የዳላስ ጉዞዬ

July 19, 2012

Click here for PDF

የጉዞዬ መንስኤ የ2004 ዓ ም በሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል የሚደረገውን የእግር ኳስ ውድድር ለመመልከት ነበር።ከሥፍራው የተገኘሁትን ብቻ ሳይሆን ፤ከሐምሌ አንድ እስከ ሰባት የተደረገውን የእግር ኳስ ውድድር በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም ቀልብ ሰቧል።ሰለ ዝግጅቱ ስኬትና ድምቀት በመገናኛ ብዙሃን ብዙ ስለተባለ የምለው የለኝም።

ሆኖም በመክፈቻው ትርምስ ውስጥ የፈደረሺኑን ፕሬዘዳት አቶ ጌታቸው ተስፋዬን አገኝቼው እግዚሐብሔር ይስጥልኝ ለማለት እድል ገጥሞኛል። በኢትዮጵያውያን ወቅታዊ መወያይያ መድረክ (ECADF) የሰጠውን ቃል ምልስስ አንብቤ ሰለነበር ሰለእሱ መልካም ነገር ሰንቃለሁ። ዝግጅቱን ስምለከት ይህ ሰው ይህን ወጣት ትውልድ በአካልም፣ በመንፈስም በአእምሮም ገንብቶ የሃገር አለኝታ እንደሚያደርገው ተስፋዬን አጠናክሮልኛል። በአንዲት ደቃቃ ውስጥ ነበር ይህን ሁሉ ያልኩት።

በእስፓርቱ ውድደር ስም የሃገር ልጆች ከዓለም ዙሪያ ሲገናኙ ታምር ሊፈጠር እንደሚችል መዘንጋት የለበትም። አልተነገረም እንጂ ይህ ፈደሬሺን ከተመሠረተ ብዙ ታምራት እንደተፈጠሩ አትጠራጠሩ።

እኔም በእስፓርት ሰም በዳላስ ጉዞዬ ያገኘሁትን እኛነታችንን የሚገልጽ ልንከባከበውና ልናደርገው የሚገባ ታሪክ ላካፍላችሁ ወደድኩ።

ከቫኮበር ስያትል በመኪና ከስያትል ፊኒክስ ከዚያም ወደ ዳላስ አይሮፕላን ለወጥሁ፤ ዳላስ አይሮፕላን ጣቢያ 3፡30 ኤ ም ጠዋት ሰደርስ የእጅ ስልኬ አገልግሎቱን አቆመ። ከሚቀበለኝ የጓደኛዬ ወንድም ተቆራረጥን፤ ከሃገር ሰወጣ በጣም ትንሽ ስለነበር የሚያውቀኝ አልመሰለኝም፤ ሽቅብ ቁልቁል ስል የባቱን ተራራ የሚያህል ጃዊሳ ሰሜን ሲጠራ በአሳንሳር ከሃኛው ፍቅ ወለል ላይ ዱብ እንደልኩ ተሰማኝ። ከነሻንጣዬ ተሸክሞ ከመኪናው ውስጥ የጫነኝን ያህል ተሰማኝ። የሰላሳ ሰምንት ዓመት ትዝታ መገለጫ መሆኑ ነው። Read more…

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>