ግዜው የሚጠይቀው ሲናሪዮ ቀማሪ ሳይሆን አቅጣጫ መሪ ነው!

July 30, 2012

Click here for PDF

አዜብ ጌታቸው

ሰለምና ጤና ፤ ክብርና ብልጽግና ፤ ኢትዮጵያን ለምትሉ ሁሉ ይሁኑ!

ውድ አንባቢያን ወገኖቼ መቼም መለስ ዜናዊ ታመሙ፤ ያልጋ ቁራኛ ሆኑ፤ ባስ ሲልም ሞቱ፤ በሚል ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ወዲህ ሲያምታቱን የቆዩ ዝብርቅርቅ መረጃዎች መጨረሻ

Ethiopian pm Meles Zenawi

ምን እንደሆነ እስካሁን በአራት ነጥብ ባይቋጭም፤ የውዥንብሩ እድሜ አንድ ቀን በረዘመ ቁጥር ግን ሞቱ የሚለው መርጃ ሚዛን እየደፋ እንደሚሄድ ከወያኔ ድርጅታዊ ባህሪ መረዳት ከባድ አይመስለኝም።

ወያኔ የጠላቶቹን ፕሮፓጋንዳ ለመስበር የሌለ ነገር ፈጥሮ የሚያወራ ድርጅት መሆኑን ስናገናዝብ ዛሬ እውን መለስ ዜናዊ በህይወት ቢኖሩ ኖሮ አልጋቸው ላይ እያሉም በቴሌቪዥን መስኮት አቅርቦ ጠላቶቼ የሚላቸውን አካሎች አፋ ባሲያዘ ነበር። እናም ወገኖቼ በኔ ይሁንባችሁ መለስ ዜናዊ ሞተዋል!!!። ስለሆነም ሃሳባችን ውይይታችንና እቅዳችን ሁሉ መቃኘት ያለበት ከቀብር መልስ ባለው ጉዳይ ላይ መሆን ይገባዋል እላለሁ።

መለስ ሞተዋል! እናም እኛ ማሰብ ያለብን የሳቸው ሞት ምን ማለት ነው? ሞታቸው በዘረኛው የወያኔ መንግስት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ምን ያህል የከፋ ነው? በምን ያህል መጠንስ ያደክመዋል ወይስ ያከስመዋል? የሳቸው አለመኖር የሚፈጠረው ክፍተት ምንድነው? በተቃዋሚነት ተሰልፎ ያለውስ ወገን ይህን ክፍተት እንዴት ሊጠቀምበት ይችላል? የቀሩት የወያኔ አመራሮች ክፍተቱን ለመጠገን ምን ሊያደርጉ ይችላሉ? እኛስ ክፍተቱን አስፍቶ ስር አቱን ለማክሰም ምን ማድረግ አለብን? የሚሉትና ሌሎችም ተመሳሳይ ጥያቄዎችን በማንሳት መወያየት ተወያይቶም ያዋጣል በተባለው አቅጣጫ እንቅስቃሴ መጀመር ነው እላለሁ፡፤

እያየሁት ያለሁት ግን ይህን አይደለም፡፡እያየሁት ያለሁት ነጻነትን በትግልና በስራ ሳይሆን በምናብና በመላምት ለማፈላለግ የሚደረግን የጠረጰዛ ዙሪያ …. ነው። አለመታደል ሆኖ የኛ ተቃዋሚዎች በራሳቸው ጥረትና ትግል የወያኔን የመንግስትነት አጥር ለመሸንቆር ሳይችሉ ቆይተዋል። ዛሬ ደግሞ ግዜ በራሱ ቸርነት እንሆ በረከት ብሎ በከፈተልን ሽንቁር ዘልቀን ለመግባትም መቻላችን አጠራጣሪ ሆኗል። ጭራሹኑ በቀዳዳው አሾልቀን እያየን መለስ ዜናዊ በሌሉበት በወያኔ ማጀት ማን ሊጎማለል እንደሚችል ሲናርዮ እየቀመርን ምሁራዊ ትንታኔ ማዝነቡን ተያይዘነዋል፡፤

