር እየተስተዋለ ነዉ፡፡

እነዚህ ተንታኞች አያይዘዉ በሀገሪቱ ዉስጥ ያለዉን የበሰበሰ አንባገነናዊ ስርዓት ለመለወጥ አመቺዉ ጊዜ አሁን ነዉ ፤ ስለሆነም ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነታቸዉን በማስወገድ ህዝቡን አስተባብረዉ ለተሻለ ለዉጥ ማንቀሳቀስ አለባቸዉ እያሉ ይገኛል፡፡ ህዝቡም ከምንግዜዉም በላይ በንቃት መሳተፍ እንዳለበት በአፅኖት ያስረዳሉ፡፡

ኢሳት ሬዲዮ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት አስመልክቶ በሰኞ ፕሮግራሙ ልዩ ዝግጅት ያስተላለፈ ሲሆን ፤ በፕሮግራሙ ላይ ጋዜጠኛ አበበ ገላዉን አነጋግሯል፡፡ አበበም “ዋናዉ ነገር የአቶ መለስ ዜናዊ የአካል ሞት የስርዓታቸዉን ማክተም የሚያበስር ስለሆነ ከዚህ በኋላ የሚኖረዉ መጭዉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እጣ ተመሳሳይ እንዳይሆን ሁላችንም አስተዋፅኦ ልናደርግበት የሚገባ ጊዜ ላይ ነዉ የምንገኘዉ” ሲል ተናግሯል፡፡

8 Responses to ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ ተገለፀ

 1. getie taklo Reply

  August 21, 2012 at 6:08 pm

  ነቭስ ይማር

 2. muhamed Reply

  August 17, 2012 at 4:49 pm

  ገዳዮ እውነተኛው ታጋይ አበበ ገላው ነው

 3. Debrework sahilu Reply

  August 4, 2012 at 4:03 am

  Like ISAT

 4. azeb Reply

  August 1, 2012 at 7:00 pm

  so what’s next

 5. tumayota Reply

  August 1, 2012 at 5:19 am

  For sure Devil meles was passed away,if not we will do it anywhere at any time.No more meles for Ethiopia. We need Democracy, Justice and freedom. Long live to mom Ethiopia.GOD bless Ethiopia.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>