Ethiopia Hot blog
ኢሳት ቤልጄም ብራስልስ ዉስጥ መቀመጫዉን ያደረገዉን የግጭት ተንታኝ ቡድን ወይም በእንግሊዝኛዉ International Crisis Group (ICG) በመጥቀስ
እንደዘገበዉ የደርግን አገዛዝ በማስወገድ ኢትዮጵያን ላለፉት 21 አመታት በሐይል የገዙት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በ57 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ የተለያዩ ዲፕሎማቶች የመሞታቸዉን እዉነት ይፋ እያደረጉ እንደሆነም አያይዞ ጠቅሷል፡፡
በዚህ የኢሳት ዘገባ እንደተገለፀዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ተከትሎ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥኑ ብዙ ሚዲያወች በጠቅላይ ሚኒስትሩ የህይወት ጉዞ ላይ የሚያትቱ ፕሮግራሞችን እያዘጋጁ ይገኛል፡፡
እንደሚታወቀዉ ግንቦት 10/2004 በዋሽንግተን ሬገን ሕንፃ ከባድ የሚባል ተቃዉሞ ከገጠማቸዉ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት 72 ቀናቶች ከአይን ተሰዉረዉ የነበር ሲሆን ፤ ይህንን ተከትሎ የተለያዩ ሚዲያዎች ፣ ተቋማት እና ግለሰቦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጠና ታመዉ በሞት አፋፍ ላይ እንደሆኑና በህክምና ላይ እንደሚገኙ ሲጠቀሱ ነበር፡፡
ለረጅም ግዜ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መታመም ሲያስተባብል የቆየዉና በቅርቡ መታመማቸዉ በለሆሳስ ይፋ ያደረገዉ የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህና ናቸዉ… በቅርቡ ወደ ስራቸዉ ይመለሳሉ እያለ ሲሆን ፤ ይህም አንዳንድ ኢትዮጵያዉያንን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህንነት ግራ እንዲጋቡ አድርጓል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙተዋል የሚለዉን ዜና ተከትሎ ብዙ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ተንታኞች በስልጣን ላይ ያለዉ ፓርቲ የሚፈጠረዉን ክፍተት ለመሙላት አቅም እንደሌለዉ እየጠቆሙ ሲሆን ፤ በርግጥም በፓርቲዉ መንደር መደናገጥና ዉዥንብር እየተስተዋለ ነዉ፡፡
እነዚህ ተንታኞች አያይዘዉ በሀገሪቱ ዉስጥ ያለዉን የበሰበሰ አንባገነናዊ ስርዓት ለመለወጥ አመቺዉ ጊዜ አሁን ነዉ ፤ ስለሆነም ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ልዩነታቸዉን በማስወገድ ህዝቡን አስተባብረዉ ለተሻለ ለዉጥ ማንቀሳቀስ አለባቸዉ እያሉ ይገኛል፡፡ ህዝቡም ከምንግዜዉም በላይ በንቃት መሳተፍ እንዳለበት በአፅኖት ያስረዳሉ፡፡
ኢሳት ሬዲዮ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት አስመልክቶ በሰኞ ፕሮግራሙ ልዩ ዝግጅት ያስተላለፈ ሲሆን ፤ በፕሮግራሙ ላይ ጋዜጠኛ አበበ ገላዉን አነጋግሯል፡፡ አበበም “ዋናዉ ነገር የአቶ መለስ ዜናዊ የአካል ሞት የስርዓታቸዉን ማክተም የሚያበስር ስለሆነ ከዚህ በኋላ የሚኖረዉ መጭዉ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እጣ ተመሳሳይ እንዳይሆን ሁላችንም አስተዋፅኦ ልናደርግበት የሚገባ ጊዜ ላይ ነዉ የምንገኘዉ” ሲል ተናግሯል፡፡
© 2012, ↑ Ethiopian News in Amharic
Log in- Posts - Add New - Powered by WordPress - Designed by Gabfire Themes
getie taklo
August 21, 2012 at 6:08 pm
ነቭስ ይማር
muhamed
August 17, 2012 at 4:49 pm
ገዳዮ እውነተኛው ታጋይ አበበ ገላው ነው
Debrework sahilu
August 4, 2012 at 4:03 am
Like ISAT
azeb
August 1, 2012 at 7:00 pm
so what’s next
tumayota
August 1, 2012 at 5:19 am
For sure Devil meles was passed away,if not we will do it anywhere at any time.No more meles for Ethiopia. We need Democracy, Justice and freedom. Long live to mom Ethiopia.GOD bless Ethiopia.