ሳሞራና አዜብ ተስማምተዋል፤ ገብረ ክርስቶስና ስብሃት ተጣልተዋል፤ ጌታቸውና እግሌ አድፍጠዋል እያልን አማራጭ ተቃዋሚ ሳይሆን የበይ ተመልካች እየመሰልን ነው ።
በጣም በጣም እያናደደኝ የመጣው ደግሞ በህገ መንግስት ላይ የሚደረገው ትንታኔና ዘገባ ነው። በኢትዮጵያ ህገ መንግስት ጠ/ሚን የሚተካው ም/ጠሚሩ ነው ይላል። ስለዚህ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሊተኳዋቸው ሲገባ ይህ አለመሆኑ ህገ መንገስቱ መጣሱን ያመለክታል ይሉናል። ይህን ሃሳብ ለማንሸራሸር እኮ በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት እውነተኛ ህገ መንግስት መሆኑንና እንደ መንግስት የተቀመጠውም ክፍል በትክክል ሊተገብረው ይችላል የሚል እምነት ሊኖር ይገባል። በጣም የሚገርመው ደግሞ ይህን የህገ መንግስቱ ተጣሰ ስሞታ የሚተነትኑት ሰዎች ራሳቸው ተጣሰ በሚሉት ህገ መንግስት መብታቸው ተጥሶ አሳር ያዩ መሆናቸው ነው፡፤

የሕዝብ ጥያቄ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ይሾምልን የሚል ነው እንዴ? ለምን እዛ ላይ መመላለስ አስፈለገ። ወያኔ ህገ መንግስት ሲጥስ ይህ የመጀመሪያው ነው እንዴ? ይህን በማንሸራሸር የሚገኘው ፖለቲካዊ ጥቅምስ ምንድነው? ምክራችሁን ሰምተናል ብለው ነገ ኃይለማሪያምን በጠ/ሚርነት ቢሾሙ ጥያቄው ተመለሰ ! አፎት ወደ ኮሮጆ ሊባል ይሆን?› ወይስ ሌላ የህገ መንግስት ጥያቄ አንስተን ሌላ ትንተና?? በተለይ ታሪክ እየሰራ ባለው ኢሣት ላይ ይህ ነገር መደጋገሙ በጣም አሳዝኖኛል።

የወያኔ ባለስልጣናት የውስጥ ሽኩቻና ለስልጣን የሚያደርጉትን ፍትጊያ ማወቅ ለያዝነው እቅድ እንደ መረጃ ሊጠቅመን እንደሚችል ምንም ጥርጥር የለውም ፡፤ ይሁንና እንደመረጃ ሊጠቅመንም የሚችለው ውስጣቸው ያለውን ችግር እንደምናውቅ እስካላወቁ ድረሰ ብቻ ነው። አልያ ጠዋት ማታ በዜና የምናውጃትን ድክመታቸውን እየሰሙ ማምሻቸውን በግምገማ እያስተካከሉ እንዲሄዱ በማድረግ እንዳናጠናክራቸው እሰጋለሁ። መረጃ ሁሉ ዜና አይሆንም።በተለይ በትግል ላይ ለሚገኝ ወገን።

እናም ግዜው የሚጠይቀው ሲናሪዮ ቀማሪ ሳይሆን አቅጣጫ መሪ ነው! ስታሊን ከሞተ በኋላ አምባገነን ብለው ለመናገር ድፍረት አጥተው 3 አመት ቆይተዋል። አቶ መለስም ከሞቱ ብኋላ የአምባገነንነት መንፈሳቸው በቤተ መንግስቱ አካባቢ እያንዣበበ ገና ይቆያል። ብሎ ትንታኔ ምን ማለት ነው? ልንለውጠው የማንችል የታሪክ ሂደት በመሆኑ መንፈሳቸው በራሱ ግዜ ከአራት ኪሎ ቤተ መንግስት ሽቅብ ተመዘግዝጎ ወደ ….. እስኪሄድ እጃችንን አጣጥፈን ከመቀመጥ ሌላ አማራጭ የለንም ማለት ይሆን? ይህ ሊነሳ የሚችለው እኮ በመጀመሪያ ደረጃ የወያኔ መንግስት አቶ መለስ ከሞቱ ብኋላም እንደ መንግስት ይቀጥላል የሚል እምነት ሲያዝ ነው። እውን እምነታችን ያ ከሆነ አውቀን እንቀመጥ ።
ይህን ትንታኔ የሰጠው አንድ የውጭ ዜጋ የታሪክ ተመራማሪ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ይህ ሰው ወያኔን ለማረጋጋት ያሰበ ነው! ለማለት አይኔን አላሽም ነበር።

ይህን ስል ሱሪ በአገት ሆኖ ማምሻውን ውጤት አሳዩ ማለቴ አይደለም። እየሰራችሁ ያላችሁትን ሁሉ በሚዲያ ላይ እያወጣችሁ ንገሩን ማለቴም አይደለም ፡፡ እኔ የምለው ትግሉን የሚጠቅምና ወቅቱን የዋጀ ጉዳይ ላይ በማተኮር ስሩ ነው። የማይጠቅመን ነገር አትንገሩን….ነው።

ባጠቃላይ በአሁን ወቅት እየተንሸራሸሩ ካሉት ሃሳቦች የተረዳሁት የፖለቲካ እንቅስቃሴን ወይም ትግልን ለመምራት ከዳበረ እውቀት ባሻገር ልዩ ተፈጥሮና ችሎታ እንደሚጠይቅ ነው። ከታሪክ ማህደር እውነታዎችን እየመዘዙ ነባራዊ ነገርን ማስረዳት ትልቅ ችሎታ ነው። የጠላትን ደካማ ጎን ገምግሞ በድክመቱ ለመጠቀም ግን ልዩ የሰውነትም የባህሪም ስጦታ ያስፈልጋል ይመስለኛል።ያ ባይሆን ኖሮ ዛሬ የወያኔን መንግስት ለመጣል ዱር ቤቴ ካሉ የድርጅት መሪዎች ከወያኔ ባለስልጣናት መካከል ማመዛዘን የሚችሉ አንድ ሁለትም ቢሆኑ አይጠፉም አይነት ተስፋን በተስፋ የሚከተል መላምት ባልሰማን ነበር።

እናም በተለይ የግንባር ሥጋ ሆናችሁ ግዜያችሁን እውቀታችሁን ገንዘባችሁን ሁሉ ሰውታችሁ ህዝብን ነጻ ለማውጣት የምትደክሙ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ይህንን የታሪክ አጋጣሚ ሳትጠቀሙ ወይም ቢያንስ ቢያንስ ለመጠቀም ሳትሞክሩ ብትቀሩ ዛሬ እድሜ ለታሪክ ሰሪው ኢ.ሳ.ት ይሁንና በከፍተኛ ሞራልና ተስፋ የተነሳሳው ህዝብ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ተስፋ ቆርጦ ራሱን በግለኝነት ኮሮጆው ውስጥ እንደሚቀብር አትጠራጠሩ።

ይህ መሆኑ እናንተን ተወቃሽ ያደርጋል አልልም፡፤ ምክንያቱም እጁን አጣጥፎ የተቀመጠ ሚልዮን ሆድ አደር አልያም ልኑርበት ባይ ባለበት፤ ውጤት አምጡም አታምጡም ጠዋት ማታ ቀና ደፋ የምትሉ ወገኖችን ለመውቅስ ማንም የሞራል ብቃት ሊኖረው አይችልምና ነው። ራሴን ጨምሮ!!!

የኔ ስጋት የታሪክ ተወቃሽ ትሆናላችሁ የሚል አይደለም። የኔ ስጋት የደከማችሁበት የለፋችሁበት፤ የልጆቻችሁን ግዜ ሰርቃችሁ የሰጣችሁበት፤ ትግል ያለውጤት ሲቀር ሊፈጥርባችሁ የሚችለው ቁጭትና የባዶነት ስሜት የከፋ ይሆናል የሚል ነው።የኔ ስጋት በምርጫ 97 ማግስት የነጻነት ጭላንጭል ያየ መስሎት ሁሉም እንዳይሆን ሲሆን ተስፋ ቆርጦ የተቀመጠው ወገን ዛሬ ከ6ና ሰባት አመት ብኋላ የታየበትን መነሳሳት ዳግም እንዳናጣው ነው፡፤ ዳግም ሲታጣ ደግሞ ለ7ና ሰባት አመታት ሳይሆን…..መሆኑ ነው።

እናም የፖለቲካ ድርጅቶች ግዜው የፈጠረውን አጋጣሚ ለመጠቀም ቅድሚያ ስጡ። ማድረግ የሚቻለውን ሁሉ በማሰብ ህዝብን የእንቃቅሴያችሁ ተሳታፊ በማድረግ ስሩ።
ማንም ድርጅት ከየትኛውም ድርጅት ጋር በዚህ ወይም በዚያኛው አንቀጽና ፕሮግራም አልስማማም እስማማለሁ የሚልበት ወቅት አይደለም ። አሁን የምንሻው አቅጣጫ የሚመራ ስልት የሚነድፍ ከመረጃ አሰባሰብ ጀምሮ አገርቤት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመከታተል ከወያኔ የድህንነት ወጥመድ ውጭ ሆኖ ህዝብን እንዴት ማንቀሳቀስ እንደሚቻል የሚቀይስና ሰርቶ የሚያሰራ ነው።

ይህን የታሪክ አጋጣሚ ለመጠቀም ሲባል ብቻ አብራችሁ መስራት ይጠበቅባችኋል። ፕሮግራምና እምነት የሚለውን ወደ ጎን ትታችሁ ወያኔ እንደተንበረከከ ለመጣል በምትችሉበትን ዘዴ ላይ መምከር አለባችሁ፡፤ ተዋሃዱ ተቀላቀሉ አንድሁኑ ግንባር ፍጠሩ አንላችሁም። ምክንያቱም ሊሆን ቢችል ኖሮ 21 አመታት ውስጥ ይሆን ነበርና ነው። እንደኔ እንደኔ አሁን ማድረግ ያለባችሁ “ማሰቢያውን” ያጣው የወያኔ መንግስት ሌላ ማሰቢያ አይምሮ ሳያገኝ በፊት ለመጣል ለግዜውም ቢሆን የተቀናጀ ስራ ለመስራት መስማማት ነው። በአሁን ሰአት እነሱ ያላቸውን ልዩነትና ቅራኔ ሁሉ ወደ ጎን አድርገው እድሚያቸውን ለማራዘም አንድ ሆነው እየሰሩ እንዳሉ ለመረዳት የበረከት ስምኦንና የአማረ አረጋዊን የሰሞኑን የተቀናጀ ስራ መመልከት በቂ ይመስለኛል። የወያኔ መንግስት ሲንገዳገድ ወደ ደጋፊነት የሚገባው ሲጠናክር ደግሞ ወደ ነጻ ጋዜጠኝነት የሚመለሰው የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት አማረ አረጋዊ ከበረከት ስሞን ጋር ያለውን ሰማይ ጥግ የደረሰ ቅራኔ ወደ ጎን ብሎ “ጠ/ሚሩ እረፍት ላይ ናቸው፡ “ ብሎ በረከት የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ ለማስተማመን ጠ/ሚሩ አሜሪካ ናቸው ብሎ ተመሳሳይና ቋጥኝ የሚያህል ውሸት በጋዜጣው ሲያወጣ ስለ ጋዜጣው ተነባቢነት ማጣት አልተጨነቀም ህውሃት ከሌለ ጋዜጣውም የለምና ። አማረ ከጋዜጣው ለህውሃት ህልውና ቅድሚያ ሰጥቶ ከበረከት እንደሰራ ሁሉ ተቃዋሚዎችም ለዋናው ጉዳይ”ለህዝብ ነጻነት” ቅድሚያ ሰጥታችሁ በስትራተጂያዊ ቁርኝት አብሮ መስራት ይገባችኋል እላለሁ። የሰው ሃይላችሁንና ገንዘባችሁን አቀናጅታችሁ መንቀሳቀስ ከነጠላ ጉዞ በተሻለ ወደ ውጤት ያደርሳችኋል ይመስለኛል ።

ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ ወያኔን ተቀየምነው እንጂ ተቃወምነው ብላችሁ ባታወሩ ይመረጣል። የተቀየመ ሰው የሆዱን በሆዱ ይዞ ቢበዛ አንገት መጠምዘዝ እንጂ ሌላ የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ እንደማይነሳሳ ሁሉ ማለቴ ነው።

በመጨረሻም ትልቁ የለውጥ ተስፋችን የወደቀው በኢ.ሣ.ት ትከሻ ላይ ነውና በዚህ ረገድ ኢ.ሣ.ት በአጭር ግዜ ውስጥ ህዝብን ወደ አንድ አቅጣጫና አላማ እንዳሰባሰበና እንዳነሳሳ ሁሉ ፖለቲካ ድርጅቶችናም እጅ ለእጅ በማያያዝና በአብሮነት መንፈስ እንዲሰሩ ለማነሳሳት እንደሚችል አልጠራጠርም!! ዋናው አስቦ ማቀድ አቅዶ መነሳት ተነስቶ መስራት መቻል ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

አዜብ ጌታቸው
[email protected]

13 Responses to ግዜው የሚጠይቀው ሲናሪዮ ቀማሪ ሳይሆን አቅጣጫ መሪ ነው!

 1. አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ Reply

  July 31, 2012 at 9:36 am

  ግዜው የሚጠይቀው “ሲናሪዮ” ቀማሪ ሳይሆን አቅጣጫ መሪ ነው!”Scenario” is not Amharic.

  Meaning:the way in which a situation may develop in a bad way.Again when we describe situation:as a nightmare scenario,we mean that it is the worst possible thing will happen.
  እንግዲህ በመሰረታዊ ቃሉ ከተግባባን ቃሉን ሥጋ ለማድረግ በትክክል በትርጉሙ መግባባት ይኖርብናል::ስለሆነም በምትኩ ትግል የሚለውን እመርጣለሁ::ምክንያቱም ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ያለውን በግልፅ ላስቀምጥና:-“የትግሉን ዓይነት ሠላማዊ እንዳይሆን በግድ እንድንመርጥ የሚያደርጉን ለጥቅማቸው ሲሉ በያንዳንዳችን ላይ ጭካኔ የተመላበት ርምጃ የሚወስዱብን የሥጋ ትሎች ጠላቶቻችን ናቸው::በሃያ አንድ ዓመታት ስንት ኢትዮጵያውያን በእንዴት ዓይነት ሁኔታ ተሰዉ???”እናስ በሰላማዊ ትግል የምንለው በእርግጥ መስዋዕት አያስከፍልም???እነማን ናቸው የሚከፍሉት ያለፉት ዓመታት የተሰዉት ብቻ በቂ አይደሉም???እናም ዛሬስ አናመርም???በሰላም ሥም እንፍተለተል???የውጊያ ችሎታ ያለው በጊዜው የዘረፈውን ንብረት ይዞ የጓሮ አትክልቱን እያጠጣ በዝምታ ምን ተፈጸመ እያለ ሲዘባነን በየአጠገባችን እናያለን የኔብጤው ግን ፈለገም አልፈለገም እየሄደ የሚፈገምበት ምክንያት አይታየኝም::ድብልቅልቁ መጀመር አለበት::አትክልት የሚያጠጣውም ሆነ ዘፈን የሚያሰማው እኛም ብንሆን መቀላቀል አለብን::በቃ ለማለት ብሶቱ ወኔያችንን ማነሳሳት አለበት::በትዕቢት የሚያደርጉትን ብታዩ እና ቢገጥማችሁ አዎ እንደኔ በየመንገዱ ሁሉ የአካል ቋንቋችሁን በወዮላችሁ ታሳዩ ነበር::እኛ የራሳችንን ድርሻ እንወጣ ዘንድ በያለንበት ትግል እንጀምር እንጂ ትግሉ ያለው ኢትዮጵያ ብቻ ነው በለን ልንተውላቸው አይገባም::በውጭ አገር ያሉ ሰላዮችን ፈልቅቆ ማሳደድ ይገባል:-እንደ የእንግሊዝና የፈረንሳይ ባንዳ የናዚ ሰላዮች::

 2. Selam Reply

  July 31, 2012 at 9:14 am

  what an advice!!! what an article!!! This is the way and the only way out from this historical dilemma ! Yes! meles is gone! Good! and Right prediction Azina! So what we goanna do now to use this GOD GIVEN opportunity ? Opposition parties should do whatever it takes to dismantle the left over of meles regime.

  They lost their thinking power! now they are nothing with out him. People like Samora “the 8th grade General” ! and others were just tools! Tools need some one to use on them that some one is gone…………………..as usual, amazing insight azina ! article of the month!!!!!

 3. Askale Dama Reply

  July 31, 2012 at 6:35 am

  Tenesa,

  You shouldn’t give too much wait for the subjective desires of individuals. Esat and Ginbot 7 will not become weak because they are the people like you and me. Also, the real leaders are there on the ground in the heat of the struggle. It from that heat they will emerge. I trust the Ginbot leadership is doing everything to guide those on the ground on commanding task of the day. A moment like this will screen the men from the boys like a sift. Chew lerasu sil yiTafiTal. ENTC, Shengo, Medrek, or any other gathering will live or die out on account of its action, actual ability of the practical movement. A group that doesn’t lead is as good as nothings. They know this. I agree with you that some of these groups are still old school. They want to conspire in darkness and appear as leaders. The true leaders will see them leading. Notice what Temesgen doing with his Feteh. That is leadership!!!!

  • Selam Reply

   July 31, 2012 at 12:58 pm

   Askale Dama,
   You did not get Azeb’s point! as far as i understood her, she is trying to advice all opposition parties to work to gether regardless of their differences.actually, Azeb arguing all oppositions to stop internal struggle and focus on common enemy weyane. when i see your comment, from this perspective, you are advocating exactly what she advice not to. you are saying G7 is the only way but others are weak… this is what we need to stop !! you support your party that is fine! but you should not insult or weaken other oppositions to glorify yours! Worshipping a leader and Group thinking are the major political sickness in our history! what i see is, you are a victim f it…WE DO NOT EXPECT SALVATION FROM ONE PARTICULAR GROUP! BUT FROM ALL UNITED ETHIOPIAN .

   Askale Dama, Be aware of that !There is no single political group or organisation that can full fill all Ethiopian interests. So, all or most.. oppositions must come together and combine their effort to reach to the big ..common goal “FREE ETHIOPIA”. Try to think how you librate Ethiopian people, not how your Group became the best opposition of all.

 4. Tenesa Reply

  July 31, 2012 at 5:10 am

  It is absolutely right. We need leaders now and not scenario cookers. No slicing and dicing now. That time is over. Cooking scenarios now is paralysis by analysis.

  Some like Elias and his transitional council peddlers run around begging for recognition. Is this leadership or is that Elias’s version of acting? You don’t beg for recognition. You get recognized by your action.

  Are these ENTC fools begging for recognition as Zenawi was begging for dollars? May be. You know what, Elias along with his transitional council farce is heading towards creating a big problem among the opposition. They are in a collision course against other opposition elements who they think are threats.

  For instance, I am sure Elias and his transitional council will do every thing to weaken ESAT,Ginbot 7,and other fronts in the coming months and years. They are going to blow up the unity of the opposition as they did Kinijit in 2005. That is why I say ENTC is infiltrated.

  Please folks, watch out where ENTC is heading. Focus on the lady secretary or vice secretary(not sure)for now. They say she is a TPLF agent. There are others too. And they will be exposed in due time.

 5. Abera M. Reply

  July 31, 2012 at 2:01 am

  Azeb,

  You really touched my heart and when you are speaking, I felt like you are speaking my mind. People with the plan and the opportunity should be doing what is best for the country. Please DO NOT ALARM WOYANE AND ITS SUPPORTERS ABOUT POSSIBLE SCENARIOS and consequences. Let the opposition and the Ethiopian people surprise them in an unexpected way. All the professors and doctors of Ethiopia are trying to legitimize woyane’s rule as if there is a rule of law in the country.
  Please understand, there is no law to be broken, there is no succession that is legal, have you forgotten 2005, the “gov’t” we have today is illegitimate since they stole the election. Hailemariam Desalegn or Meles Zenawi (simun kes yitrawna) or Bereket Simon are all thieves who stole the election in broad day light, whoever is in power it doesn’t make any difference, we have to fight all of them, in all possible ways and at all occasions.

 6. Askale Dama Reply

  July 31, 2012 at 2:00 am

  Azeb,

  Thank you. A lot of us can’t make the distinction between making the news and consuming the news. Most can’t tell the differet between ideas and actions. In the end only an act can move something. Consider this: Ethiopians live in hundreds of cities. We are not even calling for meetings and political actions. The only show on the block is Esat TV. Most of the diaspora simply consumes news and gets entertained. This is a shame. Every city must begin to hold some kind of political action. We must also deny attention to abstract academic commentators. Those with political knowledge need to combine ideas with practice. ‘Nothing happens until something moves’ – Einstein.

 7. ጞይቶም(Goytom) Reply

  July 31, 2012 at 1:06 am

  Azeb,you made my point. You mentioned everything what was in my mind about those old person gave an interview on ESAT.They are old and useless except giving or showing way to woyanne. And also some of the journalists from ESAT,they even do not for whom they are working.I sometimes ask myself am hearing ETV?

 8. Daru Reply

  July 30, 2012 at 10:58 pm

  Wow!Azeb you have agood idea and we have to help to the party we like
  Ithink they need our help.Thank-U Azeb.

 9. TED Reply

  July 30, 2012 at 9:00 pm

  Precisely! Thank you Azeb.

 10. ANDENET Reply

  July 30, 2012 at 8:25 pm

  Azeb really u wrote something wonderful.That’s the way people should think about what is going on.You fool people b/c u r living in z free world where political issues r openly discussed doesn’t mean that u should also use z same things to name yourself .Study what z strategy of my enemy is!They have closed their doors&can’t u imagine how much these people r working hard to stabilize themselves during these rainy days?!Forget about the openness of the west if that doesn’t help we the people!!!Thanks Azeb really!

 11. Robele Ababya Reply

  July 30, 2012 at 7:48 pm

  I just heard on ESAT Radio that the tyrant is dead.

 12. tewsmagn agere Reply

  July 30, 2012 at 7:01 pm

  Azeb’s advice is priceless. The opposition has done this blunder for a long time. They have alerted TPLF just about everything by posting or reporting it on their media outlets.

  To write or talk about scenarios, tactics, and strategies is totally stupid. The scholars,if they have some sense in their brain, should carefully analyze the impact of their articles before they even write. There may be ways to write things in general without being too specific. Or they may have altogether abandon writing things that may end up helping TPLF.

  The opposition media should focus on exposing TPLF crimes, and informing the Ethiopian public and international media. Analyzing scenarios, tactics, and strategy is simply foolish. Sometimes, they even mention the name of activists and private citizens risking their safety.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>